መልአክ ጣዎስ (ታዎስ) – አስቻለው ከበደ አበበ

PeacockSymbolismበጃንሆይ ዘመነ መንግስት ለትምህርት የደረስኩ ስላልነበርኩ ወይም መንገድ ላይ ስላልትግናኘን ከእጃቸው ገንዘብ አልተቀበልኩም፡፡ የሁለቱ ኮሚንሰቶች አገዛዝ ዘመንን ግን ከነስጦታው በደንብ አውቀዋለሁ፡፡ ሁለቱም በሐይማኖት ላይ ያላቸው አቋም  ከመንፈሳዊ አባቶቻቸው ማርክስ፣ ኤንግልስና ሌኒን የተወረሰ ነው፣ ምንም እነኳን መልካቸውና ተክለ ሰውነታቸው እኛን ቢመስልም፡፡ ስልታቸው ይለያይ እንጂ እግዜሩንና ተቋማቱን በማጭድ ቀርፍፈውና(ቅርፍቶኤል) በመዶሻ(ምድቅኤል) ቀጥቅጠው አስደንጋጩን ስጦታቸውን ለአርባ አራት አመታት ያህል እንሆ ብለውን አልፈዋል፡፡

በ1940ዎቹ የተጻፈ አንድ መነኩሴ ከምሞቱ በፊት ስለጻፈው ልፋፈ ጽድቅ ያነበብኩትን ላጋራችው፡፡ ነገሩ የጥንት ክርሰቲያኖች የሚጋሩት የአሌክሳነደር( እስክንድር) ታላቁ ታሪክ ነው፡፡ እስክንድር ባቢሎልን (ኢራቅን) አልፎ ካውካስ ተራራዎች ላይ ጉግ ማጎግን አገኛቸው፡፡ ሁለት መልአክታዊ ሃይሎችን በመጠቀም ተራራዎቹን፤ ምድቅኤልና ቅርፍቶኤል በሚባሉ መልአክታንት እርዳታ ዘግቶ አጋዛቸው፡፡ በኋላ ዘመን ከግዞታቸው ሲውጡ ምልክታቸውን  ቅርፍቶኤልና(መጭድና)  መድቅኤል(መዶሻ) አድርገው ይነሳሉ፣ ወንድም ከወንድም በማጋደል እሬሳ ከመንገድ ላይ ሳነሳ ለቀናት በማስቆየት ደምይጠጣሉ፡፡ ኮሚኒስም ማለት እንግዴ ይህ ነው፡፡ እኒህ የሀገራችን ኮሚንስቶች ከአርባ አመት በላይ ቆዳችንን ገፈው በመዶሻ ቀጥቅጠው ገዙን፡፡

ህወሓት/ ኢህአዲግ ሀገራችንን ለሃያ ሰባት አመታት ያህል ከገዛ በኋላ እንደ ጸሎታችንና ትግላችን ከውስጡ በወጡ ጎልማሶች፤ ትጥቅ ትግል ላይ በነበሩ ወንድሞችና በሰላማዊ ትግል በታገሉ ትንታጎች ሦስት ጎናዊ ጣምራ ትግል የዛሬ ሁለት አመት አካባቢ ለውጥ መምጣት ችሏል፡፡

የሚገርመው ነገር ደግሞ የፈጣሪን ስም የሚጠራ፣ ፈሪሃ እግዚአብሔር እንደለው ሊያሳየን የሚሞክር አመራር ብቅ ማለቱ ነው፡፡ በዚህም እኔና መሰሎቼ ከፍተኛ ደስታ ነበር የተሰማን፤ መቼም ፈጣሪን እፈራለሁ የሚል ፍጡሩን በአንድ አይን እንደሚያይ እርግጠኛ ስለነበርን ነው ያ አይነት ስሜት ሊሰማን የቻለው፡፡

ወደ ፊት የመጡት ጠ/ሚኒሰተር እናታቸው ከሰባት አመታቸው ጀምራ ለዚህ “ንግስና” እንዳዘጋጃቸው ገልፀው አመሰገኑ፡፡ ሴቶችን ለከፍተኛ ስልጣን አበቁ፡፡ እኛ የንግስት ሳባ፣እሌኒ፣ ጣይቱ… ልጆችም ሰው መጣ ማለታችን ስህተት አልነበረም፡፡ እሳቸውም የተለያዩ ወንደሞችን በኦርቶዶክስ ተዋህዶ፣ ፕሮቴሰታንትና እስልምና ሐይማኖቶች ውስጥ አሰታርቀው የጋራ መድረክ እንዲፈጠር ምክነያት ሆኑ፡፡

እነደእምነታቸው በ“ነብይት” ብርቱካን ፊት ተንበርክከው አንተ ወደ ፊት ጠ/ሚንስተር ትሆናለህ ስትላቸው፤ የእናንተ አምላክ እየሱስ …ብለው ሲያመሰግኑ በዩትዩብ መስኮት አየናቸው፡፡ ነገሩ አሁን ተገላብጦ ማለትም ከኮሮና ቫይረስ መምጠትና ፈር የለቀቀ ትንቢት በኋላ፣ ጠ/ ሚንሰትሩን የሚያመሰግኑ እሷ ሀሰተኛ ነች የሚሉ ተነሱ፡፡በዚህም ወለፈንዴ ትንቢተ ፐሮትስታንቱ ውስጥ መታየት ጀመረ፡፡

ጠቅላዩ ብሩን ከዚያም ከዚህም ብለው አምጥተው አጃይብ የሚያሰብል የቤተ መንግስት ቅጥረ ግቢ አርቲትክተራዊ ተሐድሶ አደረጉ፡፡ “የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው” በሚለው ብሂል “ይህን ታላቅ ስራ ከፍሎ ይተች ይሆናል እንጂ ማን ሊቃወም ይገባዋል?” ብለው ብዙ ሊህቃንኛ ጨዋዎች ተናገሩ፡፡

ይህ ሁሉ ስራ ሲከናወን በኢትዮጵያ ባለመሆኔ የአይን ምስክር መሆን አልቻልኩም፡፡ ነገር ግን እድሜ ለቴክኖሎጂ ሁሉኑም ነገር ቨርቹዋሊ፡ የአንድነትን ፓርክ በሁሉም እይታ ማለትም በወፍ በረር አይን፣ በትሏና በሰው እይታ አይቼዋለሁ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዶ/ር ጸጋዬ ረጋሳና አቶ ጃዋር መሐመድ ይናገራሉ

እንዳየሁት መጀመሪያ ወደ አዕምሮዬ የመጣው  በደርግ ዘመነ መንግስት የተሰራው የአራት ኪሎ ፓርላማ(ሸንጎ) ነበር፡፡ በቀድሞው መንግስት ዘመን ፓርላማው የኖህ መርከብ በመባል ይታወቅ ነበር፣ ደረጉ ከጥፋት አልተረፈበትም እንጂ፣ አሁን ጠቅላዩ መጻፊያ ቢሮቸው አድረገውታል ወይም መሰለኘ፡፡

ከዚያም ቀጥዬ እራሴን የጠየቁት ጥያቄ፣ ምነው ጠ/ሚኒስትሩ እንስሳቱን፣ አራዊቱንና ባህላዊ እሴቱን በመርከብ ቅርጽ ባለ ፓርክ ውስጥ መሰባሰብ ፈለጉ የሚል ነበር፡፡ ከዚያም እኔ አሻጋሪ ነኝ ብለዋልና የኢትዮጵያ አምላክ ይርዳቸው፣ ኢትዮጵያን እስከ ፖለቲካ ግስንግሷ ያሻገሯት ስል መልካም ምኞቴን ተመኘሁላቸው፡፡

እነዚያን ሁለት ጣዎሶች ሳይም በሶስት ቢሆኖች ተረጎምኩላቸው፡፡ያን ሁሉ ካወጣው ካወርድኩ በኋላ ግን የጠቅላዩን ሐይማኖታዊ ኋላ መመርመር ፈለግኩ፡፡ ከሞስሊምና ክርሰቲያን ቤተሰብ የተገኙ ናቸው፡፡ እሳቸው ደግሞ ፐሮቴስታንት ክርስቲያን ይመስሉኛል፤ የፕሮትስታንት ሰብሳቢ ሆነው አይተናቸዋልና፡፡ ምናልባትም ነገ የፕሮትሰታንት እምነት የበላይ ጠባቂ ይሆናሉ፡፡ ንጉስ ሆይ እዚህ ላይ ግን ጥያቄ አለኝ? “የፊውዳል ኢትዮጵያ መሪ የነበሩት ቀዳማዊ ኀይለ ሥላሴ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን የበላይ ጠባቂ ቢሆኑ ምን የሚያስነቅፋቸው ነገር ነበር?”

እርሶ የተወለዱባትን ጅማ አውቀታለሁ፡፡ እኔ ጅማን የማያት እንደ ሜትሮ ፖሊታንት ከተማ ነው፡፡ ብዙ አይነት ቋንቋ የሚናገሩ ህዝቦች፤ ኩሉ፣ኦሮሞ፣አማራ፣ጉራጌ፣ትግሬ፣ከፋ፣አረቦች(የልጅ ልጆቻቸው)…ይኖሩባታል፡፡ እምነቶችም እነደዚሁ፡፡የደህረ ምርቃት ጥናትዎን በግጭት አፈታት ላይ እንደሰሩ አምብቤአለሁ፡፡

በእርግጥ ከ1990ዓ.ም. በኋላ በዚያ አካባቢ የነበረው ሐይማኖታዊ ድባብ ተቀይሯል፡፡ ብዙ የኦርቶዶክስና ፕሮትሰታንት ቤ/ክርሰቲያናት የዛሬ አስራ ሁለት አመት ገደማ ተቃጥለዋል፣ ካህናት ታርደዋል፡፡ ይህ የተፈጸመው በኢህአዲግ ተሿሚዎች ጭምር ነበር፡፡

እዚህ ላይ በ90ዎቹ መጀመርያ በጅማ አካባቢ የፈረሱ መስጊዶች ነበሩ፡፡ በጊዜው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ በድሩ አደም ስለዚህ ነገር በፓርላማ ሲናገሩ አሰታውሳለሁ፡፡ አልቃይዳ ጂማ፣ ጉማ ላይ ለዚያ ተጠቃሸ ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ፡፡ ከ2000 ዓ.ም. (እ.ኢ.አ.) የጅማ ኦሮሞዎችም በየመን ተራሮች ላይ ለእምነታቸው እሰከ ህልፈተ ህይወታቸው ሲዋደቁ አለም አይቶታል፡፡ መረጃውም በእጁ ይገኛል፡፡

ከዚህ በተለየ ሁኔታ ከናይጄርያ የመጡ ሼክ ዝርያ የሆኑ ሱፊ ሞስሊም በዚያ በመስኪዳቸው አጥር ላይ የአይሁድና ክርስቲያን ምልክቶችን አጥራቸው ላይ ሰቅለው ስለሚመጣው ደግ ንጉስ ይናገሩ የነበሩ ሼክ እንደነበሩ አስታውሳለሁ፡፡ ምንአልባት ሰውየው ማለቴም ሼኩ የሰሜን ምዕራብ አፍሪካ ተወላጅ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

በአሜሪካ የተከሰተው የ2008(እ.ኤ.አ) ኢኮኖሚካል ሪሲሽን ባያሰቆመው ኖሮ(እንደ አንዳንድ ተንታኞች) በኦሳማ ቢላደን ወንድም የሚመራው 400 ቢሊዮን ዶላር ያህል ዋጋ የነበረው፣ የቢላደን ፐሮጀክት የመንና ጀቡቲን በድልደይ አገናኝቶ መዳርሻውን ኢትዮጵያ ያደረገ ንድፍ ነበረው፡፡ ገንዘቡም በኤምሬቶቹ ሼኮች ፈንድ የሚደረግ ነበር፡፡

እርሶ በዚህን ግዜ ለታላቁ ማንነትዎ ዝግጅት ላይ ነበሩ፡፡ የድህረ ምረቃ ጥናትዎን ተገቢና ጥብስ የሚያደርገው ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መስራቱ ነው፡፡ ያ ደግሞ በውልደትና ማንነትዎ ያገኙት ነው፡፡ ከፃፏቸው መጽሐፍትም ሆነ ከሚናገሩት ነገር መረዳት የሚቻለው አሁን ላሉበት ቦታ ለረጂም ግዜ መዘጋጀትዎን ነው የምገነዘበው፡፡ ያ ማለት የኢትዮጵያን ባህሎችና ወጎች ላይ ሐይማኖትን ጨምሮ በበቂ ሁኔታ ፈትሸው ተዘጋጅተውበታል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ለኢትዮጵያ ሕዝቦች የውይይት መድረክ - ጆቢር ሔይኢ ከሁስተን ቴክሳስ

ከኒዮርክ መንትያ ሕንጻዎች የሽብር ጥቃት በኋላ ጀርመን ባህል መአከል ጎተ ኢንስቲተዩት በወሎ ክፍለ ሀገር ያለውን የሐይማኖት መቻቻልን ለአለም ራድየት ማድረግ ይቻላል በሚል መንፈስ፤ ክርሰቲያን ሞስሊም ዲያሎግ በሚል ሦስት ተከታታይ ፐሮግራሞችን አቅረቦ ነበር፡፡

ከ 1995 ዓ.ም.  ግማሽ አመት በኋላ በተካሄደው ሁለተኛው ፐሮግራም ላይ ስድት ከአውሮፓ የመጡ ፐሮፌስሮችና ይህንኑ የሚያክሉ ካከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የተጋበዙ ሙሁራን ነበሩ፡፡ ደ/ር ነጋሶ ጊዳዳና ዶ/ር ደጃዝማች ዘውዴ ገ/ ስላሴ የፕሮግራሙ ታዳሚዎች እንደነበሩ አስታውሳልሁ፡፡

የፕሮግራሙ ሁለተኛ ቀን ላይ ፕሮፌሰር ኤልሪክ ሃጋይ እስልምናና ልጅ እያሱ(Islam and Lij Eyasu) በሚል ርእስ ጥናታዊ ጽሑፍ አቅርቦ ነበር፡፡ ድንገት እራሳቸውን አዲስ አበባ ከሚገኘው ሰዐውዲ ኤምባሲ እንደመጡ በማስተዋወቅ የተናገሩት(አምባሳደሩ?) አይሁዳዊውን ፕሮፌሰር እያቋረጡ ስለ ፓልሰታይን ይናገሩ ጀመር፡፡ ፕሮፌሰሩ በአረብኛ እያነበቡ በእንግሊዘኛ ተርጉመው ያቀርቡ ነበር፡፡

ጎይተ ያን ፐሮግራም ያዘጋጀው በአዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙ ከተለያዩ ኤምባሲዎች ጋር በመተባበር ነበር፡፡ የኤምባሲው ሰው እንዲህ አይነት ፐሮግራም ሲዘጋጅ ለምን አልተነገረንም፣ መርዳት እንፈልጋለን ብለው አረፉት፡፡ ያን ግዜ ነበር በራሳችን ሀገር ባህል፣ ፖሊቲካና ወጎች ላይ ከእኛም ሌላ ያገባኛልና ድምጽ አለኝ የሚል አካል እንዳለ ፍንትው ብሎ የታየኝ፡፡

ይህን ካልኩ ዘንዳ አሁን ወደ ርእሰ ጉዳዬ ልመለስ፡፡ ሰሞኑን በቤተ መንግስት በር ላይ ተቀርጸው በቆሙት ሁለት ፒኮኮች(ጣዎሶች) ዙሪያ በመኀበራዊው ሚድያ ከፖለቲካና ሐይማኖት አንጻር ብዙ እየተባለ ይገኛል፡፡

ጣዎስ በጥንት ክርሰቲያኖች ዘንድ ስጋዋ አይበሰብስም ተብሎ ይታመን ስለነበር የዘላለማዊነት ተምሳሌት ነበረች፡፡ በሞስሊሙ አለም ስለ ጣኦስ የሚነገሩ ሁለት ቢህሎች አሉ፡፡ የመጀመሪያው፣ አላህ የፈጠረው ጣዎስ ለሰባ ሺህ አመት መቁጠሪያውን ይዞ ቢፀልይ ፈጣሪ መሰታዎት አምጥቶ ጣዎሱ መልኩን እንዲያ አደረገው፡፡ የእራሱን ውበት በማየት የተደሰተው ጣዎስ(ፒኮክ) አምስት ግዜ ያህል በፈጣሪ ፊት በመስገድ እራሱን ለፈጣሪ ማስገዛቱን ገለፀ፡፡ ዛሬ ሞስሊሞች በቀን አምስት ግዜ ለፈጣሪ የሚያደርሱት ፀሎት ከዚያ የመጣ ነው የሚሉ አሉ፡፡

ሁለተኛው ደግሞ በአስራአንደኛው ክፍለ ዘመን ላይ መነገር የጀመረው የጣዎስ ትርክት ነው፡፡ ጣዎስ(ፒኮክ) የገነት ወፍ ነበር፡፡ ሴይጣን ጣዎስ  ወደ ገነት እንዲገባ ከረዳው እንዳይታመም እንዳያረጅና እንዳይሞት ሶስት ቃላትን እነደሚያሰተምረው አማለለው፡፡ ጣኦስም እባብን በኋላም ሄዶ ሄዋንን  የፈተናትን እባብ ወደ ገነት እንዲገባ ረዳ፡፡ በዚህም ምክነያት ጣዎስ፣እባብና ሰየይጣን ሶስቱም ከገነት ተባረው ወጡ፡፡

ከሁለተኛው ትርክት ጋር ተመሳሳይነት ያለው ታሪክ በኦርቶዶክስ አዋልድ መጽሐፍ ላይ አንብቤአለሁ፡፡ ምንም እንኳን ጣዎስን በቀጥታ ባያነሳም፤ ሰይጣን በአካል ወደ ገነት መግበት ስላልቻል በእባብ ላይ አድሮ እነደገባና ሄዋንን እንዳሰተ ነው ታሪኩ የሚናገረው፡፡ እባብ በገነት ከሚገኙ እንስሳት ሁሉ ውብ ነበረች እግርም ነበራት ይላል፡፡ ይህን ተከትሎ ነው “እባብን የልቡን አይቶ እግር ነሳው” የሚለው አባባል የመጣው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ከ1986-2006 ዓ/ም (ሚሊዬን ዘ አማኑኤል) »

እኔ እኒህን ጣዎሶች በአካል ለማየት ባልታደልም በቨረቱአል ጉብኝቴ እንዳየኋቸው መንፈሳዊ ትረጉም ለመስጠት ነው አእምሮዬ የተጣደፈው፣ ለዚህም ምክነያት ነበረው፡፡ አራት ኪሎ ቤተ መንግስትን የታከኩ ሁለት ቤተ ክርስቲያናት እንዳሉ አውቃለሁ፡፡ ባህታ ማርያምና ግቢ ገብርኤል ናቸው፡፡

በንጉሱ ዘመን የቤተመንግስቱ አካል ነበሩ፡፡በደርግ ዘመን ለንግስ ወደ ቤተ ክርስቲያናቱ ስንሄድ ቀይ ቦኔት የለበሱ የቤተ መንግስት ጠባቂዎች፣ መሳሪያ ደግነው ምእመኑ ላይ እንዳፈጠጡ ነበር የንግስና ስነ ስርአቱ የሚፈጸመው፡፡

እነደሚታወቀው ቤተ መንግስቱን በዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ግዜ ወደ ሌላ ቦታ ለመውሰድ እቅድ እነደ ነበር አስታውሳለሁ፡፡ ወ/ሮ አዜብ መስፍን ውስጡን ለማሳደስና ለማሰዋብ ጀምረው ባለቤታቸው መለስ ዜናዊ እንደ አስቆማቸውም ተጽፎ አንብቤለሁ፡፡

በግዜያችን ያሉት ጠ/ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ በኖህ መርከብ (Noha’s Ark)  ቅርጽ የአንድነት ፓርኩን በአማረ ሁኔታ አሰርተዋል፡፡ ለዚህ ታላቅ ምስጋና ሊቸራቸው ይገባል፡፡ በዚህም በኢትዮጵያ ታሪክ ከዚህ በኋላ እስከ አለም ፍፃሜ ድረስ አሻራቸውን አስቀምጠዋል፡፡

ባሌ ሄደው ካደረጉት ንግግር የሚታወሰኝ ነገር አለ “እኛ ዝሆን ነን፡፡ የሰበሩንን ሰብረናል…” በደርግ ግዜ የሰማሁትን አንድ ቀልድ እዚህ ጋር እንሆ ልበላችሁ፡፡ አንድ ግዜ አንበሳ በአራዊት መንደር ሁሉ እየሄደ የአራዊት ንጉስ ማን ነው እያለ ይጠይቅ ጀመር፡፡ ሁሉሉም አንተ ነህ እያሉ ሲናገሩ ዝሆን ግን በኩምቢው አንስቶ አፈረጠው፡፡ ከዚያም አንበሳ “እኔ ነኝ ተላለህ እንጂ ምን ያመታሃለ?” አለ ይባላል፡፡

እኔ ይህችን አገር በቀል ያልሆነች ነገር ግን እጅግ ውብ ድንቅ የሆነች ወፍ ወደ ቤተመንግስቱ ስላስተዋወቋት አይከፋኝም፡፡ ጥያቄ ግን ለምን በዝሆን ቁመት ሆነች ነው? ያውም የቤተ መንግሰቱ በር ከፋች ሆና?

ጃፓኖች ቱሪ በር የሚሉት ከአለማዊው ወደ መንፈሳዊው  ህይወት የሚያሸጋግ በር አላቸው፡፡ ሁለቱ ጣዎሶች የቆሙበትን ስፍራ ሳይ ሁለቱ በታቦቱ ላይ የቆሙ ኪሩቦችን አስታውሳለሁ፡፡ እኔ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋዎ አንድ ጥያቄ አለኝ “እኒህ ሁለት በኢትዮጵያ የቆሟቸው ነገር ግን ሀገራዊ ያልሆኑ ጣዎሶች  የያዚድስም እምነት መገለጫ መላክ ታዎሶች ናቸው ወይስ…?”

ለነገሩ የብልጽግና ፓርቲ አርማ የፒኮክ የፊት ገጽታ በጥቁርና ጭራዋነ ደግሞ በነጭ ይመስል አይደልምን? ነገሩ አይኔ ነው አንተ ነህ? ሰውዬው እንዳለ፡፡ እርሶ ምን ይላሉ – ወይም ስለዚህ ነገር ይመለከተኛል የሚልል ሁሉ ምን ይላል? አበቃሁ፡፡

አስቻለው ከበደ አበበ

ሜትሮ ቫንኮቨር፣ ካናዳ

ምያዚያ 25፣ 2020

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.