/

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 27 ፓርቲዎችን ሰረዘ!

Birtukan 1የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እስከ መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ በቀድሞ ህግ ሰርተፍኬት የነበራቸው እና በቀድሞው ህግ ምዝገባ ጀምረው ለነበሩ 106 ፓርቲዎች በአዲሱ ህግ ላይ የተቀመጡ መስፈርቶችን እንዲያሟሉ በደብዳቤ ማሳወቁ ይታወሳል፡፡ ከቦርዱ ደብዳቤ ከደረሳቸው 106 የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል 76 የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰነዶችን ያቀረቡ ሲሆን በሕጉ መሠረት ተሟልቶ የቀረበ ስለመሆኑ እየተመረመረ ይገኛል፡፡
ምርመራውም
• ፓርቲዎቹ በደብዳቤ የተገለጸላቸውን ነጥቦች ሁሉንም ማሟላታቸውን ማረጋገጥ ( የህገደንብ ለውጥ ጠቅላላ ጉባኤ ሰነዶች አቀራረብ፣ የመስራቶች ፊርማ … የመሳሰሉት)
• የፖለቲካ ፓርቲዎች በሕጉ መሠረት ማሟላት የሚገባቸውን የመሥራች አባላት ብዛት ትክክለኛነትን ለመፈተሽ ካቀረቡት የመሥራች አባላት ዝርዝር ናሙና የማውጣት
• ናሙናዎቹ በትክክል ግለሰቦቹ የተፈረሙ መሆናቸውን ወደተፈረሙበት ቦታ በመላክ ማረጋገጥ
• የህገ ደንብ ለውጦችና፣ የጠቅላላ ጉባኤ ሰነዶች በትክክል መያያዛቸውን ማረጋገጥን ያጠቃልላል፡፡

ይህ እንደተጠናቀቀም ሰነዶቻቸው ካስገቡት 76 ፓርቲዎች መካከል ምን ያህሎቹ መስፈርት እንዳሟሉ በቦርዱ ይፋ የሚደረግ ይሆናል፡፡

ነገር ግን የሚጠበቅባቸውን ሰነድ ማስገባት ያልቻሉ እና ጊዜ እንዲራዘምላቸው የጠየቁ 15 [edited] የፓለቲካ ፓርቲዎች ሲኖሩ ከነዚህ ፓርቲዎች መካከል ከስር የተጠቀሱት የ13ቱ አጥጋቢ ምክንያት ባለማቅረባቸው እንዲሰረዙ ቦርዱ ወስኗል፡፡

የተጨማሪ ጊዜ ጥያቄ አቅርበው ተቀባይነት ሳያገኙ የተሰረዙ ፓርቲዎች ዝርዝር የሚከተለው ነው

1. የኢትዮጵያውን ዴሞክራሲያዊ አንድነት ንቅናቄ (ኢዴአን) – የመስራች አባላት ዝርዝር ያላቀረበ፣ ጉባኤ ያላካሄደ
2. የገዳ ስርአት አራማጅ ፓርቲ (ገሥአፓ) – የመስራች አባላት ዝርዝር ያላቀረበ
3. የየም ብሔረሰብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ( የብዴን) – የመስራች አባላት ዝርዝር ያላቀረበ፣ ጉባኤ ያላካሄደ
4. የደንጣ ዱባሞ ክችንችላ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት – የመስራች አባላት ዝርዝርም ያላቀረበ፣ ጉባኤ ያላካሄደ
5. የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ኮንግረስ ( ኮንግረስ) – የመስራች አባላት ዝርዝር ያላቀረበ
6. የትግሪ ወርጂ ብሔረሰብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ( ትወብዴድ) – ጠቅላላ ጉባኤ ያላካሄደ
7. የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት (መአህድ) – የመስራች አባላት ዝርዝር ያላቀረበ፣ ጉባኤም ያላካሄደ
8. የኢትዮጵያን አንድነት ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኢአዴድ) – ጠቅላላ ጉባኤ ያላካሄደ
9. የመላው አማራ ህዝብ ፓርቲ (መዐሕፓ) – የመስራች አባላት ዝርዝር ያላቀረበ
10. የኢትዮጵያውያን አገር አቀፍ ንቅናቄ (ኢሃን) – የመስራች አባላት ዝርዝር ያላቀረበ
11. የደቡብ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኮንግረስ ( ደቡብ ኮንግረስ) – የመስራች አባላት ዝርዝር ያላቀረበ
12. የሸኮና አካባቢው ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ሸአሕዲድ) -ጠቅላላ ጉባኤ ያላካሄደ
13. ነጻነትና ሰላም ለኢትዮጵያ ህብረት ፓርቲ ( ነጻነትናሰላም) – የመስራች አባላት ዝርዝር ያላቀረበ

በሌላ በኩል ሌሎች 14 ፓርቲዎች ደግሞ ከቦርዱ በተደረገው ጥሪ መሰረት ሰነዶቻቸውን ከነአካቴው ያላቀረቡ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር መዋሃዳቸውን ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም የነዚህ 14 ፓርቲዎች እንዲሰረዙ ቦርዱ ወስኗል፡፡

በመሆኑም ሰነድ ባለማምጣታቸው እንዲሰረዙ የተሰወኑት ፓርቲዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡

1. የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ
2. መላው ኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
3. የከምባታ ሕዝቦች ኮንግረስ
4. የሐድያ ብሔር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት
5. የኦሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ኅብረት
6. የዲል ወቢ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ
7. የቤንች ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት
8. የስልጤ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
9. የአፋር ሕዝብ ነፃነት ፓርቲ
10. የሱማሌ አንድነት ፓርቲ
11. ነፃነት ለአንድነትና ለፍትሕ ፓርቲ
12. ብሔራዊ ተሀድሶ ለሰላም ልማት
13. የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ህብረት
14. የጋምቤላ ክልላዊ ንቅናቄ

ሁለት ፓርቲዎች ሰነዶችን ማቅረብ አለመቻላቸው በፓርቲው የውስጥ ችግር የተነሳ መሆኑ ስለታመነበት ጠቅላላ ጉባኤያቸውን የኮቪድ ወረርሽን በሚያበቃበት ወቅት አንዲያከናውኑ ቦርዱ ሲወስን ሌሎች ሰነዶቻቸው ግን ከላይ በተጠቀሰው መንገድ እየተገመገሙ ይገኛል፡፡

በልዩ ሁኔታ የሰነድ ካስገቡ ፓርቲዎች ጋር ሰነዶች እንዲታይላቸው የተደረጉ ፓርቲዎች

1. ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ( ኢዴፓ)
2. ወለኔ ህዝቦች ፓርቲ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

election 1

7 Comments

 1. ወ/ት ብርቱካን ምንም አልነኩትም እኮ 106 ፓርቲ ኢትዮጵያ ዉስጥ ምን ይሰራል? እነዛ ከዉጭ ተጠርተዉ ይሁን በሌላ ምክንያት የገቡት አዛዉንት እንዴት ከማስተካከያዉ አመለጡ። ከታገዱት የበዛዉ አማራ/አንድነት/የደቡብ ህዝብ የሚለዉ ነዉ እንደዉ ምን በደሉ ብዬ ስለነሱ ሳስብ እንደዉም ጠቅላላ የዘር ድርጅትን ድርግም አድርገዉ ቢያጠፉትና ኢትዮጵያዊ በዜግነቱ በሀገሩ ተከብሮ የሚኖርበትን ነገር ቢመክሩልን።

  እንግዲህ ለርሶም እንግዳ ነገር አይደለም ትምህርቶን ጨርሰዉ ሲመደቡ የአባቶ ስም የናቶ ስም ዘርዎ ለማስተያያነት በቀጣሪዎቾ አልታየም አንደዉ ያ ነገር ዛሬ አይናፍቆትም? ነገርን ነገር ያመጣዋል አረጋዊ በርሄ አንድ ሻንጣ ነገር ይዞ ከግደየ ዘራጽዮን ጋር መግባቱን እናስታዉሳለን ትንሺ ቆይቶ ትግራይ ትብብር ነዉ ምን የሚሉት ፓርቲ አቋቋምኩ አለ :ቢሮዉና ተቀማጭነቱ አዲስ አበባ ነዉ :ትግሬ ደግሞ ከአዲስ አበባ ብዙ ይርቃል በዚሁ ሁሉ ነገር የእርሱ ፓርቲ ደግሞ አልተባረረም ድጎማዉም አልተነሳም እንደዉ የዚህን ነገር እንቆቅልሹን ቢፈቱልን ሌላም አላስቸግርም።

 2. የፓርቲ ጋጋታ ለኢትዮጵያና ለህዝቡ ምንም አይጠቅምም ዳቦ የማያመጣ፡፡ እርግጥ ከዳቦ ነፃነትና መብት ይቀድማል ይባል ይሆናል ግን አሁንም ይህ ሁሉ የፓርቲ ጋጋታ ፋይዳ ቢስ ነው፡፡ Garbage –in – garbage –out ይመስላል፡፡ መንደርና ጎሳን የሚወክል ፓርቲ ምንም አይጠቅምም፡፡ እኔም አይቅርብኝ ይመስላል የፓርቲዎችን ስምና ሁኔታ ስናየው፡፡ የመናምን … አማራ፣ የምናምን … ፓርቲ እየተባለ የሚቋቋም ፓርቲ ለአገሪቷ አይበጅም፡፡ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ተሰጥቶ እንደነበረ አብዛኛዎቹ መዋሃድ ወይም merge ካላደረጉ በምርጫ ቦርድ መመዝገቡና እውቅና መስጠቱ ነገ ተጠያቂነት ሊያመጣበት እንደሚችል መታሰብ ነበረበት፡፡ እኒዚህ ትርኪምርኪ ፓርቲዎች ሁሉ ነገ ችግር ቢመጣ ጎሳ ለይተው ሊቧቀሱ እንደሆነ ሊታሰብብበት ይገባል፡፡

  ኢትዮጵያን አምላክ ይባርካት!!!

 3. ቦርዱ ጥሩ ስራ እየሰራ እንዳለ አመላካች ነው ። የፖለቲካ ፓርቲ እቁብ አይደለም ሁለትና ሶስት ሰው ተፈላልጎ እባካችሁ ቸግሮኛልና አንድ ላይ ሆነን እቁብ እንጣል እና የመጀመሪያውን ለእኔ ስጡኝ ተባብለው የሚስማሙበት ። ፖለቲካ ፓርቲ ሕዝባዊና አገራዊ ራዕይ ይዞ ያንን የሚመጥን ፕሮግራምና የአፈጻጸም መመሪያ አዘጋጅቶ ለተግባራዊነቱ ለመታገል ብቃትና ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦችን ያሰባሰበ ድርጅት እንጂ በአወኩህ አወኩሽና በጎጥ ተጠራርተው የሚያቋቁሙት ተማን አንሼ ጥርቅም አይደለም ።

 4. ፖለቲካ ፓርቲ ሕዝባዊና አገራዊ ራዕይ ይዞ ያንን የሚመጥን ፕሮግራምና የአፈጻጸም መመሪያ አዘጋጅቶ ለተግባራዊነቱ ለመታገል ብቃትና ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦችን ያሰባሰበ ድርጅት እንጂ በአወኩህ አወኩሽና በጎጥ ተጠራርተው የሚያቋቁሙት ተማን አንሼ ጥርቅም አይደለም ።

 5. Ethiopian National Election board is doing very good job. Please keep it up. It is difficult for Ethiopians to single out the differences in economic and other policies coming from 76 political parties. Now there is adequate time to consider merging of parties that have related policies. Members of political parties, please give priority for Ethiopia rather than other reasons. Merge and reduce the number of parties to become less than 10.

 6. EPRDF PP always by any means necessary made sure the sincere Engineer Yilkal Getnet does not get support from the diaspora, as EZEMA , Baladeras and alike who raise funds to bring in foreign currencies to Ethiopia .

  They know he got local support so they do
  not want him to get diasporas support , because then his party will become unbeatable and they couldn’t beat him easily as they did now by taking away his certificate, it is obvious he got so many records on the EPRDF PP criminal activities including this recent one that got his party expelled by the “electoral board ” so he is going to need a petition and other strong show of support to make sure he is in the arena .

  www .ethiomedia. com ›
  Ethiopia bars opposition leader from traveling to US – Ethiomedia

  https://www.ethiomedia.com/broadway/4340.html

 7. ኢንጂነር ይልቃል ጥራት ያለዉ ፖለቲከኛ ነዉ ዉይይቱም ክርክሩም እወቀትና ሀሳብ ላይ ያማከለ ነዉ። ለሚነሱት ነጥቦች በበቂ ሁኔታ ማስረጃዉን ያቀርባል የሚያቀርበዉም ሀሳብ ሚዛን ይደፋል። ይህን የበሰለ ፖለቲከኛ አደጋ ሊያደርስብን ይችላል ከሚል እሳቤ ከተወገደ የተወገደዉ ኢንጂነር ይልቃል ሳይሆን ዲሞክራሲ ነዉ። ይህ ነገር በድጋሚ ቢታይ መልካም ይመስላል። ኢንጂነር ይልቃል አረብ አገር ዜጎቻችን ላይ ጥቃት ሲደርስ፤ስለ አባይ ጉዳይ፤ ስለ ህገመንግስት ተብዬዉ የሰጠዉ አስተያየት የፖለቲካ ተክለ ሰዉነቱንና የመሪነት ብቃቱን የሚያሳይ ነዉ በእርግጥ ጠ/ሚኒስተሩን በተመለከተም የሚሰማዉን ይናገራል ይህ ጥርስ ዉስጥ ከቶት ከሆነ ያሳዝናል።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.