የኢትዮጵያ ዋና ዋና የእምነት ተቋማት በጋራ ስለሚሠሩበት ሁኔታ ውይይት ተደረገ

religion የኢትዮጵያ ዋና ዋና የእምነት ተቋማት በጋራ ስለሚሠሩበት ሁኔታ ውይይት ተደረገ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፣ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ ከኢትዮጵያ የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤትና ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አባቶች ጋር በስፋት ተነጋግረናል ።
በውይይቱ ላይ በእምነት ተቋማት መካከል አልፎ አልፎ የሚከሠቱትን ችግሮች በዘላቂነት ለመቅረፍ የሚያስችል መንገድ ለመዘርጋት፣ የሕዝቡን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ዐቅምን አቀናጅቶ ለመፍታት፣ ለአደጋ ጊዜ ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ ጠንካራ ተቋም በጋራ ለማቆም፣ በሕዝቦች መካከል መግባባትና አንድነት ለማምጣት ተቀናጅቶ ለመሥራት፣ ድህነትን ለመቅረፍ የሚያስችሉ የልማት ሥራዎችን በትብብር ለማከናወን፣ እንዲሁም የትውልዱን ሥነ ምግባር በጋራ ለመቅረጽ ሐሳብ ተለዋውጠናል።

abiy 2 የኢትዮጵያ ዋና ዋና የእምነት ተቋማት በጋራ ስለሚሠሩበት ሁኔታ ውይይት ተደረገ

የኢትዮጵያ ዋና ዋና የእምነት ተቋማት በሰላም፣ በማኅበራዊ ደኅንነት፣ በሥነ ምግባርና በዘላቂ ልማት በጋራ ስለሚሠሩበት ሁኔታ ውይይት አድርገናል።

የእምነት ተቋማት ያላቸውን መዋቅር ፣ ተሰሚነት፣ የሰው ኃይልና ተጽዕኖ ፈጣሪነት በጋራ ካቀናጁት የውጭ እጅ የምንጠብቅባቸውን ብዙ ችግሮች መቅረፍ እንደሚችሉ ገልጠዋል። ለዚህ ደግሞ ልዩነትን አክብሮ፣ የፖለቲካና የእምነት ድንበሮችን ጠብቆ፣ ነገር ግን ተጋግዞና ተናብቦ መሥራት ይገባል ሲሉ ሐሳብ ሰጥተዋል።

ከትናንት ይልቅ ዛሬና ነገ ላይ ማተኮር፣ ከግጭቶች ይልቅ በጋራ ዕሴቶቻችንና ዐቅሞቻችን ላይ መተባበር ኢትዮጵያ ዛሬ የምትፈልገው ነው። የእምነት ተቋማት በተቋም ምሥረታ ያላቸውን ልምድ በመጠቀም፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በአደጋ ሥራ አመራር፣ በድህነት ቅነሳ፣ በርዳታና በሥነ ምግባር ግንባታ ላይ የሚያተኩሩ ጠንካራ ሀገራዊ ተቋማትን በጋራ ቢመሠርቱ፤ ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካ እንደሚተርፉ እምነቴ ነው።

PMO

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.