በለይቶ ማቆያ የነበሩ 554 ግለሰቦች ከቫይረሱ ነፃ በመሆናቸው ከማኅበረሰቡ ጋር እንዲቀላቀሉ ተደረገ

ለ14 ቀናት በለይቶ ማቆያ የነበሩ 554 ግለሰቦች በተደረገላቸው ምርመራ ከኮሮናቫይረስ ነጻ በመሆናቸው ከህብረተሰቡ ጋር እንዲቀላቀሉ መደረጉን ጤና ሚኒትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለፁ።

92257414 2920068361417217 8480794301868015616 o በለይቶ ማቆያ የነበሩ 554 ግለሰቦች ከቫይረሱ ነፃ በመሆናቸው ከማኅበረሰቡ ጋር እንዲቀላቀሉ ተደረገየለይቶ ማቆያ የኮሮናቫይረስ በማኅበረሰቡ ውስጥ እንዳይስፋፋ ከሚያደርጉ የዓለም የጤና ድርጅት ምክረ ሃሳቦች ውስጥ አንዱ መሆኑን ዶክተር ሊያ ታደሰ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያም የኮሮናቫይረስ ከተከሰተ በኋላ በጠቅላይ ሚኒስትሩ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ሁሉም ከውጭ የሚመጡት መንገደኞች በለይቶ ማቆያ እንዲቀመጡ መወሰኑንም አስታውሰዋል፡፡

ለውሳኔው ተግባራዊነትም በሠላም ሚኒስቴር አስተባበሪነት፣ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዲሁም ከጸጥታ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም መሰረት ከተለያዩ ሀገራት ወደ ኢትዮጰያ የመጡ መንገደኞች በራሳቸው ወጪ በሆቴሎች ክትትል እየተደረገለቸው መሆኑን አንስተዋል።

በሌላ በኩል በአስገዳጅ ሁኔታ ከተለያዩ ሀገራት ወደ አገራቸው የተመለሱ ኢትዮጵያዊያን በዩኑቨርሲቲዎችና በተለያዩ ትምህርት ቤቶች በመንግሥት ወጪ እንዲቆዩ መደረጋቸውን ጠቁመዋል።

የአስገዳጅ የለይቶ ማቆያው ከተጀመረ እስካሁን ድረስ አስፈላጊ ምርመራ ተድርጎላቸው 14 ቀን የለይቶ ማቆያ ጊዜያቸውን የጨረሱ 554 ሰዎች ከለይቶ መቆያ መውጣታቸውን ተናግረዋል።

ሚኒስትሯ አክለውም የለይቶ ማቆያ ጊዜያቸውን የጨረሱት ግለሰቦች ወደ ማኅበረሰቡ ከተቀላቀሉ በኋላ ኅብረተሰቡ ከመድሎና ማግለል ነጻ በሆነ አኳኋን ሊቀበላቸው ይገባል ብለዋል።

ከዚህ ጎን ለጎንም በአሁኑ ወቅት 2 ሺህ 36 ሰዎች በለይቶ ማቆያ ውስጥ አስፈላጊው የጤና ክትትል በባለሙያዎች እየተደረገባቸው እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

በአገሪቱ የተጀመረው የ14 ቀናት የለይቶ ማቆያም የበሽታውን ስርጭት ለማቆጣጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረግ መቻሉን ሚኒስትሯ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

አኤፍ.ቢ.ሲ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.