ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣው የሰዎች እንቅስቃሴ ለኮሮና ተጋላጭነት ስጋት መሆኑን የምዕራብ ጎንደር ዞን ማኅበራዊ ልማት መምሪያ አስታወቀ

በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ 2 ሺህ 667 ሰዎች ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን የምዕራብ ጎንደር ዞን ማኅበራዊ ልማት መምሪያ ገልጧል፡፡

45የመምሪያው ኃላፊ ክሽን ወልዴ እንተናገሩት በሱዳን ከአራት ቀን በፊት በኮሮና ቫይረስ የተያዙት ሰዎች 36 ነበሩ፡፡ ይሁን እንጅ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ 107 ሰዎች በቫይሩሱ መያዛቸው ታውቋል፡፡

የምዕራብ ጎንደር ዞን ማኅበራዊ ልማት መምሪያ ኃላፊ ክሽን ወልዴ እንደገለጹት በዞኑ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የተላለፉ ክልከላዎች ተግባራዊ ተደርገዋል፤ በሁለቱ ሀገሮች መካከል ሲደረግ የነበረው የተሽከርካሪ እንቅስቃሴም ተገትቷል፡፡ ይሁን እንጅ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ የሰዎች እንቅስቃሴ አለመቆሙን ግን ወይዘሮ ክሽን ገልጸዋል፡፡ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥም 2 ሺህ 667 ሰዎች ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውንም አስታውቀዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ 426 ሰዎች በገንዳ ውኃ ከተማ አስተዳድር ለ14 ቀን በለይቶ ክትትል ማድረጊያ እንዲቆዩ፤ ተጓዳኝ የጤና ችግር ያለባቸውም ሕክምና ተደርጎላቸው ወደ አካባቢያቸው መላካቸውን ወይዘሮ ክሽን ገልጸዋል፡፡

በለይቶ መከታተያ ከቆዩት ሰዎች ውስጥም ሁለት ከገዳሪፍ፣ አንዱ ደግሞ ከእስራኤል የመጡ የሦስት ሰዎች ናሙና ለላቦራቶሪ ምርመራ ተልኮ ነፃ መሆናቸው መረጋገጡንም ገልጸዋል፡፡ ሚያዝያ 12/2012 ዓ.ም ብቻ 92 ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን ኃላፊዋ ነግረውናል፡፡ በዚህ ወቅትም 7 ሰዎች በለይቶ ክትትል ማድረጊያ እንደሚገኙ ወይዘሮ ክሽን ገልጸዋል፡፡ ከሱዳን ካርቱም እና ገዳሪፍ የሚመጡ ሰዎች ለ14 ቀናት በለይቶ ክትትል ማድረጊያ እንዲቆዩ ቢደረግም በኢትዮ-ሱዳን ድንበር አካባቢ ባሉ ባለሀብቶች እርሻ ላይ ቆይተው የሚገቡት ሠራተኞች ግን ቀጥታ ወደ አካባቢያቸው እንደሚላኩ ነው ያመላከቱት፡፡

በሱዳን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የገለጹት ወይዘሮ ክሽን ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው ሰው ቁጥር መጨመር ለሀገሪቱ ስጋት በመሆኑ ለሱዳን አዋሳኝ በሆኑ ቋራ እና ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳዎች ተጨማሪ የለይቶ ክትትል ማድረጊያዎች ለማቋቋም እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

የክልሉ እና የፌዴራል መንግሥታት ለአካባቢው ትኩረት ሰጥተው መሥራት ካልቻሉ ችግሩ አስከፊ ሊሆን እንደሚችልም ኃላፊዋ ገልጸዋል፡፡ ወደ ዞኑ የሚገቡ ሁሉንም ሰዎች በለይቶ ክትትል ማድረጊያ ለማሳለፍ አስፈላጊው የምግብ እና ሌሎች ግብዓቶች ሊሟሉ እንደሚገባ የገለጹት ወይዘሮ ክሽን የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት ጉዳዩን አጢነው አፋጣኝ መፍትሔ እንዲያስቀምጡም ጠይቀዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ዳግማዊ ተሠራ/ አብመድ

2 Comments

 1. እስካሁን ጊዜ ድረስ የኢትዮጵያ ሆኖ ከሚታወቀውና ግን በቅርቡ በስዩም መስፍን ደላላነት የሱዳን ወታደሮች ኢትዮጵያውያንን ከእርሻ ቦታቸው እያባረሩ የሚያፈናቅሏቸው ኢትዮጵያውያን ናቸው እየመጡ ያሉት::

  ደላላው የሚፈልገውን አግኝቷል፣ ኢንተርነት በካርቱም በኩል ይዘረጋለታል፣ እንዲሁም እርሱና መቐለ ካራንቴነ ውስጥ የተሰገሰጉት ባንዳ ቡድኖቹም በካርቱም ኢንተርናሽናል ኤርፖርት በኩል ወደፈለጋቸው የአውሮፓና ኤሽያ ሃገራት እየበረሩ ህክምናን ያገኛሉ፣ ከእንግዲህ ፊንፊነ ሆይ አታስፈልጊኝም፣ ቻው ቻው’ም ብለዋል::

  ከሁሉም የሚገርመው ግን ይሄ በህልም አለም ውስጥ ብቻ የሚኖረው የምንትሴ “አስመላሽ” ኮሚቴ ከእርሻቸው የተፈናቀሉን ኢትዮጵያውያንን ከሱዳን የመጡ ብሎ ሲል፣ በቅርቡ የሱዳን ወታደር የያዘውን የእርሻ ምድርን ለሱዳን አውቆለታል ማለት ነውን..?? ወይንስ ያኔ ዱርቡሽ ጎንደርን ስትወርና 44 አብያተ ክርስትያናት ሲጋዩ፣ ሃገርን ከመከላከል ይልቅ፣ የሸዋውና የጎጃሙ ንጉሶች ያደረጉት አይነት ሽሽት እይተደገመ ይሆንን..?

  እንግዲህ የዋሁ ሃፀይ ዮሃንስ የሉ፣ ዘለውም አገር አያድኑ፣ አትላንታ ሆነህ ስለ ዓድዋ ጀግንነት ፎካሪው ሓሳድ ከእኔ በላይ ኢትዮጵያዊ የለም ባዩ ልግመኛውሳ አሁን ታድያ ምን አልክ………!!???? ባልደራስህና መሮሾችህስ የት አሉ ታድያ…?

  ባልና ሚስት የተጣሉበት ማእድ ዘንዳ አድርሰኝ ብሎ የሚፀለየው እንዲህ አይነት ሁናቴ አሁን ለሱዳን እንደተከፈተው መና ይከሰት ዘንዳ ነው እኮ…!!!!

 2. “ዛሬ ዓድዋ ማለት ህዳሴ ነው” ባዩ ከአትላንታ ሆይ፣

  ህመሙን የደበቀ አይገኝለትም መድሃኒት እንዲሉት፣ ምንድነው ደግሞ ዘ-ሓበሻ የሚያትተው የጀመረው የግብፅ ሱዳንን ህዳሴ ግድብን አስመልክቶ በጎኗ ማሰለፍ እታይዶስ ከመይዶስ? የሱዳንን ሃሳብ አስለዋጩ ደላላስ ተገኝቷልን….?

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.