ልጆቹን የበላ ጅብ አልጮኸ አለ – ያሬድ ኃይለማርያም

Denbi Delo Students ethiopian registrar..ከዛሬ ነገ ያሉበትን ሁኔታ አፋኞቹ አካላት እደ ቦኮሃራም ደፈር ብለው ኃላፊነቱን ወስደው እንዲህ አረግናቸው ወይም በእጃችን ላይ ናቸው ብለው ይናገራሉ ወይም ጉዳዩን ለእኔ ተውልኝ ያለው መንግሥት ቁርጣችንን ያሳውቀናል ብለን ስነጠብቅ ግማሽ መንፈቅ ሊሞላ ነው። ያህያ ባል የመሰለው መንግስታችን እና በጅብ የሚመሰሉ ታጣቂ ቡድኖች በተገጣጠሙበት አገር የዜጎች እጣ ፈንታ ይሄው ነው። ታፍኖ የደረሱበት ሳይታወቅ መቅረት፣ በመንጋዎች መደብደብ፣ መዘረፍ እና በሰላም የመኖር ዋስትና ማጣት። በህውሃት ዘመን ጅቡ መንግስት ነበር። አፋኙም፣ ገዳዩም መንግስት ነበር። ዛሬ ደግሞ መንግስት ያህያ ባል ሆኖ ሌሎች ጅቦች ተፈጥረዋል።

በእነዚህ ልጆች ጉዳይ ከዚህ በኋላ ሙሉ በሙሉ ተጠያቂው መንግስት ይመስለኛል። ለዜጎቹ፤ ሊያውም ኃላፊነት ወስዶ ከቤተሰብ የተረከባቸውን ተማሪዎች ከጥቃት መታደግ ባለመቻሉ ብቻ ሳይሆን ከዚህ ሁሉ ወራት ቆይታም በኋላ በቂ ምርመራ አካሂዶ የደረሰበትን ውጤት ለቤተሰቦቻቸው ማሳወቅ ባለመቻሉ መንግሥት ኃላፊነቱን እየተወጣ አይደለም። ከአቅሜ በላይ ነው ማለትም አንድ ነገር ነው። ግን ዜጎች ከመንግስት አቅም በላይ የሆነ ቡድን በአገሪቱ ውስጥ ይንቀሳቀሳል ብለው ማሰባቸውም በራሱ ሌላ መዘዝ አለው።

ብዙ ጊዜ የእነዚህን ልጆች ጉዳይ ስናነሳ ልጆቹ እራሳቸውን ደብቀው ነው እያላችሁ የምታላግጡና መንግስትን የተከላከላችሁ መስሏችሁ የምትሟገቱ እርህራሄ የራቃችው ሰዎች አንድ የሳታችሁት ነገር አለ። እንኳን አሥራ ሰባት ተማራዎች ይቅርና አንድም ግለሰብ እራሱን ከመንግስ ሰውሮ ለስድስት ወር ያህል በአገሪቱ ግዛት ውስጥ መቆየት ከቻለ የመንግስት የጸጥታና ደህንነት ዘርፋ እጅግ ደካማ ነው ማለት ነው። አገሪቱን እና ዜጎቿን ከጥቃት መታደግ አይችልም ማለት ነው። ከዚህ በኋላ ልጆቹ የት ናቸው ብዮ አልጠይቅም። በዚህ ጉዳይ መንግስትን ቀጥተኛ ተጠያቂ ማድረጊያው ወቅት ላይ የተደረሰ ይመስለኛል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጃንሆይና ሚያዝያ 27 - ሊታይ የሚገባው ወቅታዊ ዘገባ

1 Comment

  1. The Ethiopian federal military Defense forces are weak . Sudanese military had invaded Ethiopian territory stealing cattles and burning houses in Ethiopia between five and ten kilometers deep inside Ethiopia , planing to continue heading to GERD with heavy military artillery , the Ethiopian border patrols are unable to match the attacks from Sudan without the Ethiopian Federal Military Defense Forces providing assistance to secure Ethiopia’s border by Gondar.

    የሱዳን ጦር በምዕራብ አርማጭሆ በአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ላይ ተኩስ መክፈቱ…

    https://www.satenaw.com/amharic/archives/76395

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.