አየር መንገዱ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ወደ 80 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ሲያደርግ የነበረውን በረራ አቋረጠ

Airlineየኢትዮጵያ አየር መንገድ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ወደ 80 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ሲያደርግ የነበረውን በረራ ከዛሬ ጀምሮ ማቋረጡን አስታወቀ።

አየር መንገዱ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚደረጉ የካርጎ( የእቃ ማመላለሻ) በራሮች ግን ይቀጥላሉ ብሏል።

የሀገር ውስጥ ገበያ 50 በመቶ መቀነሱን ያስታወቀው አየር መንገዱ በሀገር ውስጥ የሚያደርጋቸው በረራዎች እንደሚቀጥሉ ገልጿል።

አየር መንገዱ በመግለጫው የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑንም አስታውቋል።

ኤፍ ቢ ሲ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.