ስለ ሲኒማ አምፒርና ስለ ያኔ ሲኒማ ቤቶች

ጣሊያን ለጊዜውም ቢሆን አገራችንን በወረረችበት በሳምንቱ ፤ ሲኒማ አምፒርን ገነባች፤፤ በወቅቱ ሲኒማ አምፒር ገብተው ፊልም እንዲያዩ የተፈቀደላቸው ራሳቸው ጣሊያኖች ሲሆኑ ለሀገሬ ሰው ገብቶ መመልከት ፍጹም አይፈቀድም ነበር ፤፤ ሆኖም አንዳንድ ለጣሊያን ያደሩ ባንዳዎችና የሲኒማ አምፒር ሰራተኞች ወደ ሲኒማ አምፒር ገብተው እንዲያዩ ይፈቀድላቸው ነበር ፤፤

12642987 10154062824099587 9058021945948822933 n በነገራችን ላይ በ1902 ዓ.ም የመጀመሪያው ሲኒማ ቤት ቴዎድሮስ አደባባይ አጠገብ “ፓቲ” የሚሰኘው ሲሆን (የዛሬው ሜጋ አምፊ ቴያትር ያለበት ቦታ ላይ) የተከፈተ ሲሆን ያቋቋሙትም ሁለቱ ወንድማማቾች ነበሩ፡፡ ምንም እንኳን የፈረንሳይ ተወላጆች ቢሆኑ፣ የጣሊያን ዜግነት ነበራቸው፡፡ ሕዝቡም ሲኒማ ቤቱን “የሰይጣን ቤት” እያለ ነበር የሚጠራው፡፡

ከ1908 እስከ 1926 ዓ.ም ድረስም አምስት ሲኒማ ቤቶች ተከፍተው ሲኒማ ያሳዩ ነበር፡፡ የኢጣሊያ ወራሪዎች ወደአዲስ አበባ ሲገቡ ከሰይጣን ቤት በስተቀር ሁሉም ሲኒማ ቤቶች ተቃጠሉ (የፊልም ማዳበሪያና መቆጣጠሪያ ዋና ክፍል፣ ገጽ 4-7)፡፡

12654200 10154062824094587 7402933904834210105 n

ሆኖም ወራሪው ኃይል የሲኒማን ጠንካራ የፕሮፓጋንዳ መሣሪያነቱንና ኃይሉን ስለተረዳ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተቃጠሉትን ሲኒማ ቤቶች አድሶ፤ ሲኒማ ኢታሊያ (የዛሬው ሲኒማ ኢትዮጵያ ነው)፣ ሲኒማ አምፒር (አሁንም በቦታው ላይ አለ)፣ ሲኒማ ማርኮኒ (አሁን የብሔራዊ ቲያትር ሕንፃ ያረፈበት ቦታ ላይ ነበር)፣ ሲኒማ ቺንኮ ማጆ (አራት ኪሎ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሣይንስ ፋኩሊቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኝ ነበር)፣ ሲኒማ ዲ መርካቶ (የዛሬው ራስ ቴያትር ነው)፣ ሲኒማ ዲፖላቮሮ (የተግባረ ዕድ ት/ቤት የፊት ለፊቱ ህንፃ ወስጥ) እና በድሬዳዋ ሲኒማ አምፒርና ሲኒማ ማጀስቲ የተባሉትን፤ በሐረር ሲኒማ ዲ ሮማን፣ በጅማና በጎንደር እንዲሁም በደሴ ሲኒማ ቤቶችን የወራሪ ኢጣሊያን ሹማምንትና ዜጎቻቸው ከፍተው ነበር (የፊልም ማዳበሪያና መቆጣጠሪያ ዋና ክፍል፣ ገጽ 4-7)፡፡

10552353 10154062824714587 6353150256003906190 n

በነገራችን ላይ ብሄራዊ ቴአትር የተሰራበት ቦታ ሲኒማ ማርኮኒ ነበር ፤፤ ሲኒማ ማርኮኒ ምን መልክ እንደነበረው ምስሉ ያላችሁ ባካችሁ ጠቆም ብታደርጉን ፤፤፡የቲያትር ቤቱን ግንባታ የጀመሩት ጣልያኖች ሲሆኑ በወቅቱ ጣልያኖች ግንባታውን ያስጀመሩት ለሲኒማነት ሲሆን መጠርያውም ሲኒማ ማርኮኒ ብለውት ነበር ፤፤ 350 መቀመጫዎችን እንዲኖረው የታሰበ ነበር፤፤ ሆኖም ጣልያኖች ግንባታውን ሳያጠናቅቁ በመውጣታቸው ለአመታት በጅምር ከቆየ በኃላ 25ኛውን የቀዳማዊ ኃይለሥላሴን የዘውድ በአል ለማክበር በማሰብ የመቀመጫውን ቁጥር ወደ 1260 ከፍ በማድረግ የተቋረጠው ግንባታ ተጀምሮ በ1948 ዓ.ም ተጠናቀቀ፡፡