“የደሃ አገሮች ዕዳ ሊሰረዝ ይገባል”- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ

merlin 170827815 059cb7d1 bc32 4ad1 a27c 00f567e7cc03 jumboጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ “የደሃ አገሮች ዕዳ ሊሰረዝ ይገባል” በሚል ርዕስ የጻፉት ጽሁፍ ኒውዮርክ ታይምስ ሚያዚያ 30 ቀን 2020 በድረ-ገጹ ላይ አስፍሯል።

ጽሁፉ ሲጀምር የቡድን 20 አገራት በሚያዚያ 5 ቀን 2020 ለታዳጊ አገራት የዕዳ መክፈያ ጊዜ እንዲራዘም መወሰናቸውን ጠቅሶ ይህ ውሳኔ ታዳጊ አገራት ያላቸውን ገንዘብ ወረርሽኙን ለመከላከል እንዲያውሉት ያግዛቸዋል ይላል።

ይሁንና ዓለም ዓቀፍ አበዳሪዎች የወረርሽኙን አሳሳቢነት በመረዳት ለታዳጊ አገራት የሰጧቸውን የተለያዩ ዓይነት ብድሮች የመክፈያ ጊዜ ማራዘም ብቻ ሳይሆን ብድሩን ሊሰርዙላቸው ይገባል ሲል ጽሁፉ ይቀጥላል።

አክሎም በ2019 ብቻ የዓለማችን 64 ደሃ አገራት ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ ከግማሽ የሚልቁት ከሰሃራ በታች የሚገኙት አገራት ያለባቸውን የውጭ ዕዳ ለመክፈል ያወጡት ገንዘብ የጤና ሴክተራቸውን ለማጠናከር ከመደቡት በጀት በእጅጉ ይበልጣል። ይህ የሚፈጥረውን ጫና ለመገመት የሚከብድ አይደለም።

ኢትዮጵያ ለጤና ሴክተሯ ከመደበችው በጀት ከሁለት ዕጥፍ የሚልቅ ገንዘብ የውጭ ዕዳ ለመክፈል አውጥታለች፤ በተመሳሳይ ጊዜ አገሪቱ ከወጪ ንግድ ካገኘችው ገንዘብ 47 በመቶውን ያህል ለውጭ ዕዳ መክፈያ አውላለች።

አሁን ላይ ዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ተቋም ከፍተኛ የዕዳ ጫና ያለባት አገር ሲል ኢትዮጵያን ፈርጇታል። ታዲያ ኢትዮጵያ በዚህ የወረርሽኝ ወቅት ዕዳ ለመክፈል ትታትር ወይስ ህይወት ለማትረፍ ትታገል? በመሆኑም አበዳሪ አገራት ዛሬ ላይ የሚያሳልፉት ውሳኔ በታዳጊ አገራት ያሉ ህዝቦችን ህይወት ለማትረፍም ሆነ የቀጣይ ኢኮኖሚያቸውን ለመታደግ ወሳኝ ነው ሲል ጽሁፉ ይቀጥላል።

ሊንኩን ይጫኑ

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.