/

የኮሮና ቫይረስ የተባለው ወረርሽኝ 6 ደረጃዎች

banner 2“ከጣሊያን ዉጪ ያላችሁ ህዝቦች ሆይ ኮሮናቫይረስ የተባለው ወረርሽኝ ምን ይዞ እየመጣ እንደሆነ የገባችሁ አይመስለኝም……” አንድ ጣሊያናዊ ሃገሩ ጣሊያን ያለፈችበትን (እያለፈች ያለችበትን) የኮሮና ቫይረስ 6 ደረጃዎች(Stages) እንደሚከተለው ያስቀምጠዋል….

የመጀመሪያ ደረጃ – ኮሮና ቫይረስ ምን እንደሆነ ሁሉም ይረዳል:: የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ በሃገራችሁ ሪፖርት መደረግ ይጀምራል:: አብዛኛው ህዝብ ከባድ ጉንፋን ነው ምንም የሚያሰጋኝ የለም የሚል ምላሽ ይሰጣል:: ዕድሜየ 75+ አይደለም ስለዚህ ምንም የሚያሰጋኝ የለም የሚሉ ድምፆች በብዛት ይሰማሉ:: በሽታው እኔን አያጠቃኝም ፤ ለምን ሰዎች እንደሚያካብዱት አይገባኝም ፤ ፖኒክ (Panic) እየፈጠሩ ነው እንዲሁም የአፍ መሸፈኛና ሶፍት መጠቀም እንደማካበድ ይታያሉ:: ምንም የተለየ ነገር አልተፈጠረም ዝም ብለን በለመድነው የኑሮ አኗኗር አይነት እንቀጥል አይነት ጩኸቶች በብዛት ይሰማሉ።

ሁለተኛ ደረጃ – የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረ ይመጣል:: የመጀመርያውን ተጠቂ ያገኙበትን አካባቢ “ቀይ ዞን” ብለው የተወሰኑ ቦታዎችን ለብቻ የመለየትና የማግለል (Quarantined) ስራ ይሰራል:: አሁንም መንግስታት ምንም የሚያሰጋና የሚያስደነግጥ ነገር እንደሌለ ይናገራሉ:: (ይህም በጣሊያን የካቲት 22,2020 የሆነው ማለት ነው)። የተወሰኑ ሰዎች መሞት ይጀምራሉ ነገር ግን አብዛኛው ህዝብ ሚዲያዎችና የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ተመልካችን ለመሳብ የሚፈጥሩት ፍርሃት (Panic) እንደሆነ አድርገው ይቆጥሩታል። ዜጎች የተለመደ ስራቸውን ይቀጥላሉ … ስራ አይቆምም … ሰዎች የእርስ-በእርስ ግንኙነታቸውን እንደቀድሞው ይቀጥላሉ:: ቫይረሱ እኔን አያጠቃም….. እና ምንም አዲስ ነገር የለም… አይነት ድምፆች በብዛት ይሰማሉ::

ሶስተኛ ደረጃ – የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ቁጥር ይጨምራል:: በአንድ ቀን የቫይረሱ ተጠቂ በእጥፍ እየጨመረ ይሄዳል:: ተጨማሪ ሞቶች ይመዘገባሉ:: ቫይረሱ የተመዘገቡባቸውን አራቱን ቦታዎች (በጣሊያን የሆነው ማለት ነው) የብቻ በማግለል “ቀይ ዞን” ተብለው ይታወጃሉ:: በጣሊያን 25% የሚሆነው የአገሪቱ ቦታዎች እንዲገለሉ የተደረጉበት ወቅት ማለት ነው:: (መጋቢት 7,2020, በጣሊያን የታወጀው):: በእነዚህ አካባቢዎች ትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርሲቲዎች እንዲዘጉ ሲድረጉ ባሮች ምግብ ቤቶች ጭፈራ ቤቶችና የስራ ቦታዎች ግን ክፍት ሆነው ይቀጥላሉ። 75% የሚሆነው የጣሊያን የሃገሪቱ ክፍሎች ላይ ክልከላ ባለመጣሉ ሌሊት ላይ ወደ 10,000 የሚጠጉ ሰዎች “ቀይ ዞን” ተብሎ ለብቻ ከተከለለውና ማንም እንዳይገባና እንዳይወጣ ከተደረገው ቦታ አምልጠው ክልከላ ወዳልተጣለብት መኖሪያ ቦታቸው ይመለሳሉ(በኃላ ላይ ይህ ክስተት በጣም ወሳኝ ይሆናል):: ወደ 75% የሚሆነው የተቀረው የጣሊያን ህዝብ የተለመደ ስራውን እንደቀጠለ ነው። አብዛኛው ህዝብ በሽታው ምን ይህል ከባድ እንደሆነ እስካሁን አይገባቸውም:: መንግስት በእያንዳንዳችሁ እንቅስቃሴ እጃችሁን ታጠቡ ፤ አትጨባበጡ ፤ አትውጡ፤ በጋራ መንቀሳቀስ ክልክል እንደሆነና ሌሎችንም ህጎች በየቴሌቭዥኖቻችን በየ5 ደቂቃው ያስታውሱናል:: ነገር ግን እነዚህን ሁሉ ከቁብ የሚቆጥራቸው የለም::

አራተኛ ደረጃ – የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር እጅግ በጣም ይጨምራል። ትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርሲቲዎች በሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች ይዘጋሉ፤ ብሄራዊ የጤና አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ይታወጃል:: ሆስፒታሎችና ጤና መስጫ ተቋማት በኮሮና ታማሚዎች ከአቅም በላይ ይሞላሉ:: በቂ የህክምና ዶክተሮችና የጤና ባለሙያዎች እጥረት ይከሰትና ጡረተኞቹንና የመጨረሻ ዓመት የዪኒቨርስቲ ተማሪዎች እንዲያግዙ ጥሪ ይተላለፋል። ለዶክተሮችና የጤና ባለሙያዎች በፈረቃ መስራት በማስቀረት የተቻላቸውን ያህል እንዲያግዙ ይደረጋል። በዚህ ጊዜ ዶክተሮችና የጤና ባለሙያዎች በቫይረሱ መጠቃት እንዲሁም እነርሱም ለቤተሰቦቻቸው ቫይረሱን ማስተላለፍ ይጀምራሉ። ብዙ ታማሚዎችና ብዙ አይሲዪ (ICU) ፈላጊዎች የሚከሰትበት ነገር ግን ሁሉንም ማስተናገድ የሚከብድበት ወቅት ይሆናል። በዚህ ወቅት ሁሉም ሰው ጦርነት ውስጥ ያለ እስኪመስለው ድረስ ነገሮች ይከብዱበታል:: ዶክተሮች የታማሚዎችን የመዳን እድል በማረጋገጥ ብቻ ህክምና ይሰጣሉ:: ይህም ማለት በዕድሜ የገፉ፤ ስትሮክ ያለባቸውና የመሳሰሉት ህክምና ይነፈጋሉ:: ለሁሉም የሚበቃ በቂ ግብዓት ባለመኖሩ በሽተኛን መምርጥ ግድ ይሆናል። እየቀለድኩ ቢሆን ደስ ባለኝ ነበር ነገር ግን ጣሊያን ላይ የሆነው ይሄው ነው። የቫይረሱን ተጠቂዎች ሆስፒታሎች ማስተናገድ ባለመቻላቸው ሰዎች እዚህም እዚያም ይሞታሉ። አንዱ ዶክትር ወዳጄ አይኑ እያየ 3 የቫይረሱ ተጠቂዎች በአንድ ቀን ሲሞቱበት ይህን ክስትት “Devastated” በማለት ነበር የገለፀው። የቫይረሱ ተጠቂዎች ሲሞቱ ኦክስጅን ከማቅረብ ውጪ ምንም ማድረግ ያልቻሉት ነርሶች እንባቸውን መቆጣጠር እስኪከብዳቸው ድረስ በሃዘን ይዋጣሉ። የህክምና ባለሙያዎች በትክክል ትሪት ባለማድረጋቸው የወዳጄ ዘመድ ትላንት ሞተብኝ አይነት ድምፆች ጎልተው ይሰማሉ። እዚህም እዚያም ማጉረምረምና ስርዓቱ ፍርሷል (The system is collapsed) ዓይነት ጩኸቶች በሰፊው ይሰማሉ። በሁሉም የዜና አውታሮች የኮሮናቫይረስ ችግር በኢኮኖሚ ላይ ያለው ተፅዕኖ (The impact of Coronavirus on the economy) አይነት ዜናዎች በሰፊው ይሰማሉ።

አምስተኛ ደረጃ – “ቀይ ዞን” ተብሎ ከተከለለው 25% ከሚሆነው ከጣሊያን ክፍል ወደ ተቀረው 75% ወደሚሆነው ጣሊያን የገቡትን 10,000 ሰዎች ታስታውሳላችሁ? መላው የሃገሪቱ ቦታዎች ከማንም ጋ እንዳይገኙ (Quarantined) ይደረጋሉ (መጋቢት 9,2020, በጣሊያን የታወጀው ማለት ነው)። የዚህ ለይቶ ማቆያውም ዋና ዓላማ የቫይረሱን መተላለፍ መቀነስ እንደሆነ የሚመለከታቸው አካላት ይናገራሉ። ሰዎች ወደ ስራ መሄድ ፤ ሱፐርማርኬቶች እና ፋርማሲዎች ላይ መገበያየት እንዲሁም የተወሰኑ ቢዝነሶች ክፍት እንዲሆኑ ይታወጃል። ይህ ካልሆን ኢኮኖሚው እንደሚጎዳ ባለስልጣናት ይናገራሉ። በዚህ ወቅት አሳማኝ ምክንያት ማቅረብ ያልቻለ ሰው ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መንቀሳቀስ አይችልም። በዚህ ወቅት ከፍተኛ ፍራቻ ይፈጠራል:: አብዛኛው ሰው በአፍና በእጅ መሸፈኛ ሲንቀሳቀስ ነገር ግን አሁንም ራሳቸውን በበሽታው የማይጠቁ አድርገው የሚቆጥሩ (The invincible) ሰዎች ያለመሸፈኛ እንዲሁም በቡድን ሆነው ወደ ምግቤቶችና ምሽት ቤቶች ይንቀሳቀሳሉ።

ስድስተኛ ደረጃ – ከአምስተኛ ደረጃ ከሁሉት ቀን በኃላ ሁሉም ቢዝነስ በሚባል መልኩ እንዲዘጋ ትዕዛዝ ይተላለፋል:: ከሱፐርማርኬትና ከፋርማሲዎች በስተቀር ሁሉም አገልግሎት እንዳይሰጡ ይደረጋል:: ወደ ሱፐርማርኬትና ፋርማሲዎች ለመንቀሳቀስም የፍቃድ ወረቀት ማሳየት የግድ ይሆናል:: ይህም ሰርተፍኬት በመንግስት የሚሰጥ ይፋዊ ወረቀት ሲሆን በውስጡም ስማችሁን፤ ከየት እንደመጣችሁ፤ ወዴት እንደምትሄዱና ለምን ዓላማ እንደሆነ የሚዘረዝር ሰርተፍኬት ነው:: ይህንን ለማረጋገጥም በየቦታው ኬላዎች ይቋቋማሉ::
ያለበቂ ምክንያት ሲንቀሳቀስ የተገኙ ሰዎችም 206 ዩሮ ቅጣት ይጣልባቸዋል። ቫይረሱ እንዳለብዎት እያወቁ ከተንቀሳቀሱ ደግሞ ሆን ብሎ ሰውን በመግደል በሚለው ህግ ከ1-12 ዓመት የሚደርስ እስር ይጠብቅዎታል::

የፀሃፊው የመጨረሻ መልዕክት
ከመጋቢት 12 (March 12,2020) ጀምሮ በጣሊያን እየሆነ ያለው ከላይ የፃፍኩላችሁ ነው። እዚህ ላይ ልብ ማለት ያልባችሁ ይህ ሁሉ የሆነው በ2 ሳምንት ጊዜ ውስጥ ነው። ከሶስተኛ ደረጃ እስከ አሁን ድረስ ደግሞ 5 ቀናቶች ብቻ…ከጣሊያን ቻይና እና ኮርያ ውጪ ያላችሁና የኮሮና ኬዞችን ማየት ለጀመራችሁ የተቀረው የዓለም ህዝቦች የሚከተለውን ለማለት እፈልጋለሁኝ…ምን እየመጣባችሁ እንደሆነ የገባችሁ አይመስለኝም። አውቃለሁ እኔም ከሁሉት ሳምንት በፊት እንደናንተ ምንም አይገባኝም ነበር።

ነገር ግን ልላችሁ የምችለው ከባድ ጊዜ እየመጣባችሁ ነው። ቫይረሱ በራሱ የሚያመጣው የህመም ስሜት ወይም ገዳይ መሆኑ ብቻ እንዳይመስላችሁ ከባድ የሚያደርገው ነገር ግን ከእርሱ ጋ ተያይዞ የሚመጣው ተፅዕኖ እጅግ ከምገልፅላችሁ በላይ መሆኑ ነው። አገራት ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርገው ዜጎችን ከሚመጣው መከራ ጊዜ መጠበቅ እየቻሉ ነገር ግን ቫይረሱ ወደእነርሱ እንደማይደርስ በማሰብም ይሁን በመዘናጋት ምንም አለማድረጋቸው ኃላ ላይ ዜጎችን ከፍተኛ ዋጋ እንደሚያስከፍላቸው ማወቅ ይገባቸዋል (አሁን ላይ አሜሪካ ፤ ስፔንንና ፈረንሳይን መውሰድ ትችላላችሁ)።

እባካችሁ ይህን ፅሁፍ እያነበባችሁ ከሆነ በተቻላችሁ መጠን የራሳችሁንና በአካባያችሁ ያሉትን ጤንነት ለመጠበቅ ስትሉ የሚሰጣችሁን ምክር ተቀብላችሁ ለመንቀሳቀስ ሞክሩ። የበሽታውን እውነት ባለመቀበል ከቫይረሱ በፍፁም ማምለጥ አትችሉም። አሜሪካ ላይ እየሆነ ያለውን እውነት ማየት ትችላላችሁ። እውነቱን ባለመቀበል አሜሪካውያንን ምን ዓይነት ቀውስ ውስጥ እንዲገቡ እያደረጋቸው እንደሆነ ማየት በቂ ነው።

አሁን ላይ መንግስታችን እጅግ በጣም የሚመሰገን እርምጃ እየወሰደ ነው። ምንም እንኳ አሁን ላይ በሃገሬ ጣሊያን እየተወሰደ ያለው እርምጃ እጅግ በጣም ጥብቅ ቢሆንም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ከዚህ የተሻለ አማራጭ የለም። ቫይረሱን ለመግታት ቻይና እና ኮርያ ላይ እንደሰራው ሁሉ እዚህም ይሰራል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።

መንግስታችንም ዜጎችን ቫይረሱ እያመጣው ካለው የኢኮኖሚ ቀውስ ለመጠበቅ የወለድ መክፈያ ጊዜን ማራዘም፤ ሱቆቻቸውንና የተለያዩ ቢዝነሶቻቸውን እንዲዘጉ ለተገደዱት ቀጥታ ድጋፍ በማድረግ ለማገዝ እየሞከረ ነው። እነዚህ ሁሉ እርምጃዎች ምን ያህል ከባድ እንደሆኑ እገነዘባለሁ። ይህ ጉዳይ ደግሞ በአለም አቀፍ ደረጃ ሲሆን እጅግ ይከብዳል። ነገር ግን ከዚህ ዉጭ የተሻለ አማራጭ የለም::
ይህ ወረርሽኝ (Pandemic) ለህዝባችን እንዲሁም ለአጠቃላይ ለአለም ህዝብ አዲስ አቅጣጫ (Turning point) እንዲሆን እመኛለሁ።

(የጀስቲያንስ ኬቱርካ መልዕክት ነው)

via Asmish Ethiopia

3 Comments

  1. In the next eight weeks by May 2020 , fifty six percent of the California , USA population amounting to 25 million California residents are expected to get infected with CoronaVirus Covid-19 according to the California State in USA, Governor Gavin Newsom.

    California projects 56 percent of population will be infected with coronavirus over 8-week period | TheHill

  2. Doordash food delivery Corporation is saying it can cut the transmission by more than half in Africa if the governments of the countries such as the Ethiopian government gives Doordash Corporate business permits to start operations within weeks time from now.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.