ከምትኖርበት አዲስ አበባ በፖሊስ ተይዛ በለሊት ወደ ሐረር የተወሰደችው የህግ ባለሙያዋ ኤልሳቤት ከበደ ፍርድ ቤት ቀረበች

91792429 257515668620111 5809691150495252480 nባሳለፍነው ቅዳሜ ከምትኖርበት አዲስ አበባ በፖሊስ ተይዛ ወደ ሐረር የተወሰደችው የህግ ባለሙያዋ ኤልሳቤት ከበደ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረበች።
ኤልሳቤጥ ከበደ የህግ ባለሙያ ስትሆን ከሰብአዊ መበት ጋር የተያያዙ ስራዎችን በመስራት ትታወቃለች።
የስራ ባልደረባዋ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ኦባንግ ሜቶ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳለው የስራ ባልደረባችን የህግ ባለሙያዋ ኤልሳቤት ከበደ ባሳለፍነው ቅዳሜ ምሳ ሰዓት አካባቢ በአዲስ አበባ ከመኖሪያ ቤቷ ቦሌ አራብሳ አካባቢ ነበር በአዲስ አበባ ፖሊስ የተያዘችው።
ለእስር የዳረጋት ነገር ደግሞ በሐረሪ ክልል አስተዳድር የሚፈጸሙ ስህተቶችን መተቸቷ መሆኑን የሚናገረው ኦባንግ ይህ ፈጽሞ ስህተት እና የሰዎችን የመነጋር ነጻነት የሚጋፋ ነው ብሏል።
የህግ ባለሙያዋ ኤልሳቤጥ ቅዳሜ ሌሊት ከታሰረችበት የአዲስ አበባ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ለሐረሪ ክልል ፖሊስ ተላልፋ ከተሰጠች በኋላ ወደ ሐረር መወሰዱ ተገልጿል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም የህግ ባለሙያዋ ኤልሳቤጥ ዛሬ ረፋድ ሐረር ጠቅላይ ፍርድ ቤት መቅረቧን እና ለሚያዝያ 13 ቀን 2012 ዓ.ም መቀጠሯን አረጋግጧል።
የሐረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቢ ህግም የህግ ባለሙያዋ ኤልሳቤት ከበደ የክልሉን ባለስልጣናት በመስደብ እና ሐሰተኛ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያ በማሰራጨት ብሔርን ከብሔር ለማጋጨት ሞክራለች የሚሉ ሁለት ክሶችን እንደመሰረተባትም ኢትዮ ኤፍ ኤም ከተከሳሽ ቤተሰቦች ሰምቷል።
የህግ ባለሙያዋ ኤልሳቤጥ አሁን በእስር ላይ የምትገኝ ስትሆን የዋስትና መብቷን ለማስከበር ከሰዓት ማመልከቻዋን እንደምታስገባ ሰምተናል።
ከህግ ባለሙያዋ ኤልሳቤጥ እስር ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽንን ያላቸውን ምላሽ ለማካተት ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም ምላሽ ሊሰጡን አልቻሉም።
ኢትዮ ኤፍ ኤም

2 Comments

  1. To Obang Metho & alike:

    It is your duty to start a petition campaign on her behalf ASAP .

    As for the rest of Ethiopians, the current religious prayer campaigns should not stop us from standing up for our rights. In a country where rule of law has not been respected , with many courts closing due to the Covid-19 virus , it is highly unlikely the Courts in Harrari will serve unbiased justice to this courageous innocent brave lawyer who had the dignity to take the noble task on her own accord.

    Currently many Ethiopians residents of Tigray , Harrari , Dire Dawa and Addis Ababa among many other areas are currently being systemically victimized getting treated unjustly by those who are using this pandemic emergency as a means to get away with systemic crimes. It is a decisive time now , we should not quiet down now so their crimes go on unreported , their injustice and crimes against humanities are deadly to us same as Covid-19 is potentially.

  2. She is a racist (extremist Amhara). she was insulting Hararies and Oromos for the last 10 years. Rection of Hararies and Oromos my harm innocent Amharas because of her. I think legal action against her is justified to avoid ethnic tension.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.