የሥልጣን ጥም፣ ፖለቲካዊ ሸር፣ ድንፋታ፣ የአመጽ ጥሪ፤ ለአገርም፣ ለሕዝብም አይበጅም

95666678 10217413060260243 7800559859723665408 o e1588520515988

የጅዋር እና የልደቱ ድንፋታ አዘል ውይይት ሰማሁት። ሁለቱም አገርን እና ሕዝብን ሳይሆን ሥልጣንን ኢላማ ያደረጉ ፖለቲከኞች መሆናቸውን በደንብ ያሳዩበት ውይይት ነው። አብይ የሰራቸው እና እየሰራቸው ያሉ ስህተቶች እንዳሉ ሆነው በተቃዋሚው በኩል ነገሮችን በዚህ መልክ ማጦዝ፣ ሕዝብን ለበለጠ እልቂት ማነሳሳት፣ አንዳንድ ኃላፊነት የጎደላቸው እና የተንኮል የፖለቲካ ትንታኔዎች አገሪቱ ለበለጠ ቀውስ ይዳርጋት ይሆናል እንጂ መፍትሔ አያመጣም። ሁለቱም ደጋግመው ለአብይ አስተዳደር የሰጡት ማስጠንቀቂያ እና የሰነዘሩት ዛቻ በውይይታቸው ውስጥ ያነሱዋቸውን አንዳንድ ጠቃሚ ሃሳቦች ሁሉ አድማጭ እንዳያገኙ የሚያደርግ ነው።

የኢትዮጵያ ሕዝብ የተንኮል ፖለቲካ ታክቶታል። ዛሬ ላለንበት አስጨናቂ ሁኔታ መፍትሔው መደማመጥ፣ የእራስን ego ዋጥ አድርጎ ለሕዝብ እና ለአገር ጥቅም ቅድሚያ መስጠት እና ፖለቲካችንን ከእልህ እና ከስሜት ማጽዳት ነው። የአብይን አስተዳደር ከመስከረም ሰላሳ በኋላ አናውቀውም፤ ሁላችንም እኩል ነን፤ ሕዝቡም፣ መከላከያውም፣ ፖሊሱም አይታዘዝለትም የምትለዋ የሁለቱ ፖለቲከኞች ማስፈራሪያ ሌላ ዙር ግጭት መደገስ እና የውስጥ ትርምስ ይቀሰቅስ ይሆናል እንጂ እነሱም የተመኙትን ሥልጣን አያስገኝም።

አገሪቱ የሥልጣን ጉጉት ባደረባቸው ፖለቲከኞች እርግጫ ወደ ከፋ ሁኔታ ከመሔዷ በፊት አገራዊ የምክክር መድረክ ሊፈጠር ይገባል።

ያሬድ ኃይለማርያም

———-//————-

ጥያቄ፤ የገባው ካለ ያስረዳኝ

Yared
ያሬድ ኃይለማርያም

በቀደም ጠቅላዩ እና ከተቃዋሚ ፓርቲዎችም መካከል አንዳንዶች ሲገልጹ የሰማሁት እና አልገባህ ያለኝ ነገር አገሪቱ ከተጋረጡባት አደጋዎች መካከል አንዱ የውጪ ወረራ ሊገጥማት ይችላል የሚል ነው። እንደውም ጠቅላዩ ሲናገሩ አሁን ከዚህ አዳራሽ ስንወጣ ምን ሊገጥመን እንደሚችል ሁሉ አናውቅም የምትል ማስፈራሪያም አክለውባት ነበር። ማን ነው ሊወረን የተዘጋጀው? ግብጽ ኢትዮጵያን ልትወር የምትችልበት ምንም አይነት እድል እና ሁኔታ የለም። ወረራው ከጎረቤት አገሮች በአንዱ ሊሆን ይችላል ብዮ እንዳላስብ ጠቅላዩ ከሁሉም ጎረቤት አገሮች ጋር እጅግ ጥሩ የሆነ ግንኙነት ነው ያላቸው። ይሄም በራሱ በመንግስቱ ሚዲያ ሲነገር የኖረ ነው። እርግጥ ግብጽ ሌሎች የሽብር ኃይሎችን ልትጠቀም ትችል ይሆናል፤ ሲታደርግ እንደኖረችው ሁሉ። ግን አሁን ባለው የቀጠናው ፖለቲካ ኢትዮጵያን ለመውረር ወይም በእጅ አዙር ለማስወረር የምትችልበት ምንም አይነት እድል የለም። እና ይህ ስጋት ከምን የመነጨ ነው? ከጠቅላዩ አልፎ ተቃዋሚዎች ያንን ስጋት አብረው ማስተጋባታቸውስ ከምን ተነስተው ነው? የሕዳሴ ግድብ ጋር ተያይዞ የተነሳውን ውዝግብ እና ስጋቱን በወረራ ደረጃ ሊከፋ እንደሚችል አድርጎ ማስቀመጥስ ትክክል ነው ወይ? ወይስ የቀረቡትን የመፍትሔ ሃሳቦች ቅቡል ለማድረግ የተቧጠጠ ምክንያት? ግብጽ ከአባይ ጋር በተያያዘ ለኢትዮጵያ የማትተኛ አገር ብትሆንም ነገሩን ወደ ወረራ ደረጃ ማምጣትስ ሌላ የፖለቲካ መዘዝ የለውም ወይ?

ተጨማሪ ያንብቡ:  የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የሰኔ15 የባህርዳር ውሳኔአቸው የኢትዮጵያን የፖለቲካ  ወደ አደገኛ መንገድ ቀይሮታል። (ከተማ ዋቅጅራ)

መልስ ስድብ ስለማይሆን ተሳዳቢዎችን በቀይ ካርድ አሰናብታለሁ።

ያሬድ ኃይለማርያም

6 Comments

 1. ለምን የኔን መላምት አልነግርህም አቶ ያሬድ። በመጀመርያ ጁዋርን ይሁን ልደቱ ያሉትን አልሰማሁም ። መልካም መንደርደርያም አስቀምጠሃል። ግን አቢይ ምን ማለታቸው እንደሆነ ለጠየከው ጥያቄ የኔውን ግምት ልንገርህ ከብዙ ሺህ ማይልስ ማዶ። መቼስ ባለፈው ሰሞን የህውሃቱ ሰውዬ ስለ ሲናይ በረሀ ልማት ያለውን ሰምተሃል። ከዚያ ተነስቼ ሳስበው ባሁን ጊዜ ግብጽ ተዳፍራ ቀጥታ ባትተናኮለንም ግብጽም ወግ ደርሷት ከአገር በቀል ከሀድያን ተመሳጥራ የፕሮክሲ ጦርነት እንደማትከፍትብን ማን አወቀ? ስንት አገር በቀል ከሀድያን አሉላት አይደል? አስበው እነዚህ ህውሃቶች ምልክቱን ሁሉ ለ ሁለት እመት እያሳዩን ነው። ሲፈልጋቸው በብዙ ሺህ ቅልብ ሰራዊቶቻቸውን ብልጭ ድርግም እያደረጉ በነሱ ቤት ሲያስቦኩን ሲያሰልፉብን ሰንብተዋል። ይባስ ብሎም የሆነች ተስፈንጣሪ ሮኬት ሁሉ አሳይተውን ነበር። እንግዲህ ያ ድግስ ለኛው ካልሆነ ለሱዳን ወዳጃቸው አይደል መቼስ። ደግሞስ ካዝናው፣ ከሃዲ ፌዴራሌው፣ አክራሪው፣ ሌላው ቀርቶ የነ ፕሮ መረራው ኦፌኮ ሳይቀር አብረው ተሰልፈው እያየህ ከውስጥ ስልፈኞቹ እንዲህ ለግብጽ አምረውላት ፣ የነ ፌዴራሌዎቹ አፈቀላጤ ህወሃት በአደባባይ ወገኝትነቱን ለግብጽ እንዲህ እየነገረህ፣ የታሪክና የሰብአዊ መብት ተማጉዋቹ ያሬድ ክምር ነው ያልገባህ ወይስ ለአቢይ ያለህ አመለካከት ነው እንዳይገባህ ያደረገው? በቅንነት ነው እየጠየኩህ ያለውና እዚሁ ቶፒክህ ስር መልስ ስጠኝ። ብዙዎቻችሁ እዚህ አደባባይ ስትጽፉ ለምንድነው ተመልሳችሁ የማታወያዩት? በተለይ ያንተ አይነቱ ብዙ ተሞክሮ ያለው ሰው? ብልሀት ለአገራችን የሚሸመተው እንዲህ ይመስለኛል ምንም እንኳ ብዙ የዲጂታል መናፍስት ቢኖሩም ታዋቂ ሰዎችን ያንተን አይነቱ ማለቴ ነው ለውይይቱ። የሚገርመኝ በዘመነ ወያኔ ጊዜ ኢሳት የሳምንቱ እንግዳ እያለ ያ ሲሳይ አጌና መፍትሄ ውለዱ ይል ነበር። ያ ቀረና ዛሬ ሁሉ ለየብቻው አየር ላይ መጮህ ብቻ ሆነ። ይቅርታ ቀይ ካርድ እንዳትሰጠኝ ከአጀንዳ ወጣሁብህ። እናም ወንድሜ ጦር ከሩቅ መች ሆነና? የኛዎቹን የውስጥ ጦረኞች እንዳልሆነ አቢይ በሾርኒ እንዳልነገሩን በምንስ እናውቀዋለን? ሰዎቹ የፌዴራሉን ህግ ሆነ የምርጫ ቦርድን ከቁብ አልቆጠሩምና አገሩን የሚወድ ሁሉ ቢመክር ይበጃል።የሲናዩን ልማት እንደ አፍ ወለምታ ከታየ መጪው ወራት ምን እንደሚወልድ የማይገምት ብቻ ነው። ይህው ነው በኔ ግምት። ሌላው ጉዳይ ሁሉ በአቢይ ላይ የሚሰማው ስሞታ ኮስሜቲክ ነው ለኔ። ሉአላዊነትን ፣ አባይን ያጣቀሰ የዶር አቢይ የበቀደም “የባንዳዎች” ስሞታ እንደዋዛ መታየት የለበትም ባይ ነኝ ኢትዮጵያን ለሚል ወገን ሁሉ።

 2. አንዳዶቻችን የየራሳችን ዳር ድንበር፣ከፍታና ዝቅታ አስተሳሰባችን ላይ ከልለናል። ሌለውንም ይቺን የአስተሳሰቤን ካስማ ታልፍና ዋ ዋ እንላለን።እከሌ እንዲህ ይላል፣እከሌ ደግሞ እንዲህ ነው በሚል ብቻ ግልሰቦች ላይ ጥላቻ የለጠፍን፣ስም ያጠፋን በጣም ብዙ ነን።ይህ ዓይነቱ ጠባይ በተለያየ ምክንያት በብዞዎቻችን ላይ ሊከሰት ይችላል።አስተዳደጋችን፣የአስተምሮቱ ሰንካላነት፣የሃይማኖት ጽንፈኛነት እና የመሳሰሉት። የዛሬዋ ኢትዮጵያ የውድቀት አንዱ በሺታ ይኸው ሲሆን ሌላው የብዙሃኑ የሕሊና ብስለት ድምር ውጤት ወደ እንጦርጦሮስ ያዘቀጠ ነው።

  የሰዎችን ሐሳብ እንደ መሞገት፣ የሥልጣን ጥም ያጠቃቸው፣ፖለቲካ ሸረኞች፣ደንፎዎች፣አመጽ ጠሪዎች፣በማለት ወደ ስብስቴው ዘመን ተሻግረው ፣ተራ ተሳዳቢ ፣የአርቆ ማስተዋል ደሃ ሆነው፣የፎቶግራፍ አቀማመጣቸው አሳምረው፣የመነጽር አሰቃቀላቸው ቀሽረው እዩኝ እዩኝ ውሎአቸው ነው።እኛም ቦዶ ጭብጨባችን ይድረሳቸው እንላለን።

 3. በኣስተሳሰብ የኣንድ ምእተ ኣመት ልዩነት ያላ ችሁ የምትመስሉ የፓለቲካ ተዋናዮች የስልጣን ነገር ኣንድ
  ኣረጋችሁ ?? Amazing.
  ልደቱ የሁዋላ ታሪክህ ፓርቲ ስትገነባ ስታፈርስ የመጣህ ፣ ኣቅም መገንባት ያልቻልክ፣
  ጃዋር ኣጼ ምኒሊክን ለምርጫ እንደቀረቡ በምናብህ ኣስበህ እጸጻቸን በማጉላት ተጠምድህ የቆየህ፣ ስልጣን በወርቅ ሳህን ቢሰጡዋ ች ሁ እንዴት ኣገር ትመራላችሁ ?
  Infantile , grow up men ! የኣቀንጭራ ኣስተሳሰብ ኣራማጅ ተምሳሌቶች !!

 4. የአቶዎች ጁዋርንና ልደቱንም ሃሳብ ሰማሁ። መቼስ ድንቅ ነው። የእነዚህን ሰዎች ምኞት አይሉት ትእቢታዊ አነጋገርን ሰማሁት። ምንም አልገረመኝም። ምን ያድርጉ ለነገሩ። እነዚህ ሙዋርተኞች በአገሪቱ ለሚመጣው ተጠያቂ አይደለንም፣ ወይም መከላከያው አይታዘዝም ለምን እንደሚሉ ያልተረዳ ወገን ካለ፣ ማ በኢትዮጵያ እንደሚሰራ ግልጽ ነው። የውጭ ወረራ ሳይሆን የልደቱና ጁዋር ቢጤ ግሪሳ ወረራ ለመሆኑ አመላካች ነው። አቶ ታዬ ደንደአ ደህና አድርጎ ገልጾልኛል። አንተም በደንብ ታዝበህልኛልና ዝርዝር አይፈልግም ። ደግሞ ልደቱን ከነብልጽግና ይቀላቀል ማለቴ። ከጁዋር ጋር ተቀላቅሎ ለነህውሃት ቢያሽቃብጥ ያምርበታል። ለመሆኑ የዚህ ሰውዬ ኮንስቲትየንሲ ዬቱ ነው? ሁለቱ በትእቢት ሲወጣጠሩ ከማየት የሚደንቅ ነገር የለም። አሳፋሪዎች!

 5. ጀዋርና መሠሎቹ ጠ/ም አቢይ እንዳለው የኢትዮጵያ ሕልውና ሳይሆን የሚያስጨንቃቸው እንዴት ሥልጣን ይዘው እነሱ እየተንደላቀቁ የኢትዮጵያን ሕዝብ በተለይም እነሱ በጠላትነት የፈረጁትን ወገን አሰቃይተው ከወያኔ የተረፈችውን ወደብ አልባ ኢትዮጵያ የምትባል አገር ለማጥፋት ነው።
  እዚህ ሰው እያጫረሱ  እነሱ ተመችቷቸው ከኖሩ ይኖራሉ ። ካልተሳካላቸው ደግሞ ወደ መጡበት ይመለሣሉ።
  እንኳንስ መንግሥት ሆነው አገር ሊመሩ ይቅርና አንድ ሰሞን ጥቂት ሲለቀቁ የሰሩትን ማንም አይረሳውም።
  ስንት ምስኪኖች ተገደሉ። ጡት ተቆረጠ። የሰማኒያ ዓመት ሽማግሌ ተቆራርጠው ተገደሉ።
  አማራውንስ እንደፈረደበት ነፍጠኛ እያሉ ነው።
  ታድያ ጋሞና ከምባታውስ ምን አደረገ ተብሎ ነው?
  በየቦታው የተገደሉት የኦሮሞ ልጆችስ? የኦነግ ደጋፊ ካልሆኑ ኦሮሞ አይደሉም ማለት ነው?
  ሰዉን ወያኔ በጀመረው በዘር ከፋፍሎ መግዛት ኋላ ቀርና መሠሪ አስተሳሰብ እነሱም በዘር ከፋፍለው እያጋጩ  እያጋደሉ ተንደላቀው ለመኖር ነበር ፍላጎታቸው።
  ጭቁኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ አማራ ትግሬ ኦሮሞ ከምባታ ወዘተ ብሎ አንዱ አንዱን ገድሎ ጨቁኖ አያውቅም።
  ዕድሜ ለመሠሪው ወያኔና አሁን ደግሞ ለጀዋርና መሠሎቹ ምንም የማያውቀውን ሕዝብ የዘር ጥላቻ መርዝ እየረጩ  ሊያጫርሱት ጫፍ ደርሰው ነበር።
  ፈጣሪ ኢትዮጵያን አይተዋትም። 
  ቅን መንግሥት ያገኘን ይመስለኛል።
  አሁን ዓለም ጭንቅ ውስጥ ባለችበት ሰዓት አሁን ካሉን መሪዎች  የተሻለ ማንም አይመጣም።
  በመጀመሪያ  ይሄ ጊዜ ይለፍና የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደነጃዋር አይነት መሠሪ  የሥልጣን ጥም ያሰከራቸው ሰይጣኖች ከመረጠ
  ለመግዛቱ ይደርሱ ነበር።
  እስከዛው ጀዋርና  መሠሎቹ  አርፈው ቢቅሙ ጥሩ ነው።
  በተረፈ አቶ ልደቱን አንተ የፈለከውን ብትልም ብዙ ጊዜ የሀሳብ ልዩነት ነው መብቱ ነው እያልን ቆይተናል።
  የሚደግፈውም የማይደግፈውም አለ።
  ከጀዋር ጋር ሀሳብ መጋራት ግን በበኩሌ ጠብቄው አላውቅም። መሠረታዊ ልዩነት አላቸው። ልደቱ
  ሁል ጊዜ እንደሚለው ለአገራችን ለኢትዮጵያ የሚያስብ ከሆነ ጀዋርን ከመሰሉ ኢትዮጵያን ለመበተን ቀንና ሌሊት ከሚሠሩ ሰዎች ጋር ሆኖ ባያሳዝነን ጥሩ ነው።

 6. ኩሁለቱ ንግግር ቀድሞም ከዝንብ ማር እንደመጠበቅ ነው ነገሩ፡፡ OMN ጣቢያ ራሱ ችግር ያለበት እንደሆነ ቀድሞ የተፈታ ጉዳይ ነው፡፡ እብሪተኛን እንዲስተናግድ መፍቀድ እራሱ ነገ ረብሻ ቀስቃሽ ሚዲያ እንደሚሆን ምንም የሚወላዳ አይደለም፡፡ እንደዚህ አይነት ሚዲያን ውሎ ሳያድር አሁኑኑ መዝጋት ነው፡፡
  ህዝቡ እንደሆነ ብዙ ነገር ያውቃል ችግርንም በደንብ አጣጥሟል፡፡ እንደው ልደቱ ተብዮ ህዝብ የ97 ምርጫ ጣጣን የሚረሳ ይመስለዋል፡፡ ያ ሁሉ መንሸራተት የታየበት፡፡ ጅዋርም ቀድሞ ቁማሩን ለመጫዋት የሚጥረው የራሱ ደጋፊ የሚባሉት ቄሮዎች እንኳን የማይቀበሉት ለመሆኑ በባለፈው አመላካች ነገሮች መታየታቸውን እንዴት ይረሳል፡፡ ወጣቱ/ቄሮው/ በጣም የገባው ነው አሁን፡፡ በሁከትና በረብሻ ምንም አይመጣም፡፡

  ብልፅግና ባይመራ እንኳን ወታደሩና ፖሊሱ እንሱ እንዳሉት አይታዘዘም ማለት የዋህነት ነው፡፡ ለነገሩም ወታደሩና ፖሊሱን Brain wash ለማድረግ ታስቦ ነው ግን ሞኝነት ነው፡፡ እንደውም ይህ ሀይል በጣም ተደራጅቶ አገርን ለማስቀጠልና ረብሸኛን ወደ ዘብጥያ የሚያስገባበት ኃላፊነት እንደሚኖረው ይታመናል፡፡ እነ አብይም ይህን ሃይል/ወታደሩና ፖሊሱን/ ማብቃት አለባቸው፡፡ ዘር፣ ብሔር፣ ፓርቲ ጋር መወገን አይጠበቅም በዛ ጊዜ ይሸወዳሉ ብሎም ህዝቡ አይገምትም ምክንያቱም ቃለ-መሓላ የገቡበት ነውና፡፡ በየውስጣቸው ችግር ፈጣሪ ካለም ከወዲሁ የማጥራት ስራ መኖር አለበት፡፡ የሽግግር መንግስት፣ የሰላምና የእርቅ መድረክ፣ ወዘተ ቢባልም ብልፅግና ቀጣይ ምርጫ እስከሚደረግ የመምራት ግዴታ ይኖርበታል ህገ-መንግስቱ ባይፈቅድም የህንን የማመቻቸት ስራ አሁንም በእጁ ያለው በብልፅግና ፓርቲ ብቻ ነው፡፡ እንደው ዝም ተብሎ ከመስከረም 30 በኃላ አገርና ህዝብ የሚወክል መንግስት ለአንድም ቀን አይኖራትም ማለት ምን ማለት ነው፡፡ ህግን የፈጠረ ሰው እስከሆነ ድረስ መፍትሔ ማምጣትም ይችላል፡፡ ሰው እኮ ከኢህዲግ ብዙ ነገሮችን አይቷል፡፡ ከብልፅግና ፓርቲም እንደዚሁ የሚበጀውን ህዝብ ያውቃል፡፡ በሚዲያ ላይ ስለተወራ አይደለም፡፡ የልጆች ዕቃ ጨዋታ አይደለም እኮ፡ እንደው ሚዲያ ላይ ሁለቱ ግለሰቦች ቀርበው ለህዝብ ይህን ማለት አያሳፍርም!!!

  አገሪቷን ለማበጣበጥ ተቅዷል ለካ አይሰራም እንጂ፡፡

  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.