የሻቢያ፣ ወያኔና ኦነግ የጦር አበጋዞች መርህ አልባ የፖለቲካ ግንኙነትና የመቶ ዓመት የቤት ሥራ!!! – ሚሊዮን ዘአማኑኤል

ET34የሻብያው አንባገነን መሪ ኢሳያስ አፈወርቂና የኤርትራ የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ጂ 15 በወህኒ ቤት 20 አመታት ሞላቸው!!!

‹‹በምን አወቅሽበት በመመላለሱ
ሲታሰር ወደ እኔ፣ ሲፈታ ወደ እሱ!!!››

የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥት መርህ አልባ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የመከላከያ ኃይል ግንኙነት በጊዜው መልክ ሊይዝ ይገባል እንላለን፡፡  የሻቢያ፣ ወያኔና ኦነግ  የጦር አበጋዞች መርህ አልባ የፖለቲካ ግንኙነትና የመቶ ዓመት ስውር የፖለቲካ ሴራ ቀጣይ ፍንጮች ይስተዋላሉ፡፡

 • በአንድ በኩል በቅኝ ገዥነት የፈረጁትና የኢትዮጵያን አንድነትና፣ ብሄራዊ ፍቅር ያስጠብቃል የሚሉትን የአማራ ህዝብ መምታትና ማስመታት የሻቢያ፣ ወያኔና ኦነግ የጦር አበጋዞች  የቆየ የጋራ የፖለቲካ አቆም ነው፡፡
 • በሌላ በኩል በሃገራችን ፋሽን የሆነውን በብሄርተኛነት መደራጀት መብት የተነፈገው የአማራ ብሄርተኛነት ተጠናክሮ ከቀጠለና የአማራ መደራጀትና መታጠቅ የሚያስፈራቸው የሻቢያ፣ ወያኔና ኦነግ  የጦር አበጋዞች በአማራ ክልል  የአስቸኮኳይ ጊዜ አዋጅ፣ ኮማንድ ፖስቱ ታንኮችና ከባድ መሣሪያ ይዞ መግባት ለኮሮናቫይረስ በሽታ ማስወገድ ነው ቢባልም ለአማራ ህዝብ የሚታገሉ መኢአድ፣ አብን፣ ፋኖ፣ ከግንቦት 7 ታጋይ አርበኞችና ምሁራንን ለማጥቃት በማሴር ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡ ወያኔ በትረ ሥልጣኑን ለኦህዴድ/ ኦዴድ ብልፅግና በማስረከብ በጋራ ባላቸው አቆም የአማራ ክልል ለማጥቃት የዘመተው መከላከያ ሠራዊት በአንድ በኩል በትግራይ በኩልና በሌላ በኩል በወለጋ በኩል አድርጎ መግባቱ አሁንም የአማራን ህዝብ ለመበቀል የጋራ የፀና አቆም እንዳላቸው ያመላክታል፡፡ ወያኔ ከአማራ ክልልና ከአፋር ክልል በጉልበት የነጠቀውን መሬት ይዞ ለመቀጠል የአማራ ህዝብ ደካማ መሆን ስላለበት የዶክተር አብይን ዘመቻ ወያኔም ይፈልገዋል፣ የአማራን ዘርፈ ብዙ ጥቃት ወያኔ ያስተባብራል ብሎም ያቀናጃል፡፡
 • ኢዜማ በዜግነት ፓርቲ፣ በህብረ-ብሄር ፓርቲ ስም እየታገልኩ ነው እያለ በአማራ ክልል ተወዳድሮ ለማሸነፍ ቆምጦል፣ የአማራ ህዝብ ከእኛ ዘንድ አትድረስ፣ ‹‹ አማራ የሚባል ብሄር የለም፣ አማርኛ መግባቢያ ቆንቆ እንጂ ዘር አይደለም!!›› ብላችኃል ይላሉ ፕሮፊሰር ብርሃኑ ነጋና አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የፖለቲካው ሴራ ሚስጢሩ  መኢአድ፣ አብን፣ ፋኖን፣ ባልደራስ መኢአድ ወዘተ ትጥቅ ለማስፈታትና ለማስገበር ነው፡፡ ኦነግ/ኦዴፓ ብልፅግና ኢዜማ በዚህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣በ5ወራት ውስጥ የሚሰሩት ተቃዎሚ ፓርቲዎችንና ጋዜጠኞችን  በመክሰስና በማሰር ያሳልፉታል፡፡
 • የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦነግ) ኦህዴድ/ ኦዴድ ብልፅግና የአዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተሞች የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ስር መካለል  እንዳለበት ሻብያና ወያኔ  ኦህዴድ/ ኦዴፓ/ ብልጽግና ኢዜማ  ገፀ በረከት ማቅረባቸው ቀጣይ የፖለቲካ ሴራ ነው ንቃ እንላለን፡፡ የንጉስ ሚንልክና የእቴጌ ጣይቱ የቆረቆሮት  አዲስ አበባ ከተማ፣ የአፄ ሚኒልክ ቤተመንግስት የተገነባበት፣ የእቴጌ ጣይቱ ሆቴል፣ ትምህርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎች፣ መንግስታዊ ተቆማቶች፣ መስሪያ ቤቶች ፣ ቤተክርስቲያን፣ መስጊድ፣ የእምነት ቦታዎች የተገነቡበት፣ የአፍሪካ ህብረት፣ የአውሮፓ ህብረት፣ ቦሌ አየር ማረፍያ፣ ኢንባሲዎችና ለጋሲኖች ወዘተ የተገነቡበትን የአንድ ብሄር ነው ማለት ገንቢዎቹም ትግስት እንጅ የሚቀሰቀሰው የማያባራ ጦርነት ሃገር ይጎዳል እንላለን፡፡
 • ሻብያ ኦነግ ትጥቁን ሳይፈታ በትግራይ በወያኔ በኩል በአቦይ ስብሃት ተባርኮ የገባውን ማስታወስ ብልህነት ነው እንላለን፡፡ የሻቢያ፣ ወያኔና ኦነግ  የጦር አበጋዞች ኢትዮጵያ የምትባለውን ሃገር  ከአስር ትንንሽ ወደ መቶ ትንንሽ ክልላዊ መንግስትነት በመከፋፈል በወሰንና ድንበር የማያባራ ጦርነትና ግጭት ከትቶ የእራሳቸውን ህልውና የማስጠበቅ የመቶ ዓመት ስውር የፖለቲካ ሴራን በመተግበር ላይ ይገኛሉ፡፡ ዘረኛ የጦር አበጋዞች ክልላዊ መንግስቶች እንደ አሸን በፈሉ ቁጥር የድንበርና የወሰን የጦርነት ግጭቶች  እንደ ሰደድ እሳት ይዛመታል ጦሱም  እንደ ሶሪያ፣ የመን፣ ሊቢያ ፣ አፍጋኒስታ፣ ኢራቅ  ህዝብ የጦር አውድማ፣  የማያባራ የውክልና ጦርነት መዛመቱን ማስታዋል ይገባል እንላለን፡፡  በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ተሰደው የመጡትን የሱማሌ፣የሶሪያና የየመን ዜጎችን እያየን ከእነሱ መማር  የጊዜው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው እንላለን፡፡ ሃገራችን ለሁላችንም ትበቃለች  ፍቅር ይስጠን እንላለን፡፡

የሻቢያ፣ ወያኔና ኦነግ  የጦር አበጋዞች በኤርትራም፣ በትግራይና፣ በኦሮሞ ስም አስሬ ቢምሉም ቢገዘቱም፣ የህዝቡ እጣ ፈንታ ሞት፣ እስራትና ስደት በቀር የተረፈው  ነገር የለም፡፡ የጦር አበጋዞቹና በስልጣን ሱስ በሰከሩ፣ አድርባይ ምሁራን በዴሞክራሲ ስም፣ በፌዴሮሽን ስም፣ በህገ-መንግሥት ስም በህዝብ ላይ ጥቃት ይፈፅማሉ፡፡ የሻቢያ፣ ወያኔና ኦነግ  የጦር አበጋዞች ከህዝብ በዘረፉት ኃብትና ንብረት ተንደላቀው ይኖራሉ፡፡ ወያኔ ዘርፎ ትግራይ ገብቶል፣ ኦነግም ዘርፎ ወለጋ መሽጎል፣ ኦህዴድ/ ኦዴፓ ብልጽግናም የመቶውን አመት ስውር የፖለቲካ ሴራ ለማስፈፀም ላይ ታች ይላል፡፡  የፖለቲካው ሴራ ሲተነተን እንኮን ለኢትዮጵያ ህዝብ ለክልላቸውም ህዝብ እንደማይበጁ እውነተኛ ማስረጃውን  እንሆ እንላለን፡-

ህዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ  (ህግሓት) ከኢትዮጵያ ቅኝ ግዛትነት ለመውጥት ሲታገል ቆይቶ በሜይ 24 ቀን 1993 እኤአ ነፃ ወጥቻለሁ ይላል፡፡ ሻቢያ  አንድ አውራ ፓርቲና ብቸኛ መንግሥት በመሆን ላለፉት 27 አመታት ሕገ መንግስትና ዴሞክራሲና ምርጫ  ገለመሌ የሚባል ዜና ፖለቲካና ሃተታ ሳይኖር በአንባገነንነት የገዛ የማፍያ ድርጅት ነው፡፡ የህግሓት መንግስት የስብዓዊ መብት ምህደር በዓለማችን ካሉት ነፃነት ደፍጣጮች የመጨረሻ ደረጃ ላይ  ይገኛል፡፡ የኤርትራ መንግሥት የመገናኛ ብዙሃንና ፕሬስ ነፃነት በዓለም አቀፍ የፕሬስ ነፃነት ማህደር በመጨረሻነት ከሰሜን ኮሪያን አፋኝነት ተርታ ተሰልፋለች፡፡ የኤርትራ መንግስት መርህ አልባ የዲፕሎማሲ ግንኙነቶች በማድረግ ከአፍሪካ ህብረት፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ ኢጋድ እንዲሁም በአረብ ሊግ በታዛቢነት አባል መሆን ችሎል፡፡ ኤርትራ 117,600 ኪሎሜትር ስኩየር የቆዳ ስፋት ሲኖራት የቀይ ባህር የባህር በር አላት፡፡ ኤርትራ ህብረ ብሄር ሀገር ስትሆን የህዝብ የቌንቌ ስብጥር ዘጠኝ ዘውጌ ቡድኖች ይገኛሉ ከነዚህ ውስጥ፣ ትግርኛ 55 በመቶ፣ ትግረ 30 በመቶ፣ ሳሆ 4 በመቶ፣ ኩናማ 2 በመቶ፣ ቢለን 2 በመቶ፣ ራሻይዳ 2 በመቶ እንዲሁም የተለያዩ 5 በመቶ ዘውጌ ብሄር ብሄረሰቦች ቢኖሩም በዘር መደራጀትና እራስን በራስ እስከመገንጠል መብት የሚባል ገለመሌ የለም፡፡ በ2016 እኤአ የሥነ-ህዝብ ብዛት ቆጠራ 4,954,645 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ሃገር ናት፡፡

ኢሳያስ አፈወርቂ ተቃዋሚ ፖለቲካ የነበሩትን ጂ 15 በመባል የሚታወቁትን የህሊና እስረኞች በአሰቃቂ ሁኔታ በማሰር በአለም ህብረተሰብ በአንባገነን ገዢነታቸው የሚታወቁ ሲሆን ዶክተር ብርሃኑ ነጋ፣ አንዳርጋቸው ፅጌ  የፖለቲካ ሴራ ጠንሳሽነትና ኦቦ አብይ አህመድ፣ አሽቃባጭነት ሊወድቅ ተንገዳግዶ የነበረው የኢሳያስ ፋሽስታዊ አገዛዝ እንደ እባብ አፈር ልሶ ዳግም ተነሳ፡፡

የጂ 15 የፖለቲካ እስረኞች The “G-15” Prisoners የኤርትራ አስራአንድ ከፍተኛ ሹማምንቶችና አስር ነፃ ጋዜጠኞች ከታሰሩ 20 አመታት አለፋቸው፡፡

These are the 11 government/party critics who were arrested and are believed to have been held in solitary confinement since September 2001. Five of them (designated by asterisks) are presumed dead based on credible reports discussed later in this report:1   

 • መሃሙድ አህመድ ሸሪፎ (በህይወት የሌለ) *Mahmoud Ahmed Sherifo (born 1947), former foreign minister and former minister of local government; also former chairman of the committee drafting Eritrea’s proposed electoral law;
 • ሃይሌ ወልደትንሳይ Haile Woldetensae (born 1947), former foreign minister and former minister of trade and industry;
 • ጴጥሮስ ሰሎሞን Petros Solomon (born 1948), former minister of defense; former minister of maritime resources; former Eritrean People’s Liberation Front (EPLF) chief of intelligence;[1]
 • በራካይ ገብረስላሴ Berakai Ghebreselassie (born 1946), former minister of information; former minister of education; ambassador to Germany;
 • ብ/ጀ እስጢፋኖስ ስዩም Brigadier General Estifanos Seyoum (born 1947), former director-general of inland-revenue;
 • ሜ/ጀ ብርሃኔ ገረግዜር Major General Berhane Gerezgiher (born 1947), former commander of the armed forces; former head of the national reserve force;
 • ሜ/ጀ እቁባይ አብርሃ (በህይወት የሌለ) *Major General Ogbe Abraha (born 1948), former chief of staff of the armed forces; former minister of trade and industry; former minister of labor and social welfare;
 • ሳለህ ኢድሪስ ከክያ Saleh Idris Kekya (born 1950), former minister of transport and communication; former director of the president’s office;
 • አስቴር ፍስሃፂዮን (በህይወት የሌለ) *Aster Fezhazion (or Fesshatsion) (born 1951), Mahmoud Sherifo’s wife, the only woman arrested on September 18-19, former regional head of personnel;
 • ሃሚድ ሂሚድሃመድ (በህይወት የሌለ) *Hamed Himid Hamad (born 1955), former director of Arabic section of the ministry of foreign affairs; former member of the People’s Front for Democracy and Justice executive council;
 • ግርማኖ ናቲ (በህይወት የሌለ) *Germano Nati (born 1946), former regional director of social affairs.

“The 20 men and one woman arrested in September 2001—11 high government officials and 10 independent journalists—have never been seen again. They have collectively come to be known as the G-15 because the original group of signatories to a manifesto critical of the government numbered 15. The government has provided no information about their whereabouts or conditions in the decade since their arrests. What is known about them has been garnered largely from information supplied by defectors who have fled the country. Kept hidden in a secret detention facility, 10 of the 21 have died in prison according to reports that Human Rights Watch has not been able to independently confirm. The others remain in solitary confinement, physically or mentally incapacitated, and emaciated. None of the 21 has been formally charged with a crime, much less convicted. Since the arrest of the journalists and closure of their newspapers, no independent news media have been allowed in Eritrea.”2

የኤርትራም ህዝባዊ ትግል በሻቢያ መርህ አልባ የአፍሪካ ቀንድ የበላይ የመሆን የፖለቲካ ሴራ የተነሳ ከጎረቤት አገራቶች ጋር ሁሉ ጠብያለሽ በዳቦ ሆነ፡፡ ሻብያ ከየመን በሃኒሽ ደሴት፣ ከጅቡቲ፣ ከኢትዮጵያ፣ ከሱዳን ወዘተ ጋር አንባጎሮ ገጠመ፣ በዚህም የተነሳ ከዓለም አቀፍ ማህበራት ጋር የዲፕሎማሲ ግንኙነቶቹ ተበጣጠሱ፡፡ የሻብያው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ የአፍሪካ ሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጁንግ ኡንንነት ተፈረጁ፡፡ በመለስ ዜናዊ ዘመን ኤርትራ በአሜሪካና የተባበሩት መንግሥታት የኢኮኖሚና የጦር መሳሪያ ግዝ ማዕቀብ ተጣለባት፡፡ ኢትዮጵያና ኤርትራ ከጦርነቱ በኃላ ኢኮኖሚያው ቀነጨረ፣ የመከላከያ ሠራዊታቸው አከርካሪው ተመታ፣ የስብዓዊ መብትና ጥሰትና የዴሞክራሲ አፈና ተስፋፋ፣ ሞት፣ እስራትና ግርፈት መጨቆኛ መሳሪያቸው ሆነ፡፡  ህዝባቸውም ተስፋ በመቁረጥ ወደ ጎረቤት ሃገሮች ላለፈው ሁለት አስርታት ተሰደደ፡፡ የወጣቱ መፈክር ‹‹ለመኖር ሂድ/ተሰደድ!!›› ሲሆን በአንፃሩ የድንበር ጠባቂው ወታደር ‹‹ተኩስ ለመግደል!!›› ይላል፡፡ በ2011 እአኤአ 222,000 የኤርትራ ስደተኞች ከህዝቡ ቁጥር 5 በመቶ የተሰደደ ሲሆን በየወሩ 3000 ሽህ ወጣቶች ድንበር አቆርጠው ይሰደዳሉ፡፡ ኢሳያስ አፈወርቂ ኤርትራን ከኢትዮጵያ ገንጥሎ ለህዝቡ ያበረከተው ገፀ በረከት ይሄ ሲሆን ከዚህ የማይማሩ የእኛ ዘረኛ የጦር አበጋዞች ህወሓት ትግራይን ገንጥሎ ህዝቡን በምድር ሲኦል እንደሚከቱት ይታወቃል፣ ኦነግ ኦሮሚያን ገንጥሎ ህዝቡን በምድር ሲኦል እንደሚከቱት ይታወቃል፡፡ “Despite the mortal danger of trying to escape the country, Eritrea’s most significant export over the past decade has been its fleeing citizens. Eritrea’s youths have adopted a secret motto: “Leave to live!” Despite border guards’ shoot-to-kill orders, the exodus persists. Over 222,000 Eritreans (almost five percent of the population) had fled the country as of January 2011, with about 3,000 fleeing per month.”

የኢትዮጵያና የኤርትራ ተቃዋሚ ኃይሎች አንድም ቀን ከኢትዮጵያ ወይም ኤርትራ ህዝባዊ ትግል ጎን ቆሞው መለስ ዜናዊን ወይም ኢሳያስ አፈወርቂን ሲቃወሙ ተሰምተው አይታወቅም፡፡ የኢሳያስን ፋሽስታዊ አገዛዝ ዲሞክራቶቹ ብርሃኑ ነጋና አንዳርጋቸው ጽጌ እያወደሱ ወያኔን ‹‹ነጻነትን የማያውቁ ነፃ አውጭዎች›› እያሉ ሻብያን ያለማለት ማፍያዊ መርህ አልባ አቆም ነው እንላለን፡፡ የኤርትራ የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ጂ15ቶች  ላይ የሚደርሰው የስብዓዊ መብቶች ጥሰት፣ የዴሞክራሲያዊ መብቶች አፈና፣ የግፍ እስራት ዓለም ሲያወግዘው እናንተ የኢሳያስ ቡችሎች ግንቦት ሰባት፣ ኦነግ፣ ደህሚት፣ ወዘተዎች አሳፋሪ አቆም በታሪክ ያስጠይቃል፡፡ ኤርትራ በርሃ እያላችሁ ‹‹ ባትዋጋ እንኮን በል እንገፍ እንገፍ፣ የአባትህ ጋሻ ትሆኑ ይርገፍ!!!›› ተብሎ ተዘፍኖላችሁ ነበር፡፡ ለኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ቀን ሳትደርሱለት፣ እንደ ሳይላክ የቀረው ደብዳቤ ‹‹ሳይዘምት የተመለሰው ነፃ አውጭ›› ብሎ ግንቦት 7 ይጻፍላችሁ ይሆናል፡፡ የኢትዮጵያና የኤርትራ ተቃዋሚ ኃይሎች የጋራ ህብረት ፈጥረው ለነጻነት፣ ለዴሞክራሲና እኩልነት ቢታገሉ ኖሮ የሻብያና የወያኔ አንባገነን መሪዎች አገዛዝ በአጭር ይቀጭ ነበር  እንላለን፡፡

 • ኢትዮጵያና ኤርትራ በድንበሮች ባድማ፣ ፆረና፣ ኢሮፕ ወስን ግጭት የተነሳ የኢትዮጵያ ህወሓት መለስ ዜናዊና የህግሓት ኢሳያስ አፈወርቂ  ከ1998 እስከ 2000 እኤአ ጦርነት ገጠሙ፣  ከ70 እስከ 100 ሽህ ወታደሮች በጦርነቱ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡   በሃገራቱ የኢኮኖሚ ዘርፎችም በብዙ ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሃብትና ንብረት በጦርነቱ ወድሞል፡፡ ዶክተር አብይ አህመድ የኢትዮጵያና ኤርትራ ይግባኝ የሌለው ፍርድ የሄጉን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያደርጉት ጥረት ሁሉን አሳታፊና ግልፅ መሆን ይኖርበታል፡፡
 • የኢትዮጵያና የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በመርህ ላይ የተመሠረተ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ተፎካካሪ ፓርቲዎች መክረውበት፣ ምሁራን አጥንተውት በፓርላማ መጽደቅ ይኖርበታል እንላለን፡፡ ዶክተር አብይ አህመድ ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ያደረጉት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ ጉዳይና የመከላከያ ግንኙነቶች በመርህ ላይ የተመሠረተ ግንኙነት ለህዝብ ይፋ መሆን አለባቸው እንላለን፡፡ በሁለቱ ሃገራት መኃል ያለውም የድንበር ግጭት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በአግባቡ መፈታት ይኖርበታል እንላለን፡፡
 • የኤርትራ ህዝብ በተለይም ወጣቶች ብሄራዊ የውትድርና አገልግሎት ስልጠና እንዲወስዱ በማስገደድ ወጣቶች ጊዜቸውን ከትምህርት ይልቅ የጦርነት አባዜ አውዳሚ ኢኮኖሚ ያስከተለው ወጣቶችን ለሞት፣ እስራትና ስደት ተዳርገዋል፡፡ የኤርትራ ወጣቶች በገዛ ሃገራቸው መኖር ተስኖቸው ድንበር አቆርጠው፣ በርሃ አቆርጠው፣ ውቅያኖስ ሰንጥቀው፣ በህይወትና ሞት ትግል ያለቀው አልቆ በህይወት የተረፉት በስደት ለመኖር ተገደዋል፡፡ ለዚህም ተጠያቂው የእድሜ ልክ ፕሬዜዳንቱ የሻቢያው ኢሳያስ አፈወርቂ ለነፃነት፣ ለዴሞክራሲና እኩልነት የታገሉበት የትግል ውጤቱ ባርነት፣ ሞት፣ እስራትና ስደት መሆኑን የኤርትራ ህዝብ ምስክር ነው፡፡ ይሄንን ፋሽስት መሪ ነው ‹‹ኢሱ!!!…ኢሱ!!!›› እያለ የሚያቆላምፀው ኦቦ አብይ አህመድ ‹‹ስኮርት!›› አንባገነኑ ኢሳያስ አፈወርቂ በገነባው 300 እስር ቤቶች፣ የመሬት በታች የጉድጎድ ወህኒ ቤቶች፣ የኮንቴይነር እስር ቤቶች ውስጥ ዜጎቹን በማጎር እስረኞቹ ላይ ኢሰብአዊ ድርጊቶች በመፈፀም  ምግብ ፣ ውኃና የህክምና አገልግሎት በመንፈግ የፖለቲካ ተቃዋሚዎቹንና የኃይማኖት እምነት ተከታዬችን በማሰቃየት ይታወቃል፡፡ Since 2002 the 18-month national service requirement for Eritreans over the age of 18 has been extended indefinitely. …. Thousands of political prisoners and others who violated the terms of their national service by deserting or attempting to desert languish indefinitely in overcrowded detention centers, including underground cells and shipping containers, exposed to broiling sun during the day and freezing temperatures at night, with inadequate food, water, and medical care. Torture of prisoners is routine and deaths frequent. Most prisoners are denied contact with family, lawyers, humanitarian organizations, or other outsiders throughout their captivity. Among the thousands of prisoners held in Eritrea’s over 300 detention centers are adherents of religious groups that the government refuses to recognize as legitimate: Jehovah’s Witnesses, evangelical Christian groups, and reformist elements of the Ethiopian Orthodox Church. Adherents of “unrecognized” religions are arrested and tortured until they renounce their faiths, if then; many who do not recant die in custody.”2
 • የኤርትራው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሠራዊትን አሰልጥነውና አስታጥቀው አንድ ቀን እርማቸውን በ27 ዓመታት ውስጥ ሃገር ገብተው ከወያኔ/ ኢህአዴግ ጋር ሳይዋጉ ኦነግን በቆረጣ ወለጋ አስገብተው ‹‹ኦነግ ሸኔ›› የህዝብ ልጆች እየገደሉ፣ እያፈኑ፣ እያሰሩ፣ ባንኮች እየዘረፉ እንዲኖሩ ያደረጋቸው ስውር እጅ የሻቢያና ወያኔ የፖለቲካ ሴራ ነው፡፡ በትግራይ ክልል ደህሚት ከወያኔ ጦር ጋር ተቀላቅሎ እንዲሰራ ተደረገ፡፡ በአማራ ክልል የግንቦት ሰባት ሠራዊት በብአዲን ሠራዊትነት እንዲመለመልና እንዲሰራ ግን አልተፈቀደለትም፡፡ የአማራውን ክልል መጠናከር ኢሳያስ ሻብያውም፣ ደብረፂዮን ወያኔውም እንዲሁም አብይ ኦነጉም አይፈልጉትም፡፡ ኢዜማዎቹም ብርሃኑ/አንዳርጋቸው!!!

በኢኮኖሚ ዘርፎች ሻብያ ከኢትዮጵያ ህዝብ ዘርፎ ያስቀረው ኃብትና ንብረት ለናሙና፡-

 • የቀ.ኃ.ሥና የደርግ መንግሥት ዘመን የነበረው የኢትዮጵያ ባህር ኃይል መርከቦችና የጦር ተዋጊ ጀልባዎች ወዘተ ህወሓት/ ኢህአዴግ የት እንደሸጣቸው መጠየቁ ቀረና ያለ ባህር ባህር ኃይል ይሉናል የድንጋይ ዳቦ ዘመን ፖለቲከኞች፡፡ የኢትዮጵያ የባህር ሀይል (ከ1955 እስከ 1990) ድረስ ነበረ፡፡ ኢምፔሪያል ኢትዮጵያን ኔቪ 81 መርከቦች ነበሩት እነሱም ፓትሮል ቦትስ፣ ቶርፒዶ ቦትስ፣ አነስተኛ ስብመርሲብል (ባህር ሰርጎጂ) ቦትስ፣ ተዋጊ መርከቦች በምፅዋ ወደብ ነበራት፡፡  በወርቃማው ዘመን ቀ.ኃ.ሥ ኮማንደር ኢን ቺፍ የነበሩ ሲሆን፣ ሪል አድሚራል እስክንድር ደስታ ምክትል ኮማንደር ኢን ቺፍ ነበሩ፡፡ የኢትዮጵያ የባህር ኃይል የታጠቀው የጦር መሣሪያ ዓይነትና ተዋጊ የጦር መርከቦች ዲስትሮየር፣ ኬረር፣ ሜትሮ ሃይል ወይም ቀላል ሃይል ወይም አጃቢ ሃይል ከአፍሪካ ሃገራት ዘመናይ እንደነበር በታሪክ ይታወቃል፡፡ የመርከቦቹ እጣ ፈንታ በመለስ ዜናዊ የፖለቲካ ሴራ  በሻብያ ኢሳያስ አፈወርቂ ተዘረፈ፡፡
 • አሰብ የነዳጅ ድፍድፍ ማጣሪያ ጣቢያ በቀ.ኃ.ሥና የደርግ መንግሥት ዘመን ተገንብተው የነበሩት በሻብያው ኢሳያስ ተዘርፎል፡፡
 • ፋብሪካዎች፣እርሻዎችና ሆቴሎች፤- በቀ.ኃ.ሥና በደርግ መንግሥት ዘመን የተገነቡ በኤርትራ ይገኙ የነበሩ መንግሥታዊ ፋብሪካዎች በሙሉ በሻብያ መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ ኃብት ሆኖል፡፡
 • ባንኮችና ኢንሹራንሶች በኢሳያስ አፈወርቂ ሃብትና ንብረት መሆናቸው አንሶ፣ በመለስ ዜናዊ ትእዛዝ በብድር የተሰጠ አንድ ቢሊዮን ብር ሳይመለስ ቀርቶል፡፡
 • በኤርትራና ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት በምፅዋ ወደብ ከውጭ የገቡ በብዙ ቢሊዮን ዶላር የወጣባቸው የመንግስትና የግል ባለኃብቶች ንብረትና ኃብት ሁሉ ውኃ በልቶታል፡፡  በተመሳሳይ በወያኔ በግፍ የተዘረፉ የኤርትራዊያን ንብረትና ኃብት የነበሩ ህንጻዎች፣ ቤቶች፣ ፍብሪካዎች፣ መኪኖች፣ ወዘተ የዉኃ ሽታ ሆኖል፡፡

የኤርትራ ህዝብና የኤርትራ የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ጂ 15 ጥያቄዎች አንኮሮቹ ውስጥ፤-በኤርትራ  የስብዓዊ መብቶችና የዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ፣ በኤርትራ  የፕሬስ ነፃነት  እንዲከበር፣ በኤርትራ  ህገመንግስት አረቆ እንዲፀድቅ፣ በኤርትራ  ህዝባዊ ምርጫ እንዲካሄድ ይጠይቃሉ፡፡ መንግሥት ይሄዳል ይመጣል፡፡ የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዘብ ለዝንተ ዓለም አብረው የኖሩ ናቸውና፡፡

 

ምንጭ (መታየት ያለባቸው ዩቲዩብ ቪዲዬዎች )

1- https://www.hrw.org/report/2011/09/22/ten-long-years/briefing-eritreas-missing-political-prisoners

2-https://www.youtube.com/watch?v=Dujr-s9uQPE / Eritrea: Political Prisoners

3-https://www.youtube.com/watch?v=h61Zfm5uyb0 /Nevsun in Eritrea : Dealing With a Dictator – the fifth estate

8 Comments

 1. ሁሉንም የተዘረዘሩትን “contradictions – Widersprüche” ጥልቅትና ስፋት አውቃቸው ነበር:: አንድ ብቻ ግልፅ ሳይሆንልኝ የሰነበተ ጉዳይ፣ በዚህ ፅሑፍ አማካይነት በግልፅነቱ ተገነዘብኩኝ::

  በሻዕቢያዊው ኢሳያስ እና ወዘአምሃራዎች መሃከል ያለው ወዳጅነት እና ጠብ ሰምና ወርቅነቱ፣ በተለይም ኣይተ ኢሳያስ ጎንደር ሄዶ እንደ “በቅድመ አያቴ አክስታቸው በኩል እኔም ጎደሬ (አማራ) ነኝ” ካለበት ጊዜ ጀምሮ፣ የሻዕቢያን ዘፈን ዘማሪ “አማራ” በዝቶብኝ ነበር፣ ይሄ ፅሑፍ ግን ያው ኢሳያስን in the name of AMHARAS ወደ ጥንቱ ቦታው፣ in eyes of “AMHARAS” “ድልድይ ሰባሪነቱ” መልሶታልና ከእንግዲህ ወዲህ እኔም “ከአማሮች” የሻዕቢያ መዝሙር ዘፋኞች መደንቆር ሰላም አገኘሁኝ ማለት ነው::

  በአንድ በኩል እፎይ የሚያሰኝ እፎይታ ሲሆን፣ በሌላ በኩሉ ግን ያው ነገር ሁሉ፣ ከምብሓድሽ እንዲለው ትግርኛው፣ ከጥንቱ ደግሞ ተመልሶ ሊጀመር ነው ማለት ነው፣ አየ የአበሻ ነገር ሁሉ፣ አማርኛ እንዳበጁሽ ….. እንዲሉት..!

  • Aite Isaias has not used the Amharas as his cannon fodder during his armed struggle for independence. He used thousands of the Tigraians as his cannon fodder. He was able to mobilize and use tens of thousands Tigraians as his foot soldiers which has left a lasting scar on the psychology of the Tigraians. A feeling of inferiority complex and hate. That is what your comments show here. Even your late Tigraian ethic chief aite Meles proudly and confidenty said that listening to aite Isaias is more educative than attending the Addis Ababa University.

   • ኢሳያስን በመጀመርያ የሃይለስላሴ መንግስት ጀብሃን ለማጥፋት እንደ ሰላይ አድርጎ በሱዳን በኩል ወደ ባርካ ላከው:: ግን ከጀብሃ መጥፋት በፊት የሃይለስላሴ መንግስት ራሱው ጠፋ:: ከዚያም ከነበረው የ’east-west cold war ተነስቶ የሆኑ ሃይሎች ለጥቅማቸው ሲሉ ኢሱን ሊይዙት ፈለጉ:: ግን ይሄኛው ታክቲክ ደግሞ በስነ ስርአቱ አልተከናወነም:: ስለሆነም ደርግ ሻዕቢያን ሊያጠፋ ሊሳካለት ስለተቃረበ፣ ሻዕቢያ ናቅፋ ተራራዎች ውስጥ ተቀብሮ ወያነን አድነኝ ሲል ተማለደ፣ በኣረጋዊ በርሀ አዛዥነት መአት የትግራይ ልጅ ናቅፋ ሄዶና ከደርግ ጋራ ተዋድቆ የሻዕቢያን ነብስ አዳነ:: ትንሽ ቆየት ተብሎም በኣረጋዊ በርሀ እና በሓየሎም ኣርአያ መሪነት ጀብሃ ከኣምባሶይራ ተራራ ሁሉ ሳይቀር ተመንጥራ ወደ ከሰላ ምድረ ሱዳን ተገፍትራ ተበተነች ጠፋችም:: ከዚያን በኋላ ግን እነ ኣረጋዊ በርሀ ከትግል ሜዳው ስለተበተኑ፣ የኢሳያስን እጣ ወሳኞች እነ መለስ ሆኑና፣ ደርግ ሲወድቅ ኢሳያስ ኢትዮጵያ ውስጥ ቦታ እንደማይኖረው በድብቅም ሆነ በግልፅ አስታወቁት፣ ስለሆነም ኢሳያስ ከደርግ ጋራ በፈደረሽንና ብምንትሴ ሊግባባ ፈለገ:: ይሄን የተገነዘቡት እነ መለስ በከመ ቅፅበትና በጥቂት ቀናት በነ ሓየሎም አቀላጣፊነት ጎንደር ጎጃም ወሎን ረግጠው አምቦ ይደርሱና ለኢሳያስ ከደርግ ጋራ ድርድሩ እንደማይጠቅመውና ይልቁንስ ደርግ ሊወድቅ ስለሆነ ከወያነ ጋራ አብሮ ወደ ኢትዮጵያ ቢጎተት እንደሚሻለው ግልፅ አደረጉለት፣ ምርጫ ያጣው ኢሳያስም አብሮ ወደ አዲስ ተጎተተ፣ በዚህን ጊዜ በቅርቡ ስብሓት ነጋም እንደነገረን፣ ነፃነት የሚባለውን እንደማይፈልግና ግን የኢትዮጵያ ፕረዝደንት መሆን እንደሚፈልግ ድምፁን አሰማ፣ እነ መለስ ግን ለነፃነት የሚል ነገር አሰምተህ ስለነበረ፣ ነፃ ትወጣለህ ብለውት በእንዲህ ነገሮች እንደተንጠለጠሉ፣ የሎንዶን ስብሰባ ይከሰታል፣ ኢሳያስን ከአጥር ውጭ ትቶ ኢትዮጵያን ለብቻው ለመዝረፍ የተለመው መለስ፣ ጭራሽ ሎንዶን ስብሰባ ላይ አሰብ ለኢትዮጵያ የሚል ሃሳብ ሲፈልቅ፣ ፈጠን ብሎ፣ የለም የኤርትራ ነው በማለት፣ ኢትዮጵያን ባህር የለሽ አስደረገና ኢሳያስን ከነጠቅላላ ኮተቱ ከአጥር ውጭ አስቀመጠው፣ ግን የደርግ ወታደር ገና ደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢና ወደ ከንያም ስለነበሩና በሁለት በኩል ጦር እንዳይከፈትበት ያሰበበት መለስ፣ ኢሳያስን ኢትዮጵያ ውስጥ የቡና ኤክስፖርተር አደረገውና ኤርትራም ለሁለት አመታት ያህል ከተቀዳሚዎች የቡና አምራቾች ሃገሮች አንዷ ሆነች፣ የደርግ ወታደር ከጠቅላላው ደቡብ ወጥቶና ከከንያም ጭምር ወደ DC መሻገሩን ካረጋገጠ በኋላ፣ መለስ ኢሳያስን ወደ ኤርትራ አባረረው፣ ከዚያም መለስ ኢትዮጵያን እንዳሻው ገበያ ላይ አወጣት፣ ግን እርሱንም ሃያላት በሂይወቱ ስለመጡበትና ከዚያን በኋላ ኣይተ ስብሓት ነጋ ስላልቸለበት እነ ኣይተ አቤት ወዴቶችን ተንደፋዳፊዎችን መላላክ ጀመረ፣ ነገሩ ሁሉም ድንግርግር ገባበትና ጃፓኖ አሜሪካኖም ጫዋታቸውን ተጫወቱ፣
    ከዚህን ጊዜ ጀምሮ የጥንቱ ዋናው የመለስ አቀባባይ “ውጭ ጉዳይ ሚኒስተር” ስዩም መስፍን ወደ ደላላነት ወርዶ የት እንደሚውልና እንደሚያድር አናውቅም፣ አሁን ግን በሰሞኑ የካርቱም ተዝናኝና የኢትዮጵያን ምድር አሻሻጭ ደላላ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ እንደ ኤርትራዊ ዘ-ዓዲ ቐይሕ በውስጠ ልብ ሆኖ፣ አዲስ ዘፈን ውስጥ ውስጡን በትኗል፣ ዘፈኑም በተለይም ምኒልክንና ተከታዮቹን ይመለከታል፣ እንዲህም ይላል፣ በትግርኛም ነው:

    “ከምቲ ዝሸጥኩምናስያ ሸጥናኩም እንዶ
    ሕንኡያ ዘይፈዲስ ኣይ ወዲ ኣቡኡን እንዶ” ይላል፣

    በዚህ ሁሉ ተግባራት ታድያ በተለይም የደርግ ካድሬዎችና የምኒልክ ልጆች ዘንዳ እንዲሁም ምናልባትም በጠቅላላው ዓለም የተበተኑት ጀብሃ ወሻዕቢያ ወታደር ነበርኩኞች ዘንዳ እንጂ፣ እኔ ዘንዳ የበታችነት ስሜቱን ምን ሊያመጣው ይችላል ክብር የለሹ ሓሳዱማየየኒ…………!!?? ለበለጠ ማብራርያ፣ wo ever you are. ድምፅህን እንደገና አሰማ

   • You stroke the nail on the head. The Eritrean president and his EPLF were instrumental in creating the TPLF and leading it to seize power in Ethiopia. He clearly said in his interview a couple of years ago that he brought the TPLF to power and would bring it down this time. The fact that the Eritrean president has used tens of theousands of the Tigray poor as his cannon fodder is not forgetable despite the futile propaganda and distortion of facts by the digital weyannes like ዘረ-ያዕቖብ and Semere. The mistake the Amharas have made is their participation in the war between p the EPLF and TPLF in 1998-2000. The Amharas and other non-Tigay Ethiopians saved the TPLF from the devouring mouths of the TPLF. Despite this good gesture and taking side in the EPLF-TPLF wars by the Amharas, the TPLF thugs have not cleansed themselves of theeir racism and deep seated hatred towards the the Amharas.

   • ኢሳያስን በመጀመርያ የሃይለስላሴ መንግስት ጀብሃን ለማጥፋት እንደ ሰላይ አድርጎ በሱዳን በኩል ወደ ባርካ ላከው:: ግን ከጀብሃ መጥፋት በፊት የሃይለስላሴ መንግስት ራሱው ጠፋ:: ከዚያም ከነበረው የ’east-west cold war ተነስቶ የሆኑ ሃይሎች ለጥቅማቸው ሲሉ ኢሱን ሊይዙት ፈለጉ:: ግን ይሄኛው ታክቲክ ደግሞ በስነ ስርአቱ አልተከናወነም:: ስለሆነም ደርግ ሻዕቢያን ሊያጠፋ ሊሳካለት ስለተቃረበ፣ ሻዕቢያ ናቅፋ ተራራዎች ውስጥ ተቀብሮ ወያነን አድነኝ ሲል ተማለደ፣ በኣረጋዊ በርሀ አዛዥነት መአት የትግራይ ልጅ ናቅፋ ሄዶና ከደርግ ጋራ ተዋድቆ የሻዕቢያን ነብስ አዳነ:: ትንሽ ቆየት ተብሎም በኣረጋዊ በርሀ እና በሓየሎም ኣርአያ መሪነት ጀብሃ ከኣምባሶይራ ተራራ ሁሉ ሳይቀር ተመንጥራ ወደ ከሰላ ምድረ ሱዳን ተገፍትራ ተበተነች ጠፋችም:: ከዚያን በኋላ ግን እነ ኣረጋዊ በርሀ ከትግል ሜዳው ስለተበተኑ፣ የኢሳያስን እጣ ወሳኞች እነ መለስ ሆኑና፣ ደርግ ሲወድቅ ኢሳያስ ኢትዮጵያ ውስጥ ቦታ እንደማይኖረው በድብቅም ሆነ በግልፅ አስታወቁት፣ ስለሆነም ኢሳያስ ከደርግ ጋራ በፈደረሽንና ብምንትሴ ሊግባባ ፈለገ:: ይሄን የተገነዘቡት እነ መለስ በከመ ቅፅበትና በጥቂት ቀናት በነ ሓየሎም አቀላጣፊነት ጎንደር ጎጃም ወሎን ረግጠው አምቦ ይደርሱና ለኢሳያስ ከደርግ ጋራ ድርድሩ እንደማይጠቅመውና ይልቁንስ ደርግ ሊወድቅ ስለሆነ ከወያነ ጋራ አብሮ ወደ ኢትዮጵያ ቢጎተት እንደሚሻለው ግልፅ አደረጉለት፣ ምርጫ ያጣው ኢሳያስም አብሮ ወደ አዲስ ተጎተተ፣ በዚህን ጊዜ በቅርቡ ስብሓት ነጋም እንደነገረን፣ ነፃነት የሚባለውን እንደማይፈልግና ግን የኢትዮጵያ ፕረዝደንት መሆን እንደሚፈልግ ድምፁን አሰማ፣ እነ መለስ ግን ለነፃነት የሚል ነገር አሰምተህ ስለነበረ፣ ነፃ ትወጣለህ ብለውት በእንዲህ ነገሮች እንደተንጠለጠሉ፣ የሎንዶን ስብሰባ ይከሰታል፣ ኢሳያስን ከአጥር ውጭ ትቶ ኢትዮጵያን ለብቻው ለመዝረፍ የተለመው መለስ፣ ጭራሽ ሎንዶን ስብሰባ ላይ አሰብ ለኢትዮጵያ የሚል ሃሳብ ሲፈልቅ፣ ፈጠን ብሎ፣ የለም የኤርትራ ነው በማለት፣ ኢትዮጵያን ባህር የለሽ አስደረገና ኢሳያስን ከነጠቅላላ ኮተቱ ከአጥር ውጭ አስቀመጠው፣ ግን የደርግ ወታደር ገና ደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢና ወደ ከንያም ስለነበሩና በሁለት በኩል ጦር እንዳይከፈትበት ያሰበበት መለስ፣ ኢሳያስን ኢትዮጵያ ውስጥ የቡና ኤክስፖርተር አደረገውና ኤርትራም ለሁለት አመታት ያህል ከተቀዳሚዎች የቡና አምራቾች ሃገሮች አንዷ ሆነች፣ የደርግ ወታደር ከጠቅላላው ደቡብ ወጥቶና ከከንያም ጭምር ወደ DC መሻገሩን ካረጋገጠ በኋላ፣ መለስ ኢሳያስን ወደ ኤርትራ አባረረው፣ ከዚያም መለስ ኢትዮጵያን እንዳሻው ገበያ ላይ አወጣት፣ ግን እርሱንም ሃያላት በሂይወቱ ስለመጡበትና ከዚያን በኋላ ኣይተ ስብሓት ነጋ ስላልቸለበት እነ ኣይተ አቤት ወዴቶችን ተንደፋዳፊዎችን መላላክ ጀመረ፣ ነገሩ ሁሉም ድንግርግር ገባበትና ጃፓኖ አሜሪካኖም ጫዋታቸውን ተጫወቱ፣
    ከዚህን ጊዜ ጀምሮ የጥንቱ ዋናው የመለስ አቀባባይ “ውጭ ጉዳይ ሚኒስተር” ስዩም መስፍን ወደ ደላላነት ወርዶ የት እንደሚውልና እንደሚያድር አናውቅም፣ አሁን ግን በሰሞኑ የካርቱም ተዝናኝና የኢትዮጵያን ምድር አሻሻጭ ደላላ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ እንደ ኤርትራዊ ዘ-ዓዲ ቐይሕ በውስጠ ልብ ሆኖ፣ አዲስ ዘፈን ውስጥ ውስጡን በትኗል፣ ዘፈኑም በተለይም ምኒልክንና ተከታዮቹን ይመለከታል፣ እንዲህም ይላል፣ በትግርኛም ነው:
    “ከምቲ ዝሸጥኩምናስያ ሸጥናኩም እንዶ
    ሕንኡያ ዘይፈዲስ ኣይ ወዲ ኣቡኡን እንዶ” ይላል፣
    በዚህ ሁሉ ተግባራት ታድያ በተለይም የደርግ ካድሬዎችና የምኒልክ ልጆች ዘንዳ እንዲሁም ምናልባትም በጠቅላላው ዓለም የተበተኑት ጀብሃ ወሻዕቢያ ወታደር ነበርኩኞች ዘንዳ እንጂ፣ እኔ ዘንዳ የበታችነት ስሜቱን ምን ሊያመጣው ይችላል ክብር የለሹ ሓሳዱማየየኒ…………!!?? ለበለጠ ማብራርያ፣ wo ever you are. ድምፅህን እንደገና አሰማ

    • The TPLF thugs are pathological liars and lying is their trademark.Born lying and dying lying. The truth is that the master-slave relationship between the EPLF and TPLF that existed and continued caused crisis in the TPLF.The TPLF dissidents led by the Seye-Gebru faction revolted against the hard handed rule of president Isaias Afewerki and have been discarded.
     The other lies are during the major battles of the 1980s in Eritrea, the TPLF deployed its fighters there in excange for weapons. The EPLF was well supplied and needed the Tigray fighters in exchange. According to reliable sources the exchange rate at the time was 10 Tigray fighters for 1 Kalashinkv rifle. That was how the TPLF traded Tigray fighters for weapons with the EPLF.

 2. ወዳጄ ምሁራዊና ታሪካዊ ትንታኔ ሰጥተህበታል እኛም እነ ክንድ ጠምዝዝ በባዶ ጩኸት ክርክር ቢነሳ እንዳያደናግሩን በማህደራችን ከተነዋል። ሁሉንም ነካክተሃቸዋል ግምቦት 7 የተባለዉነ ጸረ ኢትዮጵያ ድርጅት ግን በስሱ ነዉ የሄድክበት ብርሀኑ ነጋ የኖረዉ ዉጭ የተማረዉ ነጭ አገር ሁኖ በምን አይነት አክሮባት ነዉ ገልብጦ ዋናቸዉ የሆነዉ? አንዳርጋቸዉ ጽጌ ሲቀምም ሲቆርጥ ሲቀጥል ከርሞ እሱ እንግሊዛዊ በመሆኑ እንደ ልቡ ለሚመራዉ ለብርሀኑ ነጋ አስረክቦ ከቅርብ ይቆጣጠራቸዋል።

  አንዳንድ ስብሰባ ላይ ጥላቻቸዉ በዝቶ ብርሀኑ ነጋ/አንዳርጋቸዉ ጽጌ፤ነአምን ዘለቀ፤ኢሳትና ኢትዮ ከረንት አፌየርስ በሚባል ክፍላቸዉ አማራ ከጧት እስከ ማታ ሲደበደብ ያመሻል። አማራዉ ሙቶ ካልሆነ ግምቦት 7 የሚባለዉ ጠላቱ ወደ ክልሉ እንዳይመጣ የሚቻለዉን ሁሉ ማድረግ ይጠበቅበታል አልሰማሁም አላየሁም የሚለዉ የአማራ ልሂቅ ስለነዚህ ሰዎች ለማወቅ ኢሳት አርካይብ ገብቶ መመልከት ነዉ።

  እዚህ ላይ በእርግጠኝነት ትክክለኛ አሃዙን ማስተዋስ ባልችልም ብአዴን ለ ኢሳት 20/40 ሚሊዮን ብር መስጠቱ ትዝ ይለኛል በጊዜዉ የአማራ ተወላጆች በስብጥር ፖለቲካዊና ወታደራዊ ወከባ በየጫካዉ እነደ አዉሬ ተበትነዉ ሲያድሩ ብአዴን የሚባል ጉድ ድንኳን ገዝቶ እንደመስጠት እንዲህ ያለ ነዉር ይሰራል።

  እንግዲህ ይህ የጥቃት ኢላማ የሆነዉ ህዝብ የጊዜ ጉዳይ ነዉ እንጂ ክፉ ረመጥ እነደሚሆንባቸዉ የታመነ ነዉ። 4 ሚሊዮን ትግሬ ይሄን ሁሉ አመት ቁም ስቅል ካሳየ አማራዉ ከኢትዮጵያዊነቱ እረፍት ወስዶ ወገኔን አድናለሁ ካለ ችግሩ የከፋ ይሆናል። እዚህ ላይ ዶ/ር አብይ በቅንነት ይሁን ለስዉር አላማ ከኢሳይያስ ጋር የሚያደርጉት ማንኛዉም ስምምነት የመጀመሪያዉ ተጠቂ እሳቸዉ መሆኑን ሊያዉቁት ይገባል ሰዉየዉ እነ አንዳርጋቸዉ ዲሞክራቲክ መሪ ነዉ ብለዉ የነገሩን ሳይሆን በደምና በግፍ የሰከረ ነዉ ለሌላዉ ያላዘነ ለአብይ አህመድ ያዝናል ልቡን ይሰጣል ብሎ መገመት ቂልነት ይመስለኛል።
  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር’

 3. The ሻዕቢያዎች፣ አዲስ ኢንፎርመሽን እነሆ ከ’TOL አካባቢ፣: እንዳያመልጣችሁ፣ ምናልባትም እንደገና ከአጥር ውጭ የመወርወር እጣ በሻዕቢያ ላይ እየመጣ ይመስላል፣ This time internationally …! ማን ያድን ታድያ አሁን ? ኣረጋዊ በርሀም የትግራይን ወታደር ይዞ አይደርስላችሁም፣ የጀብሃን ወታደር ደግሞ የአረቡ አለም ግርድና በልቶታል፣ የሻዕቢያው ወታደር ነበርም “የጅማት-CORONA” ኖርወይ ውስጥ አካሉን ሁሉ ጨምድዶና አፍኖ ይዞት በ’Gesundheitsschuhe እርዳታ ብቻ ነው የሚንቀሳቀሰው..! ለማንኛውም ግን ጉራን ዝቅ አድርጉና ኢንፎርመችኑን እነሆ እንደሚከተለው:

  ” It is not clear what is going on in Eritrea, but many countries including United Kingdom and the U.S.A are evacuating their staff members from their Embassies in Asmara, Eritrea.

  The reason given by the UK Embassy simply says “given the rapidly changing situation…” as you can see in the following paragraph.

  Summary
  “Given the rapidly changing situation in Eritrea we are temporarily withdrawing all UK staff from our Embassy. The Embassy will continue to carry out essential work including providing 24/7 consular assistance and support to British nationals in Eritrea. Removal of information about a flight which departed Eritrea on 18 April. (‘Summary’ and ‘Return to UK’ pages)” “

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.