በአሁኑ ሰዓት ሁለት መጻሕፍት በማፈራረቅ እያነበብኩ ነው – ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ

Getachewደራሲዎቹ መጽሐፎቻቸውን እንዳነባቸው ቸሩኝ እንጂ አስተያየቴን እንዲህ ለሕዝብ እንዳካፍል አልጠየቁኝም።

አንዱ መጽሐፍ ዓቢዩ ብርሌ (ጌራ) የጻፈው “በሀገር ፍቅር ጉዞ (ቅጽ አንድ)” ሲሆን፥ ሁለተኛው ሀብታሙ መንግሥቴ ተገኘ የጻፈው “በራራ — ቀዳሚት አዲስ አበባ (1400 – 1887 ዓ.ም.) እድገት፣ ውድመት እና ዳግም ልደት ያልተነገረው የኢትዮጵያ ታሪክ” The Red Sea Press ነው።

berera abssiniaየመጀመሪያው ድብብቆሽ የሌለበት የግራ ርእዮተ ዓለምን ይዘው እስከ ሞት የታገሉ ወጣት ኢትዮጵያውያን ታሪክ ነው። ያለፍንበትን ዘመን ታሪክ ስለሚተርክ አንድ ቦታ ስደርስ ቆም አያልኩ እገረማለሁ፥ እደነቃለሁ፥ እቈጫለሁ፥ እቆታለሁ፥ “የልጅ ነገር” እላለሁ፥ እልፍ ስል፥ “ወይ ጀግንነት” እላለሁ። ዘመኑ አገር መውደድና በአገር ልጅ ላይ መጨከን እጅ ለእጅ ተያይዘው የሄዱበት ዘመን ነበር። ይህን መጽሐፍ መነበብ የሚገባው ከሚያደርጉት ውስጥ ዋናው፥ ቅድም እንዳልኩት የደራሲው እውነተኛነት ነው። መራሩን እውነት ውጧታል።

ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ ያለውን ዕውቀት ለማሟላት የሚፈልግ ሰው ከላይ የጠቀስኩትን የፕሮፌሰር ሀብታሙን የበራራ ታሪክ ያንብብ። ደራሲው መጽሐፉን የበራራ ታሪክ ይበለው እንጂ፥ ያዘጋጀው ከ1400 ዓመተ ምሕረት እስከ 1887 ዓመተ ምሕረት ድረስ የሆነውን የኢትዮጵያን ታሪክ የሚሸፍኑ ታሪካዊ ጽሑፎችን መርምሮ ነው። የመረመራቸው መጻሕፍት ለማንም እንደልብ አይገኙም። ሀብታሙ የሚያስተምረው በስመ ጥሩው ረትገርስ ዩኒቨርሲቲ (ኒዋርክ ኒው ጀርሲ) ስለሆነ ምንጭ ለማግኘት ብዙ ችግር አላጋጠመውም። እነዚህን ምንጮች ለማግኘት የማይችል፥ ቢገኙም ሁሉንም ለማጥናት ጊዜ ስለማይኖር የሐብታሙን መጽሐፍ ያነበበ ሁሉንም እንዳነበበ ሊቈጠር ይችላል። አንዳንዶቹን ሰነዶች በአባሪ መልክ እንዳሉ ቀድቶ አስገብቷቸዋል። መጽሐፉን የሚደመድመው ምንጮቹን (Bibliography) በመዘርዘርና ጠቍሙን (Index) በመደርደር ነው።

ፕሮፌሰር ሀብታሙ ያበረከተን የታሪክ ምንጭ ስለኢትዮጵያ ለሚታገል፥ ለሚዋጋ ኢትዮጵያዊ የድል መንሻ መሣሪያ ነው። የታሪኩ እውነተኛነት ጠላትን ሳይቀር በሰላም ይማርካል።

ሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ

5 Comments

  1. ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ሰላም ለእርስዎ ይሁን እርስዎ ጥሩ ነዉ ካሉን መግዛት ነዉ እንጅ ምን ምርጫ አለን እባክዎትን ይጻፉ እነ መሀመድ ሀሰንንም ተቆጡልን ማርከሻዉን እርሶ ካልቀመሙት ትዉልድ እንደ ተሳከረ ይኖራል።

  2. “ለኢትዮጵያዊ የድል መንሻ መሣሪያ፣ … ጠላትን ሳይቀር በሰላም የሚማርክ” “ታሪክ” ምን ያህል እውነተኝነት አለው?? “ታሪክ” ከሆነ የማንም መሳሪያ ሊሆን አይችልም። እውኑት የሁሉም ናትና! የአንድ ቡድን “መሳሪያ” ነው ስትል ግን በእጅ አዙር ፕሮፓጋንዳ ነው ልትለን ፈልገህ ነው?? capito!

  3. ሂርኮ ገመታ በእውነቱ ጥልያን ትሁን ጀርመን ከጽሁፍህ ለማወቅ ተቸግረናል የጻፍከው እሳቸው የጻፉትን ሳይሆን አንተ ስለሳቸው ልትጽፍ የፈለግኸውን ይመስላል ለዚህም ነው ጽሁፍህ ከጻፉት ጋር ግንኙነት ስላጣንበት የእውቀት አምላክ ግንዛቤን ይስጥህ የምንለው ማንበብህ ጥሩ ቢሆንም ካላገናዘብክና ካልተረዳህ እንዳነበብክ ስለማይቆጠር እንዲህ ያለ ነገር ስታደርግ ጥንቃቄ መውሰድ ግድ ይላል ያለበለዚያ ስድብ ይሆንብሀል በክፉ አትየው።

  4. If Addis Ababa is at one time “Berara” at any point in history, why I (we) didn’t hear till the publication of this book. Why any of Ethiopian Historians never mentioned this word. Or did I miss someone saying?

  5. Hirko Gamta In deed, it must be a propaganda. And, Prof. Getachew is not ashamed of doing so, as he succinctly phrased in his earlier book of’ Aba Bahrey’s and Other Documents Relating to the Oromos’ (my translation), for the honesty of which I thank and respect him!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.