“ ታጋይ ሜ/ጀኔራል ተክለብርሃን  ለዓመታት ያጠለቀዉን ጭብል አወለቀ” – ንጋቱ ተፈሪ

Tigreየኢትዮጵያን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር ከበላይ አለቆቼ የሚሰጠኝን ትዕእዛዝ ያለማወላወል ለመቀበልና ለማክበር  ብሎ  ባንድራ ይዞ ምሎና ተገዝቶ ሜ/ጀነራል ሆነ። (እርሳቸዉ አልለዉም ። ለምን? የኢትዮጲያ ጀኔራል አይደለሁም ብሎ እራሱን ዝቅ ያደረገ ተራ ታጋይ ነዉና)

 ቃልኪዳን ለገባለት ሀገርና ህዝብ ሳይሆን  ለ27 ዓመታት እራሱን ሢያገለግል ሲያካብትና ዘመድ አዝማዶቹን ሲያበለጽግ መኖሩን በተዘዋዋሪ መንገድ ነገረን።  ድንገት  ክሰልጣኑ ሲባረር  ራሱና የጓደኞቹ የተሸፈኑበትን የማንነት  ጭምብልም ሠሞኑን አወለቀ።  

    ታጋይ ጄኔራሉ እንዲህ ነበረ ያለዉ!

1ኛ እኛ  ወያኔዎች የታገልነው ለኢትዮጵያ ሳይሆን ትግራይን ነጻ ለማወጣት ነዉ ። እዉነት!

2ኛ ትሩፋቱ  ለኢትዮጲያም ደርሷታል ። (እጅ በማወራጨትና በማናናቅ) ቅጥፈት!

3ኛ አማርኛ   በመማሬ እጸጸታለሁ አለ። ዉሸት! ከልቡ አይደለም!

     በቃለ ምልልሱ ወቅት የተናገርዉን  ዝባዝንኬ ሁሉ እዚህ ላይ ማንሳት እሱኑ መሆን ነዉ።   አዋቂና ተመራማሪ ለመምስል ያሳየዉ ሙከራ ግን አልተሳካለትም። ይልቁንም  ጥረቱ ባዶነቱን ይበልጥ አሳብቆበታል። ከአየር ኃይል አዛዥነት  በአገር ዉስጥ የህግ ትምህርት  ተምረዉ አዲስ አበባ ዩንቭርስቲ መምህር እስከመሆን የደረሱት ሜ/ጅኔራል አበበ ተክለይማኖት ዘረኛ መሆናቸዉ ቢነገርም  በንጽጽር ብስለታቸዉን መደበቅ  አይቻልም።

የኢንሳዉ ድሬክተር ነኝ ባዩ  ታጋይ ጀኔራል ግን እራሱን ብቻ ሳይሆን ማዕረጉን ያሸከመዉን ስራዓትና የወያኔን ባዶነት ያጋለጠ  ነዉ፡፡ ቃለ ምልልሱ ተራ የህይወት ፍልስፍና እንኳን የተነፈገዉ የእዉቀት ድንክዬነቱን ያሳየበት ነዉ። በተቃራኒዉ ጠያቂዋ ጎርጉራ ሰለጠየቀችዉ ባዶነቱን አጋልጣለች፡፡

     ጥላቻና ዘርኝነት አዕምሮዉን ስላጠለሸዉ ጀኔራል የሚለዉን ማዕረግ  ምን ያህል አቅሎት በሸበጥ እንዳስኬደዉ ንግግሮቹ ማረጋገጫ ናቸዉ። አለበለዚያ 27 ዓመታት እየረገጠና እየሰረቀ ለመኖር ያስቻለዉን ቋንቋ መማሬ ይቆጨኛል  የሚል የጅል ንግግር ከአፉ ባልወጣ ነበረ። ለዚያዉም የመረጃ ሰዉ ነኝ ባይ ነዉ። ከሆነ  አንድ አይደለም አስር ቋንቋ ቢያውቅ ለስራዉ መልካም በሆነ ነበረ።

አዲዮ እዉቀት ! የሚያሰኘዉም ለዚህ ነዉ።

ከሚፈነጭበት የዘረፋ ስልጣን ስለተወረወረ የቁጭት ንግግር እንጂ እንጀራ የበላበትን ቁንቋ  ሰዉ ለምን ይጠላል! ዉሸቱን ነዉ!

      የታገልነዉ  ትግራይን ነጻ ለማዉጣት ነዉ በማለቱ  ግን ያስመሰግነዋል። ለ27ዓመታት ሲዘርፉ ብዙዎቻቸን ስንጮህ የነበረዉንና የኢትዮጲያ ህዝብ አልሰማ ብሎ የተዘረፈበትን ጭንብል ነዉ አዉልቆ ያሳየዉ።

   ምን ትሆናልህ ! ምን ታመጣለህ? 27 ዓመታት የዘረፍንህ እኛ  ወያኔዎች ዓላማችንን ግቡ እስክናደርስ  ብቻ ነበረ ኢትዮጵያ ስንል የቆየነዉ !። እዉነቱና  ሃቁን ግን ዛሬ ልንገራችሁ ! ምን ታመጣላችሁ ነዉ ያለን።

     እዉነት ነዉ  ! ታጋይ ጀኔራል የምናዉቀዉን ሃቅ ነዉ የነገረን። የሚበቃዉን ከዘረፈ በኃላ ማመኑ እንጂ የሚቆጨዉ እዉነቱን መናገሩ ያስመሰግነዋል ።

 በሌላዉ ንግግሩ  ትልቅ ዉሸትም ዋሽቷል።   ትሩፋቱ  ለኢትዮጵያም ደርሷታል ማለቱ ትልቅ ቅጥፈት ነዉ ነዉ።  ቅጥፈቱን  ያርጋገጠበት  ደግሞ በንቀት እጁን እያወራጨ ነበረ “ቱሩፋት አግኝተዉ ይሆናል”ያለን፡፡  አንድ ነገር አስታወሰኝ ።

በ 550 B.C የነበረዉ የፕርሽያን ንጉስ  ሳይረስ ዓለምን ለመግዛት ሲነሳ በጦርነት ያስገበራቸዉን ህዝቦች …we are conquering you for your benefit.. ብሏቸዉ እንደነበረ  ካነበብኩት ታሪክ አስታዉሳለሁ፡፡ ንጉሱ  በጠመንጃ አፈሙዝ ያስገበራቸዉን ህዝቦች  በተጨማሪ እንዲህ ብሏቸዉ ነበረ፡፡  …Cyrus wanted  to count themselves lucky to be Persian vassals. ይላል።

ክቡር  ታጋይ ጀኔራልም ትሩፋቱን ለኢትዮጲያም ረጭተናል እኛ ስለገዛናችሁ እድለኞች ናችሁ እያሉን ነዉ።   ቢኒያንስ ከዘረፍነዉ የተረፈዉን ትተንላችኃል ማለቱም ነዉ። 

በእርግጥ ተሳልቆብናል! ለኢትዮጲያ ህዝብ የተሰጠዉ ”ቱሩፋት” ግን የሌብነትና የዘርፋ ባህል እንዲሰራፋ ማድረግ ፤ለ27 ዓመታት በኢትዮጲያዊነት ጭንብል ኢትዮጲያዊነትን ማጥፋት በመጨረሻም የስብእና ኪሳራ አሳይቶና አስተምሮ ወደ እዉነተኛ ማንነት መኮብለል ነዉ።

  የታጋይ ጀኔራሉን  ቃለመልልስ ወድጄዋለሁ። ስለወያኔ ትግልና ማንነት ለዓመታት ሲከራከሩ ለነበሩት የዋሆች ቁርጣቸዉን  አሳዉቋቸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ  ትልቋን ኢትዮጲያ  አስተዳድረናል ይሉ የነበሩት  ትንንሽ ሠዎች (ታጋይ ጄኔራሎች) በራሳቸዉ ጊዜ ማንነታቸዉን የገለጡበትና ይበልጥ ያነሱበት አጋጣሚ  ሆኗል

       ኢትዮጲያ  ለዘላዓለም ትኑር!

ንጋቱ ተፈሪ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.