በአዲስ አበባ ዝርፊያና ስርቆት ተበራክቷል

Addis Ababa
 “በዚህ ወቅት እንዲህ አይነቱን ድርጊት የሚፈጽሙ አካላትን ከወረርሽኙ ለይቶ ስለማይመለከት ጠበቅ ያለ እርምጃ ይወሰዳል” የአዲስ አበባ ፓሊስ ምሽት ሁለት ሰአት ሆኗል።በርካቶች እንደሰሞኑ ልማድ ወደየቤታቸው ገብተዋል።ስራ ያስመሻቸውና ጉዳይ የያዛቸው አንዳንዶች ደግሞ በሀሳብ ተጠምደው እየተጓዙ ነው።ልማደኞቹ አድፋጮች ዛሬም ዓላማቸውን አልሳቱም።ካሰቡት ጥግ መሽገው አድፍጠዋል። የእግር ኮቴ እያዳመጡ ብቅ የሚል መንገደኛን ይናፍቃሉ ። ጋዜጠኛ አዲሱ ገረመው ከሰድስት ኪሎ አፍንጮ በር ተነስቶ ወደራስ መኮንን ድልድይ የሚወስደውን መንገድ በመያዝ ወደቤቱ ጉዞ ጀምሯል።መኖሪያው በተለምዶ ሰባና አርባ ደረጃዎች ከሚባሉት አካባቢዎች መሀል ላይ ይገኛል ።
አዲሱ ይህን ሰፈር ለዓመታት ኖሮበታልና አሳምሮ ያውቀዋል።አካባቢው ከጥበቃ የተገለለና በቂ የመብራት ብርሀን ባይኖርበትም ከስጋት ላይ ጥሎት አያውቅም። አዲሱ ወደ ቤቱ መንገዱን ቀጥሏል።ድንገት ኮቴ የሰማ ቢመስለው ግን ፊቱን ዞር አድርጎ ለማየት ሞከረ።ወዲያው ከየት መጡ ያላላቸው አራት ሰዎች እሱ ካለበት ደረሱ ።ከነዚህ መሀል አንደኛው ፈጣንና ከበድ ያለ ቦክስ ከቀኝ ዓይኑ ላይ አሳረፈበት።በዚህ ብቻ አልቆመም ። ሌላው ባልንጀራው በላዩ ተጠምጥሞ የሚያቃጥል ፈሻሽ ዓይኑ ውስጥ ጨመረበት ።
አዲሱ እይታው ጨለመበት። ትግሉ ቀጠለ።በፈሳሹና በቦክስ ምቱ ስቃዩ የበረታበት መንገደኛ የእርዳታ ጨኸት አሰማ።ብቅ ያለ የለም። አራቱ ሰዎች ኪሶቹን በየተራ ዳበሱ።እጆቻቸው ባዷቸውን አልተመለሱም።ውድ ዋጋ ያለውን ሳምሰንግ ሞባይል አወጡ፡፣ፍተሻውን ቀጠሉ።ከሌላው ኪስ ያገኙትን ከሶስት ሺህ ብር በላይ ወሰዱ።እየተፈራረቁ ግራ አጋቡት።እየታገሉ አቅም አሳጡት።ብቸኛው መንገደኛ ሊቋቋማቸው አልቻለም።ተባብረው ከመሬት ጣሉት።ይህኔ ዳግመኛ ጨኸት አሰማ ። አፉን አፍነው አንገቱን አንቀው ዝም ሊያሰኙት ሞከሩ።
አዲሱ እንደምንም ዓይኖቹን አላቆ አሻግሮ ተመለከተ።ወዲያው አርባ ደረጃ ስር ያለው ሱቅ ድርግም ብሎ ሲዘጋ አስተዋለ።በአካባቢው ካለ ህንጻ ጥበቃዎች እንዳሉ የሚያውቀው ወጣት አሁንም የድረሱልኝ ድምጽ አሰማ ።ይህን ያዩት ባለመኪኖቹ ዘራፊዎች አግሮቹን ይዘው አላላውሰ አሉት። ወደመኪናቸው ለማስገባትም ትግል ያዙት። ወዲያው አንድ መኪና መብራቱን አድምቆ ጡሩንባ እያሰማ ብቅ አለ።ይህኔ አራቱ ሰዎች የያዙትን ለቀው ወደየጥጋቸው ገለል አሉ።በዚህ መሀል አዲሱ ከወደቀበት ተነስቶ ወደመንደሮቹ ተጠጋ ።
ወዲያው ላገኛቸው ጉዳዩን አስረድቶም እርዳታቸውን ጠየቀ።ባለሱቁን ጨምሮ የሰሙት ሁሉ ሊተባበሩት አልፈቀዱም ።ይህን ያዩት ዘራፊዎች ከመሸጉበት ወጥተው እጃቸውን ወደአዲሱ ጠቖሙ ።ወዲያውም ሌባ! ሌባ! …ይሉት ጀመር። አዲሱ ከኋላው የሚያሳድዱትን አምልጦ ወደሌላ አቅጣጫ ተጠጋ።የሚያውቁት ሰዎች ስለመድረሳቸው ያዩት ዘራፊዎችም በፍጥነት ለሁለት ተከፍለው ወደቪትዟና ወደ አንድ ላዳ ታክሲ ገብተው አመለጡ።በሌሎች እገዛ ለመፍትሄ የተጓዙት እነአዲሱ በአካባቢው ፖሊስ ፍለጋ ባዘኑ።
ማንንም አላገኙም ።ርቀት ተጉዘው ጉዳዩን ከመንገድ ላገኗቸው ሁለት ፖሊሶች አስረዱ። አዲሱ በአካባቢው ያለስራ የተዘጋውን የፖሊስ ማዕከል አስታውሶ ስለምን ይህ ሆነ ሲል፡ ጠየቀ። በወቅቱ የተሰጠው ምላሽ ከፖሊሶቹ አላግባባውም።የአባላት ሀይል ቁጥር ስለመኖሩ ጭምር ተነገረውና በማግስቱ የሆነበትን ድርጊት ሁሉ ለሚመለከተው ክፍል ቀርቦ አስረዳ። ይህ ድርጊት ከተፈጸመ አስራአምስት ቀናት አለፉ።አዲሱ ጉዳዩን በቀላሉ ባይዘነጋውም የህይወቱን መትረፍ ከግምት አስገብቶና የጠፋበትን ስልክ በተመሳሳዩ ተክቶ መደበኛ ህይወቱን ቀጠለ።መጋቢት 30 ቀን 2012 ዓም ቀትር ላይ ግን ዳግመኛ እንዲህ ሆነ። ከቀኑ ሰባት ሰአት ሆኗል፡አዲሱ ከመኖሪያ ቤቱ ወደስራው ለመምጣት ስልክ እያወራ መንገዱን ጀምሯል። በድንገት እሱ ወዳለበት አቅጣጫ ያተኮሩ ሶስት ሰዎች ቪትዝ መኪናቸውን ቆም አድርገው አድራሻ ጠየቁት።አዲሱ አካባቢውን ስለሚያውቀው በቅንነት ሊያመላከታቸው ሞከረ።በዚህ መሀል ከኋለ የተቀመጠው አንደኛው ተሳፋሪ ድንገት መስኮቱን ከፍቶና አነጣጥሮ አዲሱ ላይ ተፋበት። አዲሱ መላ ሸሚዙን አዳርሶ ግማሽ አካሉ ላይ ያረፈውን የሰውየውን ነውር ባየ ጊዜ ውስጡ በእጅጉ ተጠየፈ።
ቆይቶ የታኘከ ለውዝ እንደነበር የተረዳውንና በወቅቱ ከሰውዬው አፍ የወጣውን ምናምንቴ ሲያስተውልም ውስጡ ክፉኛ ተናወጠ።ይህን አይነቱን ስሜት ይናፍቁ የነበሩት ሰዎችም ወዲያውኑ ቀጣዩን ዕቅድአስከተሉ። ሰዎቹ የአዲሱን ስሜት መቀየር እንዳዩ ከመኪናቸው ፈጥነው ወረዱና ተንከባከቡት።ስለድርጊቸው የበዛ ይቅርታ ጠይቀውም ልብሱን ለመጥረግ ተረባረቡ ።በዚህ መሀል ከኋላ የነበረውና ልብሱ ላይ የተፋበት ተሳፋሪ ውሀ በእጁ ይዞ ወደ አዲሱ ተጠጋ። ጎንነበስ ቀና ብሎም ሊያጥብለት ሞከረ።
ሌሎቹም ስልኩ እንዳይርስበት በሚል እያዋከቡ ወደኪሱ እንዲከተው ነገሩት። አዲሱ የሚሉትን ሁሉ ሆነላቸው። የሰዎቹን ትህትና ባየ ጊዜም ጉዳዩን በይቅርታ ተቀብሎ ጨዋታ ቢጤ ቀጠለ። የሚፈልጉትን ውስኪ ቤት በሰም ጠርተው ጠየቁት።አቅጣጫውን አመላክቶ አድራሻውን በአግባቡ ነገራቸው። ባለመኪኖቹ በተለየ ምስጋና ተሰናብተውት ከዓይኖቹ እንደራቁ የአዲሱ ልብ ደነጠ። ከዕንቅልፉ የመባነን ያህልም ፈጥኖ ነቃ።ወዲያው ተጣድፎ እጆቹን ወደኪሶቹ ሰደደ።ዓይኑን ማመን አልተቻለውም።ከቀናት በፊት በውድ ዋጋ ገዝቶ የተካው አዲሱ ሞባይል በቦታው የለም።ያልታሰበ ዱብዳ ሆነበት።
‹‹ጅብ ከሄደ ውሻ …›› የዘገየ መንቃት ነበር።በቀናት ልዩነት በቪትዝ መኪና የመጡ ዘራፊዎቹ ስልታቸውን ቀይረው ጉድ ሰርተውታል። በዚሁ ሰሞን ምሽት በሌላ ሰፈር ደግሞ በአቶ አሉላ አየለ ላይ ተመሳሳይ ወንጀል ተፈጸመ።አሉላ ከምሽቱ ሁለት ሰአት አካባቢ ከስራ ወደቤቱ ለማምራት መንገዱን ይዟል።በተለምዶ ሀያ አራት ከሚባለው አካባቢ ጀምሮ ሰፈሩ አስኪደርስ ድረሰ በቪትዝ መኪና ሲከተሉት የቆዩ ሰዎች እንደነበሩ ያስታውሳል።ወደ መኖሪያ መንደሩ ገርጂ አካባቢ ሲቃረብ ግን እነዚሁ ሰዎቹ ከነበሩበት መኪናወርደው ትግል ጀመሩት።
የዘራፊዎቹ አመጣጥ የያዘውን ላፕቶፕና የእጅ ስልኩን ለመውሰድ ቢሆንም ድርጊታቸው ከዚህም በላይ ነበር።የአሉላን አንገት ‹‹ሀንግ›› በሚባለው አይነት ስልት አንቀው ክፉኛ አንገላቱት።የያዘውን በእጃቸው አስኪያስገቡም ጭካኔ በተመላበት ሁኔታ አሰቃዩት።የአሉላና የዘራፊዎቹ ጥምር አቅም የተመጣጠነ አልሆነም።ያሻቸውን ፈጽመው በቪትዝ መኪናቸው ከአካባቢው ፈጥነው ተሰወሩ። ጋዜጠኛ አዲሱ እንደሚለው ሀገራችንን ጨምሮ መላው ዓለም በጋራ ሀሳብ በተወጠረበት በአሁኑ ጊዜ እንዲህ ዓይነቶቹ ነፍሰ በላዎች ስራቸውን ቀጥለዋል።
ትኩረት ሁሉ በአንድ ጉዳይ ላይ ማነጣጠሩም የጸጥታና የአካባቢ ደህንነት ጉዳዮችን ጨምሮ ሌሎች ሁነቶች ላይ ያለው አትኩሮት እንዲሳሳ ምክንያት እየፈጠረ ነው። አዎ! የዓለማችን ቋንቋና ቅኝት በአንድ የሀሳብ ገመድ በተቋጠረበት በአሁኑ ጊዜ ዓላማቸውን በጎዳና ዝርፊያ ላይ ያደረጉ ራሰ ወዳዶች እየፈጸሙት ያለው ወንጀል መቼውንም ቢሆን ታሪክና ትውልድ ይቅር የማይለው እውነታ ነው።
ሁሌም ቢሆን በስንዴ መሀል እንክርዳድ አይጠፋም።ዛሬ የሁላችንም ጉዳይ በአሳሳቢው የኮረና ቫይረስ ላይ አርፏል። አንዳንዴ ግን ውስጠታችን በዚሁ ችግር ብቻ እንዳይወረስ ልንነቃ ግድ ይለናል።ለራሳችን ዘብ በመቆምም ሌሎች ጉዳዮቻችን ላይ ጭምር ልናተኩር ይገባል። ክፍት ውሎ የሚያድር ቤት የሌቦችን ዓይን ይስባልና።
ጉዳዩን በተመለከተ ያነጋገርናቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ ወቅቱን እንደ አጋጣሚ ተጠቅመው የተለያዩ ወንጀሎችንና ዝርፊያ የሚፈጽሙ ሰዎችን ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ላይተው እንደማያዩወቸው ተናግረዋል። በመዲናዋ አጋጣሚውን ተጠቅመው የተለያዩ ወንጀሎችንና ዝርፊያ የሚፈጽሙ አካላት መኖራቸው ፖሊስ ተደጋጋሚ ጥቆማ እየደረሰው ነው ያሉት ኮማንደር ፋሲካ፣ ኮሚሽኑ በዚህ ወቅት እንዲህ አይነቱን ድርጊት የሚፈጽሙ አካላትን ከወረርሽኙ ለይቶ ስለማይመለከት ጠበቅ ያለ እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።
በሁሉም ቦታ የሚገኝ ፖሊስ ቀን ከሌት ነው የሚሰራው ያሉት ኮማንደር ፋሲካ፤ የተከሰተውን ወረርሽኝ እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው ዝርፊያንና መሰል ድርጊቶችን የሚፈጽሙ አካላት ላይ ተገቢው እርምጃ እንደሚወሰድ ጠቅሰዋል። ወንጀልን ለመከላከል በየአካባቢው ያሉት ጣቢያዎች የፖሊስ አባል ቁጥር ያንሰናል የሚል መልስ ለተጎጂዎች ማቅረባቸው ምክንያታዊ አለመሆኑንም ጠቁመዋል።
የወንጀል ሰለባ የሆኑ አካላትም ከአካባቢ ጣቢያዎች ባሻገር በየክፍለ ከተማው ላሉት የጸጥታ አካላት ማሳወቅ እንዳለባቸው ገልጸዋል። ማኅበረሰቡ ወንጀል ሲፈጸም በተለያዩ መንገዶች ጥቆማዎችን መስጠት እንዳለበትና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንም አፋጣኝ መረጃ ሲደርሰው ቁጥጥር እንደሚያደርግ ኮማንደር ፋሲካ አመላክተዋል። በአጠቃላይ መሰል ድርጊቶች ሲፈጸሙ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ብቻ ሳይሆን በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽንም ቁጥጥር እንደሚያደረግ ጠቁመዋል።
አዲስ ዘመን

4 Comments

 1. የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ መኖሩ ከተረጋገጠበት ከመጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ፣ በተለይ ሰዎች ይሰባሰቡባቸዋል ከተባሉት ውስጥ ከሺሻ ማስጨሻዎች፣ ከጫት መቃሚያዎችና ከመጠጥ ቤቶች ፖሊስ ከፍተኛ የሆነ ተግዳሮት እያጋጠመው በተለይ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችን በማስተማርና በማስገንዘብ የአዲስ አበባና ፌዴራል ፖሊስ ትልቅ ኃላፊነት ያለባቸው ቢሆንም፣ ፈታኝ ሁኔታዎች እያጋጠሙ መንግሥት መመርያ በማውጣት ሰዎች በብዛት የሚሰባሰቡባቸውን ቦታዎች ማለትም የሺሻ ማስጨሻ ቤቶች፣ የጫት ማስቃሚያዎችና የመጠጥ ቤቶች ለጊዜው ሥራ እንዲያቆሙ መደረጋቸው ነገር ግን ስለወረርሽኙ ግንዛቤ ያላቸውም ሆኑ የሌላቸው ሰዎች ሺሻ ሲያጨሱባቸውና ሲቅሙባቸው የነበሩ ቤቶች ከፊት ለፊቱ ‹‹ታሽጓል›› የሚል ማስጠንቀቂያ የተለጠፈባቸው ቢሆንም፣ እነሱ በኋላ በር በኩል ከፍተው በማስገባት እንዲያውም ከበፊቱ በበለጠ ብዙ ተጠቃሚዎች እንደሚስተናገዱ ተደረሰባቸው የወረርሽኙን አይምሬነት በሚገባ የተገነዘቡ ሰዎች ከሺሻ ቤት ወይም ከጫት መቃሚያው ቦታ ወደ ሕዝቡ የሚቀላቀሉት ወገኖች በቫይረሱ የተጠቁ ቢሆኑ፣ ምን ያህል ሕዝብ እንደሚጎዱ በመረዳታቸው ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ በቁጥጥር ሥር እየዋሉ መሆኑንም ኃላፊው ተናግረዋል፡፡ ለምሳሌ ያህል በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አሜሪካ ግቢ አካባቢ በሦስት የቀበሌ ቤቶች ውስጥ 431 ሰዎች ሺሻ ሲያጨሱና ጫት ሲቅሙ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል፡፡ ይህ የሚያሳየው በአንድ ቤት ውስጥ ከ140 በላይ ሰዎች መከማቸታቸውን ነው ብለዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች በአጋጣሚ በቫይረሱ የተጠቁ ቢሆኑና ወጥተው ቢበክሉ፣ ምን ያህል ወገኖች በወረርሽኙ ሊጠቁ እንደሚችሉ ለማወቅ ነብይ መሆን እንደማያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

  ምንም እንኳን ሰዎቹ በቁጥጥር ሥር ቢውሉም ማሰር እንደማይቻል የተናገሩት ኃላፊው፣ የንግድ ቤቶቹን ባለቤቶች ለጊዜው በማሰርና ወረርሽኙን በተመለከተ የመንግሥትን መመርያ መጣስ አግባብ እንዳልሆነ በመምከር መለቀቃቸውን አስረድተዋል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በሌላ ደረቅ ወንጀል የታሰሩ ግለሰቦች በመኖራቸውና መንግሥት ከእስር እየፈታ ባለበት ሁኔታ፣ እነዚህን ሰዎች ማሰሩ ተገቢ ነው የሚል እምነት ስላልነበረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

  መንግሥት የጀመረውን ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያ በመተላለፍ በተጠቀሱት ቦታዎች ብቻ ሳይሆን፣ በሌሎችም ቦታዎች ሕገወጥነቱ በመቀጠሉ ለፖሊስ ተግዳሮት ቢሆንም፣ ለሕዝብ ደግሞ አደገኛ መሆኑን ኮማንደር ፋሲካ ገልጸዋል፡፡

  አሁን መንግሥት ሁኔታውን በማጤንና ዕርምጃም መውሰድ አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁ ጥሩ ዕርምጃ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከዚህ በኋላ ለሕዝብ ጤና በማይጨነቁና የመንግሥትን መመርያና ማሳሰቢያ የሚተላለፉ አፈንጋጮች ላይ ዕርምጃ እንደሚወሰድ ጠቁመው፣ ከፖሊስ ጎን የሚቆሙ ወገኖች ትብብራቸውን እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል፡፡ ሌሎችም የጤና ባለሙያዎችን ምክር፣ የመንግሥትን መመርያዎችና በአጠቃላይ ለወረርሽኙ ትኩረት ሰጥተው የመከላከያ ማሳሰቢያዎችን ተግባራዊ በማድረግ፣ እንዲተባበሩና ከሕገወጥ ድርጊት እንዲታቀቡ አሳስበዋል፡፡
  ቤቶች ኮርፖሬሽን ከ18 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ተከራዮች ባደረገው የኪራይ ቅናሽ 60 ሚሊዮን ብር እንደሚያጣ ኮሮና ቫይረስ ላይ የሚሠራ የሐኪሞች ምክር አዲስ አበባ አስተዳደር በሥሩ ለሚገኙ የንግድ ተቋማትና ሠራተኞች የግብር ዕፎይታ ሊያደርግ ነው::

  • ZURBAWIT

   Last Friday April the 10th ,2020 in San Francisco , California , USA Authorities Shut Down an illegally operating Nightclub which was caught red handed Violating Public Health Order on 04/10/2020 Friday , the police were able to seize evidences such as musical instruments , DISK JOKEY DJ equipment , Gambling machines holding money inside the gambling machines amounting to over six hundred and seventy thousand US dollars ($670,000 USD) inside the gambling machines , fog machines and many other equipments were seized by the San Francisco Police Department, Coronavirus:San Francisco shuts down underground nightclub , the Addis Ababa Police or the so called Ethiopian Federal Police should have seized the shisha smoking equipments too same as the San Francisco Police Department did.

   • To Nebiat T.

    The place you mentioned where the illegal gambling was being conducted had a business permit for warehouse purposes only . This warehouse had no liquor permit , no food permit , no club permit ,no public service dancing music permit. When renting it , the tenant of this warehouse claimed was using the warehouse to store equipments for the janitorial company. This warehouse club recently raided had with similar arrangements to the notorious “DEADLY GHOST SHIP WAREHOUSE” .

 2. ጎንደር ላይ አለ የተባለው ችግር አዱስ አበባም ገባ ማለት ነው ። ስለዚህ መንግስት ጎንደር ላይ በተለማመደው መሰረት ታንኩን እና ልዩ አለምአቀፋዊ የውጊያ ስልጠና ያላቸውን ቅልቦቹን ከዘመናዊ መሳሪያዎቻቸው ጋር በማሰማራት ችግሩን ይቆጣጠረዎል የሚል ግምት ስላለ ተረጋጉ አትረበሹ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.