/

ኮሮና ቫይረስ ‘ሰው ሠራሽ የላቦራቶሪ ውጤት፤ ወይስ የፈጣሪ መቅሰፍት?’ – በገ/ክርስቶስ ዓባይ  

በገ/ክርስቶስ ዓባይ
መጋቢት 27 ቀን 2012 ዓ/ም

Corona Virus WHUANኮሮና ቫይረስ-19 በቻይናዊቷ ውሐን ግዛት ከተከሰተበት እ.ኤ.አ ከታህሣሥ 2019 ዓ/ም  ጀምሮ ዓለማችንን ያንቀጠቀጠ የወቅቱ ሥጋት በመሆን ቀጥሏል። ከልሂቅ እስከ ደቂቅ፤ ሀብታም ደሀ፤ ሳይል ሁሉንም የሰው ልጅ፤ ሕይወት ከንቱ እንደሆነች በማስተማር ድንበር የለሽ ግዛቱን በየጊዜው እያሰፋ  ቁጥጥሩን አጠናክሮ ዓለምን እያስጨነቀ ይገኛል።

በተለይ በዘርና በጎሣ፤ በቋንቋ እና በክልል የሚመጻደቁትን ተስፈኛ ፖለቲከኞች ሁሉ አእምሮ ቢኖረቸው፤ ወደ ቀልባቸው እንዲመለሱ ታላቅ መልዕክት እያስተላለፈ ነው። ክልሌ፤ ግዛቴ፤ እያሉ የሚፎክሩትን ሁሉ ‘ኮሮና ቫይረስ’ ሲያሾፍባቸው ታዝበናል። እንዲሁም የኒኩሌር ቦምብ ባለቤት ነን የሚሉትን ኃያላን መንግሥታት እንኳ አንገት አስደፍቷቸዋል። እጅግ በጣም የሚገርመው ግን ኮሮና ቫይረስ-19 ግዙፍ ሳይሆን በማጉሊያ መነጽር እንኳ በቅጡ የማይታይ ረቂቅ ተህዋሲያን መሆኑ ነው።

ጥንት የሰው ልጅ ከጋርዮሽ ርዕዮተ ዓለም ወጥቶ የግል ሀብት ማካበት ከጀመረበት ዘመን አንስቶ፤ ቀስ በቀስ ኃይሉን በማጠናከር ደካማውን ለመግዛት ሲል ያልተጠቀመበት ዓይነት የማጥቂያ ዘዴ አልነበረም። በተለይ ደግሞ የሳይንስ ዕውቀት እያደገና እየመጠቀ በመጣ ቁጥር ቴክኖሎጂው ያላቸው አገሮች፤ የተለያዩ የበሽታ ዓይነቶችን በመሰብሰብና በታላቅ ጥንቃቄ በቤተ ሙከራ በማጥናት፤ ከሰብአዊነት ባህርይ ውጭ በሆነ ፍጹም አረመኔያዊ መንገድ፤ የባዮሎጅካል መሣሪያ አድርገው ለረጅም ዘመናት ሲጠቀሙበት ኖረዋል።

ጥቂቶችን ለመጥቀስ ያህል ሞጀሌ (jigger)፤ትራኮማ (trachoma)፤ቁርባ (anthrax)፤ቲቪ (tuberculosis)፤የዕብድ ውሻ በሽታ (rabies)፤ ማጅራት ገትር (meningitis)፤ ጆሮ ደግፍ (mumps)፤ ፈንጣጣ (small pox)፤ አንከሊስ (measles)፤ ልምሻ በሽታ (polio)፤ ኪርኪርታ (whooping cough) እና የመሳሰሉት ይገኙባቸዋል። ከእነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ በዓለም ጤና ጥበቃ ድርጅት የተወገዙ በመሆናቸው እንዲያውም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከምድራችን እንዲጠፉ ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ ቢቆይም፤ እነዚህና ሌሎችም አደገኛ በሽታዎች ግን በተለያዩ አገራት የምርምር ላቦራቶሪዎች፤  ልዩ ልዩ ኮድ ተሰጥቷቸው በጥልቅ ማቀዝቀዣ ውስጥ እንደሚገኙ የሚያጠራጥር አይሆንም።

ስለኮሮና ቫይረስ-19 ስናነሳ ከዚህ ከላይ ከጠቀስነው የምንረዳው ነገር አለን። አብዛኞቻችን ኮሮና ቫይረስ-19 አዲስ ተኅዋሲ አድርገን እንመለከተዋለን። ነገር ግን ከሕክምና ባለሙያዎች መግለጫ እንደምንረዳው ከሆነ ኮሮና ቫይረስ አዲስ ግኝት ሳይሆን ቀደም ሲል የሚታወቅ የበሽታ ዓይነት እንደሆነ ነው።

የዘመኑ ሳይንቲስቶች የዓለም ሕዝብ እ.ኤ.አ. በ2050 ዓ/ም 10 ቢሊዮን ይደርሳል በማለት ተንብየዋል። ከዚህም የተነሳ መንግሥታት ለሕዝባቸው ንጹሕ የመጠጥ ውሀ፤ በቂ የምግብ ፍላጎትን ለማሟላት፤ እንዲሁም የመጠለያ፤ የትምህርት እና የጤና አገልግሎቶች በስፋት እንዲዳረሱ ለማድረግ አስቀድመው ዕቅድ በማውጣት ተግተው እንዲሠሩ በማለት ‘የሚሊኒየም ግብ’ በሚል ርዕስ በተባበሩት መንግሥታት ማኅበር የተለያዩ  መመሪያዎች ወጥተው እየተሠራባቸው መሆኑን እንገነዘባለን።

ነገር ግን ይህንን በጎ አስተሳሰብ በመጻረር የዓለም ሕዝብ ቁጥር በ2050 ዓ/ም 10 ቢሊዮን አይደርስም፤ እንዳይደርስም ማድረግ ይቻላል፤ በማለት መንፈሳዊ ሳይሆን ሰይጣናዊ አስተሳሰብ ይዘው ሌት ተቀን በሚናውዙ አንዳንድ ስግብግብ ግለሰቦች የሚመሩ ኩባንያዎችም አልጠፉም።

ይህንኑም ዕኩይ ዓላማ ተግባራዊ ለማድረግ የዓለምን ሕዝብ ለመቀነስ፤ ከተለመደው የወሊድ መቆጣጠሪያ ውጭ ያለሰዎች በጎ ፈቃድና ዕውቅና፤ በክትባት መልክ በስፋት እንዲሰጥ እየተደረገ ነው። በዚህም ከፍተኛ ተጠቂ የሆነው የአፍሪካ ሕዝብ ሲሆን፤ በዓለም ከፍተኛ የመጸነስ አቅም (fertility rate) አላት ተብላ የምትታወቀዋ ኢትዮጵያችንም ልዩ ትኩረት የሳበች አገር መሆኗን በዚህ አጋጣሚ ለመጠቆም እንገደዳለን።

እንግዲህ እነዚህ ኩባንያዎች ይህንን እኩይ ዓላማቸውን ተግባራዊ ለማድረግ በዕርዳታ ስም የበጎ አድራጊ ድርጅት መስለው ሰርገው በመግባት መንግሥትን እያታለሉ፤ ንጹሑን ሕዝብ በጅምላ በማመምከን ላይ ናቸው። ዓላማቸውም በአጭሩ እንዳይደናቀፍ በማሰብ የሚሰጡት ክትባት ከአምስት ዓመት በታች ባሉ ሕፃናት ላይ በመሆኑ ውጤቱ ወዲያውኑ አይታወቅም።

መንግሥታትና ባለሥልጣናት ሕዝባቸውን የመጠበቅና የመታደግ ከፍተኛ ኃላፊነት አለባቸው። በዚህ መጥፎ ተግባር ላይ በስፋት እየተሳተፉ ናቸው በመባል የሚጠረጠሩት የዓለማችን ቱጃር፤ አገራችንን ለአለፉት ሀያ ዓመታት በላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው ብዙ ደባ ሲፈጽሙ መቆየታቸው ይታወቃል። እኒሁ ሰው በተመሳሳይ መልኩ ወደ ሕንድም ለመግባት ሞክረው ፤ “ከእርስዎ ጋር ከኮምፒውተር ሶፍትዌር ውጭ ጤናን በተመለከተ፤   ምንም ዓይነት ግንኙነት እንዲኖረን አንፈልግም፤” ተብለው  በከፍተኛ ውርደትና ቅሌት እንደተባረሩ የአደባባይ ሚስጥር ነው።

ቱጃሩ ከበለጸጉበት ከኮምፒውተር ሶፍትዌር በተጓዳኝ የዓለምን ሕዝብ ኢኮኖሚ በበለጠ የሚቆጣጠሩበትን ዘዴ በመቀየስ ፍጹም አደገኛ በሆነው የፋርማሲውቲካል ዘርፍ ዘው ብለው ገብተዋል። ይህ  ዘርፍ ከፍተኛ የሆነ ተዓማኒነት፤የረጅም ጊዜ የምርምር ዕውቀት፤ ልምድና ጥናት የሚጠይቅ በመሆኑ ፈቃዱን ለማግኘት ቀላል አልነበረም። ይሁን እንጂ ይህንኑ ሕልማቸውን እውን ለማድረግ በገንዘብ ኃይል ተጠቅመው የእራሴ የሚሉትን ሰው የዓለም ጤና ጥበቃ ድርጅት ዳይሬክተር ጄኔራል ደረጃ እስከማሾምም ደርሰዋል። ስለሆነም ዕቅዳቸውንም ያለምንም ሳንካ እየተገበሩ መሆናቸውን ነጋሪም ይሁን መስካሪ አያስፈልገንም።

እኒሁ ቱጃር ከአሁን ቀደም  ሲሪንጅ በእጃቸው ይዘው፤

 “ክትባት! ከተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች መከላከል ብቻ ሳይሆን የዓለምን ሕዝብም በሁለት ሦስተኛ መቀነስ ይችላል” በማለት እ.ኤ.አ በ2015 ዓ/ም በዩ ቲዩብ የሰጡትን መግለጫ ከጊዜ በኋላ ቢያነሱትም፤ በቀላሉ የምንረሳው አይሆንም። መልዕክታቸው ግን ምን እንደሆነ በግልጽ አስቀምጠዋል።

እኒሁ ሰው ሰሞኑንም ስለ ኮሮና ቫይረስ አስተያየት መስጠታቸው አይዘነጋም። በጥሞና ለተከታተለው ግን ማሳረጊያቸው ማለትም በ14ኛው ተራ ቁጥር ላይ የጻፉት ማንነታቸውንና አቋማቸውን ፍንትው አድርጎ አጋልጧቸዋል። ይኸውም፤ “ብዙዎቹ ሰዎች የኮሮና ቫይረስን እንደ ዕልቂትና መከራ አድርገው ያዩታል፤ እኔ ግን እንደዚያ ሳይሆን ‘አስተካካይ (አራሚ)’ ነው የምለው” ሲሉ አስተያየታቸውን ደምድመዋል።

ሕዝብ ያለፈውን እየረሳ በወቅታዊው ሁኔታ ላይ ትኩረት ስለሚሰጥ እንጂ በአለፉት አሥር ዓመታት ብቻ እንኳ የሆኑትን ብናስታውስ የተለየ ግናዛቤ እናገኛለን። እ.ኤ.አ በነሐሴ 2018 ዓ/ም በአፍሪካ የተከሰተውን የኢቦላ በሽታ፤ በ2010 ዓ/ም በቻይና ተከስቶ የነበረው በርድ ፍሉ፤ እ.ኤ.አ ከ2015-2016 ዓ/ም መጀመሪያ በብራዚል ከዚያም በላቲን አሜሪካ አገሮች ተከስቶ የነበረው የዚካ ቫይረስ፤ እ.ኤ.አ በነሐሴ ወር 2007    ዓ/ም  በአውስትራሊያ ተከስቶ የነበረውን የፈረስ (ጉንፋን) ፍሉ ማስታወሱ በቂ ነው።

በጣም የሚያስፈራው ግን አሁንም ሌሎች ዓይነት አደገኛ ተላላፊ በሽታዎች እንዲሁ ከቤተ ሙከራ ሊወጡ ስለሚችሉ ነው። እ.ኤ.አ ከ1347-1351 ዓ/ም በአውሮፓ እና በኤስያ ተክስቶ የነበረው ‘ጽልመተ ሞት’ (black death) በሚል ቅጽል ስም የሚታወቀው የቡቦኒክ ፕሌግ ወረርሽኝ በሽታ 475 ሚሊዮን ሕዝብ እጥብ እንዳደረገ ታሪክ መዝግቦት ይገኛል። ይኸው ወረርሽኝ በሽታ በ57 ቀናት ብቻ ከመቶ ሺህ በላይ የሎንደን ነዋሪዎችን እንደፈጀም ይታወቃል።

እንግዲህ ይህ አደገኛ ወረርሽኝ በሽታ፤ በቤተ ሙከራ ውስጥ በትንሽ ቢልቃጥ ሊገኝ እንደሚችል መገመት እንደ ሞኝነት ሊቆጠር አይችልም። ታዲያ ሆነ ተብሎ ወይም ደግሞ ምርምር ሲደረግበት ድንገት አፈትልኮ ቢወጣ፤ በዓለማችን ላይ ምን ዓይነት ዕልቂት ሊያስከትል እንደሚችል መገመት አይከብድም።

ያም ሆነ ይህ አባቶቻችን የሚተርቱት ነገር አለ፤ “ሽልም እንደሆነ ይገፋል፤ ቂጣም እንደሆነ ይጠፋል!”

ኮሮና ቫይረስ-19ም ሆነ ተብሎ የተለቀቀ ከሆነ በአጭር ጊዜ ውስጥ ክትባቱ በይፋ ይሠራጫል። ይህም ክትባቱን ለሚሸጠው ኩባንያ ከፍተኛ ገንዘብ የሚያስገባ፤ የዓለምን ሕዝብ እንደ ጥገት የሚያልብ ይሆናል።

ቀድሞ የባዮሎጅካል ጦር መሣሪያ የበላይነት ያለው መንግሥት ሌላውን እያስፈራራ ሲገዛ  ቆይቷል። አሁን ደግሞ በፋርማሲዩቲካል ተንኮል ላይ የተመሠረተ ሤራን በመተግበር ከዓለም ጤና ጥበቃ ጋር ስምምነት በመፈረም ብቻ ከፍተኛ የደም ገንዘብን ለማጋበስ እየተሞከረ ነው። ነገር ግን አንድ ቀን፤ ሐቀኛ ሰው ምንጊዜም አይጠፋምና እንዲህ ዓይነቱ ሤራ የተጋለጠ ጊዜ ገንዘብ አልጠግብ ያሉት ስግብግቦችና ተባባሪዎቻቸው በቅሌት ተከሰው በዓለም ፍርድ ቤት ሊቀርቡ እንደሚችሉ አጠያያቂ አይሆንም።

ውድ ወገኖቼ ያም ሆነ ይህ፤ ለዚህ ሁሉ ገፊው ምክንያት ‘ፍቅረ ነዋይ’ ሲሆን ምንጩም ከዲያብሎስ ነው። ሆኖም ዋናው ግድድሮሹ ከፈጣሪ ጋር ስለሆነ፤ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ በጾምና በጸሎት በመትጋት በአምላካችን መታመን ያስፈልገናል። ፈጣሪያችን እንዲህ ያለ መቅሰፍት አምጥቶብናል ብለው የሚያምኑ ቢኖሩ በአንድ በኩል ትክክል ናቸው። ምክንያቱም፤ አምጪዎቹ ተንኮለኞች በሕይወት እንዲኖሩ ፈጣሪ አምላክ ፈቅዷልና።

የዘመኑ የጎሣ ፖለቲከኞች ዓላማቸውን ከግብ ለማድረስ የሚጠቀሙት ሕዝብን ከሕዝብ በዘር በቋንቋና በጎጥ በመለያየት የሥልጣን ኮርቻ ላይ ለመፈናጠጥ ሲሠሩ የቆዩትን፤ እና አሁንም እያደረጉ ያሉትን እንድንታዘብ ሆነናል። ኮሮና ቫይረስ-19 ግን ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን የዓለምን ሕዝብ በአንድ ላይ እንዲቆም አድርጎታል። በዚህ ቀውጢ ሰዓት ኢትዮጵያውያን በአንድነት ቆመው እያደረጉት ያለውን የእርስ በእርስ ትብብር ስናይ፤ በጎሣ፤ በጎጥና በቋንቋ ተቧድነው የተደራጁትን ፖለቲከኞች ‘ገደል ግቡ!’ የሚል መልዕክት የሚያስተላልፍ ሆኖ እናገኘዋለን።  ሕዝቦች በሰውነታቸው ብቻ እያደረጉት ያለው ትብብር እና የእርስ በእርስ ዕርዳታ፤ ለጎሣ ፖለቲከኞች ቅስም ሰባሪ እንደሆነ ለማንም ግልጽ ነው። ስለሆነም የማታ ማታ ጸረ ሰው የሆነ ሁሉ ከምድራዊም ሆነ ከሰማያዊ ፍርድ ነፃ ሊሆን አይችልምና፤ ሰው ለስው የችግር ጊዜ ደራሽ መሆን አለበት እንላላን።

-//-

 

2 Comments

 1. የሰው ልጅ ራሱ ባመጣው ጣጣ በፈጣሪ ላይ ማላከክ ከጀመረ ቆይቷል። ያው ሰባኪውና ምህላ የሚያበዛው ህዝብም አሜን ብሎ “ይህ መከራ የመጣብን በሃጢያታችን የተነሳ ነው” ሲባል እግዚኦ ማህረነ በማለት መብላትና መጠጣትን ለቀናት አቁሞ ራሱን ለሌላ በሽታ ያጋልጣል። ይህን ስል ዓለማችን እድፋም መሆኗ አልጨመረም ማለት አይደለም። በነጻነት ስም ሃገሮች ፈርሰዋል። ሃብታቸው ተዘርፏል፤ መሪዎቻቸው ተገለዋል፤ ስለጠንኩ የሚለው ህዝብም ሶዶማዊነቱን አደባባይ አውጥቶ እኔን ምሰሉ ካለን ቆየን። እረ ይመቻቸው። እኔን ምን አገባኝ ግን ዛሬ ዓለማችንን ብርክ ያሲያዘው ቫይረስ ከፈጣሪ የመጣ ነው የሚሉ ወስላቶች ለልመና እንዲመቻቸው እንጂ ከፈጣሪ የመጣ አለመሆኑን ሳይንሳዊ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ተውሳካዊ ህዋሳቶች በመሰረቱ አብረውን ይኖራሉ። በቤታችን፤ በውጭ፤ በጫካ፤ ከለማዳና ከአውሬ እንስሳት ጋር። ታዲያ በሽታው ከወደ ቻይና ብቅ ማለቱ የሚያመለከተው ከሆድ ጋር የመጣ በሽታ መሆኑን ነው። ቻይኖችና መሰሎቻቸው ከድመት እስከ አህያ ድረስ ወደ አፋቸው የማያስገቡት ነገር የለም። ለምሳሌ አማና 10 ሚሊዪን ውሾች በቻይና እንደታረድ ጥናቱ ያመለክታል። በዚህ በበቃቸው ጥሩ ነበር። ግን ቻይኖች አፋቸው የማያስገቡት ምንም ነገር የለም። እባቡ፤ ጊንጡን፤ የሌሊት ወፉን ወዘተ.. ታዲያ ሰው ክዚህ አልጠግብ ባይ ልምድ ጋር ተያይዞ በሽታ ቢጠራርገው በፈጣሪ ላይ መሳበቡ ማንን ለማሞኘት ነው?
  በአንጻሩ በላቦራቶሪ ተቀምሞ ሰውን ለማጥቃት መንግሥታት የሚፈጥሯቸውም ሆነ ከሜዳ የተገኘውን በሽታ ለውጊያ የሚይዘጋጅበት ሁኔታም አለ። ለምሳሌ አንትራክስ ብንወሰድ ቀዳሚው የሥራ ውጤታቸው ነው። ሌላም ሌላም እልፍ አይነት ሰው ሰውን የሚገልበት ሰውር መርዝ በእጃቸው ላይ አለ። ለአንዳንዱ አፍራሽ ተሰርቶለታል። ለምሳሌ የፓለሲቲያን ታጋይ የነበረውን አንድ ሰው በጆርዳን አማን ላይ በእስራኤል ለመግደል የተደረው ሙከራ ከተከናወነ በህዋላ ሙከራውን ያደረጉት የሞሳድ ሰዎች በመያዛቸው እስራኤል የመርዙን ማርከሻ ሰውየው ከሞመቱ በፊት በማቅረብ የሰውየው ህይወት እንዲተርፍ አርጋለች። Mossad: The Greatest Missions of the Israeli Secret Service የተሰኘውን መጽሃፍ በማንበብ የበለጠ መረጃ ማግኘት ይቻላል። አሁን ወደ ገባንበት የኮሮና ቫይረስ ስንመጣ ጭብጥ እውቀቶች ሊሰጡ የሚችሉ መጽሃፍትን ማገላበጥ ተገቢ ይመስለኛል። ከዘመናት በፊት የተጻፉ እውነትን ተመርኩዘው በልበ ወለድነት የቀረቡና እውን የምርመራ ውጤት ሥራዎችን ማገናዘብ ተጨባጭ እውቀትን ይሰጣል። ከእነዚህ መጽሃፍቶች መካከል የሚከተሉት ለግንዛቤ ይረዳሉ።

  The plague – Albert camus, The Coming Plague: Newly Emerging Diseases in a World Out of Balance – Laurie Garrett and Spillover: Animal Infections and the Next Human Pandemic – David Quammen የተጻፉበትን ዘመን በማገናዘብ ማንበቡ ችግሩ የመነጨው ከፈጣሪ ወይም ከሰው መሆኑን አበክሮ ለማወቅ ይረዳል። ወንድሜ አቶ ገ/ክርስቶስ ዓባይ የመከራው ምንጭ ከሰማይ የመጣ አለመሆኑን ጠንቅቆ ያውቃል። ችግሩ እኛው ነን። ግን ሁሉን ነገር በሌላ ነገርና ሰው ላይ ማላከክ ተፈጥሮአዊ
  ባህሪያችን ነው። ቢከፋም ይህ የመከራ ጊዜ ደስ የሚለው ሁሉንም የነካ መሆኑ ነው። ሃብታም የለ፤ መሪን አልተወ ቄስ የለ ዲያቆን የሁሉ ቤት እያንኳኳ እንዴት ሰነበታችሁ ማለቱ እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ለሚለው የሰው ልጅ ጭንቅላት አንድ መሆናችን አስመስክሮአል። ሃብት ቢኖርህስ እንደ አይጥ ሁሌ ጉድጓድ ውስጥ ተደብቀህ ኑሮህ እንዴት ይጣፍጣል። በጉራ የተሞላው የአሜሪካ ኢኮኖሚ እየተሽመደመደ ሁሉን ተመጽዋች ሊያረገው ሳምንት ቀርቶታል። ይታያቹሁ አሜሪካ ከራሽያና ከቻይና መጽዋት ስትቀበል። 23 ቲሪሊየን እዳ ውስጥ የተዘፈቀቸው አሜሪካ አንዴ ይህን አንዴ ያን እያደረገች ኢኮኖሚውን ለማረጋጋጥ ብትሞክርም አልሆነም። አሽዋ ላይ እንደተሰራ ቤት በዚህ በኩል ሲደግፉት በዚያ በኩል ይንጋደዳል። አለማችን ከዛቢያዋ ውጭ ናት። ይህም መከራ ቢያልፍ ሌላ ይከተላል። ሰው አይገባውም። ይህ በቫይረሱ ብቻ የመጣ አይደለም። በየመን፤ በሶሪያ፤ በኢራቅ በሊቢያ የሆነውንና የሚሆነውን አይቶ እኔ ከሞትኩ ምን አገባኝ የሚል የጅል መንጋ በሚኖርበት አለም ላይ አሁን ኡኡታ ማሰማት ምን ይባላል? ይህ ቫይረስ አለፈ አከተመ ቢባልም ሰው እንደገና መልሶ የመተማመኑ ገመድ ተበጥሶአል። ከደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ ይሉሃል ይህ ነው። ድሮስ ቢሆን ይህ ኢንተርኔት የሚባል ከመጣ ወዲህ መቀራረብ የት ነበረና ነው። ቁስ አካል አምላኪዎች ከሆንን እኮ ሰነበትን። በመዚጊያው እባካችሁ እናንተ ለሰማይ ቤት ቅርብ ነን የምትሉ ሰዎች ህዝባችን አታታሉ። ከቻላችሁ ለተጎዱ፤ ለተራቡ እጃቹሁን ዘርጉ። ስብከታችሁ ይብቃ፤ ስራችሁ ይመስክር። የኮረና ቫይረሱም ሰው ሰራሽም የፈጣሪ መቅሰፍትም አይደለም። በሆድ የመጣ መቅሰፍት ነው። እስቲ ጥራ ጥሬና ቅጠላ ቅጠል እንመገብ። ሁሌ ሥጋ፤ ለዛውም ምርጫ ያጣ ሥጋ? በሰማይ የሚበርም በምድርና በውሃ የሚራወጥን ሁሉ እያነቁ ወደ አፍ። ኸረ አቁሙ፤ አታስጨርሱን!

 2. Breaking News: “Nadiya the wild animal/Tiger, in New York City , USA’s zoo tested posetive to Covid-19 which suggests that neither our pet animals nor our farm animals are considered safe to get closely in physical contact with humans.”

  All human beings who got coronavirus symptoms are urged to stay away from animals inorder to minimize the spread of the virus to animals from humans . Also Abeshas humans are urged to exercise caution while eating raw Kitfo or Qurt tire Siga since there is a chance that the meat might come from an infected animal, Abesha single men are advised to learn how to fully cook meat in a sanitary manner ASAP, if they decide to continue consuming meat.

  PM Abiy ” Every family in Ethiopia is begged to give one free meal per day to the homeless Ethiopians so the homeless Ethiopians donot die of hunger while waiting for food from the government’s war on poverty initiative actors who are overwhelmed with the demands for meals ” , the decade plus long Ethiopi’s war on poverty initiative actors are currently doubting their ability to feed the needy homeless , especially in city settings since urban areas population malnutrition cases had been neglected by the medical profession for too long in Ethiopia .
  Right now the neglected agriculture development sector with the leaders concerning themelves with industrial parks rather than developing food self sufficient security initiatives made the malnutrition epidemic cases go on unnoticed exacerbating the need for nutritious meals in Ethiopia a number one priority to defeat the pandemuc , currently food price had reached an all-time high due to the virus with roads in and out of many cities are routinely getting blocked closed illegally by vigilantes .

  CNN.com › 2020/04/02 › home…
  Web results
  South Africa coronavirus: homeless people gathered into sports stadium as …

  The South African › lifestyle › s…
  South Africans encouraged to ‘buy a bed’ for homeless community members

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.