በአሜሪካ ቢያንስ 100 ኢትዮጵያውያን በኮሮናቫይረስ ሞተዋል ተባለ

areagaበአሜሪካ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ከ100 ያላነሱ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውን መሞታቸውን በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ ተናገሩ።

አምባሳደር ፍጹም ለአሜሪካ ድምጽ ሲናገሩ፤ “ቁጥሩን በትክክል ማስቀመጥ አስቸጋሪ ነው። ከምናገኛቸው መረጃዎችን እስካሁን ከ100 ያላሱ ህይወታቸውን እንዳጡ እየሰማን ነው” ብለዋል።

አምባሳደሩ ጨምረውም፤ የሟቾች አስክሬን ወደ ኢትዮጵያ መላክ እንደማይቻል ጠቁመዋል።

“ዲፕሎማቲክ በሆነ መንገድ የነገሩን [የአሜሪካ መንግሥት] አስክሬን የማውጣት ሃሳብ በመንግሥት ደረጃ እንደሌላቸው ነው” ብለዋል።

ይህም ለሁሉም ጥንቃቄ ሲባል የተደረገ እንደሆነ አምባሳደሩ አስረድተዋል።

አምባሳደር ፍጹም ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውን በኮሮናቫይረስ ተይዘው በቤት እና በጤና ተቋማት ውስጥ እንደሚገኙም ጠቅሰዋል።

httpsbc.in/2RIg0Iw

1 Comment

  1. Forget the Los Angeles Ethiopian embassy broken Booth/office.

    Ethiopian in California says We are with you ambassador in Washington District of Columbia the Ethiopian real embassy.

    Ethiopia give permission the remains go to America from Ethiopia.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.