///

ታንኩም ባንኩም ፣የሻቢያ፣ ወያኔና፣ ኦነግ ጦር አበጋዞች ሆነ፣ የኦሮሙማ ፓርቲ ንግድ ድርጅቶች ዘረፋ!!! – ሚሊዮን ዘአማኑኤል

(ክፍል ሁለት)

et66ሻብያ፣ ወያኔና ኦነግ የጦር አበጋዞች መንግሥት!!!

“የጦር አበጋዝ ማለት የግል ሽምቅ ወታደራዊ ኃይል በማደራጀት፣ ለግል ጥቅም ስልጣንና ኃብት ገንዘብ፣ ወርቅ፣መሬት ወዘተ የሚያካብት የዘር ፖለቲካ ተዋናይ ሲሆን ለወንዜ ልጆቹ የማንነት መታወቂያ በመስጠት ጫካ የሸፈተ ሽፍታ ነው፡፡ ኢሳያስ አፈወርቂ ሻብያን በአፋቤት ፣ መለስ ዜናዊ ወያኔን በደደቢትና ሌንጮ ለታ ኦነግን በወለጋ፤ ምስኪን  የመንደር ልጆች በዘርና ቌንቌ በማደራጀት በነፃነት ስም ባርነት፣ በዴሞክራሲ ስም አንባገነንነት ህዝብ ላይ ለመጫን ዱር ቤቴ ያሉበት ዘረኛ የሽፍትነት ዘመን እንደ ተስቦ ተስፋፋ፡፡  ‹‹የማንነት መታወቂያ የሚሠጥ የንግድ ድርጅት አመሰራረቱ፣ በግለሰብና በቡድን የተደራጁ ግለሰቦች የግል ፍልጎታቸውንና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ የቡድን የማንነት ጥያቄን በማራገብ  ዘውጌ ብሄርተኛነትን በህዝብ ላይ በኃይል የሚጭኑበት ስርአት ነው፡፡ የጦር አበጋዞቹ በተለይ ተለዋዋጭ ሁኔታዎቹን ሁሉ በመጠቀምና ያለውን ክፍተት፣ልዩነትና ጥላቻን በማራገብና እንዲሁም አዲስ ልዩነቶችን በመፍጠር በኃይል በመጠቀም  ዘውጌ ብሄርተኛነትን ይፈበርካሉ፡፡››(የጦር አበጋዝ፣ ቶማስ 2005 ገፅ 79)”

የኢትዮጵያ የመዕድን ዘርፍ (Mining)

{1} የኢትዮጵያ የነበረ፣የወርቅ ማዕድን የሻብያ ኢሳያስ አፈወርቂ ኃብት ሆኖል !!!

 • ሻብያ መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ ቢሻ የወርቅ ማዕድን ለካናዳ ካንፓኒ ኒቨሰን የኮፐር፣ ዚንክና ወርቅ ማዕድናት ቆፋሪ ካንፓኒ በሽርክና ኢንቨስተሮች 60 በመቶ ሻብያ 40 በመቶ ድርሻ ከወርቅ ማዕድን ኃብት 200 ሚሊዩን ዶላር በአመት ገቢ ያገኛል ፡፡ የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በዓለም አቀፍ መድረክ የተገለሉ፣ አመለካከታቸው የተንሸዋረረና ለህዝባቸው አንባገነን መሪነት ይታወቃሉ፡፡ ኢሳያስ በቢሻ የወርቅ ማዕድን ሥፍራ ሠራተኞቹን አስገድደው በማሰራትና በዘመናዊ ባርነት እያሰሩ ከሲዊዘርላንድ በሚሊየን የሚቆጠር ዶላር ያገኛሉ፡፡ በሃገረ ሲዊዘርላንድ 10,000 ሽህ የኤርትራ ስደተኞች የሰደተኛነት ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ የጦር አበጋዝ ኢሳያስ  የኤርትራን መሬት፣ ገንዘብና ወርቅ እየዘረፉ ህዝቡን ለሞት ለእስራትና ለስደት ዳርገዎል እንላለን፡፡  የሻብያ የጦር አበጋዝ በነፃነት ስም፣ በዴሞክራሲ ሰም፣ በእኩልነት ስም የተራ ሽፍታ ስራ እየሰሩ በእድሜ ልክ ፕሬዜዳንትነት ገና በድዳቸው ይገዛሉ፡፡

Swiss-Eritrea Links in Gold Mining

“The controversial Eritrean gold comes from the Bisha gold mine, located in the middle of the desert. Since 2010, the Canadian company Nevsun mines copper, zinc and especially gold, 40 of which per cent is owned by the Eritrean regime. In order to purify the extracted raw gold into bars, the mining company needs a refinery partner. And this partner has been found in Switzerland, the Eldorado of the gold industry. There is no other country, which melts as much gold as Switzerland. 22 tonnes of raw gold from Eritrea came into Switzerland. A deal worth several hundred million”

“The Eritrean President Isaias Afwerki is internationally isolated and ostracised. Despite that, his regime was able to use Switzerland for gold business and earned millions. There is also a second, very dark side of the gold from Eritrea.

There is a pending civil lawsuit in Canada that has been filed by former mineworkers, who claim: “The mine was constructed by forced labour, a modern form of slavery.” During this period of time, about 10, 000 Eritreans asked for asylum in Switzerland.”

http://erilaw.org/swiss-eritrea-links-in-gold-mining/ Swiss-Eritrea Links in Gold Mining

{2} የኢትዮጵያ የነበረ የወርቅ ማዕድን ህወሓት ኃብት ሆኖል !!!

 • ከካናዳ ኢንቨስተሮች ጋር ከኢዛና የወርቅ ማዕድን ኃብት ብዙ ሚሊዩን ዶላር በአመት ገቢ ያገኛል ፡፡ ከኢትዮጵያ ህዝብ ዘርፎ የገነባቸው ፋብሪካዎች ማኃል ለመጥቀስ ያህልየህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት በኢትዩጵያ ብሄራዊ ባንክ ዘርፎ ያከማቸውን 850 ኪሎ ግራም ወርቅ ወደ መቐለ ማጎጎዙን ውስጥ አዋቂዎች ገልጸዋል፡፡ ህወሓት በዘረፋ ያገኘው 850 ኪሎ ግራም ወርቅ 850,000 ግራም ወርቅ የህወሃት ጦር አበጋዞች በብሄራዊ ባንክ አከማችተዋል ማለት ነው፡፡ ዝርዝሩን ከድረ-ገፁ ያንብቡ፡፡

Since 1999, geological map survey has been conducted so as to identify the type, coverage and amount of mineral resources in our region. Up to now, the activities of collecting geological information from 24,780 meter square and consolidating reports have been finalized. The geological map coverage of our region has reached 46.2% and around 850 kg gold is already deposited in the national bank of Ethiopia. In this regard, there were some limitations which need due attention such as fulfilling enough skilled manpower and inspecting equipments and laboratory services among others. (Tigray Regional State, Five Years 2010/11-2014/15, Growth & Transformation Plan, Bureau of Plan and Finance, September 2003 E.C, Mekelle, page 17) Next Five Years (2010/11-2014/15) Regional GTP: Tigray Region Plan and Finance Bureau.

 • ኢዛና ካንፓኒ በትግራይ ክልል በ7 ሚሊዩን ብር ወይም (17.8 ሚሊን ዶላር) የፕሮጀክት ወጭ 2017 ኪሎግራም ወርቅ በሁለት ዓመታት ውስጥ ለመማምረት አቅዶል፣ኢዛና በመዐድን ዘርፍ ለ106 ሠራተኞች የስራ እድል ፈጥሮል፡፡ በትግራይ ክልል ውስጥ የተገኘውን 13 ቶን ወይም ፣13,000 ሸህ ኪሎ ግራም የወርቅ ማዕድን ለዓለም ዓቀፍ ጨረታ በማውጣት የካናዳዊያን የወርቅ ማዕድን ካንፖኒ ጋር ህወሃት/ኢፈርት በትግራይ ህዝብ ስም የሚዘረፈው የወርቅ ሃብት ሲሆን ሲሆን ስለ ካንፓኒው ብዙ መረጃ አይገኝም፡፡ ኢዛና ካንፓኒ 393.7 ሚሊዩን ብር የፕሮጀክት ወጪ 2017 ኪሎግራም ወርቅ በሁለት ዓመታት ውስጥ ለመማምረት አቅዶል፡፡በዚህ መሠረት 2017 ኪሎ ግራም ወርቅ 2,017,000 ግራም ወርቅ ይሆናል ይሄን ለ29 ግራም (1 ወቄት ማለት ነው) ስናካክለው 69,552 ወቄት ወርቅ ይሆናል ይሄን በ1 ወቄት ዋጋ 1218.80 ዶላር ስናባዛ 84,769,977.6 ሚሊዩን ዶላር ይሆናል በብር ስንቀይረው ደሞ አንድ ዶላር በ20.34 ብር በነበረ ጊዜ ሲባዛ 1,724,221,344.384 ቢሊዩን ብር ሲሆን በ2020እኤአ አንድ ዶላር በ40.68 ብር ሲባዛ 3.4 ቢሊዮን ብር የህወሃት ጦር አበጋዞች በሃገር ውስጥና በውጪ ሃገር ባንኮች አከማችተዋል፡፡

ኢዛና የወርቅ መዕድን ኃብት ኃ/የ/ግ/ማ (Ezana Mining)

ኢዛና የወርቅ ማዕድን ልማት ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማሕበር (Ezana Mineral Development Private Limited Company (EFFORT)  በህወሃት/ ኢፈርት ባለቤትነት የተቆቆመ ካንፓኒ ሲሆን ዋና የበላይ ተቆጣጣሪዋ ወ/ሮ አዜብ መስፍን ስትሆን አታክልቲ አርዓያ ጀነራል ማናጀር ነበሩ፡፡ ኢዛና የወርቅ ማዕድን በ1993እኤአ ሲመሠረት በ1.4 ቢሊዩን ብር መነሻ ካፒታል ነበር፡፡ ካንፓኒው በ 17.8 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር የወርቅ መዕድን ማውጫ ፋብሪካ በቱርክ ማንሃተን ኮርፖሬሽን ተገነባ፡፡ ኢዛና የወርቅ መዕድን ማውጫ ፋብሪካ ሲገነባ ለአራት ዓለም ዓቀፍ ኮንትራክተሮች ጨረታ ወጥቶ ተሠጠ:: በትግራይ ክልል ውስጥ የተገኘውን 13 ቶን ወይም ፣13,000 ሸህ ኪሎ ግራም የወርቅ ማዕድን ለዓለም ዓቀፍ ጨረታ በማውጣት የካናዳዊያን የወርቅ ማዕድን ካንፖኒ ጋር ህወሃት/ኢፈርት በትግራይ ህዝብ ስም የሚዘረፈው የወርቅ ሃብት ነው፡፡ ኢዛና ካንፓኒ 393.7 ሚሊዩን ብር የፕሮጀክት ወጭ 2017 ኪሎግራም ወርቅ በሁለት ዓመታት ውስጥ ለመማምረት አቅዶል፣ኢዛና በመዐድን ዘርፍ ለ106 ሠራተኞች የስራ እድል አንበሽብሾል፡፡ ለሙሰኛው ህወሃት/ ኢፈርት ‹‹የአዶላና የለገደንቢ ወርቅን የህወሃት መንግስት ለአላሙዲን ያለጨረታ ሸጦል በሃያኛ አመቱ በ 2017 እኤአ ስምምነቱ አከተመ፡፡ በ1998 እኤአ የለገደንቢ ወርቅ መዕድን በ172 ሚሊዩን ዶላር ለአላሙዲን በርካሽ በሙስና ሲሸጥ 98 እጅ ለሼኩና ለሚስታቸው ድርሻ ሲሆን 2 በመቶ የኢትዩጵያ ህዝብ ድርሻ ሆኖ መለስ ዜናዊ ቸበቸበው፡፡ የትግራዩን ወርቅ ለእራሱ ፓርቲ፣ ለኢፈርት ድርጅት ኢዛና አደረገ፡፡ የሚገርመው በሌሎች ሃገራቶች የወርቅ ማዕድን የኃብት ክፍፍል ለምሳሌ፣ በኢንዶኔዢያ 49 በመቶ እጅ የህዝብ ኃብት ነው፣በዚንባዌ 51  በመቶ እጅ የህዝብ ኃብት ነው፣በሞንጎሊያ 49 በመቶ እጅ የህዝብ ኃብት ሆኖ ቀሪው የኢንቨስተሩ ነው፡፡  በቻይናና በህንድ የወርቅና የተወሰኑ ማዕድናት በውጭ ሃገር ሰዎች ንብረት መሆን ሕጉ ይከለክላል፡፡                                                                                                                             “While it is not at all a new phenomenon, some authorities are trying to retain possession of their minerals. This was the third trend identified. The country also plans to introduce mandatory participation of a state-owned mining company. Other countries are doing the same. Indonesia has revealed a strategy aimed at capping external ownership of mines to 49 percent after 10 years. Zimbabwe has already started its 51 percent ‘indigenisation laws’. Mongolia has put a 49 percent limit on foreign ownership of strategic mines. China and India have constraints on foreign ownership of certain minerals. Changes to ownership laws can have a major bearing on the prize miners anticipate receiving for their risk.›› Source:-Resource Nationalism – Risky For Africa’s Economic Growth-November 2, 2013 ventures-africa Economic development, Economics.”

{3} የኢትዮጵያ የነበረ የወርቅ ማዕድን በኦነግ  ኃብት ሆኖል !!!

የወርቅ ማእድን ድንበር ዘለል ንግድ የሃገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ገቢ ድባቅ መቶታል፡፡ በማዕድኑ ዘርፍ ወርቅ ለማምረት አስፈላጊ የሆኑት ግብዓቶች በውጭ ምንዛሪ እጥረት የተነሳ ተገዝተው ወደ ሃገር ውስጥ መግባት አልቻለም፡፡ ከወርቅ ማዕድን ሃብት ሌላ ሳፊየር (እንቁ)፣ኦፓል፣ታንታለም፣ ኢምራልድ፣ ጂምስቶንስ፣ ማርብል እንዲሁም ሜታሊክና ሜታሊክ ያልሆኑ ማዕድናቶች የዓለም አቀፍ ንግድ ገበያ፣ የውጭ ምንዛሪ ገቢ ተሸመድምዶል፡፡ የሃገሪቱ ማዕድን ኃብት ፎስፌትና ፖታሽ ከፍተኛ ክምችትም  ለውጭ ምንዛሪ ገቢ አስተዎፅዖ በጣም ዝቅተኛ ሆኖል፡፡

 • የወርቅ ማዕድን፣ በ2001 እኤአ የውጭ ምንዛሪ ገቢ 5 ሚሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን፣ በ2012 እኤአ 602 ሚሊዮን ዶላር ደርሶ ነበር፡፡ በ2017 እኤአ መንፈቅ አመት ሃገሪቱ 92 ሚሊዮን ዶላር አግኝታ ነበር፡፡ በተመሳሳይ በ2018 እኤአ መንፈቅ አመት ሃገሪቱ 95 በመቶ የወርቅ ማዕድን ኃብት የውጭ ምንዛሪ ገቢዎን አጥታለች፡፡ ሃገሪቱ የውጭ ገቢ ንግድ እቅድ 528 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ የተገኘው 30 ሚሊዮን ዶላር (የእቅዱን አምስት ፐርሰንት ) ብቻ ማግኘቶ ታውቆል፡፡ የሜድሮክ ጎልድ የወርቅ ማዕድን የሃያ አመት ፍቃድ ካለቀ በኃላ በሃገሪቱ በተከሰተው ህዝባዊ አመፅ  ህወሓት/ ወያኔ የትግራይ ክልላዊ መንግስት የኢዛናን የወርቅ ማእድን ሃብትን የግላቸው አድርገው ሲመዘብሩ እስከዛሬ ይገኛል፡፡
 • ዛሬም የኦህዴድ/ ኦዴፓ ቄሮ መንግሥት የለገደንቢ፣ የአዶላና ኢንጤቻ ማእድናት የክልላቸው ሃብት ብቻ ለማድረግ በማሰብ የማእድን ሃብት የውጭ ንግድ ገቢ መቀነስ ዋነኛ ምክንያት የዘር ፖለቲካው የሃብት ቅርምት የተነሳ መሆኑ እሙን ነው፡፡ ኬክ አበላችኃለሁ የሚለው የዘር ፖለቲካ ህዝብን ከማጋደል በስተቀር ዳቦም ሊያበላ እንዲሁም ስራም ሊፈጥር አልቻለም፡፡

“Ethiopia misses 95% minerals’ export target (January 31, 2019) Partly impacted by the revocation of MIDROC Gold license of Ethio-Saudi billionaire Al Amoudi, Ethiopia has missed 95 % of its mining export target for the first six months of the current fiscal year started July 8, 2018. Though the country planned to export different minerals worth $528 million, the country has only got $30 million achieving only 5% of its target, according to the latest report New Business Ethiopia received from the Ministry of trade. The country earned equal amount of hard currency for the same period last year. Meanwhile the target for the first six months last year was $92 million.”

 • አረንጎዴ የከበረ ድንጋይ፣በኢትዮጵያ የከበረ ድንጋይ ለ30 ሽህ ኢትዮጵያኖች ሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን ወደ ሲዊዘርላንድ፣ አውስትራሊያ እና አሜሪካ ምርቶቹ ይላካሉ፡፡ በ2017 ኢትዮጵያ 2290 ኪሎ ግራም የከበረ ድንጋይ ወደ ውጭ ተልኮ ነበር፡፡
 • ኢትዮጵያ ከተለያዩ ማዕድን ኃብቷ ወደ በውጭ ንግድ ገቢ 528 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት አቅዳ ያገኘችው 30 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን ይህውም የእቅዱን 5 በመቶ ብቻ እንዳሳካች ለማወቅ ተችሎል፡፡ ዋናው ምክንያትም የለገደንቢ የወርቅ ማዕድን ገቢው ለተረኛው ኦሮሚያ ክልል እንዲሆን ስለተፈለገ ነው፡፡ የኦህዴድ/ ኦዴፓ የፖለቲካ ካድሬዎች የለገደንቢ የወርቅ ማዕድን ገቢ ለኦሮሚያ ክልል እንዲሆን በድብቅ በመስማማታቸው ነው፡፡ ህወሓት የኢዛና የወርቅ ማዕድን ኃብትን የሕወሓት ኃብት አድርገው እንደዘረፉት ኦህዴድ/ ኦዴፓ ብልፅግና ፈለጉን በመከተን የካድሬዎቹ ድርሻ ማድረጉን ለህዝብ ማስታወቅ የፖለቲካ ፓርቲዎች ነን የሚሉ ሁሉ ኃላፊነት ነው እንላለን፡፡
 • ኦነግ በለማ መገርሳ ‹‹በኦሮሚያ ኢኮኖሚ አብዬት›› በኦሮሚያ ክልል የሚገኙትን የወርቅ ማዕድን ቦታዎችን በመቆጣጠር አዶላ፣ ለገደንቢ፣ ሳካሮ፣ ቀንጤቻ የማዕድን ኃብት ይገኝ የነበረ 500 ሚሊዩን ዶላር በአመት የውጭ ምንዛሬ ገቢ ዶክተር አብይ አህመድ ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ እየሞሸሸ መሄዱን የኢትዮጵያ ባንክ የቦርድ አባላቶች ዶ/ር ፍፁም አሰፋ፣ ወ/ሮ ደሚቱ ሃምቢሳ፣ አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ አቶ አድማሱ ነበበ፣ አቶ ማሞ እስመላለምምህረቱ፣ ዶ/ር አብርሃም በላይ፣አቶ በየነ ገብረመስቀል፣ አቶ ነብዮ ሳሙኤልና ዶ/ር ኢዮብ ተስፋዬ በኃላፊነታችሁ አንድ ቀን ያስጠይቃችሆል እንላለን፤ የምትበሉትም እንጀራ ሊያንቃችሁ ይገባል፡፡ የለገደንቢ የወርቅ ማዕድን በኦነግ፣ ኦፌኮ፣ኦዶፓ ብልፅግና ኃብት ሆኖል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ኃብት የነበረው የማዕድን ኃብትና የውጭ ምንዛሪ ምንጭ የነበረው  በኦዴፓ ብልጽግና የጦር አበጋዞች በተረኛነት ገቢው ተነጥቆ ቀልጦል፣ ይህን ያልተረዳ በመርፌ ቀዳዳ ግመል ይሾልካል ተረትን ያልተረዳ የባንክ የቦርድ አባላቶችና ምሁራንና የፖለቲካ ካድሬዎች ብቻ  ይሆናሉ፡፡ የዶክተር አብይ መንግሥት ወርቅ የተገኘባቸው ክልሎች 40 በመቶ የወርቅ ሽያጭ ገቢ ይኖራቸዋል፣ 10 በመቶ በዛ አካባቢ የሚኖሩ ህብረተሰብ ተጠቃሚ ይሆናሉ፣ 50 በመቶው የገቢ ድርሻ የፌዴራል መንግስት ይሆላል የሚል የማዕድን ኃብት አዋጅ ማወጁን ስንቶቻችን እናውቃለን፡፡ ሃገሪቱ መንኮራኩር በአመጠቀች ማግስት ባንካችን ባህር ሰርጉዶ፣ አለቱን ንዶ፣ ከርሰ ምድር መስመጡ እንቆቅልሹ የወርቅ መዕድን ኃባታችን በሻብያ፣ ወያኔና ኦነግ ቅርጫ ተደርጎ ነው እንላለን፡፡

ሚድሮክ ጉልድ፤MIDROC Gold

‹‹የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ›› ከዴሬክተር ጀነራል አሰፋ አብርሃ እስከ ዴሬክተር ጀነራል በየነ ገብረመስቀል  የደርግን መንግሥታዊ ዘርፍ ወደ ህወኃት/ኢህአዲግ የፓርቲዎች መንግስታዊ ዘርፍነት በማዘዋወር ወያኔ ‹‹በልማታዊ መንግሥት ስም›› የሃገሪቱን ምጣኔ ኃብት በሞኖፖል ተቆጣጥረዋል፡፡ በኢትዮጵያ የመለስ ዜናዊና የሼህ አላሙዲን  ስውር የወርቅ ማዕድን ኃብት የሽርክና ሚስጢር ታሪክ ያወጣዋል፣የወያኔ መንግሥታዊ ዘርፍ ነቀላና ተከላ ጥናታዊ ዘገባ ሚስጢር ዋነኛው፣ የመለስ ዜናዊ  ውርስና ቅርስ የሆነው የሙስና ፋብሪካ ወፍጮ ስራውን የጀመረው ከመንግስታዊ ዘርፍ ወደ ግል ዘርፍ ኃብትን በማዘዋወሩ ፕራይቬታይዜሽን ስም የተከናወነ ድራማ! የደደቢቶች ትያትር! በሃገሪቱ ታሪክ ወደር አይገኝለትም፡፡

 • ‹‹የሜድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ/የተ /የግ/ መሃበር በ2014 እኤአ በዓለም ባንክ በተዘጋጀው ፎረም ላይ ባቀረበው ሪፖርት መሠረት የሚድሮክ ለገደንቢ የወርቅ ማምረቻ እኤአ ከ 1997 እስከ 2014 ድረስ ባሉት 16 ዓመታት71 ኪሎ ግራም ወርቅ እንዲሁም 14670.6 የብር ማዕድን አምርቶ 17.24 ቢሊዮን ብር እንደሸጠ ያሳያል፡፡››
 • {ሀ} የለገደንቢ የወርቅ ማዕድን፣ ሜድሮክ ኢትዩጵያ ኢትዮጵያ በአራቱም አቅጣጫ የወርቅ ማዕደናት እንዳሎት የዳሰሳ ጥናቶች ቢያመላክቱም፣በደርግ ወታደራዊ መንግሥት ዘመን፣ በ1972 ዓ/ም ተገኝጦ በ1982 ዓ/ም ተመርቆ ሥራ የጀመረው የለገበንቢ የወርቅ ማዕድን፣በፕራይቬታይዜሽን የመንግሥት ልማት ድርጅት ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ በ172 ሚሊዮነረ ዶለር ለሚድርክ ወርቅ ባለቤት ሼክ መሃመድ ሁሴን አላ-አሙዲ የባለቤትነት ድርሻ 98 በመቶ ሲሆን የህወሃት/ኢህአዲግ መንግስት ድረሻ 2 በመቶ በንግድ ሽርክና ላይ የተመሠረተ ካንፓኒ ተመሠረተ፡፡ ተሸጠ፡፡ ሜድሮክ የወርቅ ማዕድን ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማሕበር (MIDROC Gold Mine Pvt Ltd. Co. (MGOLD) የሜድሮክ ኢትዬጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ አካል ነው፡፡ የሜድሮክ የወርቅ ማዕድን በ1990 እኤአ (6/19/97)  በሼክ መሃመድ ሁሴን አላ-አሙዲና በሚስታቸው ሶፊያ ሳላህ አላ-አሙዲና በኢትዬጵያ መንግስት6 ሚሊዬን ዩኤስ ዶለር መነሻ ካፒታል የተቆቆመ ድርጅት ነው፡፡ ከብሄራዊ ማዕድን ኮርፖሬሽን ( National Mining Corporation (NMC)  ከተቆቆመ ጥቂት አመታት በኃላ ሜድሮክ የወርቅ ማዕድን ተመሰረተ፡፡ በ1997 እኤአ የህወሃት/ኢህአዲግ መንግስት ለሜድሮክ የወርቅ ማዕድን (የወርቁ ክምችት መጠኑ 37,215 ኪሎግራም ነበር) 1,290,796,624 ብር (በ172 ሚሊዬን ዩኤስ ዶለር) የለገደንቢን የወርቅ ማዕድን  ለሃያ አመታት ፈቃድ ተሸጠ፡፡ በ1997እኤአ እሰከ 2017እኤአ ሃያኛ ዓመቱ ውል ተጠናቀቀ፡፡ የለገደንቢ የወርቅ ማዕድን በ6/19/1997 እኢአ የተሸጠው ለሃያ አመት ኮንትራት ውል እስከ በ6/19/2017 ዓ/ም ድረስ የኮንትራት ውሉ አበቃ፡፡ እንዲሁም በ7/7/2000 ዓ/ም ቀንጢቻ ታንታለም  በብሄራዊ ማዕድን ኃ/የ/ግ/ማ ስም ለሼህ አላሙዲን 215,800,000 ብር ተሸጠ፡፡ የህወሃት/ኢህአዲግ መንግስት ለሜድሮክ የወርቅ ማዕድን የለገደንቢን የወርቅ ማዕድን የ10 ዓመት ውል አደሰ፡፡  የወርቅ ማዕድኑ ከአዲስ አበባ በስተ ደቡብ 500 ኪሎ ሜትር  ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ የሜድሮክ የወርቅ ማዕድን በአዶላ- ለገደንቢ የማዕድን አሰሳ ፍቃድ ሲኖረው አጠቃላይ አመታዊ ምርት 1.6 ሚሊዬን ቶን ያልነጠረ የብረታብረት አፈር ያመርታል፡፡ አመታዊ አማካኝ ምርት 4,500 ኪሎ ግራም የወርቅና ፣ብር ቅልቅል ተመርቶ በመጨረሻው 3,500 ኪሎ ግራም  የነጠረ የወርቅ ምርት ያመረታል፡፡
 • {ለ} ሳካሮ የወርቅ ማዕድን፣ ሁለተኛው የወርቅ ማዕድን ክምችት በተጨማሪ በዚሁ ጉጂ ዞን ሳካሮ አካባቢ ሁለተኛውን ወርቅ ማውጫ ፍቃድ አግኝቶ ወደ ግንባታ ገብቶል፡፡ በእምራብ ሳካሮ በ57 እስኩየር ኪሎሜትር ራዲየስ /ኩታገጠም ቦታ ውስጥ እስከ ለገደንቢ የሚገኝ ሲሆን የወርቁ ክምችት 17,250 ኪሎግራም ነው፡፡ በዓመት 2300 ኪሎ ግራም ወርቅ ማምረት ይችላል፡፡ በዓመት ከዚህ የወርቅ ወጪ ንግድ 87.2 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እንሚገኝ የሚድሮክ ወርቅ ጥናት መረጃ  ያመለክታል፡፡

{4}  ኢህዴን/ብአዴን/አዴፓ ብልፅግና አሣማ የጦር አበጋዞች ናቸው፣ መተከል/መቸከል የወርቅ የማዕድን፣ ሦስተኛው የወርቅ ማዕድን ክምችት በሰሜን ምስራቅ አዲስ አበባ 600 ኪሎ ሜትር ርቀት በመተከል የማዕድን አሰሳ ፍቃድ አለው፡፡ የሜድሮክ የወርቅ ማዕድን ሃላፊነቱ፤ የግል ድርጅት 7, 2011 ሰብ ሰሃራ መረጃ በወጣው ዜና መሰረት 33,000 ኪሎግራም ያለው የወርቅ የማዕድን ክምችት መተከል የአማራ ክልል የነበረው፣ በሻብያ ፣ወያኔና ኦነግ የፖለቲካ ሴራ ቅኝ የገዛቸው አማራ እንዳያንሰራራ የሃገሪቱን ጅኦፖለቲካ አከላለል ከአማራው ህዝብ ግዛት ቆርጠው ለትግራይ (ወልቃይት፣ራያ ወዘተ)፣ ለኦሮሚያ (ሸዋ፣ ደራ፣ አዲስ አበባ ወዘተ)፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ (መተከል ወዘተ) ለሌሎች በመስጠት በመለስ ዜናዊ አከላለል መቸከል በቤኒ ሻንጉል ጉምዝ  ክልላዊ መንግስት  ማግኘቱ ተገልፆል፡፡ የመተከላ የወርቅ መዕድን በዛን ግዜ ባለው የዓለም ዓቀፍ ንግድ የወርቅ ገበያ መሠረት የተገኘው ወርቅ ዋጋው ሲሰላ 19 ቢሊዬን ብር እንደሚሆን ተገምቶል፡፡  የወርቅ ማዕድን ክምችቱ በኢትዩጵያውያን ኤክስፐርቶች ምርምር የተገኘ ሲሆን ቦታውም (በቀድሞው ጎጃም ክፍለ ሃገር) በመተከል ዞን ጂላ በሚባል ቦታ በአሁኑ የህወኃት ኢህአዲግ አከላለል ቤኒ ሻንጉል ጉምዝ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ካንፓኒው የወርቅ ማዕድን ማሽን ተክሎ የወርቅ ምርቱን ማውጣት ጀምሮል፡፡ ካንፓኒው ከመንግስት 7,000 ሄክታር መሬት በመውስድና 46 ሚሊየን ብር መዋለ-ንዋይ/ኢንቨስት/ በማድረግ የወርቅ ማዕድን ምርት በማምረት ላይ ይገኛል፡፡ በ1998 እኤአ ካንፓኒው ከማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር ፍቃድ ተሰጥቶት ሥራውን ጀምሮል፡፡‹‹ ይህ  ትልቁ የወርቅ ማዕድን ክምችት በመተከል ዞን ባገኘው የወርቅ ፍለጋ ፈቃድ በተባሉት ሦስት ቦታዎች  በጀላይ፣ፌቲንና ቻሎ በሜድሮክ ካንፓኒ  እንደተገኘ ጥናቱ ያስታውቃል፡፡ በእነዚህ ቦታዎች ላይ ባካሄደው ጥናት በአጠቃላይ 50.6 ቶን የወርቅ ክምችት መግኘቱን አስታውቆል፡፡ በ2008 ዓ/ም 3066.67 ኪሎ ግራም ወርቅ ወደ ውጭ ለመላክ አቅዶ 2754.93 ኪሎ ግራም ወርቅ መላክ ችሎል፡፡ ዕቅዱን 89.8 በመቶ ማሳካት የቻለ ቢሆንም፣ ይህም መረጃ የተገኘው ከሚድሮክ ለገደንቢ ወርቅ ማውጫ እንደሆነ ተጠቁሞል፡፡››  የመቸከል የወርቅ ማዕድን ኃብት በተመለከተ የአማራው ክልል ኦዴፓ ብልፅግና ለአማራ ህዝብ የሚታገሉ ድርጅቶች መኢአድ፣ መአህድ፣ አብን፣ የዜግነት ፖለቲካ አራማጆች ሰማያዊ ፓርቲ (የሽህዋስ አሰፋ)፣ አርበኞች ግንቦት ሰባት (ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ)፣ አንድነት ፓርቲ (አንዱዓለም አራጌ )፣ ባልደራስ መኢአድ፣ (እስክንድር ነጋ)፣ የአብሮነት ፓርቲ (ልደቱ አያለው)፣ መድረክ (በየነ ጴጥሮስ) ከሃገር ሽማግሌዎች ጋር ሆነው የወርቁን የህዝብ የጋራ ኃብት በማድረግ ችግሩን መፍታት እንዲሁም የክልሎች የድንበር ግጭቶችን በሰላመዊ መንገድ በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈቱ የብሄር ፖለቲካና በዜግነት ፖለቲካ አራማጆች መጣር አለባቸው እንላለን፡፡

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የወርቅ ሰንዱቅ ተጨማሪ ወርቅ ያልሆነ አርቴፊሻል ወርቅ ተገኘ

‹‹በኢትዮጵያ መዓከላዊ ባንክ ተጨማሪ ወርቅ ያልሆነ ወርቅ ቅብ ባሌስትራ ብረት ከወርቅ ማስቀመጫው ሰንዱቅ ወስጥ ለዓመታት ተከማችቶ ተገኝቶል፡፡ ከኢትዮጵያ  የወርቅ ማዕድን ሥፍራ  ብዙ ቶን ወርቅ ተጭኖ እንግሊዝ ለንደን በሼክ አላሙዲን ትብብር ና በቢዝነስ ባልደረቦቹ  አዜብ መስፍን ፣ ስብሃት ነጋ እንዲሁም ሌሎች የወያኔ ቤተሰቦች ባህር ማዶ መላኩ ታውቆል፡፡ የቢቢሲ ጋዜጠኛ የሆነችው ኤልሳቤት ብለንት  ዘገባ መሰረት፤  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሚልካቸውን የወርቅ ጥፍጥፍ ባር ከወርቅ መጋዘኑ ሳጥን ያለው እውነተኛ መሆናቸውን መርምሮና አጣርቶ እንዲልክ በእንግሊዝ ሙያተኞች ተመከረ፡፡  ብሄራዊ ባንኩ ባጣራው መሠረት በብዙ ሚሊዮን ዶላር የተገዛው ወርቅ ያልሆነ ወርቅ ቅብ ባሌስትራ ብረት እንደሆነ ተደረሰበት፡፡ የመጀመሪያው ፍንጭ የተገኘው የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ባንክ ወደ  ደቡብ አፍሪካ የሺያጭ ሰነድ ስምምነት መሠረት  የወርቅ ቡችላ ጥፍጥፍ ባር ሃሰተኛ መሆኑ ሪፖርተ በቀረበለት ጊዜ ነበር፡፡  ከደቡብ አፍሪካ የተመለሰው ወርቅ ያልሆነ ወርቅ ቅብ ባሌስትራ ብረት ለባንኩ  አቅራቢ የነበሩ የአገር ውስጥ ነጋዴዎች ነበር፡፡ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋላቸው የወርቅ አቅራቢ ነጋዴዎች፣ የብሄራዊ ባንክ ሹማምንቶች፣ ከኢትዮጵያ ጅኦሎጂካል ስርቬ ሠራተኛ የሆኑ ኬሚስቶችና፣ ሌሎች ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡ በምርመራው መሠረት ከባንኩ የወርቅ መጋዘን  ሣጥን ውስጥ ተጨማሪ ወርቅ ያልሆነ ወርቅ ቅብ ባሌስትራ ብረት   ለብዙ አመታት ተቀምጦ መገኘቱ የባንኩ መበስበስ፣ ሌብነትና ሙስና እስከ አጥንታቸው መቅኒ ድረስ ሌብነትን ቻርጅ የሚያደርጉ የባንክ ሠራተኞች የተነሳ ሃገራችን ስም በወርቅ ቅብ ባሌስትራ ብረት የተነሳ በዓለም ባንክ ታሪክ ሰሟ ጠፋ፡፡ እንቆቅልሽ የሆነው ሚስጢር ግን እውነተኛ የሆነው ወርቅ ባንክ ከገባ በኃላ በወርቅ ቅብ ባሌስትራ ብረት ተቀይሮ ተቀመጠ ወይስ መጀመሪያውኑ የወርቅ ቅብ ባሌስትራ ብረት ነበር ከባንኩ የወርቅ መጋዘን  ሣጥን ውስጥ የተቀመጠው፡፡ እንቁላል፣ጫጩት! የወርቅ ቡችላ… ወርቅ ቅብ ባሌስትራ ብረት….የወርቅ ቡችላ…›› ሳይማር ያስተማራቸው ከትብያ አንስቷ ሰው ያረገቻቸው እምዬ ኢትዮጵያ በእነ ግርማ ብሩ፣ ሶፍያን አህመድ፣ ተክለወልድ አጥናፉ፣ ዮሐንስ አያሌው፣ አብርሃም ተከስተ፣ይናገር ደሴ፣ ባጫ ጊና ጡቷን ተነከሰች!!! ለትውልዱም መጥፎ ስነምግባር ተክለው አለፉ፣ ታሪካቸው ይሔው ነው፡፡ የእውቁ የብሄራዊ ባንክ ፕሬዜዳንት ክቡር ዶክተር ተፈራ ደግፊ በሰሩት ሥራ ትወልድ ሲያወድሳቸው ይኖራል፡፡

More fake gold found in Ethiopian bank

Posted on March 13, 2008, Updated on March 13, 2008 by Elias Kifle

Why doesn’t BBC investigate the illegal shipment of tones of gold bars from Ethiopian gold mines directly to London by Al Amoudi, in collaboration with his business partners, Azeb Mesfin, Sebhat Nega and other members of the Woyanne crime family?

By Elizabeth Blunt/ BBC News, Addis Ababa

Ethiopia’s national bank has been told to inspect all the gold in its vaults to determine its authenticity. It follows the discovery that some of the “gold” it had bought for millions of dollars was gold-plated steel. The first hint that something was wrong reportedly came when the Ethiopian central bank exported a consignment of gold bars to South Africa. The South Africans sent them back, complaining that they had been sold gilded steel. An investigation revealed that the bank had bought a consignment of fake gold from a supplier, who is now under arrest.

Other arrests followed, including business associates of the main accused; national bank  officials; and chemists from the Geological Survey of Ethiopia, whose job it is to assay the bank’s purchases of gold and certify that they are real. But what has clearly now got the [fake] government even more worried is that another different batch of gold in the bank’s vaults has also been found to be fake, and this time it was gold which had been there for several years, after being seized from smugglers trying to take it to Djibouti.

Mining

Ethiopia’s [fake] parliament ordered the inspection of all gold in the national bank’s vaults.

A report from the [fake] auditor-general on the affair is expected to be presented to [fake] parliament during its current session. Gold is mined in Ethiopia in considerable quantities, and a trader selling gold to the central bank has to have it tested and certified by the Geological Survey. Whether the bank bought fake gold in the first place, or whether real gold from the vaults has been swapped for gilded steel, the fraud has cost the bank many millions of dollars, and it must have involved collusion on a considerable scale.

ከወርቅ ቡችላ ወደ ቡችላ ካድሬዎች!!!

የ‹‹አገር በቀል›› የኢኮኖሚ ፖሊሲ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አማካሪ አቶ ግርማ ብሩና የባንክ ባለሙያዎች አድርባይነት የተነሳ፣ የሃገሪቱ የማዕድን ኃብት፣ የባንክ ተቀማጭ ገንዘብ አድሎዊ ብድር አሰጣጥ፣ መሬት ኃብት የሙስና አስራር እንዲሁም  በውጭ ምንዛሪ ከወርቅ ማዕድን ገቢ ማሽቆልቆል ከህወሓትኢህአዴግ የ27 ዓመታት የማራቶን ዘረፋ የኦሮሙማ  ከ2010 እስከ 2012 ዓ/ም፣ በሁለት አመት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ የባንክ፣ የወርቅና መሬት ዘረፋ የመቶ ሜትር ዘረፋ አዲስ ሪከርድ ሰብረዋል፡፡ የወያኔና የኦነግ የጦር አበጋዞች የወርቁን ኃብት እንደተቆጣጠሩትና ሃገሪቱ ያለባትን ብድር መክፈልም እንደማትችልና በኢኮኖሚ ማገገም  ተስኖት ህዝብ በከፍተኛ ችግርና በድህነት አረነቆ ተዘፍቆ ዳግም ካመጸ፣  መሪዎቹን እንደሚበላ መገንዘብ ይኖርባችኃል እንላለን፡፡

ህወሓት ኢህአዴግ ሆናችሁ ገምተናል ብላችሁ ህዝብ ሁለተኛ እድል እንደሰጣችሁ በመርሳት ዛሬ  በኦዴፓ ብልፅግና ስም ያንንው ምህታተኛ የፖለቲካ ሴራ የሻብያ፣ የወያኔና ኦነግ የመቶ አመታት የቤት ሥራ፣ ስውር ስራ ህዝቡን ከፋፍሎ በመግዛት ተሻሽሎ የነበረውን የአማራና ኦሮሞ ህዝብ ግንኙነት በማበላሸት፣ ህወሓትን ፈርታችሁ የትግራይን ህዝብ ከኢትዮጵያ ህዝብ መገለሉ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝብ ህብረትን በመከፋፈል የ56 ብሄር ብሄረሰብ እጣ ፈንታ እንደ ሲዳማ ክልላዊ መንግስት ለመሆን ሲዘፈን፡-ሲዘፈን የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ኦዴፓ)፣የኦሮሞ ብሄራዊ ኮንግረስ (ኦብኮ)፣የመላው ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የገዳ ስርዓት አራማጅ ፓርቲ፣ የኦሮሞ አቦ ነፃነት ግንባር፣ የኦሮሞ ነጻነት አንድነት ግንባር፣ የኦሮሞብሄራዊ ነፃነት ፓርቲ ፣ የኦሮሞ ነፃነት ንቅናቄ፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (አቶ ዳውድ ኢብሳ)፣ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና)፣ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ሌንጮ ለታ) እና ሲፋቁ ኦነግ ናቸው ትሉ የነበር የኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ ኦሮሚያን እንደገነጠሉ ካልገባችሁ  መራራ ጉዲና ያለውን ‹ህዝብ መሪዎቹን ይበላል!!!› ትዝ ይበላችሁ፡፡ ጅዋር ያላችሁን ‹‹ ወይ በምርጫ ወይ በሜንጫ›› እንድታስታውሱ እንበል አስራሁለት!!! ሽመልሰስ አብዲሳ ያላችሁን ‹‹የሰባበሩንን ሰባበርናቸው›› ቃል ወደ ተግባር መለወጫው ቀን የቀረበ ይመስላል፡፡ በቀለ ገርባ ‹‹ኦሮምኛ ካልተናገሩ አትሽጡላቸው!!!›› ወዘተ የመከላከያ ሚኒስትሩ ኦቦ ለማ መገርሳ የፖለቲካ ሴራው በደንብ ገብቶታል ከትዕይታ ሥራ፣ ከመድረክ ትወና ሥራ ርቆል፡፡ የፖለቲካ ጥንካሬ የሚለካው፣ በገንዘብ፣ በወርቅ፣ በመሬት፣ በጦር መሣሪያና፣ በፀጥታና ደህንነት መረጃ  ኃብት የተቆጣጠረና የጠነከረ ለመከላከያ ሠራዊቱ ደሞዝ ይቆርጣል፣ እህል ይሰፍራል ጦሩንም በየአቅጣጫው ያሰማራል የመንግስትና የኦነግ ሥራ ሁሌ ስውር ነው፡፡ መንግስት መሆን የምትሹ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የፖለቲካ ሀ፣ሁ ለማወቅ ሞክሩ ገንዘብ፣ ወርቅ፣ መሬት፣ ጦር መሣሪያና፣ ፀጥታና ደህንነት መረጃ  ኃብት ከሌለህ እራስህም የለህም ‹‹የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም!!!›› አበው የሚሉት ለዚህ ነው፡፡ ከድሮ ጀምሮ ህዝቡ ‹‹ተባበሩ ወይ ተሰባበሩ›› ያላችሁ ዛሬም አልገባችሁ፡፡ ኦነጎች በተረኝነታቸው ሲተርቱ የዜግነት ፖለቲከኖች ሲፋቁ አማራ ናቸው!!!

ከወርቅ ቡችላ የወርቅ ቅብ ባሌስትራ ብረት!!! ….አባ ቶርቤ!!!

 • ‹‹ጋዲሳ ሆገንሳ ኦሮሞ!!!›› በማለት ለማ መገርሳ፣ ዳውድ ኢብሳ፣ መረራ ጉዲና፣ በቀለ ገርባና ከማል ገልቹ ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያቸው ይገባሉ!!!፡
 • ‹‹ትብብር ለዴሞክራሲያዊ ፌዴራሊዝም›› የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር መረራ ጉዲና (ፕሮፌሰር)፣ ፣ ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ ኦብሳ፣ እና ከኦሮሞ ብሔራዊ ፓርቲ (ኦብፓ) ሊቀመንበር ብርጋዴር ጄኔራል ከማል ገልቹ ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያቸው ይከታሉ!!!፡
 • ጁዋር መሃመድ በነደፈው ‹‹ኦሮሞ ፈርስት›› ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያውን በገንዘብ፣ በወርቅ፣ በመሬት፣ በጦር መሣሪያና፣ በፀጥታና ደህንነት መረጃ ኃብት አሰባስቦ የኦሮሞ የክልልና የፌዴራል መንግሥትን ይቆጣጠራሉ፡፡
 • ታከለ ኡማ የአዲስአበባ መሬት ለቆሮ ያድላል፣ የከተማውን ህዝብ ስነህዝብ ስብጥር (ዴሞግራፊ) ለመቀየር በአንድ በኩል፣ የህዝብ ቤቶች እየፈረሰ፣ በሌላ በኩል፣ ለወደዳቸው ቤት መገንቢያ መሬት ይሰጣል ከንቲባው የኮዬ ፈጬ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በአርሶአደሮች ስም ግማሽ ያህሉ ያለዕጣ ለአቶ ሽመልስ አብዲሳና ለከንቲባ ታከለ ኡማ ብሎገሮችና የማህበራዊ ሚዲያ አክቲቪስቶች እንደተሰጠ ተጋልጦል፡፡ መሃንዲሱና ሰባበርናቸው የጥላቻ ፖለቲካ በመስበክ አንድ ቀን ለፍርድ እንደሚቀርብ መጠራጠር የለብንም፡፡ ዶክተር አብይ አህመድ (ስኳርት) ሁሉን እንደማያውቅ አርጎ ይተውናል፣ እንኳን ይሄን የዝንብ ጠንጋራ ያውቃል፣ በኢንሳ ዋናው ስራው ስለላ መሆኑን አትዘንጉ፡፡ ጊዜ የሰጠው መሓንዲስ ታከለ ኡማ መስቀል አደባባይ፣ ጃንሆይ ሜዳ፣ የከተማዋን ቅርስ ማጥፋት ወዘተ ከስር ከስር ይሰራል፡፡ ታከለ ኡማ ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያውን  ከአዲስ አበባ መሬት ላይ ቸክሎ ዴሞግራፊውን ለመቀየርና ለቀጣዩ ምርጫ ኦነግ እንዲያሸንፍ ስራውን እየሰራ ይገኛል፡፡

·         ዶክተር አብይ አህመድ Confederation states ፡- የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰብ ክልላዊ መንግስቶችን በኢትዮጵያ የኮንፌዴሬሽን መንግስቶች በአንድ ኢትዮጵያ ድንበርና ወሰን ብቻ ክልሎች ድንበርና ወሰን ሳይኖራቸው በጋራ የሚተዳደሩበት መንግስት ምስረታ ነው፡፡  ዘርና ቌንቌ ተኮር ክልላዊ መንግስቶች  ነፃ በመውጣት በጋራ ስምምነት የሚያቆቁሙት በኦሮሙማ የሚመራ ወርካ መንግሥት ዣንጥላውን ለሁሉ በማልበስ የኦሮሞ፣ የትግራይ፣ የደቡብ ህዝቦች እና አጋር ክልላዊ መንግሥቶች በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ አዲስ ስምምነት በመንደፍ፣ በጋራ በመከላከያ ሠራዊት ግንባታ፣ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ፣ የአገር ውስጥ ንግድና የገንዘብ ኖቶችና ሣንቲሞች በጋራ አጠቃቀም፣ የኮንፌዴሬሽን መንግሥቶች የሹመት ክፍፍል የሚኒስትርነት፣ የአንባሳደርነት፣ የጀነራል መኮንንነት ወዘተ የስልጣን ከፍፍል ወዘተ  ላይ ስምምነት የኮንፌዴሬሽን መንግስቶች የሚመራ መሪ ይመረጣል፡፡

A confederation is a union of sovereign groups or states, united for purposes of common action. Usually created by a treaty, confederations of states tend to be established for dealing with critical issues, such as defense, foreign relations, internal trade or currency, with the general government being required to provide support for all its members. Co

በኦሮሙማ እግሩ የሸበተ፣ ፀጉሩ የሸበተ፣ልቡ የሸበተ ፈላስማ፤  የኢትዮጵያን ህዝብ በዕለት ከዕለት የብሄርና የዘር ፍጅት እንዲሁም የኃይማኖት ግጭት ውስጥ በመዶል ህዝቡ በፍርሃት ውስጥ ተዘፍቆ እንዲኖር በማድረግ፣ የህዝቡን አትኩሮት ወደ ሌላ በማዞር የፖለቲካ ሴራ የኦሮሞ መንግሥት ማስቀደምና የኦሮሞን የኢኮኖሚ ዘረፋ መገንባት ዋነኛ ዓላማቸው መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡  ኦነግ/ ኦዴፓ ብልፅግና  የኦሮሞ የክልልና በኮንፌዴሬሽን መንግሥትነት በሚቀጥለው ምርጫ ይጨብጣል፡፡  ደኢህዴን ደቡብ ክልል የማንነት ጥያቄ ሁሉንም በመመለስ ከፍተኛ ድጋፍ ኦሮሙማ ያገኛል፡፡ ከህወሓት ጋር  ከትግራይ ክልላዊ መንግሥትነት ጋር በመስማማት በኮንፌዴሬሽን ትግራይን ይቀላቀላል፣ የአማራ ክልል ወደ አጋር ክልልነት ዝቅ ያደርጉታል፡፡  ስድስቱ አጋር ድርጅቶች ሱማሌ፣ አፋር ፣ ቤኒ ሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ሃረሪ፣ አማራ በእኩልነት በኮንፌዴሬሽን መንግሥትነት ይታቀፋሉ፡፡ የለማ መገርሳ ‹‹ጋዲሳ ሆገንሳ ኦሮሞ!!!›› ፣የጁዋር መሃመድና ‹‹ኦሮሞ ፈርስት›› እና የመረራ ጉዲና ‹‹ትብብር ለዴሞክራሲያዊ ፌዴራሊዝም›› የሚንስትርነት፣ የአንባሳደርነትና የጀነራል መኮንንነት ማዕረግ ይበልጥ ይጠናከራል፡፡ ኦሮሙማ የኮንፌዴሬሽን መንግስቶችን በዴሞክራሲያዊ መንገድ ማስተዳደር ይሳነዋል፡፡  በዚህ አገዛዝ የዜግነት ፖለቲካ አራማጆች ተከታይ ህዝብ ላይ የስብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ጥሰት ሞት ፣እስራትና ስደት  ይፈፀማል፡፡ አንድ ሽህ አንድ የየክልሎቹ የጦር አበጋዞች በክልላቸው የሚገኙ የማዕድን ሃብቶች፣ ቡና፣ ጫት፣ ሰሊጥ፣ የቀንድ ከብት  ወዘተ የክልላቸው ያደርጋሉ በዛም ምክንያት ግብር ጠያቂ መንግሥቶች ይበዛሉ፣ ህገወት የኮንትሮባንድ ንግድና የጦር መሣሪያ ዝውውር ይጦፋል፣ መንገዶች ይዘጋሉ፣ በዛም የተነሳ የድንበር ግጭት እንደ ሰደድ እሳት ይቀጣጠላል፡፡ የዘር ጦርነትና የውክልና ጦርነቶች ይስፋፋል፡፡ ጎረቤት አገሮች ኤርትራ፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ሰሜንና ደቡብ ሱዳን ጣልቃ ገብነት ከሩቅም የግብፅና አረብ አገሮች ጣልቃ ገብነት  ይስተዋላል፡፡ የኦነግ የጦር አበጋዞች መግሥት የህዝቡና  የዓለም አቀፍ ዲፕሎማቶች ፀጥታና ደህንነትና ማስከበር ይሳነዋል፡፡ በኮንፌዴሬሽን ኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አዲስ አበባና ድሬዳዋን በኦሮሚያ ክልል ሥር በኃይል ለመቆጣጠር በሚያደርጉት የጦርነት ዘመቻ በከተሞች ውስጥ ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያቸውን ይገነባሉ፣ የከተሞቹን ጥንታዊ ቅርሶች ያወድማሉ፣ መስቀል አደባባይ ጃንሆይ ሜዳ፣ የአንበሳ ኃውልቶች በጣኦስ መተካት፣ የሚኒልክ ኃውልት፣ የራስ መኮንን ኃውልት ወዘተ በህዝባዊ እንቢተኛነትና ህዝባዊ አመፅ ይነሳል፣ በህዝብ ላይ እልቂት ይፈፅማሉ!!! በሃገር ውስጥ አማፂያንና በባህር ማዶ  ደጋፊዎች ህብረት በኦሮሙማ  የኮንፌዴሬሽን መንግስቶች የኦነግ ጉጀሌ ኃይልና በሃገሪቱ የሰፈነው የጦር አበጋዞች ዘመን በወታደራዊ መፈንቅለ አገዛዝ ይወገዳል፡፡  በፊዴራል መንግስት ስም፣በዴሞክራሲ ስም ፣ በአብታዊ ዴሞክራሲ ስም፣ በልማታዊ መንግሥት ስም ፣ የኮንፌዴሬሽን መንግስቶች ስም፣ ዘርና የቌንቌ መታወቂያ ካርድ  የሚሸጡ ነጋዴ የፖለቲካ ካድሬዎች ለፍርድ ይቀርባሉ፣ የህግ የበላይነት በኢትዮጵያ ይሰፍናል፣ ፍትህ ይሰፍናል፡፡ ከሁሉም በላይ የህግ የበላይነትን የሚያሰፍን መንግሥት ታላቅ ድጋፍ የሚያገኝበት ዘመን ይመጣል እንላለን ፡፡

 

ፖለቲካ ከከፍተኛ ትምህርት ተቆማት፣ዮኒቨርሲቲዎች ጣልቃ አይግባ!!!

የህግ የበላይነት ከሌለ መንግሥት የለም!!!

የህግ የበላይነት ከሌለ ዴሞክራሲ የለም!!!

መንግሥት ከኃይማኖት ጣልቃ ገብነት ይውጣ !!!

በሃገራችን የፖለቲካ ካድሬዎች በመንግሥታዊ ተቆማት ሥራ ጣልቃ ገብነት እስካልተወገደ ድረስ ዘመናዊ አስተዳደር አይገነባም!!!

ቸር እንሰንብት (5/1/2020)

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.