ብጹዕ ቅዱሰ አቡነ ማቲያስ የትንሳኤ በዓልን በማስመልከት ቃለ ቡራኬ ሰጥተዋል

abune mathias 1 300x200 1 ብጹዕ ቅዱሰ አቡነ ማቲያስ የትንሳኤ በዓልን በማስመልከት ቃለ ቡራኬ ሰጥተዋልምዕመናን የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ አክብረው በየቤታቸው በመሆን እንዲጸልዩ ቤተ ክርስቲያኗ አሳሰበች፡፡
ምእመናን በቤታችው ሆነው በመጸለይ የኮሮና ወረርሽኝን እንዲከላከሉ ቅዱስ ሲኖዱሱ ያሳለፈውን ውሳኔ በመተገበር የትናሳኤ በዓል መከበር እንዳለበት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያሪክ ብጹዕ ቅዱሰ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ አሳስቡ፡፡ ምዕመናን በመጸለይና የተቸገሩትን በማገዝ በዓሉን ሊያከብሩ እንደሚገገባም መክረዋል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያሪክ ብጹዕ ቅዱሰ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የትንሳኤ በዓልን በማስመልከት ቃለ ቡራኬ ሰጥተዋል፡፡ በቡራኬያቸውም ‘‘ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሲል የከፈለውን መሰዋእትነት በሕመሙ ለሰው ልጆች ሁሉ ቤዛ ሆነ’’ ሲሉ አውስተዋል፡፡
ብፁዕነታቸው ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋ የታመሙትን በማዳን፣ በሐጢአት የሞቱትን ይቅር ያለበት፣ በሞት እና በመቃብር የተያዙትን ከሞት ያስነሳበት፣ ፍጹም አዳኝነቱን ለዓለም ያሳወቀበት እና ለሰው ልጆች ሲል መዳን መሰዋዕት የከፈለበት ወይም መከራ የተቀበለበት ዕለት ነው’’ ሲሉም በዓለ ስቅለትን ገልጸዋል፡፡
በእግዚአብሔር የተሰጡ ሕጎች ሙሉ ዓላማቸው ሰውን ለማዳን ነው ያሉ ፓትሪያሪኩ ‘‘ምእመናን ማስተዋል ይገባቸዋል’’ ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያ የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል ቅዱስ ሲኖዶሱ ያስተላለፈውን ውሳኔ ምእመናን በቤታው ሆነው በመጸለይ እንዲያከብሩም አሳስበዋል፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.