“ምርጫ ቦርድ የሄደበት መንገድ ትክክል አይደለም” ኦነግ እና ኦፌኮ

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ቀጣዩን ምርጫ የመሰረዝ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የሄደበት መንገድ ትክክል አይደለም ሲሉ የኦሮሞ ነጻነት ግንባርና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ገለጹ።

ሁለቱ ድርጅቶች ባወጡት የጋራ መግለጫ ላይ እንዳሉት “ኮቪድ-19 በምርጫ 2012 እቅድና የጊዜ ሰሌዳ አፈጻጸም ላይ ተግዳሮቶችን ደቅኖ ቦርዱን እየተፈታተነ መሆኑን” እንደሚረዱ አመልክተው፤ ነገር ግን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስ “የሄደበት መንገድ ትክክል አይደለም ብለን እናምናለን” ብለዋል።

111549313 pjimage 7
አቶ ዳውድ ኢብሳና ፐሮፌ. መረራ ጉዲና

ጨምረውም ቦርዱ ከዚህ መደምደሚያ ላይ ለመድረስ መጋቢት 12 ቀን 2012 ዓ.ም ገዢውን ፓርቲ ጨምሮ የኦሮሞ ነጻነት ግንባርና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) የተገኙበት የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰብስባ አዘጋጅቶ ምክክር ተደርጎ እንደነበር ጠቅሶ፤ በስብሰባው መጨረሻ ላይ ሌላ ዙር ወይይት እንደሚኖር ቢገለጽም ይህ ሳይሆን ውሳኔ ላይ መድረሱ አግባብ አይደለም ብሏል።

ነገር ግን ወረርሽኙ በሁሉም ዘርፍ የሚያስከትለውን ችግር ለማስወገድ ቅድሚያ በመስጠት የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልጸው፤ ከዚሁ ጎን ለጎን ለቀጣዩ ምርጫ ለመዘጋጀት አስፈላጊው ሁሉ እንዲደረግ ፓርቲዎቹ ጥሪ አቅርበዋል።

በተጨማሪም ምርጫውን በተመለከተ ቀጣይ እርምጃ ለመውሰድ ሁሉም ባለድርሻ አካላት መሳተፍ እንዳለባቸው ፓርቲዎቹ አመልክተዋል። ከዚህ ውጪ”ምርጫውን ማራዘምና ቀጣዩ የአገሪቱን ዕጣ ፋንታ ለመወሰን መሞከር የባሰ አገራዊ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል” በማለት ስጋታቸውን ገልጸዋል።

መግለጫው በተጨማሪም አገሪቱ አሁን ባለችበት ሁኔታ ውስጥ “ምርጫውን የማራዘም ውሳኔም ሆነ ከመስከረም 2013 በኋላ ሊኖር የሚችልን መንግሥት መወሰን አሁን ላለው መንግስት ብቻ የሚተው ጉዳይ አይደለም” በማለት ጉዳዩ አጠቃላይ አገራዊ ተሳትፎን እንደሚፈልግ ጠቅሷል።

ከበሽታው ጋር በተያያዘም ወረርሽኙን ለመግታት ተብለው በመንግሥት የሚወጡ ሕጎች፣ ደንቦችና ውሳኔዎች “እየጠበበ የመጣውን የተፎካካሪ ፓርቲዎችን እንቅስቃሴ የባሰ ለማጥበብ መንግሥት እንዳይጠቀምበት ቁጥጥር ማድረግና አላስፈላጊ የሆኑ ሕጎችን ከማውጣት” እንዲቆጠብ ጠይቀዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:   የዘመናችን ታላቁ ትንሽነት ፊቺ እንደማንፌስቶ! - ታዬ ደንደና

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ወረርሽኙኝን የሚመለከቱ መመሪያዎችና መልዕክቶችን በዋናነት ለሕዝብ ጤና ጥበቃ ተቋማትና ባለሙያዎች እንዲተዉ አሳስበዋል።

በማጠቃለያ ላይም ምርጫውን ለማራዘምም ሆነ በቀጣይ እርምጃ ላይ መንግሥት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቭክ ማኅበራትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገናኝተው ተከታታይ ውይይትና ምክክር በማድረግ ሁሉም አማራጭ ሃሳቦች ማቅረብ እንዲችል መንግሥት ሁኔታዎችን እንዲያመቻች ፓርቲዎቹ ጠይቀዋል።

BBC

4 Comments

 1. አይ ፓለቲከኛ። እስቲ ፎቶዎቻቸውን ትኩር ብላችሁ ተመልከቱ። አሁን እነዚህ ፓለቲካ ውስጥ መግባት ነበረባቸው? እድሜ ልካቸውን ሮጠው ያሳኩት አንድም ነገር ሳይኖር አሁንም ከፊት ቆመው እኔን ስሙኝ ማለታቸው አያስተዛዝብም? በእኔ እምነት እነዚህ ሰዎች አንድ እግራቸው መቃበር ውስጥ የቆመ ከሚኖሩበት ዘመን ይልቅ ኑረንበታል ያሉት ጊዜ የረዘመ ናቸው። አርፎ መቀመጥና ለወዲያኛው ዘመን ማሰብ ግድ ይል ነበር። ግን የዘር ፓለቲከኞች እይታቸው ሁሉ ማጉረምረም ሌላውን ማጣጣል የመፍትሄ አካል ከመሆን ይልቅ እሳት ጭሮ መለኮስን ተክነውበታል። አሁን በዓለማችን በምናየው ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር እንዴት ያለ ምርጫ ነው የሚካሄደው? ሰው ከድመት እንዳመለጠች አይጥ በየጉድጓድ ገብቶ እግዚኦ በሚልበት በዚህ ሰአት ላይ የቋንቋና የዘር ፓለቲከኞች ጥሩንባ ማብቂያ የለሽ መሆኑ የተግባራቸውን ርካሽነት ያሳያል።
  ይህ የኮሮና ቫይረስ ሰውን በየቀኑ ከመቅጠፉ ሌላ የተሽከርካሪዎች በብዛት በመንገድ ላይ አለመታየት ከባቢ አየሩን ከሞላ ጎደል ንጽህ አድርጎታል። ትላንት በአስም ይጨነቁ የነበሩ ሁሉ አሁን ወጣ ካሉ ቀለል ያለ አተነፋፈስ ያገኛሉ። በጅምር የቀሩ መንገዶች አሁን ያለምንም የትራፊክ ችግር በፍጥነትም የሚሰሩበት ሁኔታ ይታያል። ሌላም ሌላም ብርሃን መሰል ነገሮች በዚህ ነፍስ ግቢ ነፍስ ውጭ በሚያሰኝ ጊዜም ውስጥ ይስተዋላሉ። ትላንት በሃብትና በንብረቱ በእውቀትና በዘመድ ይመካ የነበረው ሁሉ ሃብቱ የገለባ ክምር ሆኖ እሳት ሲበላው ሲያይና እውቀቱና ዘመድም ከዚህ ክፉ በሽታ የማይታደጉ መሆናቸውን ስንረዳ አንድ ነገር ግልጽ ሆኖ ይታየናል። እኩልነት በሞት። አንድ ጊዜ አንድ ፊደል ቆጥሬአለሁ ብሎ እኔን ስሙኝ የሚል የሶሻል ፓለቲከኛ ስለ እኩልነት ስናወራ እንዲህ አለኝ “Equal rights is not equal worth”. አሁን ባገኘው ምን ይለኝ ይሆን?
  ኦነግ እና ኦፌኮ ያረጅ ያፈጅ ጥርሳቸው ያለቀ የሜዳ ላይ አንበሶች ናቸው። የሚገርመው የሃገራችን ፓለቲከኞች የሰው መብት እየረገጡ መብታችን ተረገጠ ብለው ማልቀሳቸው ነው የሚያስተዛዝበው። ከራሱ ጋር የታረቀ ሰው ምርጫው መቼ እንደሚሆን አሁን ባለንበት ግንዛቤ መገመት ያዳግታል። በመሆኑም ኦነግ እና ኦፌኮ በስሙ ለሚነግድበት ለኦሮምም ህዝብ ሆነ ለሃገራችን መላ ህዝብ በዚህ አስጨናቂ ጊዜ ምግብ፤ ውሃ ለማቅረብ ቢሰሩ ለምርጫውም ይረዳቸዋል። ሶፋ ላይ ተቀምጦ በኦሮሞ ህዝብ ከየዓለማቱ የተለመነና የተደጎመ ገንዘብን እየበሉ ሺህ ጊዜ ለኦሮሞ ህዝብ ቆመናል ማለት ማፌዝ ነው። 60 ዓመት ያልመጣ ለውጥ አሁን ይመጣል ብሎም መገመት መጃጃል ነው። ጡረታ ውጡ! ለነገሩ የዘርና የቋንቋ ፓለቲከኞች ጡረታን አያውቁም። እንዳለቀሱና እንዳስለቀሱ አፈር ይመለስባቸዋል። አይጣል። የውሾች ፓለቲካ። ሁሌ መነካከስ!

 2. According to Adler’s Theories, “Komplexe እና Geltungsbedürfnis” የሌለው ሰው የለም::
  ታድያ ፍወሳን በምንፈልግበት ጊዜም ሆነ ወይንም ደግሞ መሸከሙ ከብዶን ለመጮህ ሲያሰኘንም ቢሆን፣ በሌላው ቁስል ላይ እንጨት እየሰደድን ባይሆን ይመረጣል::
  ስማቸው የተጠቀሱት የኦሮሞ ጓዶች፣ ለብዙ ዘመናት ትግልን ያካሄዱ ወገኖች ናቸው:: በስራ ላይ የተሰማራ ሁሉ ዘንዳ ጥፋት ላይታጣ ነውና፣ እነሱም ዘንዳ እንዲሁ:: ደግሞም በእንደዚህነታቸው እንዳሉ ነው ከእስር ቤትም ሆነ ከአሜሪካም ወይንም ከአስመራ ስልጣን እንዲካፈሉ ወደ ኢትዮጵያ ተጋብዘው የመጡት»
  ህሉው ሁናቴ በእንዴህ እያለ፣ በርግጥ ፖለቲካቸው ላይ እንከን ሲገኝ መታገል የግዴታ ነው:: ማንነታቸውን አስመልክቶ ግን ሁልጊዜም በታላቅ RESPECT ስማቸውን ማንሳት የጨዋነት አንደበት ግዴታ ይሆናል::

  • Zere-Yakob,
   You may worship them; that is your right. For me, these OLF guys are criminals. Imagine a professor in political science calling one ethnic group to kill and displace another one. Imagine a guy who has lived in USA-a country in which people from different countries live together in relative peace and harmony-agitate the killing of christians by moslems and non-oromo Ethiopians by oromos. Believe it or not, if these guys come to power, the consequence will be clear: Potential separation of the oromos from the rest of the country leading to lasting civil war.

 3. meseret,

  ፅሁፎችህን ብዙ ጊዜ አንብቤያለሁኝ:: ግን ከዚች ከዛሬትዋ አስተዋፅኦህ በስተቀር አንዳችም ለ’harmony እና ለ’peace የሚጋብዝ አስተዋፅኦ አይቸብህ አላውቅም:: ታድያ የዘነጋሄው ጉዳይ ምናልባት ሁሉ ነገር ከራስ እንደሚጀምር ነው:: እስካሁን ጊዜ ድረስ ቁጥር የለሽ ጠቦችን ጭርሃል፣ እስኪ ደግሞ ለሚቀጥለው በሰላሙ መንገድ ሞክር::
  አለ አይደል፣ የዘሩት ነውና የሚታጨደው………………….!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.