/

ፖሊስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ሲያስተገብር በሰብዓዊ መርሆች እንዲመራ ተጠየቀ

VOA ዜና
ሀብታሙ ስዩም

Danielየኮቪድ 19ን ስርጭት ለመከላከል የወጣውን አዋጅ ጥሳችኃል በሚል የቤተሰብ አባላቶቻቸው በቁጥጥር ስር ከዋሉባቸው ግለሰቦች አንዱ በፈቃዱ ሃይሉ ነው። በፍቃዱ እህት እና ወንድሙ ግንቦት 5.2012 ዓመተ ምህረት ማለዳ ላይ ወደ ስራ በሚየቀኑበት ወቀት ፖሊሶች «ተነካክታችኋል» በሚል በቁጥጥር ስር እንዳዋላው ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ተናግሯል።

ወላጆቻቸው በዕድሜ የገፉ ስለሆኑ ቫይረሱ ወደ ቤታቸው ዘልቆ የጤና ስጋት እንዳይሆን መላ የቤተሰብ አባለት ከፍተኛ የጥንቃቄ ርምጃዎችን እንደሚወስዱ የሚያወሳው በፍቃዱ ፣ፖሊስ እህት እና ወንድሙን በቁጥጥር ስር ባዋለበት አፍታ ባይገኝም-በቁጥጥር ስር ሊያውል የሚያስችል ተግባር እንደማይፈጽሙ እንደሚያምን ያስረግጣል።ከዚያ ይልቅ ወንድም እና እህቱ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኀላ የተከተለው የጤናም ስጋት የሰብአዊ መብት ጥሰትም እንደሆነ ያወሳል።በሰብአዊ መብት ተሟጋችነቱ የሚታወቀው በፍቃዱ ሃይሉ በትናንትናው ዕለት በተለያዩ የአዲስ አበባ ስፍራዎች በእሱ አነጋገር «የጅምላ እስር »ሲከናወን ውሏል።

ፈረንሳይ ለጋሲዮን እና አራት ኪሎን በመሰሉ ስፍራዎች ፖሊሶች በርካታ ሰዎችን በመኪና ሲጭኑ ማየቱንም ይናገራል። መሰል የፖሊስ እርምጃዎችን ህጋዊነትም ሆነ ውጤታማነትም ይጠራጠራል።

መሰል ቅሬታዎች ለመስሪያቤታቸው እንደደረሱ የሚናገሩት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ በበኩላቸው ፖሊስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈጸም በአስተማሪነት ሊረዳ ይቻላል በሚል ዕምነት ግለሰቦችን እየሰረ መሆኑን መስማታቸውን ይናገራሉ። ሆኖም የተወሰደው እርምጃ ከሁኔታው ጋር የማይመጣጠን እንደሆነ ይጠቅሳሉ።

ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ካለው ሀገራዊ የጤና ስጋት አንጻር ፖሊስን የመሰሉ ህግ አስፈጻሚ አካላት ፣ አዋጁን ለማስፈጸም ያሉባቸውን ፈተናዎች የሚረዱ መሆናውን አውስተዋል። አዋጁን ለማስፈጸም የሚወሰዱ እርምጃዎች መሰረታዊ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችን በማይጥሱ መልኩ ሊተገበሩ እንደሚገባም መክረዋል።

በቀረቡ ቅሬታዎች እና ሀሳቦች ላይ ምላሽ ለማግኘት በተደጋጋሚ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ስልክ ላይ ደጋግመን ብንደውልም ሳይሳካልን ቀርቷል።

ይህ በእንዲህ እያለ በኮሚሽኑ የፌስቡክ ገጽ ላይ ህዝብ በስፋት በሚገኝባቸው ቦታዎች ላይ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ሳይጠቀሙ በተገኙ እና እርቀታቸውን ባልጠባቁ 1305 ሰዎች ላይ በአዋጁ መሰረት እርምጃ መውሰዱን ገለጿል፡፡
ኮሚሽኑ ህዝብ በብዛት በሚንቀሳቀስባቸው 23 ስፍራዎች ግንቦት 5 ቀን 2012 ዓ/ም ባደረገው አሰሳ በቁጥጥር ስር ያዋላቸው 990 ወንዶችና 315 ሴቶች መሆናቸውን አክሎ አስታውቋል።

ሙሉ ዘገባውን ያዳምጡ፦

1 Comment

  1. Daniel is the voice of reason and the voiceless. He is not afraid to say the ‘unsayable’ and to face officials, including those who have appointed him to Chair the EHRC, ( for whom I raise my hat for their right choice in appointing him !) when they get it wrong. and should be held accountable That is a true test of a real whistleblower! Keep up the good work Dani, we hear you loud and clear.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.