ኮሮና ሆይ! እንደ ይህ አድግ ሰይጣን ስለላከሽ እግዜር ይይልሽ! – በላይነህ አባተ

EPDF Coronana Virus abssnia ኮሮና ሆይ! እንደ ይህ አድግ ሰይጣን ስለላከሽ እግዜር ይይልሽ!    በላይነህ አባተበላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

ኮሮና ሆይ! በህይወቴ እንደ አንቺ የጉልቤዎች ጉልቤ የሚባሉትን ሳይቀር ቤት አዘግቶ © ያንቦቀቦቀ ተዋጊ አላውቅም፡፡ በቅዱሱ መጽሐፍ አምላክ ምድርን ያሰመጠ የጥፋት ውሀ ልኮ በስግብግብነት፣ በሆዳምነት፣ በቀጣፊነት፣ በአስመሳይነት፣ በአድርባይነት፣ በሌብነት፣ በሴሰኝነት፣ በውሸትና በጭካኔ ሰክሮ ይሽቅብ ይሸና የነበረውን ልክ እንዳስገባውና  እንደጠረገው አውቃለሁ፡፡ በራሴ የህይወት ዘመን ግን ምድርን እንደ ገንፎ ተማማሰል አልፎ ህዋን እንደ አህያ የኋሊት በመራገጥ ያለን ጉልቤ አንጦርቅቆ ተቤት ያዋለ የማይታይ ኃይል ታንቺ በቀር አላውቅም፡፡

የሚያርመሰምሱት ታንክም ሆነ መርከብ በምድርና በባህር ሊያጠቃሽ አልቻለም፡፡ ተታንካቸውና ተመርከባቸው ተጣብቀሽ እሳት ትለቂባቸዋለሽ፡፡ አረቄ ትን እንዳለው በሳል ታንተከትኪያቸዋለሽ። እንደ ቀፈታም ሙሰኛም ተላይ ተላይ ታስተነፍሻቸዋለሽ፡፡ በተምዘግዛጊ ጀቶቻቸውም ሊከላከከሉሽ አልቻሉም፡፡ በድሮንም ሊያጠቁሽ አልቻሉም፡፡ ኑክሊየሩም እንደ ክረምት አይጥ ተቤት ተመደበቅ አላዳናቸውም፡፡ ተፈጥሮን በቁጥጥራችን ሥር እናውላለን የሚለው ቱሪናፋ በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመንም አልሰራም፡፡

መሰሪዋ ኮሮና ሆይ! ችግሩ አንቺም እነደ ሰው መሰሪዎች አውሬና ፍርደ ገምድል ነሽ፡፡ አንቺም ለገሰ ዜናዊና ጆሮ ጠቢዎቹ ህዝብ አንድ እንዳይሆንና ተበተታትኖ የጎሪጥ እየተያዬ እንዲኖር አስገድደሻል፡፡ እንኳን የአገርና የሰፈር ህዝብ ቤተሰብም እንዳይጨባበጥ፣ እንዳይሳሳም፣ እንዳይተቃቀፍና አብሮ እንዳይበላ አድርገሻል፡፡

አንቺም ወንድም ተወንድሙ፣ ወላጅ ተልጁ፣ እህትም ተህቷ እንዳይገናኙ እንደ እርጉሙ ይህ አድግ በክልል ከልለሻል፡፡ ምእመናን አብረው እንዳይፀልዩ፣  ሀዘንተኞች አብረው እንዳያዝኑ፣ ሰርገኞች አብረው እንዳይሰርጉ፣ ጎረቢቶች አብረው ቡና እንዳይጠጡ፣ እቁብተኞች አብረው እቁብ እንዳይጥሉና እንድርተኞች አብረው እንዳይቀመጡ እንደ ይህ አድግ የቁም  እስር አርገሽ አስቀምጠሻቸዋል፡፡ ይኸ ባህሪያችሁ አንቺንንና ይህ አድግን ወደ ምድር የላከው ቆራጣ ሰይጣን መሆኑን ያስረዳል፡፡

እንደ ይህ አድግ ሰይጣን ባይልክሽ ኖሮማ ፍትሀዊ ትሆኝ ነበር፡፡ ሰይጣን ባይልክሽ ኖሮማ እውነተኛውን፣ ባለማተቡን፣ ደካማውንና በሽተኛውን ትተሽ ነፍስ አጥፊውን፣ ተነፍስ አጥፊ የሚሞዳሞደውንና የሚወባራውን፣ ዘራፊውን፣ ሌባውንና በሰላሳ ዲናር እየተገዛ ንፁሀንን ለጲላጦስ አሳልፎ የሚሰጠውን ይሁዳ እየለየሽ እስተንፋሱን አፍነሽ ለኑዛዜና ንስሃ ታበቂው ነበር፡፡

እንደ ይህ አድግ ሰይጣን ባይልክሽማ የእጅ መታጠቢያ ውሃና የአፍንጫ መጥርረጊያ መሐረብ የሌለውን ትተሽ በድሃ ጉረሮ ጦር እየሰደደ፤ እየዘረፈና ተነፍሰ ገዳዮች እየተወባራ በንብረት የደለበውን አጋሰስ እየመረጥሽ አስጨንቀሽ ንስሃ ታስገቢው ነበር፡፡

እንደ ይህ አድግ ሰይጣን ባይልክሽ ኖሮማ ይህ አድግ ተእግዚአብሔር መንበር የኮፈሳቸውን ወስላታ ፓትሪያሪክና ጳጳሳት በሚያቃጥል ሙቀት እየለበለብሽ ለንስሃ እንዲበቁ ታናዝዣችቸው ነበር፡፡

እንደ ይህ አድግ ሰይጣን ባይልክሽ ኖሮማ ተማሪ ልጃገረዶች ተጅብ ላንቃ ገብተው በይህ አድግ መሪዎች አጀንዳ እየተመሩ ተጆሮ ጠቢዎች ጋር የሚያረጠርጡ ድስኩራም ምሁራንን የተወለዱበትን ቀን አስቆጥረሽ ቅሌታም ታሪካቸውን መርምረው ንስሃ እንዲገቡ ታስገድጃቸው ነበር፡፡

እንደ ይህ አድግ ሰይጣን ባይልክሽና እግዚአብሔር የላከሽ ብትሆኝማ ኖሮ ሕዝብ እንደ ፈንድሻ መበታተኑን ትተሽ በአንድ መስመር እንዲራመድና በቋንቋም እንዲግባባ ታደርጊው ነበር፡፡

ኮሮና ሆይ! ሰይጣን ሰለላከሽ ይኸንን ያህል ዘመን አድፍጠሽና ተደብቀሽ ኖረሽ በዘር፤ በክልልና ሕዝብን በቋንቋ ለመለያየት ዲያብሎስ በክርኑ በጎነጠው ለገሰ የተጠመቀው ጉድ ተዓለም ጤና ብጥበጣ  ቢሮ እንደ ቶፋ ሲጣድ “ጊዜው አሁን ነው!” ብለሽ መጣሽ፡፡ እንደመጣሽም ሕዝብን በቋንቋው እንዳይግባባ ተመለያየት አልፈሽ የዓለም ሕዝብ በክልልም ብቻ ሳይሆን ተቤቱ ታስሮ እንዲውል ያስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጅሽ፡፡

ይኸንን ከይህ አድግ የምትጋሪውን ሰይጣናዊ ባህሪ አይቶ ቀናውን ሕዝብ በጥሙናው፣ በተጸሎቱና በንስሃው እግዚያብሔር ይፍታው፡፡ አንችን ግን በኢትዮጵያ እንደ ተጣለው መርገምት ይህ አድግ ሳይታሰብ ሰይጣን በዓለም ስለላከሽ እግዜር ይይልሽ፡፡ አውሮጳና አሜሪካ ልክ ሲያስገቡሽ እንደ ይህ አዴግ በአፍሪካ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተመፈፀምሽ በፊት እድሜሽን ያሳጥርልሽ፡፡ አሜን፡፡

መጋቢት ሁለት ሺ አስራ ሁለት ዓ.ም.

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.