በእስራኤል መንግሥት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የመጀመሪያዋ ቤተ እስራኤላዊት በሚኒስተር ደርጃ ተሾመች

በሚቀጥለው እሑድ ቀን(17/5/2020 ዓ/ም) 120 የእስራኤል የፓርላማ(ክኔሴት)አባላት የቃለ መሓላ ስነ ሥርዓት ይፈፅማሉ፡፡  ከነዚህ መካካል ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ቤተ እስራኤላዊት ወ/ሮ ፕኒና ታምኖ እሸቴ የመጀመሪያዋ የአዲስ ገቢዎች (አልያና ክሊታ) መሥሪያ ቤተ  ሚ/ር በመሆን ቃለ መሓላ ትፈፅማለች።

23 1
ወ/ሮ ፕኒና ታምኖ እሸቴ ከ“ካሆል ላባን”(ሰማያዊና ነጭ) ፓርቲ ሊቀመንበር ከጄኔራል ቤኒ ጋንጽ ጋር

ፕኒና ታምኖ ሸቴ (በኖቬምበር 1/1981 ዓ.ም ተወለደች)፡፡ በ 21ኛው የእስራኤል ምክር ቤት (ክኔሴት) በ‘ካሖል ላቫን’ ጥምር የፖለቲካ ድርጅቶች ሥር የም/ቤት አባል ነች፡፡ በ 19ኛውና በ 20ኛው የእስራኤል ም/ቤት በየሽ ዐቲድ የፖለቲካ ድርጅት ሥር አገልግላለች፡፡

ፕኒና በሙያዋ የሕግ ጠበቃ ነች፤ ቀደም ሲል በሬዲዮና ቴሌቪዥን መገናኛ ብዙሃን የሠራች ሰው ስትሆን በተለያዩ ማህበሮችና ሕዝባዊ ድርጅቶች የቦርድ አባልና ሊቀ መንበር በመሆን አገልግላለች፡፡

ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎቿን የጀመረችው በ 2000 ዓ.ም  መጀመሪያ  በችግር ላይ ያሉ ታዳጊ ወጣቶችን በምትረዳበት ወቅትና የሴቶች ዐቅም ግምባታ ላይ ስትሠራ ሲሆን፣ ከዚህ ጋር አያይዛም ልዩነትንና ዘረኝነትን በመቃወም ለእኩልነት በመታገል ንቁ ተሳትፎ ያላት አክቲቪስት ነበረች፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በዚሁ መስመር የምትገኝ በመሆኗና በምታካሂዳቸው እንቅስቃሴዎቿ በ 2016 ዓ.ም የሉተር ኪንግ አርማ እና በሃኬሬን ለየዲዱት በእስራኤል አርማ ተሸላሚ ሆናለች፡፡

22 1
ወ/ሮ ፕኒና ታምኖ እሸቴ በምርጫ ቅስቀሳ ላይ

በ 2012 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ለም/ቤት አባልነት ተመረጠች፤ በተመራጮች ም/ቤት የመጀመሪያዋ ፈር ቀዳጅ ኢትዮጵያዊት ሴት ነበረች፤  በዚህ የአገልግሎት ዘመኗም የም/ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ ሆና ተሹማለች፡፡ በ 20ኛው ም/ቤት በሴቶች ላይ የሚፈጸመውን አምባጓሮ  የሚታገል ሎቢ (ሽዱላ) አቋቋመች፤ እንዲሁም ለደረሰባቸው ችግር አዕምሯዊ ብቃት መቋቋሚያ ሎቢ ሊ/መንበር በመሆን አገልግላለች፡፡

ፕኒና፣ በእስራኤል ጎልተው ከሚታዩት ወጣት ሴቶች የም/ቤት አባላት አንዷ ነች፤ የእሷ አብዛኛዎቹ ድርጊቶቿ የሚያተኩሩት ለደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች ሲሆን፣ በዋነኛነት ትኩረት የምትሰጠው በእስራኤል የሚገኙትን ኢትዮጵያውያን በማጠናከር ነው፡፡ የም/ቤት አባል ሆና ባገለገለችባቸው ጊዜዎች የልጆችን መብት አስጠባቂ ኮሚቴ ላይ የጎላ ተጽዕኖ አሳዳሪ ስትሆን፣ ልጆችንና ለአደጋ የሚጋለጡ ታዳጊዎችን በተመለከተ ከፍተኛ መሻሻል እንዲያሳዩ ከማድረጓም በላይ ጾታዊ ትንኮሳና አምባጓሮን በትምህርት ሰዎች ላይ ፈጥረዋል በመባል ለሚከሰሱ ልጆች መከላከያ ይሆን ዘንድ በም/ቤቱ ሕግ እንዲደነገግ አድርጋለች፡፡

21
ከቀኝ ወደግራ፡ የእስራኤል ጠ/ሚ ቢንያሚን ኔታኒያው፤ የሀገሯ ፕሬዜንዳንት ርኡቤን ርብሊን፡ ወ/ሮ ፕኒና ታምኖ እሸቴ

በ 2015 ዓ.ም ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከአደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ በኋላ፣ ፕኒና ‘ አዲሱ መንገድ ‘ የተባለውን ፕሮግራምና በሕግና ፍትሕ መ/ቤት ዘረኝነትን መታገል ያስችላል በሚል መንግሥት የወሰነውን የፌልሞር ሪፖርት የማደራጀት ሃላፊነትን በመውሰድ የጎላ ሚና ተጫውታለች፡፡

በ 2014 ዓ.ም MOST INFLUENTIAL PEOPLE OF AFRICAN DESCENT (MIPAD) የተባለው ድርጅት፡ በዓለም ላይ 100 ተጽኖ አድራጊዎች ተብለው ከተዘረዘሩት አፍሪካዊያን መካከል፤ ወ/ሮ ፕኒና ታምኖ እሸቴንም  አካትቷል፡፡

በዚህ ዓመት The American Israel Public Affairs Committee (AIPAC) በዋሽንግተን ዲሲ፤ በሚያዘጋጀው ዓመታዊ ኮንፈረንስ፡ የአሜሪካ ፕሬዜንዳንት፣ የኮንግረስ እና በሺ የሚቆጠሩ ታዋቂ አሜሪካዊያንና እስራኤልዊያን በሚሳተፉበት ፤ ወ/ሮ ፕኒና ታምኖ እሸቴ ወደ መድረክ በክብር ተጋብዛ አስደናቂ ንግግር አሰምታለች፡፡

የም/ቤት አባል ፕኒና ታምኖ – ሸቴ በ 3 ዓመት ዕድሜዋ ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል የገባችው “በሚቭጻ ሞሼ ወይም በተግባረ ሙሴ” በ 1984 ዓ.ም ነው፡፡ ፕኒና የማስትሬት ዲግሪዋን በፐብሊክ ፖሊሲ በከፍተኛ ማዕረግ ከቴል አቪቭ ዩኒቨርሲቲ፣ የመጀመሪያ ዲግሪዋን በሕግ በቅሪያት አካዳሚት ኦኖ አግኝታለች፡፡

 

1 Comment

  1. እስቲ እናንተ ድረሱልን እንጂ አረብ አሰፍስፎ ሊበላን ነዉ። መንግስት የተባለዉም እናንተን እንደመማጸን አረብን ሂዶ ጉልበት ይስማል።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.