አባይ ወንዝ ምነው ለኢቶዮጵያ … አለ! – በቀለ    

Nileበዘመናችን እና በቀድመው ትውልድ በአባይ ወንዝ ያልተፎከረበት እና ያልተዘፈነበት አጋጣሚዎች የሉም። የተሰራ ስራ የለም ጊዜው ደርሶና በአምላካችን ፈቃድ ትውልድን ከርሃብ አገሪቷን ለብልፅግና የሚያነሳሳ ስራ ሲሰራ በ 1000 አመት የመጀመርያው ነው። 1 ሺህ አመት ያልኩት ግብፃውያን የወንዙን ፍሰት መለካት የጀመሩበትን ዘመን ለማመልከት ሲሆን። በአንፃሩ ደግሞ አባይን ለልማት ማዋል ቀርቶብን በተገቢው ሁኔታ ሳናጠናው እና የወንዙን ፍሰት መረጃ ሳንሰበስብ መቆየታችንን ለመግለፅ ነው። የፍሰቱን መጠን መረጃ ቢበዛ ከ100 አመት አይበልጥም አገራችን ያላት፣ የለም አፈራችንልም በደለል መልክ የሚጓዘው እንዲሁ ከዚሁ አመት መረጃነት አይበልጥም። ግብፅ የተመሰረተችው በአባይ ነው ይሉናል! ሌላ የመሰረታት አገር ስለአለ እውነት ነው። የአባይ ወንዝ ከኢትዮጵያ ከወጣ ጀምሮ በሚጠለው አፈር ሱዳንም ተጠቃሚ ስትሆን ግብፅ ደርሶ የህልውና መሰረታቸው የሆነው የእርሻ መሪት እና የህዝብ መኖርያ የሆነው ቦታ የተፈጠረው በኢትዮጵያ አፈር መሆኑን በአይኑ የተመለከተ ይመሰክራል። በግራና በቀኝ ወንዙ ባለፈባቸው በተለይ ናይል ደልታ ተብሎ የተጠሩትን አካባቢ የተመለከተ ወይ አገሪ ኢትዮጵያ ተንደሽ እዚህ ደረሽ ያስብላል ልብ ለአለው።ለግብፅም ሆነ ለሱዳኖች አሁን አፈር አያስፈልጋቸውም። ለም አፈርም ቢሆን በማዳበርያ ተተክቷል የሚፈልጉት ወሃ ነው።

ትውልድ እየጨመረ ነው የትውልዱ አስተሳሰብ ተለውጦል፣ በቀን ቢያንስ አንዴ መታጠብ የሚፈልግ ትውልድ እየጠበቀን ነው ፣ አገራችን ስለድህነቷ  ጥያቄ አምጥታለች ወደፊትም ብዙ የመብት ጥያቄዎች እንደምታነሰ ታሳቢ ነው። ግብፅች የሚሰሩት ለትውልድ ነው። ለመቶ፣ ለሁለት መቶ አመት፣  የአገሪ ኢትዮጵያ ጥያቄ ለዛሪ  ህዝቤን እንዴት ልመግብ ነው።በርሃብ በድንቁርና እየተሰቃየ ነው። ህዝቦቼ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ፣ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ያስፈልጋቸዋል እያለች ነው። ከአስዋን ግድብ በስተፍለፊት የተንጣለለው ሰው ሰራሽ ባህር በአውሮፕላን ሆነው ሲያዩት ከአፍሪካ ወጥተን ሌላ አለም የተቀላቀልን ያህል ይረዝማል በመረጃነት ስፍሮ የሚገኘው 550 ኪ.ሜ ርዝመት እና 35 ኪ ሜ ስፋት የሚለካው የግድቡ የውሃ ማጠራቀሚያ ቢሆንም በአሁኑ ግዜ ፣ ከ700 ኪ.ሜ ርዝመት በላይ የተንጣለለ ነው። በግራ  እና ቀኝ የሚታዩት የባህሩ ዳርቻ በወንዙ ውሃ ሞልተው ወደ ድንጋያማው ሜዳ ሰርጎ በመግባት ለመጪው ትውልድ  ሲጠራቀም ታይና ምነው እነዚህ አገሮች ውሃውን አትንኩብኝ አይሉን ከማለት ውጪ በመተከዝ ታልፈዋለህ። ግብፆ በትንሹ አገራችንን ኢትዮጵያ ለሁለት ምእተ አመታት ለማደኅየት ሰርተዋል ተሳክቶላቸውም አጥፍተዋታል። ወደ ሊላ ገብቶ ከመቀባጠር በአንድ ወቅት ኢትዮጵያ 20 ቢሊዮን ዶላር ብታገኝ እድገቷ ምን ያህል እንደሚሆን ሲተነብዩ ስሰማ አገራችንን ኢትዮጵያ እንዳትለማ፣እንዳታድግ ገቢዋን የሚቆጣጠ ተቋም እንዳለ ተረዳሁ። ለዚህም ነበር ወደአገር የሚገባውን የውጭ ምንዛሪ መቆጣጠር ስራቸው የነበረው። በጥናታቸው መሰረት የቀመሩትን እንዳይደርስ ስራዎችን ይሰራሉ። በተለይ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኃላ አገራት በደረሱበት የእድገት ደረጃ እነሱንም ጨምሮ እንዳንጠቅም ስራዎችን ሲሰሩ ቆይተዋል። የአለም ባንክ እና በተባበሩት መንግስታት ውስጥ ተሳተፎአቸው የጎላ ስለነበር የሚያስፈልገንን ልማት ይወስኑልናል ተርማል ኢነርጂ፣ የጉድጓድ የመጠጥ ውሃ ፣ ትናንሽ የእርሻ ልማት እና የመሳሰሉት ብቻ ጥቅም እንድናገኝ ሲያደርጉን ኖረዋል ። በአለም ባንክም ሆነ በእርዳታ የሚገኘውን ዶላር እየቀመሩ ያማክሩናል፣ መስራት ያለብንን ጭምር በተለይ በውሃ ሃብታችን ዙርያ የውጭ አማካሪዎች ስናስተናግድ ኖረናል ስሪታቸው ከግብፅ መሆኑ አሁን በቅርብ ዘመናትም ማገናዘብ አልቻልንም፣ የራሳችንም ዜጎች የሆኑ የሚንስተሮቻችን አማካሪዎች እንደነበሩ ሁሉ። በተለያየ ሁኔታ እና አጋጣሚዎች በብድር የምትገኘው አነስተኛ የውጭ ምንዛሪ በአገራችን ለውጥ ማምጣት ሳይችል ቀርቷል።ትንሽም በደርግ ዘመን የተጀመሩት ከ10 በላይ ትላልቅ የእርሻ ልማት ግንባታዎች ለፍሪ ባይበቁም መና ሆነው እንዲቀሩ ተደርገዋል።አገራችንን ለባለእዳነት ሲዳርገን   ከልማቶቹ የሚገኘው ጥቅም አገራችንን እንዳትበለፅግ ሲያደርግ ለሰራው አካል ግን የስኪቱ መገለጫዎች ነበር።

ግብፆች በአባይ ወንዝ መጠቀምን ከአገራችን በፊት እንዳልጀመሩ የሚያስረዱ የውሃ ልማት ስትራክቸር መኖራቸው፣በውሃ ሃብታችን ተጠቃሚ እንደነበርን ያስረዳል ።ቀደም ባሉ ዘማናት በነበረን ስልጣኔ ይጠቀሙባቸው የነበሩ የወሃ ማስተላለፍያ ግንቦች በአገራችን እንዳሉ ይታያል፣ እንዲሁም የዘመናዊ ፓንፕ ሳይኖር ትላልቅ በእንስሳ ሃይል እየተሽከረከረ ውሃን ከወንዝ የሚያወጣ ቴክኖሎጂንም ይጠቀሙ ነበር። ጥያቄው ለምን አልቀጠለም ነው! እውነት ነው አልቀጠለም፣ በአጭሩ አገራችን ጣርነትን የምታስተናግድ አገር መሆኗ ነው። የጥንታዊ ስልጣኔ በር ከፋች የሆነች አገር በተደረጉ ጦርነቶች እውቀቶቿ ተቃጠሉ ህዝቦቿም ተገደሉ ማን ያስረዳ የነበረ ሆነ። የተረፉትም መዛግብት ወደ ለሌሎች አገራት ተሰደዱ።

ወደዛሪው የአባይ ወንዝ ንትርክ የመግባታችንን ሚስጥር ግብፆች ለምን ውሃው ኢትዮጵያውያን ይነኩብናል እንጂ ያንሰናል ብለው አይደለም እላለሁ። አባይ ወንዝ ከአምላክ ለኢትዮጵያ የተሰጠ በረከት ነው ። ግብፅች የወንዙን ውሃ ለሚፈልገው አገልግሎት ለማዋል ፈልገው  በቂ ባይሆን  ወይም ኢትዮጵያ መጠቀም ብትጀመር የውሃ እጥረት ስለሚገጥመን አይበቃንም ብለው አማራጭ ማየትም የጠብቅባቸው ነበር፣ አያደርጉትም የተትረፈረፈ ወሃ ከአባይ ስለሚያገኙ ምንም ያህል ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ብታለማ አሁን ለደረሱበት እድገት እንቅፋት እንደማይሆን ያውቃሉ። ሆኖም የሚያስቡት ለቀጣዩ ትውልድ የመኖር ህልውና ነው። የህዝብ ቁጥር በሁለቱም አገራት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱ ያሳስባቸዋል።ኢትዮጵያ የወንዙን ባለቤትነት መብቷን  ስትጠይቅ ቆይታለች፣ ግብፅ በዚህ በሰለጠነው ዘመን የተፈጥሮን ወንዝ ውሃ በአለም ደረጃ ህግ ወጥቶለት ሲተገበር አላየሁም ማለቷ የሚያሳዝን ነው። የአለም የወንዝ የውሃ አስተዳደር ህግጋትን ተግባራዊነት በአግባቡ በተጠቀመችበት ነበር። ግብፅ እያባከነች ያለውን የተፈጥሮ የውሃ ሃብት የሚያሳዝን ነው። በሌሎች የመጠቀም መብት ባላቸው አገራት የሚነሱትን ፍትሃዊ የሆነ የውሃ ሃብት ባለቤትነት ጥያቄዎች መመለስ ይኖርባታል። አብሮ  ስራዎችን መስራት የሚጠቅመው ለመላው አፍሪካ ነው።የውሃው  የአጠቃቀም ስራቶቿን አስተካክላ አለም ባስቀመጠው  ቆጥቦ የመጠቀም ስራቶችን ተግባራዊ ማድረግ መጀመር ይጠበቅባታል። ለትውልድ የምታስብ ከሆነ የአለም ህዝብ አንድ ሆኖ እየሰራ ባለበት ለእራሴ ብቻ የሚለው በዘመናችን የማይሰራ አስተሳሰብ ነው። ካይሮ ውስጥ አባይን የተመለከተ አባይ ወንዝ ስንት ነው ብሎ መጠየቁ አይቀሬ ነው።  እውነት ነው ትልልቅ 3 ወንዞች ተለያይተው እየፈሰሱ ወደሜትራንያን ባህር ይቀላቀላሉና።

ትልቁ አባይ የሚያለማውን ትልልቅ እርሻዎች ውሃ አጥግቦ ቀሪው አባይ ተኮፍሶ ወደ ሜድትራንያን ባህር የሚፈሰውን አንድ ትላለህ ። ሁለተኛው ከእርሻ መሪቶቹ  በፍሳሽ ማስወገጃ  (Drainage ) የተሰበሰበው ውሃ  ነው ሌላ አባይ ወንዝ ሆኖ የሚፈሰው።  ሶስተኛው የሚዘገን  ከተማዋን የሚያጥበው የአገሪ ህዝብ ለመጠጥ የሚናፍቀው ውሃ ስታይ ነው ፣ ለቤት ወስጥ አገልግሎት ሰጥቶ በፍሳሽ ማስወገጃ (sewerage) ከየቤቱ ተጠራቅሞ የሚፈሰው ከአንደኛው አባይ የማይተናነሰው ወንዝ ነው። አራተኛ ብዬ ባልገልፀውም ከዋናው አባይ ተወስዶ ሆሪዞንታል ኤክስፖንሽን (Horizontal Expansion

) ብለው ለሚጠሩት ፕሮጀክት ለልማት የሚውለው ሰው ሰራሽ የውሃ ማስተላለፍያ ወንዝ  ነው ። በአመት 10 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ እንደሚያስተላልፍ እገምታለሁ። የአረብ አገሮች ለግብፅ ወግኘው በአገራችን ላይ መነሳታቸው የሚገርም አይደለም፣ የዚህ ፕሮጀክት በለውለታዎች ናቸውና፣ ወደፊትም ከሚገኘው ልማት ተጠቃሚዎች ናቸው። በግብፃውያን የሚወዳሱ አባቶች አድርጓቸዋል። የአሚር ስሞች እየጠሩ ከዚህ እስከዚህ ያለው ኪ.ሜ የሰራ ነው ትብሎ ስማቸው ይነሳል።

በአሁኑ ሰአት የሱዳናውያን ሃሳብ መቀያየር የማይመች ቢሆንም ፣የሱዳኖቹን አቋም ብዙ ትኩረት የምንሰጠው መሆን የለበትም, ለራሳቸው ሲሉ የሚተገብሩት ነው።  በነገሮች ላይ ግዜ ማራዘምያ ትሆናለች። ከኢትዮጵያ ጋር የሃሳብ ልዩነት መታየቱም ተገቢ ሊሆን ይችላል ውጥረት ላይ ስለሆነች ወደፊት የካፈ ችግር በኢትዮጵያ በኩል ስለሚገጥማት አስተሳሰቦች ይስተካከላል እላለሁ። በቀላሉ የአባይ ወንዝ የውሃ ንፅህና የሚያጠቃው እነሱን በመሁኑ ቀረበው የጀመሩትን የትብብር ስራዎች መስራታቸው አይቀሪ ነው። የማንፈራው ግን የምንጠነቀቀው ለሩቅ ለአለየለት ጠላታችን ነው ። ለሚጠብቀን ችግሮች አፀፋውን ለመመለስ መዘጋጀት አለብን። ግብፆችም ቢሆኑ የጣርነትን አላስፈላጊነት ያውቃሉ በቀደም ዘመናት ሞክረው አልተሳካላቸውም፣ አሁን ደግሞ ኢትዮጵያም የተደራጀ የጦር ሃይል አላት። ግብፅቹ ጦርነት የተሻለ አማራጭ አለመሆኑን ይረዳሉ እስከዛሪ  ብዙ ባጀት መድበው አንድነታችንን ለመናድ የሚሞክሩትም ይህንን ታሳቤ አድርገው ነው።በአገራችን ሰላም እንዳይሰፍን ለተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ድጋፍ ባልሆኑም ነበር። አሁንም እየሰሩ ያለውም ይሄንኑ ነው። እርስ በርስ ወደጦርነት እንድንገባ መታገል። ግብፅ ጠበብት ሳይንቲስቶች የሚመሯቸው በከፍተኛ ባጀት የሚንቀሳቀስ ተቆም ያላት ፣ የፖለቲከኞቻችንን እና  የህዝብን ስነ ልቦና የሚያጠና ብሎም የሚሸረሽር ስትራተጂ የሚነደፍበት አገር ናት። አገራችን ውስጥ በራሳችን ባለስልጣናት፣ ሙያተኝኞች ከተራ ሰራተኛ ጀምሮ የምታሰልፈው ባለ ጥቅም ያፈራች በሰፊው የተዘረጋ መዋቅር ያላት አገርም ናት ። አገር የሚያጠፋው ፈንጂ ወርዋሪዎቹ እኛው ነን።

በአንዳንድ የየሃድሮ ፖለቲካው ምሁራኖቻቸን የሚሰጠውን የአለም ባንክ ሆነ የአሜሪካ ጣልጋግበነት  በአገራችን የሚፈጥረውን እና የሚመጣውን ሁኔታ የከፋ ነው ብዬ አላምንም። ችግር ፈጣሪው የግብፅ እጅ መስራት የሚገባውን አቁሞ አያውቅም ወደፊትም አይለውጠውም። ሆኖም ግን በመንግስታችን መሰራት የሚገባውን የዲፕሎማት ስራዎች መቀጠል አለበት። ለእኛም የሚረዳ አካል እንዳለ ማስብ አለብን። አፍሪካኖችን ተፅእኖ ማምጣት ሊሰራ የሚችለው NBI ውስጥ ተሳታፊ አገራት በነበራቸው አቋም ፅንተው ፍትሃዊ የሆነውን የውሃ አከፋፈል ስምምነት ግብፅ እንድትቀበል በማድረግ ይጀምራል ወደፊት  የሚታይ ነው። ወዳጃችን አገር ከምስራቅ አፍሪካ አገራት በቅርባችን የምትቆመው ኤርትራ ብቻ መሆኖን ማጤን ይኖርብናል። ከጎረቤት  ኬንያ የተሳሰርነው በወሰኖች አካባቤ በሚኖሩት ህዝቦች ጥቅም እንጂ በአገር ደረጃ የተከናወኑ ስራዎች አለመኖራቸው ለኢትYኦጵያ ብላ ስራዎችን እንደማትሰራ ይገመታል ። ኡጋንዳ የአባይን ውሃ በነፅነት መምልከት እንድትችል ስለሚያደርጋት አብራን የምትቆም ትሆናለች። ሌሎቹ የወንዙ ተጋሪ አገራት አስተሳሰባቸው የቀኝ ግዛቱን እድሜ ከኬንኛው ጋር ሰለሚያመሳስላቸው ተፅእኖ የመፍጠር ባህርይ ጎልቶ ሊታይ አይችልም።

ለአገራችን ኢትዮጵያ የሚበጀው መፍትሄ ህዝባችን አንድነት ላይ የተመሰረት ቆራጥነት ሲኖረን ነው። የግድቡን ስራ መቀጠል አለብን፣ ግብፆች ምንም ይበሉ ምን አሁን እንደተጀመረው የውሃ መሙላት ስራዎቻችን በታቀደው መሰረት በዚህ አመት መጀመር  አለብን።ለጦርነትም ቢሆን አየር ሃይላችንን ማደራጀት ይኖርብናል ። ገፍተው ከመጡም አንድ የጦር ጀት ማብረር አያቅተን ። አስዋን ግድብ እንደ እንቁላል የሚጠብበቅ  ነው እግዚያብሔርም ከእኛ ጋር ነው  ግድቡ አይደል ካይሮ የምትባል የግብፅ ከተማ አትኖርም። በግብፆች በኩል የሚነሱት ልጅን ጅቦ እንዳልጠራው አይነት የልጆች ማስፋራሪያዎች እየሆነ መጥቷል ፣ የሚጥቅማቸው ከኢትዮጵያ ጋር ተስማምቶ መኖርን መልመድ  ነው። እኛም ብንሆን ትንሽ የዲፕሎማቲክ ግንኝነቶች ይጠበቅብናል፣ ከ20 አመት ገደማ በፊት አስተሳሰባቸውን አርግበው በመቅረብ የተለያዩ በጋራ የሚያሰራን ሃሳቦች የሚያነሱ የፕሪዜዳንት ሙባረክ ዲፕሎማት ፣ባለስልጣነት እና የውሃ ሃብት ሙሁራን ነበሩ ፣ በዚህ ወቅት አብዛኛቸው በስራው ቦታ ብይኖሩም የተሻለ ብስለት አላቸው በዲፕሎማሲው ስራ ቢክተቱ ጥሩ ነው እያልኩ። ማንም ጣልቃ ገብቶ ለማደራደር የሚደረግ ጥረት እኛ እስካልተስማማን ድረስ የምንሰራውን ሊያስቆመን አይችልም። ግድቡ ሲጀመር በግብፅች ፈቃድኝነት ላይ ተመስርቶ በመሆኑ አንድን ሉአላዊ አገር ተገቢ ባልሆነ ምክንያት ተፅእኖ ይደርስበታል ማለት አንችልም። ድርድራችንን አሁን በተያያዘው የድርድር መርሃ ግብር መቀጠል የምንሰራውን እየሰራን ነው እላለሁ።

አገራችንን ኢትዮጵያን እግዜያብሒር ይጠብቅልን

በቀለ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.