“ቀባሪ አታሳጣኝ”!  (በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ፣ ውዶቻቸውን በክብር ለመሸኘት ላልቻሉ ሁሉ)

456

ይገርመኝ ነበረ፣ ያገሬ ሰው ምኞት፤ ፈጣሪን ልመና፣
“ቀባሪ አታሳጣኝ” ሲለው እሰማና..፤

ባለማወቅ “እውቀት” ከንቱ ስፈላሰፍ፣
መሬት ያለን ትቼ ዓየር ላይ ስንሳፈፍ..፣
‘ፍጡር ካለቀለት ከሞተ በኋላ፣
ምንስ ይገደዋል? ለቀባሪ መላ..፣’
እያልኩኝ ሳጣጥል፣ ታላቁን ቁምነገር፣
አሁን ገና ገባኝ ዓለም ስትቸገር።

እያለ በቁሙ ለሞቱ እሚመኘው፣
“ቀባሪ አታሳጣኝ” ብሎ እሚለምነው፣
ለካስ ለቀሪው ነው! ለዘመድ አዝማድ ነው።

ሰው እንዳላስቸግር፣ መሬት እንዳትጠበኝ፣
አቤቱ አምላኬ! ቀባሪ አታሳጣኝ!

ጌታቸው አበራ
ሚያዚያ 2012 ዓ/ም
(አፕሪል 2020)

ተጨማሪ ያንብቡ:  አብርሃ ደስታ ሃብታሙ አያሌዉና እና ኤርትራ ( ግርማ ካሳ)

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.