የኢትዮጵያዊያን እህቶች ባለውለታ ታላቋ ካትሪን አረፉ

89947417 3099728410048766 1787697802436935680 nከስድስት አስር አመታት በላይ ለኢትዮጵያ እና ለልጆቿ በተለይ በርካት ሴቶች ከፍተኛ ህመም እና ስቃይ የሚዳርጋቸው የፊስቱላ ህመምን በማስወገድ ዘመቻ ግንባር ቀደም ሚና የተጫወቱት ዶ/ር ካትሪይን ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።

ከባለቤታቸው ከዶ/ር ሪግራግ ሀመልተን ጋር ከ ስዲኒይ፣ አውስትራሊያ ወደ ኢትዮጵያ የዛሬ ስድሳ አንድ አመት በፊት በመምጣት ለአቅመ ሄዋን ያልደረሱ ሴት እህቶች በወሊድ ጊዜ የሚገጥማቸው የማህጸን መስንጠቅ(ፊስቱላ) ችግርን በመቅረፍ ረገድ የሚታወቁት የዘጠና ስድስት አመቷ ዶ/ር ካትሪን ከስድሳ አምስት ሺህ በላይ እህቶቻችንን ከስነልቦናዊ እና አካላዊ ቁስለት አድነዋቸዋል።

ዛሬ እሮብ አ/አ ውስጥ ከዚህ አለም በሞት የተለዩት የማህጸን ዶ/ሯ ካትሪን በብዙዎች ዘንድ” ተአምረኛዋሴት ፣ጻዲቋ ዶ/ር ፣የብዙሃኑ እህቶች እናት፣የእግዚአብሔር መልእክተኛ፣የኢትዮጵያ ማዘር ተሬዛ …ወዘተ “በሚሉት ስያሜዎች የሚታወቁ ሲሆን ቀደም ባለ ቃለምልልሳቸው ላይ የበጎ አድራጎት ስራቸውን በተመለከተ በስጡት አስተያየት”እኔ እንኳን ብሞት በኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉም ሴት እህቶች ከወሊድ ጋር በተያያዘ የሚደርስባቸው ህመም እና ስቃይ ጨርሶ እስከሚወገድ ድረስ የጀመርነው ዘመቻ መቋረጥ አይገባውም” በማለት ተማጽነዋል።

በአዲስ አበባ ፣በባህር ዳር እና በተለያዩ ከተሞች በሚገኙ ሆስፒታሎች እና ክልኒኮች ጋር የተጣመሩ ከአምስት መቶ ሀምሳ በላይ የሕክምና ባለሙያዎችን ያፈራው የዶ/ር ሪግራንድ እና ዶ/ር ካትሪን የፊስቱላ መታሰቢያ ተቋም በሚያደርጋቸው ምግባረ ሰናይ ተግባራት በአውስትራሊያ እና በተለያዩ አለማት ከፍተኛ እውቅና ለማግኘት ችሏል።

መልካም ተግባር ሁሌም ከመቃብር በላይ እንደሆነ የኢትዮጵያ እና የሴት ልጆቿ የክፉ ቀን ባለውለታዎች የሆኑት ዶ/ር ካትሪን እና ሟቹ ባለቤታቸው ዶ/ር ሪግራንድ በተግባር አስመስክረዋል። ለሦስት አመታት የስራ ኮንትራት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ከስድሳ አመታት በላይ ጉልበታቸውን፣እውቀታቸውን ፣ገንዘባቸውን እና ህይወታቸውን ጭምር ለኢትዮጵያ እና ለልጆቿ በገጸ በረከት ያበረከቱት ዶ/ር ካትሪን እና ባለቤታቸው አንድ ወንድ ልጅ ያፈሩ ሲሆን የአራት ልጆችም አያቶች ለመሆን በቅተዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  መምህር ግርማ ወንድሙ በ50 ሺህ ብር ዋስ ፍርድ ቤት ከእስር እንዲለቀቁ ወሰነ

(ታምሩ ገዳ/ህብር ራዲዮ)

4 Comments

  1. A sad day for Ethiopian women to have lost such a great caring and loving mother of all. We are very grateful to you Dr.Catherine for all what you did for Ethiopia and our helpless girls and women.RIP

    Very respectfully.

  2. Dr Hamlin was a true friend of Ethiopia who gave her life to the well being of Ethiopian Women for more than 50 years. Rest in peace, your legacy and amazing sacrifice will continue to live in the hearts of Ethiopians for generations to come.

  3. ፈጣሪ አምላክ ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑርልን ። ስማቸውም ከመቃብር በላይ ሆኖ በሕዝባችን ሲዘከር እንደሚኖር ተስፋ አደርጋለሁ ። በድጋሚ ነፍስ ይማር ።

  4. 61 golden years lived for those who were outcasts by no fault of their own. I remember reading about you decades ago and how you and your late husband just started to walk with your luggage from the old airport when you first arrived from Australia. you are our own saint Catherine of Ethiopia. RIP

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.