ምእመናን ቅዱስ ቁርባን አይቀበሉ የሚለው የብሄራዊ ግብረ ኃይሉ ውሳኔ ፍትሐዊነት የሌለውና የቤተክርስቲያኒቱን ሕልውና አደጋ ላይ የሚጥል ነው

ሁለት ወር ሙሉ ሲፆሙ የቆዩ ምእመናን ቅዱስ ቁርባን አይቀበሉ የሚለው የብሄራዊ ግብረ ኃይሉ ውሳኔ ፍትሐዊነት የሌለውና የቤተክርስቲያኒቱን ሕልውና አደጋ ላይ የሚጥል ከመሆኑ በተጨማሪ ከምእመናን ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን በመቀስቀስ ወደ አላስፈላጊ ግጭት የሚከት ሆኖ ስላገኘነው በ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ

93111691 649642045858901 5593652135137902592 o ምእመናን ቅዱስ ቁርባን አይቀበሉ የሚለው የብሄራዊ ግብረ ኃይሉ ውሳኔ ፍትሐዊነት የሌለውና የቤተክርስቲያኒቱን ሕልውና አደጋ ላይ የሚጥል ነው

3 Comments

  1. እኔ ኦርቶዶክስ ነኝ እንደተለመደው በእምነቱ ቀኖና መሰረት ቢከበር ደስ ይለኛል ነገር ግን በዓለም ላይ የሰው ልጅ እንደቅጠል እየረገፈ እያየንና እየሰማን ለሁለት ቀን ይፈቀድልን ማለት ከሥጋው ጾመኛ ነኝ ከመረቁ ስጡኝ አይነት ነገር ነው ። ሌላው ሰው የጥንቃቄ መመሪያውን አላከበረምና እኛም እንጣሰው ማለቱም ከአባቶች የሚጠበቅ አልመሰለኝም ። ወደፊት እናደርጋለን አሁን ግን ርብርቡ ከኮቪድ 19 ጋር ቢቻ ይሁን ፈጣሪ አምላክ መልካም አውዳመት ያርግልን ።

    • ለ አንድ ቀን መንፈሳዊ ደስታ ዘለዓለማዊ በሽታ ሽመታ ወይም ሞት ማለት ይህ ነው። በ እኔ ግምት ይህ ተግዳሮት እግዚአብሔርን መፈታተን ነው። በ ቅርቡ አሜሪካ ውስጥ አንድ የ ባፕቲስት ቄስ እግዚአብሔር ከዚህ ወረርሽኝ ይጠብቀናል ብሎ ምዕመናኑን ሰብስቦ በ ሰበከ በ ሳምንቱ በ በሽታው ታሞ ሞቷል። ስለዚህ ህግን አክብሮ በ ቴሌቪዥን ሥነ ሥርዓቱን መከታተል ኃላፊነትን መወጣት ነው። እግዚአብሔር ልብን ያያል። በተለይ ከ ፀሎተ ሐሙስ እስከ ትንሣኤ ለሚጾሙ ሰዎች ሥጋ ወደሙን በ ዕለቱ አለመቀበል እጅግ ቅር ያሰኛል። ነገር ግን የ ህይወት ጉዳይ ነውና መቀበል ያስፈልጋል። መልካም የ ትንሣኤ በዓል ይሁንልን። ይህን ወረርሽኝም ያጥፋልን። አሜን!

  2. እኔ መጣም የማጠብቅ ኦርቶዶክስ ነኝ።ቢሆንም ፓትርያሪክ በደብዳቤ ለሁልት ቀን ለቁርባን ለምዕመናን ይፈቀድልን ብለው መጠየቃቸውን በጣም አድርጌ እቃወማለሁ፡፡ ምክንያቱም በአቁራቢ ከህናት እና በቆራቢ ምዕመናን መሀከል የ6 ጫማ እርቀት ከቶውን የለም፡፡ የቤተ ክርሥቲያን ምስጢር በመሆን እዚህ ላይ አይነገርም እንጂ በማቁረብ እና በመቁረብ እርገድ እጂግ በጣም መከናወን ያለበት ተግባሮች አሉ፡፡ ፓትርያሪኩም ሆኑ ረዳቶቻቸው እያወቁ በደብዳቤ መንግሥትን መጠየቅ በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች እና በመንግሥት መካከል ችግር ለመፍጠር ይመሥላል፡፡እንዲሁም የፓትርያሪኩ እና ረዳቶቻቸውን የዕውቀት ሚዛን ያስገምታል፡፡ ይሕን ከማልት እና ከመጠየቅ ይልቅ ንግሥተ ነገስት ነኝ እህተ ማርያም ነኝ እያለች የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትን እየበከለች ያለችውን መሥመር ማስያዙ አይቀልምን? ሥራችው ያሣዝናል፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.