ምርጫው የግድ በጊዜው መካሄድ አለበት የሚሉ ሃይሎች ማዕከላዊ መንግስትን ለማዳከም የሚያደርጉት ቁማር ነው – የህግ ምሁራን

95542999 1626310987520243 2970239334252281856 n
በአገሪቱ ምርጫን የሚያስፈፅመው ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫው እንዲራዘም እየጠየቀ ባለበት ወቅት ምርጫውን በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ መፈጸም አለበት’ የሚሉ አካላት በህገ-መንግስቱ መሰረት ተቀባይነት የሌለው አካሄድ እንደሆነ ገልፀው ”ይህ ተግባር ሁኔታዎችን እየጠበቁ የማዕከላዊ መንግስትን ለማዳከም የሚደረግ ቁማር ነው” ብለዋል ምሁራኑ።‘

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግና የፌዴራሊዝም መምህሩ ዶክተር ሲሳይ መንግስቴ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ለመቀነስና ስርጭቱን ለመቆጣጠር የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አገራዊ ምርጫውን የሚመለከት በመሆኑ የህግ አማራጮችን አስመልክቶ የቀረበው ምክረ ሃሳብ ተገቢ መሆኑን ገልጸዋል።

ምርጫ ቦርድ ወቅቱ ምርጫውን ማድረግ የሚቻልበት አለመሆኑን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማሳወቁንና ምክር ቤቱም ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራቱን አንስተዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህርና ጠበቃ የሆኑት ሌላው የውይይቱ ተሳታፊ አቶ ቸርነት ሆርዶፋ መንግስት አማራጮቹን ማቅረቡ የህግ ሙያን የሚያስከብር የመንግስት አካሄድ በመሆኑ አመስግነዋል።

”ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ራሱን በማደራጀት ለምርጫ ሲዘጋጅ እንደነበር ይታወሳል” ያሉት አቶ ቸርነት ሆኖም ምርጫ የምርጫ ቅስቀሳ፣ ሰላማዊ ሰልፍና ድጋፍ የሚያሰባስቡ ሰዎችን መምረጥ የሚጠይቅና በቦታው ሄዶ መምረጥን የሚጠይቅ በመሆኑ አሁን ካለው ሁኔታ ጋር አብሮ እንደማይሄድ ገልጸዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የህግ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ አብነት ዘውዱ በበኩላቸው የኮቪድ-19 ወረርሽኝን መከሰት ተከትሎ የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በርከት ብሎ መሰብሰብና መሰል ተግባራት ላይ ገደብ በመጣሉ የምርጫው የጊዜ ሰሌዳ እንዲራዘም ያደረገ ምክንያት መሆኑን ያነሳሉ።

መንግስት ከዚህ ቀደም ምርጫውን ለማካሄድ ቁርጠኛ መሆኑን ማሳወቁን አስታውሰው እንደ ሀገርና መንግስት ምርጫውን ለማድረግ ዝግጅት ሲደረግ እንደነበር ገልፀዋል።

የኮቪድ-19 መከሰትን ተከተሎ ሌሎች አገሮችም የምርጫ ጊዜያቸውን ማራዘምንና ሽግሽግ ማድረጋቸውን ተናግረው፤ በኢትዮጵያም የህዝቡ ጤንነትና ደህንነት ቅድሚያ የሚሰጠው በመሆኑ አራቱ የህግ አማራጮች እንዲቀርቡ መነሻ መሆኑን አስረድተዋል።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት መንግስት ጠንካራ መሆን እንዳለበት የተናገሩት ምሁራኑ፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትን መበተን መንግስት የሚያስፈልጉትን አዳዲስ ህጎችን እንዳያጸድቅ የሚያደርግና ደካማ የሚያደርገው መሆኑን ተናግረዋል።

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መቼ እንደሚገታ የሚታወቅ አለመሆኑን ተከትሎ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትን መበተን ከስድስት ወር በኋላ ምርጫ ማድረግን የሚጠይቅ በመሆኑም ጭምር አማራጭ መፍትሄ እንዳይሆን የሚያደርግ መሆኑን ጠቁመዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአንዳንድ መብቶች ላይ ገደብ የሚጥል በመሆኑ የሚገደቡ የፖለቲካና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በመኖራቸው ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ እንዳይካሄድ የሚያግድ እንደሚሆንም ምሁራኑ አስረድተዋል።

ወረርሽኙ እያደረሰ ያለውን ጫና ለመቀነስና ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት መንግስት ዘርፈ ብዙ ድጋፎችን እያደረገ መሆኑን ተከትሎ ህገ-መንግስትን ለማሻሻል የሚያስችል የኢኮኖሚ አቅም የለም ብለዋል አቶ አብነት።

አራቱም አማራጮች ህገ-መንግስታዊ መሰረት ያላቸው ቢሆንም አገሪቱ አሁን ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ህገመንግስትን መተርጎም የተሻለ መሆኑን ነው ምሁራኑ የተናገሩት።

የፖለቲካ አማራጮችን መውሰድ የሚያስፈልግበትን ሁኔታ ማየት ተገቢ እንደሆነ ያስረዱት ምሁራኑ፤ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በፖለቲካና አስተዳደር ልዩነት አሊያም በሰላም እጦት የታወጀ ቢሆን በመሰል አካሄድ ሊዳኝ ይችል እንደነበር አስገንዝበዋል።
የፖለቲካ መፍትሄ ህገመንግስታዊ አማራጮች ከታጣ የሚወሰድ መፍትሄ መሆኑንም በመጠቆም።

በአገሪቱ ምርጫን የሚያስፈፅመው ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫው እንዲራዘም እየጠየቀ ባለበት ወቅት ‘ምርጫውን በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ እንፈፅማለን’ የሚሉ አካላትም በህገ-መንግስቱ መሰረት ተቀባይነት የሌለው ተግባር እንደሆነ አብራርተዋል።

”ይህ ተግባር ሁኔታዎችን እየጠበቁ የማዕከላዊ መንግስትን ለማዳከም የሚደረግ ቁማር ነው” ብለዋል ምሁራኑ።
የፖለቲካ ፓርቲዎች የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በአንድነት በመቆም የአገር ህልውና ከፖለቲካ ጨዋታ ውጪ መሆኑን የሚያሳዩበት ጊዜ እንደሆነም ነው የገለፁት ምሁራኑ።
ምንጭ ኢዜአ

1 Comment

  1. የኢትዮጵያን የፖለቲካ መድረክ ለታዘበ የኢትዮጵያ ፖለቲካ በእንጭ ጩ ያለ፣ ኣክተሮቹ በኣብዛኛው ማስተዋል የጎደላቸው፣ ሁሉም በሚያሰኝ Wisdom የሌላቸው ፣ ትግላቸው በህዝብ ስም ለስልጣን ብቻ እና ስልጣን ሊያስገኝ የሚችለውን ጥቅም ለራሳቸው እና ለዙሪያቸው ለማዳረስ ነው።በየብሄሩ ሁለት እና ሶስት ከዝም በላይ የተፈጠሩ ፓርቲዎች በቂ ምስክሮች ነው። Wisdom is the scarcest commodity among so called Ethiopian politicians and /or elites . It was buried fifty years ago when Marxism destroyed our centuries old religious and secular wisdom by replacing it with proletarian openness ,a mere reflection of vulgarity , greed and hate.
    ስለዚህ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ከዘቀጠበት ፣በትምህርት፣ስልጠና፣ ውይይት፣ የተማሩ እንዲገቡበት በማበረታታት፣የሀገር ምንነትእና ስነ ማግባርን በማሰረጽ ….etc ከፍ ለማድረግ እና ለእውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ለማድረስ ቢያንስ ከ 5 እስከ 10 ኣመት የሽግ ግር ጊዜ ያስፈልጋል።ተቻኩለን ነገ የድም እንባ እንዳናለቅስ።
    ኣሸጋጋሪው ማሙዋላት ካለበት ባህሪያት ውስጥ ሀገር ወዳድ፣ የዘር ኣደልዎ የማያደርግ፣ ሙስናን የሚጸየፍ፣ የተማረ ሰውን የሚጠቀም፣መሰረታዊ የኣመራር ችሎታ ያለው ፣ልማት ተኮር ከሆነ ካለንበት ደረጃ ይበቃናል።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.