በ24 ሰዓታት ለ1 ሺህ 80 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ 2 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው

94511285 10217312395023675 2921687284476542976 nበ24 ሰአታት ውስጥ ለ1 ሺህ 80 ሰዎች ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ መደረጉን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ገልፀዋል።

ሚኒስትሯ በተደረገው ምርመራም ተጨማሪ 2 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የገለፁ ሲሆን፥ ይህንን ተከትሎም በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 126 ደርሷል ብለዋል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሁለቱም ሰዎች የ42 ዓመት እና የ50 ዓመት እድሜ ያላቸው የብሪታኒያ ዜጎች ሲሆን፥ በቅርቡ ከብሪታንያ የመጡ እና በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ የቆዩ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 126 ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 71 ሰዎች በለይቶ ህክምና ላይ፤ 50 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ማገገማቸው ይታወቃል።

ኤፍ.ቢ.ሲ

ተጨማሪ ያንብቡ:  በኦሮሚያ ሰበታ አንድ የመድረክ አባል ተገደለ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.