የኮሮና ቫይረስ መከላከል የሁላችንም ኃላፊነት ይጠይቃል – ቫይረስ

ገዢዉ ፓርቲ ብልፅግና በመላው ሀገሪቱ የሚያደርገውን የፖለቲካ ስብሰባና የምርጫ ቅስቀሳ እንዲያቋርጥ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ በደብዳቤ ጠየቀ።
በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ብልፅግና እያደረገ ያለዉ ስልጠና የፖለቲካ እንቅስቃሴ ለአስከፊዉ የኮሮና ቫይረስ ያሳየዉ ቸልተኝነት እና ለህዝብ ያለዉ ንቀት የሚያሳይ መሆኑን የጠቀሰው ባልደራስ በሀገር ደረጃ ከፍተኛ ማህበራዊ ቀውስ ከመድረሱ በፊት ቅድመ ጥንቃቄ ባለማድረግ የሚከሰት ችግር ገዢዉ ፓርቲ ብልፅግና ኃላፊነቱን ሊወሰድ እንደሚገባ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ አስጠንቅቋል። ለብልፅግና ጽ/ቤት ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ለጤና ጥበቃ ሚኒስትር ጽ/ቤት ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ እንዲያውቁት ሲል በደብዳቤ ጠይቋል።

23

ተጨማሪ ያንብቡ:  በኢትዮጵያ የተጀመረው ለውጥ ግቡን እንዲመታ የአውሮፓ ህብረት ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል

2 Comments

 1. በሃገራችን አሳዛኙ ነገር በሆነውም ባልሆነውም መወነጃጀላችን ነው። ምንም ተተኪ ሃሳብ ሳያቀርቡ መንግሥት እንዲህ አደረገ እንዲህ ሳያደርግ ቀረ የሚሉ እንደ መስከረም አደይ ጊዜ ያበቀላችውና ነባር የዘርና የጎሳ ፓለቲከኞች እጅግ ያሳዝኑኛል። ምን ልስራ? በእኔ በኩል የምችለው የሥራ ድርሻ ምን ይሆን ማለት የለም። መግለጫና ጫጫታ ብቻ። ተጎዳሁና ድረሱልኝ ብቻ። በሽታው የሚገለው ዘር ለይቶ አይደለም። የሚናገረውም ቋንቋ ኦሮምኛ ወይም አማርኛ አይደለም። የሞት ቋንቋ ነው። እንዴት ሰው ባለቀ ሰዓት እንኳን ልዪነትን ወደኋላ አርጎ የሰው ነፍስ ለማዳን አይጥርም። ግን እድሜ ልኩን በሰው ነፍስ ሲቀልድና ሲነግድ የኖረ የፓለቲካ ድርጅት ነፍስ ማጥፋትን እንጂ ነፍስ ማዳንን የት ያውቅበታል? እንኳን አሁን ቀርቶ በደህናው ጊዜም ሆስፒታል ገብቶ ድኖ የሚወጣው ሰው በጣት የሚቆጠር ነው። የህክምናው ሥራም በዘር ከሆነ ሰንብቷልና!
  ይህ አመጣጡ ከወደ ቻይና ነው የተባልነው ለካፊ ቫይረስ ዓለም ከገጠማት የሁለተኛው የዓለም ጦርነት የባሰ መሆኑን የጀርመኗ የጣሊያኑ እንዲሁም የፈረንሳዊው መሪ ሌሎችም አስረግጠው ለህዝባቸው ተናግረዋል። ትላንት ብቻ 608 የሞተባት ጣሊያን አስከፉ ደረጃ ላይ ስትሆን፤ በአሜሪካ ኒውዪርክ ስቴት በሚጨበጥ መረጃ መሰረት ገመናቸው የከፋ እንደሚሆን የግዛቷ አስተዳዳሪ የራሳቸውን ዝግጅትና የድረሱልኝ ጥሪ አሰምተዋል። ቫይረሱ በፍጥነት የሚተላለፍ በመሆኑ እኔን አይነካኝም ማለት ጭራሽ አይቻልም። ይሁን እንጂ ይህን የቫይረስ ወረርሽኝ ተጠቅመው ለመበልጸግ የፍጆታ ዋጋ ከፍ የሚያረጉ፤ ያለሆነ ስራ ስር ነገር መድሃኒት ነው ብለው የሚሸጡ፤ የማላሪያ መድሃኒት እንደ አበባ ቆሎ የሚቅሙ፤ የውጭ ሃገር ሰው ሲያዪ ከሃገራችን ውጡልን የሚሉ፤ ሳልክብኝ ወይም ከፊቴ ላይ አስነጠስክ ብለው ድላ የሚገጥሙ ብዙ ናቸው። ይህ ሁሉ ግን ውስልትና ነው። ያለማውቅ ድንቁርና!
  ጠበል ያድናል ተብለው ከሃገር ሃገር የሚንከራተቱ፤ ጸሎትና ምህላ ይፈውሳል ተብለው ያላቸውን የሚያስረክቡ፤ ምንም ዓይነት ክሊኒካል መረጃ ባልደገፈው የቻይና እና የህንድ መድሃኒት እድናለሁ በማለት እንደ ቆሎ የቃሙ እና የታመሙ ቁጥራቸው እየበዛ ነው። ሌላው አሳዝኝ ተግባር መንፈሳዊ ነን የሚሉት ወስላቶች የሚያስተላልፉት ወሬ ነው። የዓለም ፍጻሜ እየሆነ ነው ይላሉ። ሌላው ደግሞ ተነስቶ ይህ ጉድ የመጣብን በበደላችን ምክንያት ነው ይለናል። 8ኛ ሺህ አይቶን ካለፈ ቆየን። ይህ የውስልትና ስብከት ህዝባችንን ያማታዋል እንጂ አይጠቅመውም። በልቶ ማደር የማይችል ህዝብ በሃጢአትህ ምክንያት ነው እዚህ ውስጥ የገባኽው ማለት ወንጀል ነው። ሞት መጣ ቢሉት አንድን ግባ በለው አለ የሃገሬ ሰው ለምኑ ነው ይህን ያህል ፍራቻው? የሽሮና የበርበሬ ማሰብ ይቀራል እንጂ ሌላ በዚህ ምድር ላይ የሚያጓጓን ምን ነገር አለ? ይህ ሲባል ሰው ለራሱ ብቻ እንደማይኖር አውቃለሁ። ታዲያ ግን በፍርሃትና በጭንቀት በሽታ እንጂ ጥንካሬ አይገኝም።
  ቫይረሱ ዓለምን ገና ጉድ የሚያሰኝ ይመስለኛል። ህንድ፤ ኢንዶኔዢያ፤ ፊሊፒንስ፤ በጣም ህዝብ ያለባቸው ሃገሮች ገና አልተነኩም። የቻይናው ወረርሽኝም በቻይና ሙሉ በሙሉ አልፏል ብሎም ማመን ጭራሽ አይቻልም። ስለሆነም ህዝባችን ለማያድን ነጭ ሽንኩርትና ሌላም አስመሳይ መድሃኒቶች መሰለፉን ትቶ የሚበላ ነገር በማከማቸት የመከራውን ጊዜ ለማለፍ መደበቁ መልካም ይመስለኛል። እናንተ የዘር ፓለቲከኞችም ዘርና ቋንቋቹሁን ወደ ጎን አርጋቹሁ በሰውኛ ቋንቋ ተናገሩ። ህዝብ ከሌለ ሃገር የለም። ሃገር ከሌለ ህዝብ የለም። ሃገርና ህዝብ ከሌሉ ደግሞ የምትፎልልበት የቋንቋ ፓለቲካህ ገደል ገባ ማለት ነው። በመዝጊያው ዘርን ጎሳን ሃይማኖትን ቋንቋን ተገን ሳናረግ ለህዝባችን የምንችለውን ሁሉ እናድርግ። ዝም ብሎ እርስ በርስ መዘነጣጠል ለህዝባችን አይጠቅምም። ህዝቡ የጠቀመውንና የበደለውን የፓለቲካ ፓርቲ ለይቶ ያውቃል። መልካም በማድረግ ራሳችንና ህዝባችን እንታደግ። ዓለም አጣብቂኝ ውስጥ ናት።

 2. በጣም አስቸኳይ!!!

  በመንግስት በኩል እና በህብረተሰቡ እየተደረገ ያለ ጥረት ጥሩ ቢሆንም መንግስት ግን የበለጠ ቫይረሱ እንዳይሰራጭ የሚከተሉትን ነጥቦች ቢያደርግ የተሻለ ይመስለናል፡
  1. ከውጪ አገር የሚገቡ በአንድ ቀን እስከ 400 ሰው እየገባ በመሆኑ በማቆያ ለመያዝ አስቸጋሪ ስለሚመስል ከውጪ አገር የሚገቡ ግለሰቦች በጣም አስፈላጊ ለሆነ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ላልተወሰነ ጊዜ ሙሉ የመግባት ዕገዳ ቢደርግ በ Video conference, Skype ወዘተ የሚፈልጉትን የስራ ትዕዛዝ ወይም ስብሰባ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ዘመድ ጥየቃ እና ሌላ ነገርም አስቸኳይ ስላልሆነ ለጊዜው በያሉበት አገር ቢቆዩ፡፡

  2. የጓንት፣ የአፍ ማስክና አልኮል እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ ስላላ በዚህ ላይ ጠንከር ያለ ስራ ቢሰራ፡፡ የውጪና የአገር ውስጥ ግብረሰናይ ድርጅቶች (NGO’S), ECA, AU Office እና ሌሎችም ይህንን ችግር ለመቅረፍ በአፋጣኝ ቢሰሩ፡፡ በዚህ ጊዜ ህዝብን ማዳን ካልቻሉ እዚህ ቢቀመጡ ምን ዋጋ አለው፡፡ የግላ ባለሃብቶቹም በየቤታቸው እኛን አይነካም ብለው ከሚደበቁ ያለህዝብ የነሱ ሃብት ዋጋ እንደሌለው አውቀው ያለቻውን በመርዳት ችግሩን ቶሎ ለመቆጣጠር ቢረባረቡ፡፡ መመሸጉ ዋጋ የለውም፡፡

  3. መንግስት ለጊዜው ከአዲስ አበባ ወደ ክፍለሃገርና ከዛም ወደ ከተማ የሚደረግ የትራንስፖርት እንቅስቃሴን ቢያስቆም፡፡ በጣም አስፈላጊ የሆኑ የምግብና ፍጆታ ቁሳቁስ እንቅስቃሴ በስተቀር፡፡

  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.