የዶክተር አብይ ፒኮክና የይሁዳ አንበሳ – ገለታው ዘለቀ

abiyወደ ዛሬው ርእሴ በቀጥታ ከመግባቴ በፊት ወቅቱ የኮረና ቫይረስ ሃገራችንን ስጋት ላይ የጣለ በመሆኑ ህዝቡ ራሱን እንዲጠብቅ እንደ ዜጋ እየጠየኩ በውነት እግዚአብሄር ሃገራችንን ከዚህ በሽታ ይታደግልን።

ይህንን ካልኩ በሁዋላ ዛሬ ወደ ተነሳሁበት ርእስ ልምጣ። እንደምታውቁት ሃገሮች  የየራሳቸው የእንስሳ ብሔራዊ ምልክት አላቸው ፡፡ ለምሳሌ  አሜሪካ  ብሔራዊ  ምልክቷ ንስር ነው ፡፡ ቻይና ደግሞ ፓንዳ ነው ምልክቷ፣ ሩስያ ድብ፣ ቬትናም ወተር ቡፋሎ፣ አንዳንድ  አገሮች  ነብር  ታላቁዋን ብሪታኒያን ጨምሮ ኬንያና አንዳንድ  ሃገሮች  ደግሞ የእንስሶች ንጉስ የሆነውን አንበሳን መርጠዋል፡፡ ኢትዮጵያ ሃገራችን አንበሳን ከመረጡትና በአንበሳ ጥንካሬ ከተማረኩት የመጀመሪያዋ ሀገር ናት፡፡  የዓለም ሃገራት ከእንስሳቱ ዓለም ምልክት ሲሹ የዚህ  ምልክት  ዓላማ  ከእንሰሳቱ  ጠንካራ  ጎን  በመውሰድ  ያንን  ጠንካራ  ጎኑን   ለማህበረሰቡ ሀይል፣ ሃሴትና ርካታ  ይሆናል  ከሚል  ስሌት ነው ፡፡  ይህ  የየሃገሩ  ምልክት  ዘመን  ተሻጋሪ ነው ፡፡  መንግስት ሄዶ መንግስት ሲመጣ፣ ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ ፣ ብሄራዊ ምልክቶች ይኖራሉ ፡፡ ወደ ሃገራችን ኢትዮጵያ ስንመጣ የረጅም ዘመናት ታሪክ ያለው፣  እልፍ  ዘመን  ተሻግሮ የመጣው፣ ብሔራዊ ምልክት  አንበሳ  ነው ፡፡ ኢትዮጵያዊ  በባህሉ  ጥንካሬን ፣ ጥረትን፣ ጉብዝናን፣ በዚህ እንስሳ በኩል ይገልጻል ፡፡ ከዚህም በላይ  በኢትዮጵያ  ሃገረ መንግስት  ታሪክ ውስጥ  አንበሳ  የጥንካሬ፣ የሃይል ፣ የብርታት ምልክት ብቻ  ሳይሆን ለረጅም ዘመን የቆየው  የሰለሞን  ስርወ መንግስት ምልክት ነው፡፡ ሞአ አንበሳ ዘእም ነገደ ይሁዳ የሚለው የነገስታቱ ማእረግ የዘመናት መጠሪያ ነው፡፡ በሌላ በኩል ከሃይማኖት አንፃር ደግሞ የይሁዳ አንበሳ የተባለውን ኢየሱስ ክርሰቶስን የሚያሳይ ነው፡፡ መጽሃፍ ቅዱስ ክርስቶስን የይሁዳ አንበሳ ይለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ክርስትናን ለረጅም ዘመን  ከቤተ-መንገስት ጋር አያይዛ ስለኖረች አንበሳ ምልክቴ ነው ስትል ሞአ አንበሳ ትላለች፡፡ ሞአ ማለት አሸናፊ ማለት ሲሆን አሸናፊው አንበሳ ክርስቶስ ነው ከሚል የመጣ ትርጓሜ  ነው፡፡ በአንድ በኩል የሰለሞንን ስርወ መንግስት  እያሰበች  በሌላ በኩል ደግሞ አሸናፊውን ክርስቶስን ሃይሌ ነው እያለች የምትኖርበት ምልክት ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር ደግሞ በዘመናት መሃል አንበሳ የኢትዮጵያውያን የጀግንነት፣ የሰራተኝነት ምልክት ነው፡፡

በ1966 ለውጥ ሲመጣና የሰለሞን ስርወ መንግስት በሃይል ሲቋረጥ ወታደራዊው መንግስት  ብዙ እሴቶቻችንን የሰበረ ቢሆንም በህዝቡ ልብ ውስጥ ይህ ምልክት ግን ህያው ነበር ፡፡ ምንም እንኳን ስርወ መንግስቱ ቢቋረጥም ብሔራዊ ምልክታችን አልተነካም፡፡ ህብረተሰቡም ለአንበሳ ምልክት ትልቅ ክብር ሁልጊዜም አለው፡፡

በቅርብ ቀን ከአንድ ቦታ ታክሲ ይዤ ወደ ፒያሳ ስመጣ አንድ አካባቢ ተቀየረብኝ፡፡ የት እንዳለን ማወቅ አቃተኝ፡፡ ወደ ግራ ወደ ቀኝ  እያማተርኩ የት ነን አሁን?  ብዬ ታክሲ ውሰጥ እያለሁ ጠየኩ፡፡

“ቤተመንግሰት ነን “ አለችኝ አንዷ ተሳፋሪ፡፡

ዘወር ስል ሁለት አንዳች የሚያካክሉ የወፍ ዘሮች አየሁ፡፡ እነዚህ የወፍ ዘሮች ፒኮክ የተባሉት ወፎች ሲሆኑ  ቤተ-መንግስቱ በር ላይ ግራና ቀኝ ተፋጠው ይታያሉ፡፡ ግዙፍ ሃውልት ነው የተሰራላቸው፡፡ በውነት ተገረምኩ፡፡

ከዚህ በፊት <<ርካብና መንበር>> የተሰኘውን  የዶ/ር አብይን መጽሃፍ  አንብቤ እጅግ አዝኜ ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንበሳ ላይ ያላቸው ጥላቻ ምንም ስም የለውም፡፡ ይህንን ስነ ልቡና ከየት እንዳመጡት መገመት ከበደኝ፡፡ በኢትዮጵያ ህዝብ እምነት፣ ባህል፣ ሰነ-ቃል ውስጥ አንበሳ መልካም ምልክት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ አንበሳን መጥላት ብቻ ሳይሆን ይህንን እንስሳ ለማስጠላት መጽሃፍ ጽፈዋል፡፡ የአንበሳን ደካማ ጎኖች እየፈለጉና አንበሳ የሌለውን ተፈጥሮ አለው እያሉ የኢትጵያን ህዝብ ከዚህ ምልክቱ ለማፋታት ያልሆኑት የለም፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ አኚህ ሰው አንበሳን ህዝቡ እንዲጠላ በመሞከራቸው አዝኜባቸው ነበር ከልቤ፡፡ ያሳዘነኝ ለእንስሳት ሰብአዊ መብት በመቆሜ ሳይሆን ከምልክቱ ባሻገር ያለውን እሴት ለመስበር ያላቸውን መሰሪ ጥረት  በመረዳቴና ትውፊታችንን በምናብ በማየቴ ነው።

አሜሪካውያን ንስርን ሲመርጡ ከዚህ ፍጡር ያዩት ብርታት ለህብረታቸው ጥንካሬ በጎ ምሳሌ ስላለው ነው። ንስር ከፍ ብሎ ይበራል፣ ንስር በእርጅናው ወራት ሃይሉን ያድሳል፣ ንስር ከካይ እየበረረ ከታች ምድር ላይ ያለውን ረቂቅ ነገር ያያል። በዚህ ፍጥረቱ የተደነቁ አሜሪካውያን እኛም እንደዚህ ሃይላችንን እናድሳለን ፣ ከፍ ብለን እንበራለን፣ ረቂቅ ነገሮችን እናያለን፣ ብሩህ ነን ለማለት ንስርን ብሄራዊ ምልክት አደረጉት፤ ይሄ የአሜሪካውያን እሴት ነው። ኢትዮጵያውያን ደግሞ የተደመሙት በአንበሳ ነው። አንበሳ ያሉትን ጠንካራ ጎኖች ወስደን ለማህበራችን ምልክት ካደረግን ሽህ አመት ሆነን። አንበሳ እሴታችን ነው። ትውፊታችን ነው። ገበሬው አገላብጦ ሲያርስ አንበሳው ይባላል፣ ሩዋጩ ሩጦ ሲያሸንፍ አንበሳ ይባላል። ተማሪው በትምህርቱ ሲሳካለት አንበሳ ይባላል። ጅግናው ወታደር ጀብዱ ሲፈጽም አንበሳ ይባላል፣ መሪው ጀግኖ ሲገኝ አንበሳው ይባላል።  ጅግናዋ ሴት ስታሸንፍ አንበሲት እንላታለን። ምልክታችን ነውና ዘወትር አንበሳን ከፍ አድርገነው  እንኖራለን። በባህሎቻችን፣ በሃይማኖታችን፣ በትውፊታችን ሁሉ አንበሳ የጥንካሬና ድፍረት ምልክት ነው።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህንን እሴታችንን ለማጣጣል ብዙ ጥረዋል። “ርካብና መንበር” በሚለው መጽሃፋቸው ላይ አንበሳ ምልክት መሆን አይችልም እያሉ የሚታገሉ አስገራሚ ሰው ናቸው። በአስተዳደር በኩል የገጠሙንን ችግሮችና እልቂቶች ሁሉ አንበሳን ብሄራዊ ምልክት ከማድረጋችን ጋር ያያይዛሉ። ይገርማል። ሌላ እንስሳ መፈለግ አለብን እንጂ አንበሳ ብሄራዊ ምልክት  አይሆንም ብለዋል። ትውፊታችንን የተዳፈሩ የመጀመሪያ መሪ ናቸው።

በእሴታችን ላይ ጥላቻ ያላቸውና “ርካብና መንበር” የሚለውን መጽሃፍ የጻፉት እኚህ ሰው  ወደ ስልጣን መጡና እነሆ ዛሬ አንዲት እንስሳ ይዘውልን መጡ ማለት ነው። ዶክተር አብይ እነሆ ዛሬ በቤተ መንግስቱ በር ላይ ፒኮክ ለተባለችው ወፍ በአንበሳው ምትክ ሃውልት አቁመዋል። እኚህ ሰው ስለምን አንበሳ ጠሉና ፒኮክ ወደዱ ብሎ መጠየቅ ይገባል። ምን አልባት አንበሳ ደካማ ጎኖች ስላሉት ነው እንዳንል ፒኮክ የተባለችው ወፍም ብዙ ደካማ ጎኖች አሉዋት። ፒኮክ ነጭናጫ ወፍ ናት ይባላል። ከሌሎች ወፎች ጋር አብራ መኖር አትችልም። ሲበዛ ግዛታዊ ናት። ወደ ክልሉዋ አታስገባም። ስስታም ናት ማለት ነው። ከሁሉ በላይ ንቃተ ህሊናዋ ዝቅተኛ ነው። ፒኮክ ራሱዋን በመስታወት ብታይ ከራሱዋ ምስል ጋር ካልተደባደብኩ ብላ አምባጉዋሮ የምትገባ ፍጡር ናት። ከአንበሳ ጋር በኢንተለጀንስ አይገናኙም። ሳይንቲፊክ አሜሪካን የተሰኘው መጽሄት ሳይንስ ስለ አንበሳ የደረሰበትን ሲገልጽ አንበሳ የፐዝል ጥያቄ መመለስ የሚያስችል አእምሮ እንዳለው ገልጹዋል።

በርግጥ ህንዶች ይህቺን ፒኮክ የተባለች እንሰሳ ምልክት ሲያደርጉ ቀለሙዋ ከነሱ ቀለም ምርጫ ጋር ይሄዳል መሰለኝ። ትውፊትም አላቸው ይሆናል። በባህላቸውም ደግሞ ፒኮክ ትወደዳለች። እኛ መጀመሪያ ነገር ስሙዋንም አናውቅም። ስንት ኢትዮጵያዊ ፒኮክ የምትባል ወፍ እንዳለች እንደሚያውቅ አላውቅም። በስነ-ቃላችንም ሆነ በባህላችን የለችም። ትውፊታችን አንበሳ ነው። አንበሳ በኢትዮጵያውያን ብሄሮች ዘንድ በጎ ምሳሌ ነው። ከሰማይ በራሪ ሌላ የብሄራዊ ምልክት ብንጠየቅ ርግብን ነው የምንመርጠው። ኢትዮጵያውያን ርግብ የሰላም፣ የቅድስና፣ የርህራሄ ምልክት አድርገው ያያሉና። ነገር ግን ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህቺን ወፍ በአንበሳው ቦታ ሲያኖሩ አንደኛው ነገር እሴትን መስበር ነው አጀንዳቸው። ይሄ ነው አሳዛኙ ነገር። መደመር ማለት ይሄ ነው። ሁለተኛ ነገር እኚህ ሰው የራሳቸውን አሻራ መተዋቸው ነው መሰለኝ። ይህ በውነት ተገቢ አይደለም። አንደኛ ነገር እኚህ ሰው በህዝብ አልተመረጡም። ሁለተኛ በየዘመኑ የመጣ መሪ ሁሉ ብሄራዊ ምልክታችንን እየለወጠ የራሱን እንስሳ ሃውልት አይሰራም። እኚህ ሰው ሲወርዱና ነገ ሌላው መሪ ሲመጣ ሰጎን የተሰኘችውን ወፍ ቢያቆም፣ ቀጥሎ የሚመጣው ወይፈን ቢያቆም ቀጥሎ የሚጣው ጉሬዛ ቢያቆም ቤተ-መንግስቱ የእንስሳት ሙዚየም ከመሆኑ አልፎ ብሄራዊ ምልክት አይኖረንም።  የአንድን ማህበረሰብ እሴት መጠበቅ የሁላችን ድርሻ ነው፡፡ እሴቶች በዘመናት መሃል አይነኩም፡፡ አሜሪካውያን መሪ በመረጡ ቁጥር ብሔራዊ አንስሳቸውን አይለውጡም፡፡ ኦባማ ይህንን አላደረጉም። እሴቶቹ ታሪኮች ናቸውና ይጠበቃሉ፡፡

አንበሳ ጠሉ ዶ/ር አብይ ፒኮክ በቤተመንግስቱ በር ላይ ማድረጋቸው እንደ ትንሽ ነገር አይታይም፡፡ ትውፊትን መስበር ነው። እኚህ ሰው በአንድ በኩል መደመር እያሉ በሌላ በኩል ግን ትውፊታችንን እሴቶቻችንን እየሰበሩ ይገኛሉ። ቤተ መንግስት እያስዋብኩ ነው እያሉ የታሪካችንን ቀለም እያጠፉ ነው። ሃይ ሊባሉ ይገባል። ከፍ ሲል እንዳልኩት ኢትዮጵያውያንን ፒኮክ የምትባለውን ወፍ ምንም አያውቁም፡፡ ስሟንም አያውቁም፡፡  ይሄ ትውፊታችንን ማቅለል ብሔራዊ ስሜትን መጉዳት ነው፡፡ ቤተንግስት ታሪካዊ ቦታ ነው፡፡ እንደፈለግን የፈለግነውን የምንገነባበት የምናፈርስበት የግል ቤት አይደለም፡፡ ታሪካዊ ውበቱን ጠብቆ ሊቆይ ይገባል፡፡

የዶ/ር አብይ ወፍ ቤተመንግስቱን ግርማ ሞገስ አሳጥቶታል፡፡ ለታሪካችን ስድብ ነው። ሃይማኖትን ማቅለል ነው። ከሁሉ በላይ እኚህ መሪ ህዝብ እስኪመርጣቸው እንኳን አልታገሱም፡፡ እኒህ ሰው ፒኮክ የተባለችውን ወፍ ከወደዱ ወይ በራሳቸው ግቢ  ወይ በሆነ ስፍራ ሃውልት ሊያሰሩ ይችላሉ። ነገር ግን ይህ ቤተ መንግስት የግል ቤታቸው አይደለም። በዚህ ቤት ብሄራዊ ምልክታችን ነው ከፍ ብሎ መታየት ያለበት። ሌላ እንስሳ የተባለ ነገር ቤተ መንግስት አይታይ ሳይሆን ጠቅላይ ሚንስትሩ በመጽሃፋቸው አንበሳ ብሄራዊ ምልክት መሆን የለበትም ባሉት መንፈስ በምንም አይነት ሊሆን አይገባም ለማለት ነው። ክብር ለትውፊታችንና ለእሴቶቻችን።

 

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ

[email protected]

7 Comments

 1. አቶ ገላታው ላቀረቡት በመረጃ የተደገፈ አስተያየትዎት ምስጋናየ ይድረስዎይ ። እኔ ርካብና መንበርን አግኝቼ የማንበብ ዕድሉን ባላገኝም ጋዜጠኛ ክንፉ አስፋ ያቀረበውን የግል ምልከታ ማንበቤ ትንሽ ግንዛቤ ሰጥቶኝ ነበርና የርሶ ሲጨመርበት የዶክተሩን ማንነት ፣ ዓላማና ግብ ምን መሆኑን ለማወቅ ከጥርጣሬ በዘለለ መረጃ እየሆነን ያለ ሀቅ ነው ። የተቸገርነውኮ አማራጭ ማጣታችን ነው ። ግራ የተጋባው ሕዝብ የሚታደገው እምነት የሚጣልበት የምድርም ሰማያዊ ኃይል ሲያጣ ምህታተኛ ጠንቋን ነብይ ብሎ ፤ እንደ አሸን የፈላውን ተለጣፊና እርስ በርሱ የሚባላ የፖለቲካ ድርጅት እያወቀ ዐይኑን ጨፍኖ ይሸነገላል ። በአንድ በኩል መደመር ማለት በጎደለው መሙላት ባለው መጨመር ይለናል በሌላ በኩል ደግሞ አሁን እርሶ እንዳሉት የነበረውን አጥፍተው የራሳቸውን አሻራ ለማኖር ሌት ተቀን ይባዝናሉ ። የሀገር መሪ ሆነው አመራር በመስጠት በአገር አቀፍ ደረጃ ሊተገበር የሚችለውን ነገር ሁሉ አዲስ አበባ ላይ ብቻ በካሜራ ታጅበው ለእይታ የሚያደርጉት ነገር ሁሉ አማካሪ የላቸውም ወይ የሚያስብል ነው።

 2. Some times I wonder if we really know what we want.

  Abiy was only a young teenager when he joined the armed struggle against DERG.

  Ethiopia had an army which was a century old by then.

  To this day the soldiers are praised for what they did but the govt.

  Unlike most of the world the soldiers of Ethiopia did not believe their guns was their main weapon. Ethiopia needs principles and causes to fight for. Some of the opposition Ethiopian fighters found them selves in the same predicament as the century old Ethiopian army.

  The best way to defeat the Ethiopian army, they thought, was to make him lose his core purpose. But you can’t make Ethiopian submit that way, you only make him mad. He would rather die.

  Ethiopians come in many shapes and forms. When one gets weak the weak gets strong and takes over. More than anybody in the entire world they get satisfaction from being local heroes. It paid in the past.

  Abdissa Aga, Abebe Aregay etc were great warriors because their base supported them. And they knew what they were fighting for. Abdissa fought in Europe but the same enemy that took away his country from him. In 1977 he was called back from retirement to help out. highest rank Colonel. Abebe was the HQ of the entire resistance for five years. His son Daniel was only 14 when the flag rose up again. Daniel Abebe was one of the ‘I wish me was him’ kind of people with flair. A Captain in the Airlines. His son Tewodros Daniel didn’t make the cut. Captain Daniel paid cash to see his son graduate in a second chance.

  Abiy by now is aware not everything he had to say ‘yes’ to was the whole truth. He had learned Aba Jiffar built a house in Mecca so that Ethiopians can stay there on their Haj. All kinds of Ethiopians. Queen Tayitu and Aba Mela had properties in Jerusalem for all kinds of Ethiopians to stay without a charge just because they were Ethiopians. Abiy is touched those 19th century leaders had that kind of self awareness.

  I think he is also aware that what has been tried so far hasn’t worked, evidently.

  Millions of Ethiopians love the emblem of the lion of Judah on the flag with his own flag AND the plain Green Yellow/Gold and Red. If you look closely the tip is a cross which can’t be acceptable. The last emperor officially changed the cross at the tip into a spear because Muslim Ethiopians complained. Besides that flag was only waved at the Palaces and never in schools. When the emperor was out of the country it was not there. The lion of Judah was there when he too was safely at home.

  The twelve tribes of Jacob’s children who sold their own brother into slavery? And the Levites were the church and it took the small Benyam’s house to get Saol, the first king, and then David and Solomon from the Judah tribe.

  I don’t think all that was true. How retard was Issac for Rebeka to be fetched for him? And not to know the difference between Jacob and Esau? And why couldn’t he change his mind if he blessed his mama’s baby son Jacob by trick? And most of all why were they marrying each other’s children when they were blood relatives? Ishmael did nothing wrong and he had to suffer. Ishmael is the first born to Abraham who had yet he had to let him suffer, the very Abraham who had slaves and servants couldn’t spare a few for his first born? What kind of father was that Abraham guy? Jacob would go to his uncle and marry both his cousins and have children with them. That is very nasty bro. No wonder they were all retards. They sold their own brother Yosef into slavery and if it wasn’t for Rueben they would’ve killed him. And the story continues with Joseph being the star in Egypt until Mosses was born. If it wasn’t faith it wouldn’t make any sense at all. Why would a god choose one tribe over another? And if he chose them why did he made them suffer so much? And if Christians and Muslims believe the Jewish people were the chosen people why did they do what they did to them? As far as I know the Torah is the first five books of the old testament. Why did a ‘Christian’ named Adolf Hitler, a corporal in the Keizer’s army and a reject of art school be so cruel?

  What if all the bible stories were fake? If the bible is fake millions of people are going to be pissed off. The sufferers who were victims of Hitler and Mussolini would’ve died in vain.

  We are mostly Christians and also Muslims. We were in Ethiopia for at least 200 000 years. Archeologically. We separate the church from the state. When we separate the two life becomes easier.

  Some people are taking the ‘love’ wrongly. We got every kind of Ethiopians in this day and age. Thousands are qualified to take a spot if necessary and they are just a phone call away. And they are also diversified people for generations in some cases. Ethiopia is a very addictive country and soon thousands upon thousands will come home physically or virtually/AKSION-MAHBER.

  abiy ahmed ali is doing a great job. May be he is doing it for his children or his own ego but he is doing it and that is all that matters. If he continues this way and serve two or more terms Ethiopia will detoxify from three decades of poison and become herself once again.

 3. የተሰጠው አስተያየት የራሱ የሆነ ግላዊ አመለካከትን ፓለቲካዊ ይዘት እንዲኖረው አድርጎ የመሪን ጥላቻ ለመግለጽ መሞከር በግሌ የበጎ መንፈስን አስተሳሰብን መቀየር ይመስሉኛል:: ለመግለጽ ያህል እኚህ ጸሀፊ በአንበሳው ቦታ ፒኮክ ተተካ ነው: እኔ ደግሞ መሪው ልክ ናቸው ምክንያቱም ፒኮክ መገኘዋ አበባትና አረንጓዴ መዝናኛ ስፍራ እንጂ ጫካ አይደለም: የጫካው ንጉሰማ አንበሳው ያውም ነጩ አንበሳ በተዘጋጀለት ቦታ ከነክብሩ ከፒኮኳ ሰር ነው ያለው: ምናልባትም ማየት ከፈለጉ በውጭ ማየት ሳይሆን ወደ ፓርኩ ገባ ብሎ ማየት ሙሉ እውቀትን ይሰጣል:: አመሰግናለሁ

 4. እኔ በሃይለስላሴም ጊዜ በደርግም ጊዜ አገር ቤት ነበርኩ። በኢሕአድግ ጊዜ አብዛኛው ሕይወቴን ያሳለፍኩት በውጭ ነው። የዓለምንም ሆነ የሃገሬን ፖለቲካ በሚገባ አረዳለሁ፣ ጠቅላይ ሚንስትሩን አላውቃቸውም። የሚነዛባቸውን ፕሮፓጋንዳ ሳይ ግን የኢትዮጵያ ነቃሁ ባይ ጋዜጠኞችና እንዲሁም ፀሃፊውች ምን ያህል ሚዛን የጎደላቸው እንደሆኑ፣ የቱን ያህልም የዘመኑ የፊደል ሰዎች በተቃውሞ ብቻ የሰለጠኑ እንደሆኑ ለመረዳት ችያለሁ።ኢትዮጵያ አሜሪካን አይደለችም፣ እጅግ ባልወዳቸውም ለሃገራቸው ካላቸው ፍቅር አንፃር የፈረንጆችን ጋዜጠኞች አደንቃለሁ። የአሚሪካን ጋዜጠኞች ለምሳሌ በሃገር ደሕንነትና በወታደራዊ ዘገባዎች እጅግ ጥንቃቄ ያደርጋሉ። ባሜሪካ 80% ተቃውሞ ካለ 20% እውነት ይኖራል። ባለፉት 60 ዓመታት ለውድቀታችን ሁሉ መንሰኤ የሆነው ሁሉንም መንግስታት 80/20፣ 90/10 99/1 ስናጣጥላቸው ነው ለብዙ ችግር በሩን የከፈትነው። ጠቅላይሚንስትሩ ቤተመንግስቱን እንደሃገር ሃብት ለታሪክ እንዲቆይ በማሳደሳቸው በአክራሪ ቡድኞች ምን ያህል ስድብ እንደወረደባቸው የማያውቅ አለ ብዬ አላምንም። በዛሬ ትችትና ሕትመት ግን እጅግ አዝኛለሁ። እኔንም በአፍላ ወጣትነት ዘመኔ በማላውቀው መፈክር ሳይገባኝ ስለዘለፍኳቸው አባቶቼ የእግዚአብሔርን ይቅርታ እጠይቃለሁ። የዛሬው ፀሃፊ ጠቅላይ ሚንስትሩን መሰሪ ይላሉ እንጂ ፅሁፋቸው የመሰሪ “ልዕለ-ገቢር” (Masterpiece) ነው።

  አብራልኝ

  ባለመድረኩ ወንድም ጋሻዬ፣ ድንግዝግዙ ይዞኛልና
  ከእንስቷ ጀግኒቷ እህት…..ድረስልኝ ቶሎ ና
  የውነት መንገዷ ጠፍታኝ ፣ በውል አልቆምኩም ገና
  የማታውቀው ሽርጥ አይኖርም፣ ክውድቅቱ ምነና
  አንደ ፀጋዬ አምቦ.…….. አቀብለኝ ያን ላምባዲና።
  አንተ የሃገር ባላ.…የፊደል ሁሉ ከመዘና።

  ገድል-አብ ዮፍታሔ

 5. የፀሐፊው ትችት ተራ አሉባልታ ይመስላል። አይደለም። አዲስ አበባ ውስጥ ብዙ በጸጥታ ውስጥ ውስጡን የሚካሄዱ ድርጊቶች ተበራክተዋል ። ይሄም የአዲስ አበቤን ገጽታ ለማጥፋት በጥናት የተካሄደ መምሰል ብቻ ሳይሆን ፣ነውም።ሐገር ያለ ቅርስ ተከታይ ትውልዱን ምንነቱን የሚያሳይበት የሚያስተምርበት እሴቶች ናቸው።አዲስ አበባ የቅርስ ሐብትን ማጥፋት እንደስልጣኔና እድገት በበማስመሰል ጥፋቱን ተያይዞታል። ጥላቻና የበታችነት ስሜት ኢትዮጵያን ገና ለብዙ ነገር ይዳርጋታል።አስገራሚው ደግሞ ለዚህ ፀረ ቅርስ መንግሥት ህዝብ ዝምታ መምረጡን ነው።
  ፀሐፊው እደገለፀው ይህች አቀንቃኝ የወፍ መሳይ ፒኮክ ሐገር በቀልም አይደለችም። በአውሮፓ በየአውሬ መጎብኛዎች(Zoo)እንደምናየው ይህች ወፍ ልታይ ልታይ ስል የምትታወቅ ፣ለመታየትም ጩኸቷን የምታቀልጥ ናት።መልከኛ ናት ግን መልክ ጊዜያዊ ነው ።
  የአንበሳ ምልክታችን ታሪካዊ አመጣጡ ብቻ ሳይሆን፣ አንበሳችን በዓለም ምርጥዪ ከሚባሉትም አንድዪ እንስሳት ነው።አንበሳችን ባለ ጥቁር ጋማ የሚባለው ሲሆን ፣መሰረቱና ብቸኛነቱ ለኢትዮጵያ ሲሆን ፣በዝርያው(በጂኑ ) ተመሳሳይነት በአሁን ጊዜ በደቡብ አፍሪቃ ይገኛል።ይሄ ጉዳይም በተወሰነ ጊዜ(በደርግ ይሁን በኋላ) ንግግር ፈጥሮ ነበር።በደርግ ዘመንም ከአውሮፓ ለአንበሳ አደን ወደኢትዮጵያ የሚመጡ አዳኞች ከ20 እሰከ 50ሺ ዶላር ይከፍሉ ነበረ። እንግዲህ አንበሳችን ሰለሞናዊ ተዋረድ ብቻ ሳይሆን ለዓለማችን እንደዋልያ ብርቅዬ ነው። ጠባዩንም ብንመለከት ኩሩ፣ፍረደገምድል ያልሆነ፣ለመገደል ብቻ ብሎ ሌላ አናሳ የዱር አውሬዎችን የማያድን እንስሳ ነው።
  ይህችን ወፍ አምሳል ለማድረግ የሚደረግ የመጀመሪያ ማለማመጃ ሙከራ ብቻ ሳይሆን የአፄ ሚኒሊክ ቤተመንግስትንም ስሙን ለማስረሳትም በሰፊው ተሰርቶበታል፣ስሙንም ወደ ፓርክነት ተለውጧል። ለዚህም የመንግሥት ሜድያ በሰፊው ታምቡር ሲደልቁ ይታያሉ።
  የወፊቱን ቂን ቂን ሰውዬው ለምን እደወደው ማቀንቀኑ አሉባልታ ስለሚያስመስል ለአንባቢ ትቸዋለሁ ።

 6. Peacock is a territorial violent bird that got a herd mentality which is violent in a herd, while peacock by nature is shy and peaceful when found alone. That’s why tedemer tedemer preaching and avoiding press conferences or avoiding debates is the Abiy Ahmed’s way since he is nothing by himself. He got no substance . I wish Abiy Ahmed against Lidetu Ayalew or any other sane Ethiopian stand in a debate now so people really know how the nutty professor Alemayehu Gebremariam errand boy Abiy Ahmed just bubbles what Professor Alemayehu Gebremariam coaches him , he lacks originality. He just copied his enemies he was hunting down while working at INSA to get rehabilitated into the palace save his behind from justice by turning against his own party the OPDO.

 7. አንድ ሰው ከመሬት ተነስቶ ምን ሊሆን ይችላል!?
  አኽቲቪስት ሊሆን ይችላል??????

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.