ኢትዮጵያ በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚደረገዉን ጥረት ለማሳለጥ ተመረጠች

93375320 10217216776113262 2036037484416073728 nየዓለም የጤና ድርጅት ለ50 የአፍሪካ ሀገራት የሚውል የመከላከያ ግብዓቶች እና መድሃኒቶችን ያበረከተ ሲሆን ይህን ግብዓት የምታከፋፍለው ኢትዮጵያ እንድትሆን ተመርጣለች፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንግድ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የተሻለ ብቃት እና አቅም ያለው በመሆኑ ይህን ተግባር እንዲያሳልጥም ተመርጧል፡፡

ከዚህ ቀደም ከጃክ ማ ፋዉንዴሽን ለ54 የአፍሪካ ሀገራት የተበረከረተዉን የግብዓት አቅርቦት ኢትዮጵያ ማከፋፈሏ የሚታወቅ ነው፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ በዓመት ከ1 ሚሊዮን ቶን በላይ እቃ የማከማቸት አቅም ያለው ሲሆን አሁን በዓለም የጤና ድርጅት በኩል የተበረከተዉን ከ30ሺህ ቶን በላይ የግብዓት አቅርቦት ለ50 የአፍሪካ ሀገራት ያከፋፍላል፡፡

በኢትዮጵያ የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቦሬይማ ሳምቦ (ዶ/ር) እንደገለፁት ኢትዮጵያ በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስን ወረርሽኝ ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ውስጥ ከፍተኛ ሚና የምትጫወት ሀገር ነች ብለዋል፡፡

ለዚህም የሃገሪቱን መንግስት እየመሩ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ሊመሰገኑ ይገባል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ይህን ግብዓት በማከፋፈልም ከ10 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ እንደሚታገኝም ተነግሯል፡፡

በቀጣይም በአፍሪካ አህጉር የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ እንደሚሰሩ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር በኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

(በሚልኪያስ አዱኛ)

1 Comment

 1. France 24
  ‘If you’re black you can’t go out’: Africans in China face racism in Covid …

  CNN.com › 2020/04/13 › asia
  Web results
  Beijing faces a diplomatic crisis after reports of mistreatment of Africans in China…

  France 24
  McDonald’s apologises after China store bans black people

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.