ኪራይና መስፍን – ፕሮፌሶር   መስፍን ወልደ ማርያም

mesfinፕሮፌሶር   መስፍን ወልደ ማርያም
ሚያዝያ 2012

ሰሞኑን ስሜን ከቤት ኪራይ ጋር አንሥተው ነበር፤ እርግጥ ቤት የለኝም፤ ነገር ግን አግዚአብሔር ይመስገን አልተጎዳሁም፤ ልጆች የሚባሉት አድገው ራሳቸውን ችለዋል፤ ብርግጥም ጡረታዬ በዛሬው ጊዜ አያኖርም፤ በዚህም በኩል እግዚአብሔር ይመስገንና ጥቂት ሰዎች ሥራቸው አድርገውት በሚያስፈልገኝ ነገር ሁሉ ይረዱኛል፤ የእነዚህ ሰዎች ውለታ በጣም ይከብደኛል፤ እግዚአብሔር ጤንነትና ዕድሜ፣ ሰላምና በረከቱን ይስጣቸው፤ የቤት ኪራዬንም ደርግ ምስጋና ይድረሰውና ጎምዶልኛል፤ ለሁላችንም ማለቴ ነው፤ እነዚህ አሥር የማይሞሉ ሰዎች ባይኖሩ ምን እንደሚደርስብኝና የት እንደምወድቅ አላውቅም፤ ስደትን ግን ጭራሽ አላስበውም! እኔን የሚያሳዝኑኝ ግን የኔን ዕድል ያላገኙ ስንትና ስንት ኢትዮጵያን ያገለገሉ ሰዎች በችግር ሲቆሉ ሳይ ነው፤ የምንችል ሰዎች በወር አንድ ብር ብናዋጣ ብዙ ሰዎችን መርዳት እንችል ነበር፡፡

በቤት ኪራይ በኩል ያለውን ሙስና ሲያስቡት ያንገሸግሻል! ቤታቸውን በብዙ መቶ ሺዎች ብር እያከራዩ በመንግሥት ዝቅተኛ ኪራይ የሚከፍሉና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ቆመናል የሚሉ ሞልተዋል፤ አይከነክናቸውም፤ ስንቱ ዳያስፖራ በብዙ ሺህ ብር እያከራየ እዚያ ደግሞ እንደደሀ በምጽዋት ይኖራል፤ የባሰም አለ፤ ሌላ ቀርቶ የኢጣልያን ባንዳዎችም እንደምንረዳ አውቃለሁ፤ የቱ ባለሥልጣን ነው ይህንን የሙስና ምንጭ በሰይፍና በሕግ ሊያጠፋው የሚችል?

 

7 Comments

 1. ፕ/ር መስፍን፣
  ለ ንጉሡ መውደቅ የተጫወቱትን ትልቅ ሚና እረሱት እንዴ? የመርማሪ ኮሚሽን ሊቀመንበርስ ሆነው እነዚያን ንጹሐን ሚኒስትሮች ያሰቃዩዋቸው ተረሳዎት?
  ደርግን ተቀባይነት እንዲያገኝና ያን ሁሉ ጥፋት እንዲያደርግ ሚና እንደነበርዎት የሚዘነጉት አይመስለኝም።
  የ ኢሰመጉ ሊቀመንበር ሆነው ሳሉ የሚያኮራ ሥራ ቢሠሩም ለ አገራችን ውድቀት ከ ተጠያቂ ሰዎች አንዱ ነዎት። አሁን ላለው ምስቅልቅልም እንዲሁ።
  በ ሙስና ሳይጨማለቁ በ መኖርዎ ግን አደንቅዎታለሁ።
  ጤና ይስጥዎት።

  • Zewdu Gebre-Hiwet Inameseginalen

   Gud gud gud Ere mech awqen mech tenegron wetat lijoch.
   Wana meseri silsa ministerrochun yasgedele neww leka, teqelbso sebeawi mebt askebari yehonew bewoyane zemen. Profesoru sewye mesfin news leka lesilsawochu ministeroch gidiya astebabari yih teqelebabash professor baschekuway tekeso lefird yiqrebilin degmo degmo sayiqelbabeis. Demo ersun bilo sebawi mebt tekerakarii , At yewoyane tenkol silsa yereferwfewun tekeraker bilo asqemto referefen

   Gud gud gud leka Mesfin Woldemariam yeQelbesa Negewo teqelbash neww.

 2. Indeed you are lucky to be alive when considering your unforgettable crime of prosecuting PM Aklilu Habte.
  Please be remorseful and repent.

 3. ሙስና የትናንሽ ሰዎች መገለጫ ነው። ሙሰኛ ማለት ሌባ ማለት ነው። እንግዲህ ከ10ቱ ትዕዛዛት ውስጥ አንዱ አትስረቅ ነው። ሌብነት ከሞራልም ይሁን ከሃይማኖት ተቀባይነት የሌለው ነገር ነው።

 4. Professor Mesfin is an exeplary to the so called scholars.The beloved Professor shoud’t give a damn to shabby ideas. Long live professor.I love U to the bottom of my heart. I never gorget the books and articles U wrote so far. Long live the HERO.

 5. Prof. Mesfin is an extraordinary person who is irreplaceable citizen of our country. Dear prof. We’re thankful for your valuable and immense contributions in several disciplines. I wish you peace and to live a healthier long life to see the rebirth of a unified and thriving Ethiopia.

 6. መስፍኔ!! ኣለህ እንዴ?? እኔ ደግሞ፣ ያለፍክ መስሎኝ ነበር። መቼ ነው ሞት የሚጠራህ? የህዝባችን በሽታና ዘረኛ እኮ ነህ!! እባክህ በቶሎ ሙት!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.