በቦርድ አመራሮች ውዝግብ ሳቢያ የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ህልውና አደጋ ውስጥ መውደቁ ተሰማ

‹‹በቀን አንድ ዶላር›› በማዋጣት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውን ድጋፍ እንዲሰጡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት የተመሠረተው የኢትየጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ፣ በቦርድ አመራሮች ውዝግብ የህልውና አደጋ ውስጥ መውደቁ ተሰማ፡፡

በቦርድ ዳይሬክተሮች የሚመራው የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በአባላቱ መካከል ውዝግብ መነሳት የጀመረው ካሰባሰው የስድስት ሚሊዮን ዶላር ውስጥ አምስት ሚሊዮን ዶላር በመመደብ፣ ከ22 ፕሮጀክቶች ውስጥ ለአምስቱ ድጋፍ ለመስጠት ስምምነት አድርጎ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ ሒደት ውስጥ ተከሰቱ በተባሉ የሥነ ምግባርና ሌሎችም በርካታ ከአሠራር ያፈነገጡ ተግባራት ምክንያት፣ የተቋሙ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ኢየሱስ ወርቅ ዛፉ ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን በመግለጽ ደብዳቤ ይጽፋሉ፡፡ እንደ አቶ ኢየሱስ ወርቅ ሁሉ የእሳቸው ምክትል የሆኑት ምሕረት ማንደፍሮ (ዶ/ር) እና የቦርድ ሥራ አስፈጻሚው አቶ ፍቅሬ ዘውዴም ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

አቶ ኢየሱስ ወርቅ መልቀቂያ ካስገቡ በኋላ በአስቸኳይ ስብሰባ ያካሄደው የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ፣ በምትካቸው አሜሪካ የሚገኙትን አቶ ዮሐንስ አሰፋን በቦርድ ሊቀመንበርነት ይሾማል፡፡ ምክትል የነበሩት ምሕረት (ዶ/ር) አቶ ኢየሱስ ወርቅን ለመተካት መወዳደራቸውን፣ ሆኖም አቶ ዮሐንስ በሙሉ ድምፅ በመመረጥ አዲሱ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የቦርድ ሊቀመንበር መሆናቸውን ቦርዱ አስታውቋል፡፡

ነገሮች በዚህ መስመር ሲጓዙ የኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ማኅበራት ኤጀንሲ ካለው የኃላፊነት ድርሻ በሚመነጭ አግባብ በነገሩ ጣልቃ በመግባት የአቶ ዮሐንስ የቦርድ ሊቀመንበርነት ምርጫ፣ ተገቢውን የሕግ ሒደት ያልተከለ ነው በማለት ውድቅ ያደርገዋል፡፡ ኤጀንሲው አቶ ዮሐንስ የተመረጡበት የስብሰባ አጀንዳ፣ የተያዘው ቃለ ጉባዔና ድምፅ የተሰጠበትን አግባብ ገምግሞ ሒደቱን ውድቅ በማድረግ አቶ ኢየሱስ ወርቅ ሕጋዊ ዕውቅናና ተቀባይነት ያላቸው በመሆናቸው፣ አግባብነት ባለው ምርጫ ሥርዓት እስካልተተኩ ድረስ በኃላፊነታቸው እንዲቆዩ በመጠየቅ እንዲመለሱ ያደርጋል፡፡

አቶ ኢየሱስ ወርቅ ሪፖርተር ስለጉዳዩ ጠይቋቸው እንዳብራሩት፣ በዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ቦርድ አሠራር ውስጥ የሚታዩ ግድፈቶችና ሕጋዊነት የጎደላቸው እንቅስቃሴዎችን ሊታገሱ ባለመቻላቸው መልቀቂያ ቢያስገቡም፣ ኤጀንሲው ጥያቄያቸውን ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡ ይኸው ለበጎ አድራጎት ማኅበራት ኤጀንሲ ይፋዊ መልቀቂያቸውን በቦርዱ በኩል አስታውቀውና በምትካቸው የሚሾሙ ኃላፊዎች ታውቀው በርክክብ እንዲሄዱ በመጠየቁ፣ ወደ ኃላፊነታቸው መመለሳቸውን  ተናግረዋል፡፡

ለማኅበራት ዕውቅናና ፈቃድ የመስጠትና የመሰረዝ ሥልጣን ለተሰጠው ኤጀንሲው በተቋቋመበት አዋጅ መሠረት የበጎ አድራጎት ማኅበራት የአመራርና የአሠራር ለውጥ ሲያደርጉ ማሳወቅ እንደሚጠቅባቸው፣ ይህ በዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በኩል እንዳልተተገበረ ከመግለጹም በላይ በምርጫ ሒደቱ ላይ የተሳተፉ የቦርድ አባላት ስምንት መሆናቸው ቢገለጽም ፊርማቸውን ያኖሩት አምስት ብቻ መሆናቸው፣ የቦርዱ ሥራ አፈጻሚና ሊቀመንበሩ በሒደቱ አለመሳተፋቸው፣ ቃለ ጉባዔውም በማን እንደተያዘ አለመታወቁና መሰል ክፍተቶችን በማውሳት የአዲሱን የቦርድ ሊቀመንበርነት እንደማይቀበለው አስታውቋል፡፡

የቦርዱ አስፈጻሚ አባል መሆናቸውን ጠቅሰውና ፈርመው ለኤጀንሲው ምላሽ በሰጡበት ደብዳቤ አብዱልዋሀብ አደም ኢብራሂም (ዶ/ር)፣ ስድስት ዋና ዋና የሕግ ክፍተቶች በኤጀንሲው መፈጸማቸውን በመግለጽና አንቀጾችን በማጣቀስ የቦርድ አባላቱ ያካሄዱት ምርጫ ምንም ዓይነት የሕግ ጥሰት እንዳልተፈጸመበት ተከራክረዋል፡፡ እንዲያውም ኤጀንሲው ያላግባብ ሥልጣኑን በመጠቀም ጫና ማሳደሩንና አቶ ኢየሱስ ወርቅን ዳግም ወደ ኃላፊነት ለማምጣት ጣልቃ መግባቱን በመግለጽ ጭምር፣ የበጎ አድራጎት ማኅበራት ኤጀንሲን ኮንነዋል፡፡ ደብዳቤው የኤጀንሲውን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦን በስም ጠቅሶ፣ ጣልቃ ከመግባት አልፈው ጫና በማሳደር አቶ ኢየሱስን ወደ ኃላፊነት መልሰዋቸዋል ሲል ይከሳል፡፡

ክርክሩ ይህን የሚመስል ገጽታ ይላበስ እንጂ፣ ውስጥ ውስጡን ግን የገንዘብ ድጋፍ ሊደረግባቸው ከቀረቡት ፕሮጀክቶችና ውድቅ ከተደረጉት ጋር እንደሚያያዝ አቶ ኢየሱስ ወርቅ አስታውቀዋል፡፡ በስም ያልተጠቀሱ የቦርድ አባላት የቦርዱ የሥነ ምግባር ደንብ የሚከለክለውን የጥቅም ግጭት ድንጋጌ በግልጽ በመተላለፍ የሥነ ምግባር ጥሰት መፈጸማቸው እንደተደረሰበት የተናገሩት አቶ ኢየሱስ ወርቅ፣ የሥጋ ዝምድና ያላቸው ግለሰቦች የተሳተፉበትና አንድ የቦርድ አመራር አባልም ድርጅታቸው የተወከለበትን ፕሮጀክት በማቅረብ ጭምር አብረው ለግምገማ መቀመጣቸው እንደተረጋገጠ በመግለጽ፣ እንዲህ ያሉ መሠረታዊ ችግሮች ቦርዱን እንደ ተፈታተኑትና እሳቸውንም ለመልቀቅ እንዳነሳሳቸው አስታውቀዋል፡፡

ስለጉዳዩ ማብራሪያ ለማግኘት አሜሪካ ከሚገኙት ከአቶ ዮሐንስ አሰፋ ምላሽ ለማግኘት ተሞክሮ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ ሌሎችም በጉዳዩ ላይ ይመለከታቸዋል የተባሉ አካላት ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

አቶ ኢየሱስ ወርቅ አሁንም ሕጋዊ የቦርዱ ሊቀመንበርታቸው በመንግሥት ተቋማት ዕውቅና ያለው መሆኑን አስታውቀው፣ በቅርቡ የአምስት ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ከሚያገኙ አምስት ፕሮጀክቶችን አስፈጻሚ ድርጅቶች ጋር ቦርዱን በመወከል መፈራረማቸውን፣ ለጤና ባለሙያዎች መከላከያ የሚውሉ የፊት መሸፈኛ ጭንብሎች፣ የፊት መከለያዎች፣ የመከላከያ አልባሳትና የመተንፈሻ መሣሪዎች የተካተቱበት ከ1.37 ሚሊዮን ዶላር በላይ ግምት ያለው ቁሳቁስ ለጤና ሚኒስቴር ለማስረከብ ዝግጅት ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡

በቦርድ አመራሮች መካከል በመላው ዓለም እንቅስቃሴ በማድረግ ፈንድ በሚያሰባስበው የትረስት ፈንዱ አጋር ተቋማትና በአማካሪ ቦርዱ ኃላፊዎች መካከልም፣ የከረረ አለመግባባት ተፈጥሮ እርስ በርሳቸው ተከፋፍለው በመወነጃጀል ላይ እንደሚገኙ ለሪፖርተር የደረሱት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ እነዚህ ተደማምረው የትረስት ፈንዱን ህልውና አደጋ ውስጥ እንደጣሉትና በርካታ መዋጮ ያደረጉ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም ማዘናቸውን ለቦርዱ ጭምር እያሳወቁ ናቸው፡፡

https://www.facebook.com/sgadissa/videos/10217559005388780/

ሪፖርተር

 

5 Comments

 1. This board had been standing on a shaky ground ever since the first Chairman of the board , Tamagne Beyene resigned from his duty right after eighty six innocent Ethiopians were mutilated and killed by a genocidal mob in Oromia . The stand the “Ethiopian government” took in regards to the incidents surrounding the incident which caused eighty six people’s lives had made diasporas loose any trust on the PM Abiy Ahmed’s failed administration.

  Eritreans diasporas had sent more money to the covid-19 fight in Eritrea compared to how much Ethiopian diasporas sent to fight covid-19 in Ethiopia thus currently Eritrea got zero people sick from coronavirus or noone is sick with Covid-19 now in Eritrea with all people that previously were infected with Covid-19 fully recovering by recording a fantastic record of not a single person dieing from Covid-19 in Eritrea .

 2. ጎበዝ ይሄ ሪፖርተር የተባለዉ የዜና ተቋም ባለቤቱ የሰየ አብረሀ ወንድም ነዉ ይባላል (አማረ አብረሀ) ወንድሙ አገርና ወገንን አጥንት የጋጠ ሌባ እያለ ስለሱ ሳይጽፍ ስለዚህ ይፅፋል ነገርን እንመርምር እንጂ ይንቁናል እኮ። ሰየ አብረሀ ጻድቃን ገ/ተንሳይ ከተባለዉ ትግሬ ጋር ጦርነቱን የመራነዉ አሁንም በህይወት አለን ብሎ ሲነግረን ያንን ተችቶ አይጽፍም ነበር? የድር ገጾች የዚህን የዜና ተቋም ዜና ብላችሁ ባታወጡልን መልካም ነበር የነሱ ፍላጎት ከመቀሌ በሚሰጣቸዉ መመሪያ መሰረት አገርን መበጥበጥ ነዉ ሌላዉ ለሀገሩ ብዙ ያደርጋል ስፍር ቁጥር የሌለዉ ዲያስፖራ ወደ መንግስት የማይገባ በጎ አድራጎት በራሱ ተወካዮች አማካይነት ለወገናችን ቢልክ ችግሩ ምንድነዉ? ስራቸዉን በሰላም እየሰሩ ነገር ማጦዝ ትግሪያዊ ተልእኮ ካልሆነ ምን ሊባል ይችላል?
  ከእንደዚህ አይነት ተቋማት እንደዚህ አይነት ፍሬ ከርስኪ አንድነታችንን የሚበተን ምናለ አንብባችሁ የሳይበር ቅርጫት ዉስጥ ብትጥሉት? ስንት የሚጠቅም አንድነትን የሚያጠናክር ይላክልላችሗል ምን እንዲህ አይነት ቁሻሻ ጽሁፍ ላይ ልባችሁ እንደሚያርፍ አይገባኝም። አገልግሎታችሁ ትልቅ ሁኖ ሳለ እንደነዚህ አይነት የአንድነት ጸሮች ሰርገዉ ይገቡባችሗል። ለማንኛዉም ኢትዮጵያን አምላክ ይጠብቅ በዚህ ላይ አረብ ተነስቶብናል እስቲ እሱ ያዉቃል።
  ዉድ ዲያስፖራዎች ትልቅ ነገር ማድረግ የምትችሉ ወገኖቻችንን ቀዳዳዎችን ድፈኑ በእናንተ መሀል ልዩነት የለም ልዩነት ለመጫር ግን አሰፍስፈዋል ከታሪክ ተማሩ በየሀገሩ ያለዉን ቤተ ክርስቲያን በነዚህ ሰዎች አማካይነት ነዉ እንዳልነበረ የሆነዉ ባስቸኳይ ክፍተት ካለ ድፈኑ። ስራችሁ ጥሩ ነዉ በርቱ መዳረሻዉ ይህ ብቻ መሆን የለበትም የተሻለ ነገር ለመስራት ጣሩ እንዲህ ያለዉ በጎ አድራጎት ለህዝባችን እንጂ ለፓርቲ አይደለምና። ህዝባችን ከኛ ብዙ ይጠብቃል።

 3. አይ እናንተ ደግሞ አሁን ይህን ወሬ ብላችሁ መለጠፍ ምን ይባላል። የሃበሻው ታሪክ እኮ አፍርሶ በመስራት ሰርቶ በማፍረስ ገድሎ መስክርነት በመቆም ዋሽቶ በመክበር የተገነባ ነው። ብርቅ የሚሆነው አብረው ሰርተው ችግርና መከራን አልፈው ሃገርና ህዝብን አኮሩ ቢባል እንጂ እንዲህ ያለው መወሻከት አይደል እንዴ ሃገሪቱን እንጦሮጦስ የከተታት። በታሪካችን (እኛ የፈጠርነውን ሳይሆን) እውነተኛውን ከተመለከትን እንደ ተልባ ነዶ አንድ ጋ አብረን ተቋጥረን አይደል እንዴ ሳይታሰብ አፈትልከን በሌላው ላይ የመከራ ዝናብ የምናዘንበው። አብረን መክረን፤ ማህላ ተጋብተን እኮ ነው እልፎችን እሳት ውስጥ ከተን ባለ ደማቅ ኮኮቦች እኛ ነን የምንለው። ባለታሪኮቹ እማ አፈር ተመልሶባቸዋል።ኡኡታ ነጋሪውና ፈርቶ የሸሸው ነው ከፍታ ላይ የወጣው። በፓለቲካም ይሆን በሶሻል በጥምር ህብረት ሃበሻው አንድ ሆኖ ሳያፈነግጥ የኖረበትና አብሮ የሰራበት ዘመን የለም። ለዚህም ነው ዛሬ በሃገራችን የፓለቲካ ሂደት ውስጥ እንደ ጉንዳን የፈሉ የፓለቲካ ድርጅቶች የምናየው። ከልጅነት እስከ ሽበት ሁሌ በዘርና በጎሳ ፓለቲካ ሃተፍ ተፍ ስንል መሽቶ የሚነጋው። የክልል ፓለቲካ ናላውን አዙሮ ቆንጨራና ገጀራ አስይዞ የሰው አንገት የሚቆርጠው እኮ በዘሩ ተሰላፊ የደንቆሮ መንጋ ነው። እንደ ጀዋር፤ በቀለ ገርባ፤ የጫቱ ዶክተር ህዝቅየል የትግራዪ የወያኔ ቁንጮ ዶ/ር ደብረጽዪን ስራቸው ለየቅል ይምሰል እንጂ አፍራሽ ሃይሎች ናቸው። እነዚህ በስም ይጠቀሱ እንጂ ክልሉ ሁሉ የእብዶች ጥርቅም ነው በወንበር ላይ ያለው። ያው ከአንድ የደፈረሰ ወንዝ የተቀዳ ሃሳብ የሚያፈልቁ። ዛሬ የተናገሩትን ነገ የሚሽሩ። ቆመናል ለሚሉት ህዝብ ግድ የማይሰጣቸው በራሳቸው ዓለም ብቻ የሚኖሩ። የሰው ልጅ መለኪያቸው በዘሩ፤ በቋንቋው፤ በሃይማኖቱና በጎጡ ስለሆነ እይታችው ከአፍንጫቸው አይርቅም። ዶ/ር፤ ሶሻል ሳይንቲስት የሚባለው ሁሉ የደንቆሮ ስብስብ ነው። እይታ አለም አቀፋዊና ሰዋዊ ሲሆን ለራስም ለሌላም የሚጠቅም ነገር ሰርቶ ማለፍ ይቻላል። ግን ከአመልካች እጣት አውራ እጣት ይበልጣል የሚል የሙታን መንጋ መኖሩም መሞቱም ለሃገራችንም ሆነ ለህዝባችን ደህንነት ለውጥ አያመጣም። 71 ዓመት ሰው የተገበረለት የሶቪየት የአስተዳደር መዋቅር በአንድ ጀንበር ነው ፍርስርሱ የወጣው። የጆርጂያው ኤድዋርድ ሽቭርናዜ የውጭ ጉዳይ የሆነባት ሶቪየት ናት ራሺያ ሆና ሃገሩን የወረረቸው። ፓለቲካ የእብዶች ግብግብ ነው። እናማ እነዚህ ከላይ የቦርድ አባሎቹ አለመግባባት አስደናቂ አይሆንም። ፓለቲካ ፓለቲከኞችን ሲወልድ፤ መልሶ ሲበላ፤ ሲገለብጡ፤ ሲገለባበጡ ዓለም ይኽው ትሽከረከራለች። ጅመራን እንደፍጻሜ ለሚቆጥሩ ብዙ ተጀምረው የቆሙ ህንጻዎች በሃገራችን ላይ አሉ። ሂደው ይመርቁና ይግቡበት። ውሃ በባልዲ የሚያቀብላቸው ከተገኘ። እኔን የናፈቀኝ መቼ ነው አንድ ልብ ሆነን አንድን ነገር ወጥነን ከግብ የምናደርሰው። ለእኔ አይታየኝም። በቃኝ።

 4. ሪፖርተር ያቀረበው ዘገባ ከመንደር ወሬ አይሻልም። ከአንድ ጋዜጣ ይኸ አይጠበቅም!

  ዳያስፖራ ፈንዱ አጭርና ግልጽ መግለጫ ለህዝብ ማቅረብ አለበት።

  ኮሚቴ ሰይሞ የችግሩን ምንጭ ካጣራ በሁዋላ የሚሰናበቱትን ማሰናበት፣ ችግሩ እንዳይደገም ማገጃ ማበጀት ይገባል። ህዝቡ በፈንዱና በአመራሩ እንዲተማመን ባፋጣኝ መደረግ አለበት።

 5. እንዲህ አይነት አሰቃቂ ዜና ሳይ ከመተቸት ምናለ ቶሎ ከእይታ ቢጠፋ የምልበት ቀን አለ። ከዚህ ኛው በታች ያለውንም ጨምሮ። ወያኔዎቹ ሳይሆኑ የትግራይ ህዝብ በነቂስ ቀሪውን ያገሩን ህዝብ ይቅርታ ይጠይቅ የሚል የዘቀጠ ፖለቲካ። ታድያ ፈጣሪን እራሱ ይቅር በለን ማለቱ አያሳፍርም?

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.