አንዳንድ ሰዎች የዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ጉዳይ የሀገር ጉዳይ ነው ይሉናል – ጌታቸው ሽፈራው

93543731 3386606288035013 5516875866690289664 n አንዳንድ ሰዎች የዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ጉዳይ የሀገር ጉዳይ ነው ይሉናል  ጌታቸው ሽፈራውአንዳንድ ሰዎች የዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ጉዳይ የሀገር ጉዳይ አድርገው ሊከራከሩ ይሞክራሉ፣ ይህን ሰው የሚተቸውን ሀገር የሚጠላ ለማስመሰል ይጥራሉ። ስህተት ነው። የሀገር ገፅታ ቅብጥርጥስ የሚባለው ትህነግ/ሕወሓት ሲያደነቁረን የኖረው የተለመደ ሙዚቃ ነው። የሀገር ገፅታ እያሉ እያደነቆሩን ክብሯን ሲንዱት ነው የኖሩት።

ቴዎድሮስ የዓለም ጤና ድርጅት ላይ የተወዳደረው ለራሱ ብሎ እንጅ ለኢትዮጵያውያን ብሎ አይደለም። “እኔም ወያኔ ነኝ” እያለ የሚፎክርለት ድርጅቱ “ወያኔም” ሆነ፣ የጤና ጥበቃ እያለ ብዙዎች እንዲመክኑ ያደረገው ቴዎድሮስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አስቦ የዓለም ጤና ድርጅትን አልተቀላቀለም። አሁንም ለኢትዮጵያ የህክምና ባለሙያዎችም ሆነ ለዜጎች የዓለም ጤና ድርጅት በኮንጎ፣ በአውስትራሊያ፣ በችሊም ሰው ተያዞ ከምናገኘው የተለየ ጥቅም አይሰጠንም። እንደ ሰሞኑ ደካማ መከራከሪያማ ቴዎድሮስ ብቻ ሳይሆን፣ የጭራቆቹ አለቃ መለስ ዜናዊ በዚህ ዘመን ኖሮ የሆነ ዓለም አቀፍ ድርጅት አለቃ ቢሆንም ከጎኑ ሁኑ ልንባል ነበር። ዋናው ጉዳይ የቀበሌ፣ የክልል፣ ዓለም አቀፍ ስልጣን ጉዳይ አይደለም። ዋናው ጉዳይ ስብዕናቸው ነው፣ ሕዝባችን ላይ የፈፀሙት ነውር ነው።

በማንነቴ ተሰደብኩ የሚለውም ብዙም የሚያስኬድ አይደለም። የቴዎድሮስ ወያኔ ዜጎችን በማንነታቸው ሲያሸማቅቃቸው፣ ለይቶ ሲገድልና ሲያሰቃይ ነው የኖረው። በዚህ ዘመን በማንነት በማጥቃት የእነ ቴዎድሮስን ድርጅት ያህል አረመኔ የለም! የዘር አጥፊው ወያነ አባል ቴዎድሮስ አድሃኖም የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ መሆን የአባቶቻቸው ፋሽስትነት ከሚያሳፍራቸው የዛሬዎቹ ጣሊያኖች፣ ጀርመኖች፣ ጃፓኖች ሊሻለን አይችልም። በተለይ ተለይቶ፣ በሰነድ ሲጠቃ ለኖረ ሕዝብ። እንዲያውም ቴዎድሮስ በሰራው መጥፎ ስራ ሲተች፣ የዓለም ጤና ድርጅትም ሆነ የወያነ አባል ሆኖ ያልጠቀማትን ኢትዮጵያን በክፉ ሲያስነሳ ነው የኖረው።

ይልቁንስ፣ ይህን እድል ተጠቅሞ የሚፎክርለት ድርጅትም ሆነ ራሱ ኢትዮጵያ ውስጥ የፈፀመውን ወንጀል ለማጋለጥ መጣር ነው። በተለይ በውጭ ያላችሁ ወገኖች ይህን እድል ተጠቀሙበት። ከጎኑ እንቁም ሲባል ከመቃወምም ባሻገር የሰራውን መጥፎ ስራ እንዲገለጥ በማድረግ ተደናግረው ከጎኑ እንቆማለን ያሉትን ማስተማር፣ ፈልገው ከጎኑ እንቁም የሚሉትን ማሳፈር ተገቢ ነው። (ሆን ተብሎ እንዲመክኑ የተደረጉ ሰዎችን አድራሻ ማቅረብ እንችላለን።)

እሱ ስልጣን ላይ ላቆየቻቸው ቻይና እንዲህ ሲንበረከክ እኛም ሲገዙን፣ ሕዝባችን ሲያመክኑ ለነበሩት ጠባሳውንና ማንነታቸውን ረስተን ልናሽቃብጥ ግዴታችን አይደለም። ግዴታችን እነዚህን አረመኔዎች በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ማጋለጥ ነው! እደግመዋለሁ፣ ቴዎድሮስ አድሃኖም ከቻይናውና ከወያኔው ጋር እንጦረጦስ ቢወርድ በማንነቱ የተጠቃ፣ እንዳይወልድ የተደረገ ሕዝብ ታላቅነቱ ይዞት “እሰይ” ባይል እንኳ የተፈፀመበት በደል ከጎኑ አያስቆመውም!

10 Comments

 1. Look at that ባንዳ mentality, የፈረንጅ ውሻ እንኳን ጌታውን ሲያይ ይሄን ያህል ጭራውን አይቆላም..!

  ወደታች ደግሞ ሌላኛውን ሲበድል እና ሲሰርቅ የዚያኑ ያህል ነው::

 2. አቶ ጌታቸው ሽፈራው እግዚአብሔር ይባርክህ እነትህን ነው ሕዝባችን በኮሌሪያ ሲያልቅ አተት ነው እያለ ሲቀልድ ነበር ። በቀላሉ በመድሃኒት መዳን የሚችሉ ወገኖቻችን በወባ ሲያልቁ ሴት እህቶቻችን ዘር እንዳያፈሩ ክትባት እየሰጠ ያመከናቸው እንዴት ይረሳል ? ለዓለም የጤና ድርጅት እንዳይመረጥ ያደረግነውን ተቃውሞ ጆሮ ዳባ ልበስ ያሉ ዛሬ ኮቪድ 19 ያመጣውን ችግር መወጣት ያልቻሉ የአሜሪካው ፕሬዝዴንት ድክመታቸውን የሚሸፍን የጭዳ ዶሮ ሲያደርጉት ትናንትና ያሰቃየውን ሕዝብ መሸሸጊያ ሊያደርግ ቢፈልግ ስራህ ያውጣህ ነው የምንለው ። ሀጢአቱን ላልተናዘዘ ሰይጣን ማዘን በምንም መልኩ ለአገር ገጽታ መቆርቆር ሊሆን አይችል ። ዘረኛ የሆነ ግለሰብ የዘር ጥቃት ደረሰብኝ ሊል የሞራል ልዕልና የለውም ። በለመደው ቅጥፈት ጥቁሩን ሕዝብ ከጎኑ ለማሰለፍና ስልጣኑን ላለማጣት የሚያደርገው ሌብነት ነው ።

  የኢትዮጵያ አምላክ የስራቸውን ይስጣቸው

 3. የቴድሮስ አድሃኖም ጉዳይ ስሜትን ለማርኪያ ድረገጽ ላይ ተጯጩኸዉ የሚተዉት ጉዳይ አይደለም የኢትዮጵያ አምላክ አምበሳ መንጋጋ ዉስጥ ከቶታል ኢትዮጵያዊ ነኝ ምሁር ነኝ የሚል ችሎታዉን የሚያሳይበት ጊዜ ነዉ ለሰብአዊነት ሲባል።
  ጉዳዩ ቀላል ነዉ ምሆራን ከቢሮዋቸዉ ተጠራርተዉ እድሜ ለዶ/ር አሰፋ ነጋሺ በቂ ሰነድ አለ ያንን አያይዘዉ ለምእራብ ኤምባሲዎች በኢሜል በሰነድ ነገሩ ሳይበርድ መላክ ነዉ። ይህ በገዛ ህዝቡ ላይ ይህን የሚፈጽም ሌላዉ ያስባል ብሎ ማሰብ ቀልድ ነገር ነዉ እሱ የሚያስበዉ በገፍ አለአቅሙና ችሎታዉ የሚሰጠዉን ደሞዝ ነዉ። እሱ ብቻ አይደለም ሌላዉ አራጂ ሰየ አብረሀ ትልቅ ሰብአዊነት በሚጠይቀዉ በተባበሩት መንግስታት ቢሮ በትግሬዎች ጥልፍልፍ አሰራር ተቀምጦ ከተጠያቂነት ሊያልፍ ትንሽ ሰለቀረዉ ሰለሱም ስለፈጃቸዉ ኢትዮጵያን ታሪኩን አያይዞ ለቦታዉ አለመመጠኑን ለአለቆቹ ማሳወቅ ነዉ።፡የእዉነት ቀን መምጣቱ አይቀርም ከሌሎች ወንጀለኞች ጋር እጁ በእግረ ሙቅ እንደሚገባ ጥርጥር የለንም።
  ጸሀፊዉ ይህ የተለሳለሰ ጅምርህ ነዉ ይህ ነገር ለያዝከዉ ሙያ ትልቅ ሪሶርስ ስለሆነ አትልቀቀዉ ብዙ ወንጀለኞችን አጋልጥበት በየቦታዉ የቆመዉ የነሀጎስ ሀዉልት ከየት መጥቶ ተሰራ ደሞዝተኛዉ ጻድቃን ገ/ተንሳይ ከየት አምጥቶ በወር 5000 ዶላር የሚያወጣ ቤት ሰራ? ነቃ በሉ እንጂ ጋዜጠኞች።

 4. You stupid nonsense. He is Ethiopian hero.
  Do you know Koffi Anann? He was from Gana but he was African and black too. Tewdrose is the same; he is Ethiopan and african all Africans are proud of him; exept you stupid NONSENSE Negro.
  Nobody is expecteing from you and your fellow positive things. All of you are jealous. Tewdrose is a “HERO!!”for all Africans.You Think with your “Stomach.”
  Fucccck……

  • You low IQ TPLFite. You guys do not know even how to humbly address your opinion. I do not know why you people resort to violence, hate and character assassination. Everybody has the right to say whatever she/he wants about Adhanom. The fact is Adhanom is a liar, incompetent, criminal TPLFite. No way to get sympathy in the name of being black. Look at how he greets Chineses`s dictator; he lacks self-respect. In fact
   China is the master of TPLF.

   • ኣይተ መሰረት፣

    They have never been productive, they were always a ዝቃጭ፣ ለዚህም ነው እረኛ ተጠራርቶ በመሰባሰብ ከስልጣን አባሮ በቀላሉ ካረንቴና ውስጥ የከተታቸው፣ ይሄንን ስል ግን የቄሮን productive ተግባራትን ዝቅ ዝቅ ማድረግ መስሎ አይታይብኝ….!

 5. The World was prewarned that Dr. Teodros Adhanom is not the right person to leadd the WHO. Even though he is incomptetent and corrupt, the expensive investment of the TPLF in the western and other lobbysist groups faciliated his acsent to this top international position. The TPLF has close ties to China and vested interest with the country. China threw its weight behind the capiagn to elect Dr.Teodros. The corruption culture and incomptence of the TPLF has made its way into the WHO and crippled it. Dr. Teodros should resign with honour and dignity. Failing this,the world should force him out of this office. Africans should not be deceived by Dr. Teodros`claims of racism against him.

 6. Thank you Getachew. As a man who hate TPLF from the bottom of his heart I support your assessment of Dr Theodros 100%. Unfortunately, I am here to share you different perspective or a secret why he became the first non-doctor leader of WHO. Believe or not the post requires a cruel leader who can protect the interest of the elites and big pharma. There are plenty of records that Bill Gates and big pharma have the biggest and the only investment on mandatory vaccine projects for more than 76 nations (non western). In stead of boosting natural immunity through healthy eating, using anti microbial vitamins and supplements (such as high dose of vitamin C, Vitamin D and Zinc) they intentionally promote to make vaccine mandate/mandatory for their biggest investment as Bill Gates declared a week a go. To materialized his investment TPLF leaders have the best merciless credentials. In order to verify what I am taking about please visit the following links.

  % years ago bill gates predicted there will be a huge viral threat for the world. People view this Gates financed the creation of COVID for the Chinese (Wuhan institute of Virology) to profit from the vaccine that has been patented to Melinda and Bill Gates foundation THE NEXT OUTBREAK (26 million viewers)
  Bill and Melinf=da Gates foundation conducted event 201 a conference of outbreak readiness a couple of monts ahead of COVID outbreak in china

  Please listen the analysis of an MIT Dr Shiva on the outbreak (7 million viewers)

 7. United Nations › cct
  UN Counter-Terrorism Centre (UNCCT) | Office of Counter-Terrorism should investigate Teodros Adanhom Ghebreyesus and his history with the TPLF for the last three or four decades , after doing that the recent scandal will not surprise anyone.

 8. History bears witness that Dr. Teodros Adanhom Ghebreyesus’s political party the EPRDF had won majority of the votes at every governmenral elections in Ethiopia for close to three decades continuously until now, which is proof enough for everyone that Dr. Teodros Adanhom Ghebreyesus was and still is very well liked by almost all Ethiopians regardless what few jealous Ethiopian people say about him , Dr. Ghebreyesus only left the Ethiopian politics for the time being because he knew he can contribute better to the world if he joined W.H.O. , besides that he is confident he can run for the PM’s office of Ethiopia if he chooses to with EPRDF winning sweeping votes when he comes back to the Ethiopian politics,sooner or later the resilient EPRDF will be EPRDF once again just like before once Dr. Teodros A. Ghebreyesus returns back to the Ethiopian politics since he is tested by fire and percivered with his long time comrades such as the late World Class leader his Excellency the late PM of Ethiopia Dr. Meles Zenawi Asres who lifted most Ethiopians out of poverty in a very short period of time while bringing equality , justice , democracy and freedom to Ethiopia for the first time in the Ethiopian history.EPRDF has full authority to hold the election as scheduled in August 2020 if Dr. Teodros Adanhom Ghebreyesus chooses to return back to the Ethiopian politics before then.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.