“ስልጣኔን አለቅም፣በስራዬም አልቦዝንም ” ዶ/ር ቴዎድሮስ – ታምሩ ገዳ

93049508 1596076923878773 8621576870200082432 n ስልጣኔን አለቅም፣በስራዬም አልቦዝንም ዶ/ር ቴዎድሮስ   ታምሩ ገዳየአለም ጤና ድርጅት፣ (WHO )ዋና ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድህኖም ከድርጅታቸው ጋር ሰሞኑን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እስጣ ገባ ውስጥ የገባው እና ለተቋሙ የሚያደርገውን የገንዘብ እገዛ እንደሚያቋርጥ የገለጸው የአሜሪካ አስተዳደር ሀሳቡን እንደሚቀይር ፣ እርዳታውም የሚጠቅመው ሌሎች አገራትን ብቻ ሳይሆን አሜሪካንንም ጭምር ለመታደግ እንደሚውል ተስፋቸውን ገለጹ፣ከስልጣን ይለቁም እንደሆን ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጡ።

መቀመጫውን በጀኔቭ፣ ስዊዘርላንድ ያደረገው የአለማቀፉ የጤና ተቋም ኃላፊው ዶ/ር ቴዎድሮስ በወቅታዊው የኮሮና ፣ሳንባ ቆልፍ ወረርሽኝ ዙሪያ ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቆይታ ድርጅታቸው ወረርሽኙን በተመለከተ ደባብቋል፣ አፍቃሪ ቻይና የሆነ የተሳሳታ መረጃን አናፍሷል የሚለው ውንጀላን ተከትሎ አንዳንድ የአሜሪካ የሪፐብሊካን ፓርቲ የህዝብ እንደራሴዋች ባለፈው ሳምንት ” ፕ/ት ትራምፕ ለጤና ተቋሙ በዚህ አመት የገንዘብ ፈሰስ እንዲያደርጉ ከተፈለገ ዶ/ር ቴዎድሮስ በቅድሚያ ከሀላፊነት በፍቃደኝነት መውረድ አለባቸው”የሚለውን ጥሪን ከግንዛቤ ውስጥ በመክተት ከጋዜጠኞች ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።

ዶ/ር ቴዎድሮስ ሲመልሱ ” የተያያዝኩትን ስራ ቀንም፣ ማታም መስራቱን እገፋበታለሁ ። ምክንያቱም የተቀበልኩት ኃላፉነት የሰዎችን ህይወትን ማትረፍ እና በረከትነትም ስለ አለው ነው፣ትኩረቴም እዚያ ላይ ይሆናል”ብለዋል።ዶ/ር ቴዎድሮስ የሚመሩት ተቋም በወረርሽኙ ሳቢያ በተከተላቸው የተለያዩ ፖሊሲዎች የተነሳ “ዶ/ር ቴዎድሮስ ብቁ ባለመሆናቸው ስልጣን ባስቸኳይ ይልቀቁ የሚሉ እና ይህንን አቋም የሚቃወሙ” ሁለት ጎራዎች ሰሞኑን ተስተውለዋል ።

ይህ በዚህ እንዳለ የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚንስተር ማይክል ፖምፔዬ ባለፈው ሚያዚያ 22,2020 እኤአ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አገራቸው ለተለያዩ አገራት ለጸረ ኮሮና ዘመቻ የሚውል ወደ ሰባት ሚሊዮን ዶላር እንደምትስጥ የጠቆሙ ሲሆን አንዳንድ የህዝብ ኢንደራሲዎችም አሜሪካ ለአለም ጤና ተቋም የምትለግሰው ገንዘብ ለአገራቱ በተናጥል እንዲስጥ ሲሉ ጠይቀዋል።

በተያያዘ ዜና የኮሮና ወረርሺኝ መነሻ አገር የሆነችው እና በወረርሽኙ ሳቢይ ከፕ/ት ትራምፕ አስተዳደር ጋር በቅርቡ አተካሮ ውስጥ የገባችው ቻይና የአለማቀፉ የጤና ተቋም ወረርሽኙን ለመዋጋት በሚያደርገው ዘመቻ ይረዳ ዘንድ ዛሬ ሐሙስ ተጨማሪ የሰላሳ ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ እገዛ ማድረጓን በውጪ ጉዳይ ሚኒስተር በኩል አስታውቃለች። ቻይና ቀደም ሲል ባለፈው መጋቢት ወር ሀያ ሚሊዮን ዶላር መለገሷን ዜና አገልግሎት ሮይተርስ አውስቷል።

(ታምሩ ገዳ/ህብር ራዲዮ)

4 Comments

 1. ወይ ጣጣ ዉጪ ነብስ ግቢ ነብስ ሆነበት እኮ። ትግሬዎች ገፋፍተዉ ሎቢ አድርገዉ ቢልጌት እግር ላይ ወድቀዉ ተመረጠ ሰዉየዉ በቃለ ምልልሱ ጥያቄዉ አልገባ ብሎት ሌልኛዉ ተፈታኝ ሲያስተሩምለት አይተናል ከአሱ በስተቀር የህክምና ዶክተር ያልሆነ ሰዉ እዚህ ቦታ አልተቀመጠም እነሱ ግን የመሀይም ድፍረት ስለሚበዛባቸዉ ደብረዘይት ሳምንት ስልጠና ከወሰዱ በሗላ ሔሊኮፕተሩን ከየጋራዉ እያላጉ እንደጨረሱት ሁሉ እሱም አቅሙ የማይችለዉን ስራ ዘዉ ብሎ ገባ ገብቶ ሲያየዉ ለሱ ያለመመጠኑን አይቶ ሐይለ ማርያምን ፈንጎሎ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስተር ለመሆን ሃሳብ ነበር ግን ምን ይደረጋል የወደፊቱ በአምላክ እጂ በመሆኑ ነገር እንዳልነበረ ሁኖ ተገለባበጠ። ትራምፕ ካባረረዉ ያለዉ እድል ወደ መቀሌ ተጉዞ የደብረጽዮንን ቦታ መዉሰድ ነዉ። አሁንም የቅርብ ዘመድ ካለዉ ቶሎ ብሎ ቢለቅ የጡረታ ጠቀም ያለ ገንዘብ ያገኛል ለነገሩ ገንዘብ እሱ መች አጣ። ድሮ ቀለድከብን አሁነ ተራችን ነዉ።

 2. The guy called a taxi and asked him to take him to the casino(this is before COVID 19).HE GAMBLED and lost his money. After some time when he met the taxi driver he blamed him for his gambling.
  So does Mr.Trump and his state Secretary who are blaming WHO and Dr. Twedros this shows the real character of the US President who blames his weakness on WHO or on some one who comes from a shithole country.
  There is a time for the blame game now we have to focus on saving lives. It is time to support WHO and correct mistakes after COVID IS BEATEN.
  STAY SAFE, PRAY AND FOLLOW ALL THE ADVICE AND PRECAUTIONS FROM THE WHO.

  THANK YOU.

  MUCHFUN
  CANADA.

 3. መደዴው-ስግብግቤው፣

  የስልጣን ጥም እንዳለብህ ከመዘርጋትህ በፊት፣ ምን አለበት ሃላፊነቴንም ትቼ አልሸሽም እንኳን ብትል::

 4. The WHO under the leadership of the incompetent and corrupt TPLF executive committee member Dr. Teodros Adhanom will not be in a position to combat the current COVID-19 epidemic and the future ones. Combating the epidemic and applying pressure on him to resign and make way for a competent director general should go side by side. In the first place.his election was fishy. The culture of prevalent corruptiom in Africa has made it possible for Dr. Teodros Adhanom to get the job. Africa has competent candidates who have the medical profession.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.