እናንተና ዶክተር አብይ ከመስከረም 30 በኃዋላ እኩል አይደላቸሁም – ወንድማገኝ

abiyሰሞኑን የህዝቡን የልብ ትርታ ለማዳመጥ ይሁን ወይንም የማተራመስ አመላቸዉ ተነስቶባቸዉ ባይታወቅም በማስፈራሪያና በትእቢት የተሞላዉ የአቶ ልደቱና የአቶ ጁሀር እንዲሁም የአቶ በቀለ ገርባ የተናበበ በሚመስል መልክ ከመስከረም 30 በኃዋላ ማንም ከማንም አይበልጥም የምትለዋ ከንቱ ድንፋታ በምንም መመዘኛ አሁን ካለዉ መንግስት ጋር አሁንም ሆነ ከመስከረም 30 በኋላ ቀቢጸ ተስፋ ካልሆነ በቀር እኩል የሚያረጋቸሁ ህጋዊም ሆነ ሞራላዊና ህዝባዊ መሰረት የላቸሁም፣ ብዙ ምክንያቶችን መዘርዘር ይቻላል፣ ከብዙ በጥቂቱ ግን :

1ኛ የኢትዮጵያ ህዝብ ከዳር እስከዳር ለ 27 አመት ይደርስበት የነበረዉ ስቃይና መከራ እንዲያቆም የታገለዉና አሁን ለደረሰበት ለውጥ የበቃዉ ህዝብ የስልጣኑ ባለቤት አንዲሆንና እራሱ በመረጠው መንግስት እንዲመራ እንጅ በየምክንያቱ ብልጣ ብልጦችና ጉልበተኞች እንዲረግጡትና እንዲመዘብሩት ስላልሆነ ከአሁን በኋላ ህዝብ መርጦ ከሚያስቀምጠዉ መንግስት ውጭ የኢትዮጵያ ህዝብ ሰርጎ ገቦችንም ሆነ በአቋራጭ ወደስልጣን የሚመጡትን ተቀብሎ ለማስተናገድ አቅሙም ትእግስቱም የለዉም፣ በህዝብ የተመረጠ መንግስት መምጣት እዉን መሆን ድግሞ በዶክተር አብይ መንግስት እየተሰራ ያለዉ የምርጫ ዝግጅት ተስፋ የሚያሰጥ ስለሆነ ይህ አለም አቀፍ ወረርሽኝ እስኪያልፍ ድረስ እነዶክተር አብይ እንጅ ልደቱን፣ ጁሃርንና በቀለን የመሰሉ ጽንፈኞች መጥተዉ እንዲመሩት የኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎት አይደለም።በዛ ላይ የምርጫ ህግን ተከትሎ ከየአንዳንዱ ህዝብ የድምጽ ካርድ ባይሰጠዉም ዶክተር አብይ የለዉጥ መሪ ሆነዉ ከሁለት አመት በፊት ወደ ስልጣን ሲመጡ የኢትዮጵያ ህዝብ ከዳር እስከዳር ከሀገር ውስጥና እስከ ሀገር ዉጭ ያሳየዉ ድጋፍ እንደ የህዝብ ይሁንታ(VOTE OF CONFIDENCE) ሊወሰድ ይገባል።እናንተ ግን የሚከተለን ህዝብ አለ አላችሁን እንጅ አንዳንዶቻችሁ የምርጫ ቦርድ የሚጠይቀዉን የአራትና የአስር ሺ ሰዉ ፊርማ አሟልታችሁ እንኳን ለማቅረብ እንዳልቻላችሁ ነዉ የምንሰማዉ ታዲያ ምርጫ ቢደረግ በዘጠኝ ሽ ሰዉ ድምጽ ነዉ ለስልጣን የምትበቁት? ያ በራሱ እኩል አያደርጋችሁም::

2ኛ ዶክተር አብይ ለህዝብና ለሀገር ያላቸዉን ፍቅርና አክብሮት እንዲሁም ፈሪሃ እግዚአብሄርነታቸውን ለመተቸት እነ አቶ በቀለ ገርባ ምንም የሞራል ብቃት የላችሁም። አወ ስታስገድሉ ስታዘርፉና መረን በለቀቀ መልኩ ህዝብን ለብጥብጥ እንዲነሳሳ ባደባባይ ስትናገሩ እርምጃ አለመዉሰዳቸው ደካማ ሊያስመስላቸዉ ይችላል ግን ትእግስትን ይቅር ባይነትን የመናገርና የመጻፍ ነጻነትን እንዲህ እየታገሱ ካላለማመዱትና እንዳለቃችሁ ወያኔ ማሰርና መግረፍ ቢጀምሩ ለዉጡ ከምኑ ላይ ነዉ? እርግጠኛ ነኝ ከልክ ሲያልፍ ግን የሳቸዉም ትእግስት የሚያልቅበት ጊዜ ይኖራል፤ ያ በራሱ እኩል አያደርጋችሁም::

3ኛ ዶክተር አብይ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ስልጣን ከያዙበት ጀምሮ የታስረዉን ሲያስፈቱ፣ ስደተኛዉን አቅፈዉና ደግፈዉ ሲመልሱ፣ መሳሪያ ያነገቡትን መሳሪያቸዉን ጥለዉ ለሀገራቸው ምድር እንዲበቁና በሰላም እንዲታገሉ ሲያደርጉ፣የተከፋፈሉ ሀይማኖቶችን አቀራርበዉ ወደ አንድ ማምጣታቸዉ፣ በጦርነት የሚፈላልገዉን የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝብ ወደ ወንድማማችነት ሲያመጡ፣ አዲስ አበባ የጸዳችና ያማረች ዋና ከተማና የአለም ቱሪስቶቹ መናኀሪያ እንድትሆን ፕሮጀችት ቀርጸው ቤተመንግስቱንና አዲስ አበባን የማስዎብ ስራ ፕሮጀክቶችን ሲያንቅሳቀሱ፣ የከተማን ቆሻሻ ለማጽዳት መጥረጊያ ይዘዉ በመጥረግ ያሳዩት አርያነት፣ ወደፊት የአለም ስጋት የሆነዉን የአየር መበከል ቀድመዉ በመገንዘብ ኢትይጵያን ከአየር ብክለት ለመከላከል ሲሉ ያደረጉት በቢሊየን የሚቆጠር የችግኝ ተከላና የችግኝ ተከላ ዝግጅት፣ በሱማሌ ክልል ያለዉ አንጻራዊ ሰላምና የልማት እንቅስቃሴ ያበረከቱት የመሪነት ብቃት፣ ኢህአዴግ የተባለዉን ከፋፋይ ፓርቲ አፍርሰዉ ሁሉንም እኩል የሚያስተናግድ ፓርቲ መመስረታቸዉና ባጠቃላይ በፖለቲካዉ፣ በማህበራዊና በኢኮኖሚ ዘርፉ ያከናዎኑትን ስራወች ወደፊት ታሪክ በዝርዝር የሚያቀርበዉ ስልሆነና በእናንተ በኩል ግን አባሎቻችሁም ሆኑ ተከታዮቻችሁ ምንም አይነት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ስታደርጉ ስላላየናችሁ   ያ በራሱ እኩል አያደርጋችሁም::

ዶክተር አብይ በመደመር ፍልስፍናቸዉ  ለኢትዮጵያ ያላቸዉ ሀገራዊ አንድነት፣ ሀገራዊ ኩራትና ሀገራዊ ብልጽግና ራእይ አንጻር ከአንዳንዶቻችሁ የከፋፋይነት ፍልስፍና ጋር ሲመዘን ያ በራሱ እኩል አያደርጋችሁም

እኩል የምትሆኑት ግን (ግለሰቦች ሳትሆኑ ፓርቲያችሁ) የኢዜማዉ ፕሬዜዳንት ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ እንደሚሉት በጨዋታዉ ሜዳ ላይ የጨዋታውን ህግና መራጩን ህዝብ አክብሮ እራስን ለምርጫ ማዘጋጀትና እንደምትሉት በልምድና በትምህርት ያካበታችሁት እዉቀት ካላችሁ ገዢዉንም ፓርቲ ይሁን ሌሎችን በሃሳብ ሞግታችሁ የሃሳብ የበላይነታችሁን ለህዝቡ ማሳየት ነዉ የፕለቲካ ብስለትና ማንም ከማንም አያንስም ሳይሆን መብለጥም ይቻላልና አሁን ካለው ችግር እንዴት እንዉጣ የሚለዉን በየዘርፉ ካሉ ባለሙያዎችና ከህዝብ ጋር እየተመካከራችሁ ወደፊት የሀገርን መሪነትን ስልጣን ብታገኙ እንኳን የህዝብ ተቀባይነት እንዲኖራችሁ በሃላፊነት ስሜት ተንቀሳቀሱ ስልጣን ቀሪ ነዉ እኛም ሟቾች ነን ሀገርና ህዝብ ግን ቀጣዮች ናቸዉና ልብ ይስጣችሁ ሰከን በሉ።

ወንድማገኝ
ከሰሜን አሜሪካ

1 Comment

 1. ፀሐፊው አንድና አንድ ብቻ ነው የሚያስረዳው፣ የኢትዮጵያ ሁኔታ ባለበት የአሁኑ ሂደት ጠ/ሚሩ እያንደፋደፉ ይቀጥሉበት ነው። ምናልባት ጸሐፊው ሰሜን አሜሪካና ኢትዮጵያ በምን ርቀት እንደምትገኝ አቅራቢ መነፅር ቢያደርግየተሻለ ይመስለኛል።
  ከላይ የተዘረዘሩት ገለፃዎች አልፊ ሙግቶች ለመሆናቸው አደብ ገዝቶ መወያየት ይበልጥ ጠቃሚ ነው። አንድን መንግሥት አንድን መሪም መሞገስ ግላዊ መብት ነው ግን ጭልጥ ያለ ድጋፍ ግን አምልኮት መሰል ስለሆነ፣ እምነትንና የፓለቲካን ሂደትን ማደባለቅ ከባድ ስህተት ነው።
  ወደ ቁም ነገሩ ስንመለስ፣ የጀዋር ጠላትነትን መድገም አልፊ ጉዳይ ነው ።የርሱን መንጠራራት እና ሥርአት አልበኝነት ፈቃጁ ይሄው መንግሥት ነው።ወሳኝና አቅመቢስነትን በትእግስት መተርጎም በተጨማሪ በጊዜው ያስጠይቃል
  ። በህጉ መሰረትና በተጨማሪ የወጣው የሽብርተኝነት አዋጅ ቅሊንቶ ቀርቶ ሌላም የሚያስወርደው ለመሆኑ ቢዘረዘርም፣በርሱ ፋንታ ንጹሐን ጋዜጠኞች ፣ፓለቲከኞች፣ የሰብአዊ መብት ታጋዮች ወዘተ ለእስር ተዳርገዋል። ይህ ደግሞ ታጋሽነትን ሳይሆን የሃሳብ ተቀናቃኝን መቋቋም አለመቻሉን አጣቃሽ ነው።
  የሰው ልጅ የእኩልነት መታያው በመጀመሪያ በመፈጠሩም ሲሆን የተባበሩት መንግሥታት ይሄንን ያለገደብ ሲያስቀምጥ ፣ኢትዮጵያም አሁን እንኳን ባላት ህገ መንግሥት ብትቀበለውም ፣መሬት ላይ ያለው ሐቅ ግን በክልል የተሸነሸነው ኢትዮጵያችን ከአማራው ክልል በስተቀር ይሄንን ህግ በተግባራዊነት ያሳዪ የሉም።እንዲያውም ክልሎቹ የማጥቂያ መሣርያ አድርገውታል። የጥቅሉን ሂደት ትተን ወደ ግላዊ ስብእና ስንመጣ ይሄ መንግሥት በተለይም ጠ/ሚሩ የሚፈሩት ከአይምሮ የፈለቀን ትግልን ነው ።ለዚህም ነው አሁን የገዢነት እድሜ ለማራዘም የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። ይሄ ካልሆነማ ለምን ተቀናቃኞች ስብሰባ ሠላማዊ ሰልፍ እንዳያደርጉ የሚከለከሉት። በተቃራኒው ብልፅ(ግ) ና እንዳሰኘው መሰብሰቢያ ቦታ ፣የመንግስት ሜዲያንና ገንዘብን የሚጋልብበት። አስቲ የሃሳብ አብላጫ ከሆነም ተቀናቃኞችን በእኩል ሜዳ ይወዳደሩ። ውጤቱ ስለሚታወቅ አይደረግም። የጨቋኝ ዋናው ፍርሃት የሃሳብን አሸናፊነት ስለሆነ መከልከልና ማሰር መርሃ ግብሩ ነው።
  ከኤርትራ ጋር የተባለው ሰላም ፣ፀሐፊው የሚያውቀው ምስጢራዊ መረጃ ከሌለ የኢትዮጵያ ልጆች ምንም የተገለፀላቸው ፣ውል ቀርቶ አረፍተነገርም የለም። የምእራባዊያን ጀሌዎች ለመሆንና የልመና ገንዘብ ከማቀራመት በስተቀር እስቲ ካልተፈራ ሰነዱ ግለፅ ይሁን።ወያኔ ኤርትራን አስገንጥሏል ፣ለዚህም የአሁኑ ጠ/ሚር በሕወሓት ተኮትኮ ያደገ ለመሆኑ የአልጀርሱን የሚባለውን ስምምነት ያለቅድመ ሁኔታን ተቀብሎ ዘላለማዊ ሲያደርግ ፣ያውም ውክልና የሌለው መንግሥት ፣ወደፊት ደግሞ ይህ ከኢሳያስ ጋር ጭድ ያቃጠለ ፍቅር ወደየትኛው ቀጣይ የኢትዮጵያ እዳ ተረኞች እንደሚጋር ጡን ብንጠረጥርም ፣አምላክ ይሰውረን።
  አዲስ አበባ ስታምር የአዲስ አበባ ተወላጆችና ነዋሪዎች ደስታቸው መጠን የለውም። ፀሐፊው እንደሚለው ግን አአደባባይ አማረ፣ቤተመንግስት ታደሰ ወዘተ …እያለ የሚጠቅሰው ከጀርባው ያለውን የፓለቲካ ሸር በከንቱ ውዳሴ ለማሳመን ነው። ከምክትል ከንቲባው ሹመት ጀምሮ ያለው የልዩ ጥቅም ፍላጎትን እሳቤ አለመገንዘብ ብቻ ሳይሆን በሰፊው አጎብዳጅነትን ያመላክታል ። የምኒልክ ቤተመንግሥት ከቤተመንግሥትነት መሆኑ ቀርቶ እየተሸረሸረ የአንድነት መናፈሻ ሆኗል ።ታሪክ በክፉም በደጉም ሐገራዊ በመሆኑ ተረኛ ባይ ሁሉ መሰረዝ መደለዝ የለበትም ።ይሄንንም ከሌላው ዓለም መማር ነበረብን ። የመስቀል አደባባይን ተመሳሳይ እድል ገጥሞታል ማፅዳትና መለወጥ ለየቅሉ ናቸው ። የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ጥላቻ ከበፊት ከባእድ ጠላቶች ጀምሮ አሁንም ተከታይ ዘረኞች የሚያካሂዱት የጥላቻ ዘመቻ ነው። ትልቁ ጥያቄ ግን አሁን በኮሮና ወረርሺኝ ጊዜ 2,5 ቢሊዮን ብር ለዚህ ግንባታና ቤት ላፈረሱባቸው፣ብሎም በወረርሽኙ ለተጎዱት የንግዱ ሕብረተሰብ ክፍል መልሶ ማቋቋሚያ ድጎማ ባይሆንም በብድር ማነቃቃት አንገብጋቢ ና ቀዳሚ ስራ ነበር።ቂን ቂንና ልታይ ልታይ ማለትም ለሚወዱ ከንቲባና ሐገር መሪ ሌላ የሚጠበቅ ነገር አለመኖሩ ግን ያሳዝናል።ያው ጊዜም አላፊ ለመሆኑ ሕወሓት መስክሮልናል።
  ስለ አየር ብክለት የተጠቀሰው ፣የዛፍ ችግኝ ትክክል ሆኖ አሁን በአጭር ጊዜ ጉዞ ምን የሚለውን አያካትትም ።የአውሮፓ እና ከሌላ ቦታዎች የሚመጡ ዘመን ያስቆጠሩ መኪናዎች ፣ፀሀፊው አማረች የሚላት አዲስ አበባና ሌላ ትላልቅ ከተሞች በተበከለ አየር ኑወሪዎችን ንፁህ አየር አሳጥቷል ። ፀሐፊው የአየርን እንክብካቤ በአቅምም ሆነ በሃሳብ ደረጃ አኳያ ለምሳሌነትና ለምክር ቢለግስ ትምህርታዊ በሆነ ነበር። ግና ምን ያደርጋል ፣የ ጠ/ሚሩ የ cyber ወታደሮች በውዳሴ ከንቱነት ተሰማርተዋል ። በዚህ አንድ ገፅ በማይሞላ ጽሑፍ ሰውዬውን 6ት ጊዜ ሲያነሳ በተዘዋዋሪ ደግሞ በግማሽ ገፅ ገልጾታል ። መጀመሪያ ንባብ ላይ ያልተገለፀልኝ በድጋሚ የገባኝ ፣ለካስ ግንቦት ሰባትን ከነአለቃቸው ለማወደስ የቀረበ ሙጥኝ ነው።
  ምርጫው መጥቶ ይሄን አወናባጅ የሕወሐት ርዝራዥ መዥገርን ነቅሎ እንደሚያላቅቀን ሙሉ እምነት አለኝ። ያኔም እንደሰውዪው አላየሁም አልሰማሁም እንዳትሉን ።
  ኢትዮጵያ ዘላለማዊ ናት

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.