ጠቅላይ ሚንስትሩ ደግ አደረጉ~~~ (ዘላለም ጸጋዬ)

abiyከጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰሞኑ ንግግር ሊያስወቅሳቸው የሚገባ ነገር ቢኖር ምንአልባት ቁንጥጫውን ማሳነሳቸው ብቻ ይሆናል…እስቲ እኔም በጥንጡ በሳቸው ንግግር ላይ ላክልበትና አንዲያው ለመሆኑ በዚህ ዘመን ስላሉ ስለአፍሪካ በተለይም ስለኢትዮጵያ ምሁራን ከየት ልጀመር? የቱን አንስቼ የቱንስ ልተወው?

በየትኛውም የትምህርት ዘርፍ ብንሄድ ለአገር እድገት ከሚደክሙ እና ከሚጥሩ ምሁራን ይልቅ አገር የሚዘርፉ እና ኑሮዋቸውን እንዴት ማደላደል እንዳለባቸው ሲዶልቱ የሚውሉ የምሁር ነጋዴዎች በቁጥር ይበልጣሉ…የአገራችን መንግዶች እኮ ጠዋት ተመርቀው ከሰአት የሚፈራርሱት…ድፎ ዳቦ በሚያክል መጠን መደፋት ያለበትን ገረጋንቲ እና የአስፋልት ጨጭ ኢንጅነሮቹ ከህዝብ ሰርቀው እየሸጡ የጤፍ ቂጣ በሚያክል መጠን እየሰሩት አይደልም እንዴ?

ሁሉም ባይሆኑም የገዛ ወገኖቹ የመንግስት ሆስፒታል ሊታከሙ ሲሄዱ ወደ ግል ክሊንኩ የሚመራ ዶክተር አይደለም እንዴ አገሪቱ ያፈራችው? በመንግስት ተቀጥረው የሚሰሩትስ ዶክተሮች ቢሆን ግዳጅ ያለባቸው እንጂ ተከፍሎአቸው የሚሰሩ ይመስላሉ እንዴ? ስንቱንስ ያለአግባብ ሲያንገላቱት እይደለም እንዴ የሚውሉት?መንግስት ሆስፒታል ሲኬድ እንደ እንጀራ አባት እያኮረፉ በግል ሆስፒታላቸ እንደ ልጃገረድ የሚሽኮረመሙ ምሁራን አይደል እንዴ ያሉን? አጠፋሁ እንዴ? በየመንግስት መስሪያቤቱ በትምህርት ደረጃው የተቀመጠው ምሁር ተብዬ አኮ ባለጉዳይ ታክስ ከፋይ የአገሩ ሰው ሊያናግረው ሲሄድ የአባቱ እርስት ላይ የተቀመጠ ነው የሚመስለው…መማር ያደነቆራቸው ግብዞች፤መታበይ የሸፈናቸው ትእቢተኞች አይደሉ እንዴ ምሁራኖቻችን…እስኪ የምሁር ትሁት ጥሩልኝ አንድ ብለን ስንት ድረስ እንዘልቅ ይሆን? ፈረንጅ ሲማር ትህትና ይለብሳል የኛ አገር ሰው ሲማር ግን•••ጨርሱት

የፖለቲካል ሳይንስ ወይንም በጥቅሉ የሶሻል ሳይንስ ምሁራኖቻችንስ ቢሆን ለህሊናቸው የማይገዙ ገንዘኛ እና ለመጣው ስርአት ሁሉ አጎብዳጆች አይደሉም እንዴ? አውራውን ለመጥቀስ ያክል አዲስ አበባ ዪኒቨርስቲን የሚያክል ተቁዋም ይመራ የነበርው ዩኔስኮ ይከፍለው የነበረው፤ ጠዋት ሌላ አፍሪካ አገር አስተመሮ ማታ ስድስት ኪሎ ይገኝ የነበረው፤በምስራቅ አፍሪካ CIA ኤጀንት የነበረው የኢንተር አፍሪካ ግሩፕ መስራቾች አንዱ፤ አንቱ የተባለው የህግ መምህር ፕሮፌሰር እንድርያስ እሸቴ ኢትዮጵያ በእንብርክክዋ ስትሄድ የመለስ ልዪ አማካሪ አልነበረም እንዴ? ሁሉንም ባይሆን የተወሰኑቱ የዩኒቨርስቲ ምሁራንስ ተማሪን አሸማቃቂ አይደሉም እንዴ? እንደ ንጉስ እንድናያቸው እንድንሰግድላቸው ሁሉ ይሹ አልነበረም እንዴ?•••ወንድሜ ዶ/ር ደረጄ ጸጋዬ እኛ እኮ አንዲት ነገር ላይ አተኩረን ነው ማስትሬት እና ዶክትሬት የምንይዘው ህዝቡ ደርሶ ሊቃውንት ያረገናል እንጂ ይለኝ ነበር እናም በዛች አንዲት ነገር እየተጨበጠች በመጣ ምሁርነት ስም ነው የሚነገድበት የምንሰግድበት።

መቼም የቀድሞ ስርአት ውስጥ ገብቼ…ሶፍያን አሕመድ የገንዘብ ሚኒስትር ሆኖ ከሀገር ውስጥ ገቢ እስከ ጉምሩክ በዘረጋው የሌብነትና የዘረፋ መረብ በአጠቃላይም በሃገሪቱ የፋይናንስ ፍሰት ሲቀልድና ሲያስቀልድ የኖረ፤…ሽፈራው ጃርሶ የውሃ ኃብት ልማት ሚኒስትር ሆኖ ሳለ የውሃ ኃይል ማጎልበት ቴክኒዎሎጂ ከማስገባት ጀምሮ…ሲዘርፍ የኖረ እያልኩ መቀሌ ድረስ ከተነተንኩ ኮሮና ጠፍቶ ሌላ ተስቦ ይመጣል…እናም በመሪነት ይቀመጡ የነበሩት የሌብነት ሮል ሞዴል በመሆናቸው በርካታ ምሁራን ከመደበኛው ባለሙያነቱ ይልቅ ወደ ፖለቲካ ሎሌነት ሲሽቀዳደም ይታያል።

ተቃዋሚ ፖለቲከኖቻችንስ ቢሆኑ የተማሩ ግን ጥበብ የጎደላቸው ሆነው አይደለም እንዴ አገር የሚያምሱት…አንዳንዶቹስ እድሜ የማያስተምራቸው ከ66 የተማሪዎች እንቅስቃሴ ጀምሮ ዛሬ ከዚህኛው ፖለቲካ ድርጅት ነገ ከዛኛው ሲያመንዝሩ የሚኖሩ አይደሉም እንዴ…ከዚህኛው ተጋብትው ፊርማቸው ሳይደርቅ የድርጅታቸውን አባሎች ምን ይላሉ ሳይሉ አይደለም እንዴ ነገ ከሌላኛው ተጋብተው የሚገኙት…ግማሾቹስ አልፈው ተርፈው ለህዝብ ጥቅም ሳይሆን ለግል ጥቅም ሲሉ ከገረፋዋቸው፤ያቺን ታላቅ አገር ለዚህ ትርምስ ከዳርጉት ጋር አይደለም እንዴ አሸሸው ገዳሜ ሲሉ የሚውሉት::በውጪው አለምስ ተምረናል እያሉ የሚኮፈሱት ምሁራን የዘር ክፍፍልን ከማባባስ ያለፈ ምን ጠቀሙ።ምድረ ምሁር ነኝ ባይ እና ፖለቲከኛ ዶ/ር አብይ ዲሲ የመጣ ግዜ ገበናቸውን አልገለጠውም እንዴ? የድርጅታቸውን አቁዋም እንክዋን ለይተው የማይውቁ አይደሉም እንዴ?

ብዙዎቻችን ፖለቲካ እንደኮምጣጤ ስለሚጎመዝዘን ዝም ብንልም ከምናየው ከምንሰማው እንክርዳድ እና ስንዴ መለየት አያቅተንም…ይሄን ሁሉ ስል በጥቂት ክፍያ አገሬ ብለው በየዘርፉ ከልባቸው የሚሰሩትን ንኡዳን ክቡራን ምሁራኖቻችንን አይወክልም…አንደኛ አመት አያሉ ይዘውት የመጡትን የክርስትናም ሆነ እስልምና ሀይማኖት ዶክትሬት ላይ ሲደርሱ ያልጣሉ…ያስተማራቸውን ገበሬ ያልረሱ…የአገር ፍቅራቸው ያልከሰመ…ግለኝነት ያልጎበኛቸው…ትህታና እና ግብረገብነት ያልተለያቸው…ክብር ለጥቂት ግን ብርቅዬ ምሁራኖቻችን ይሁን…በተረፈ ግን ጠቅላይ ምኒስትሩ ደግ አደረጉ!

አበቃሁ!

11 Comments

 1. Thank you even though it is sour to swallow among the Ethiopian elite there is pride deep in our blood and it is a barrier to understanding each other. why do we need over hundred parties if we really think first to Ethiopian unity before our own fame, control, power and prosperity.
  Why are we afraid of the coming election? Because the parties, the elites, even the government thinks first for the power and control of each and everyone and we do not trust each other and education is used for the wrong purpose and these kind of evil mentality has hindered us from moving forward and to live in distrust and fear.
  we need to detoxify ourselves from cancerous thought to ourselves and our country.
  God bless and protect Ethiopia.

 2. ልጠይቅህና፣ እንቁላል ወይስ ዶሮ ነው የመጀመሪያው? እዉቀት አልባ ሃገር እንዲፈጠር ያደረጉት እንደ መንግስቱ፣ መለስ እና አቢይ ያሉ ዲክታተሮች አይደሉም እንዴ ስንቱን ብሩህ አዕምሮ ጨፍጭፈው፣ ወይም ካገር አባረው፣ የተቀረው አቀርቅሮ የማህይማን መሪዎች መቀለጃ እንዲሆን ያደረጉት??

  ልጠይቅህና፣ ያለ ምሁራን አስተዋጽዖ በስልጣኔ ወደፊት የገፋ ሃገር የምታውቀው አለህ?

  የምናውቃቸው በስልጣኔና በሃብት የመጠቁ ሃገራት፣ የሃሳብ ነጻነትን ያለገደብ በመፍቀድና ምሁሮቻቸውን በደንብ በመንከባከብ፣ ንዋይ አፍስሰው ሳይንሳዊ እና የተክኖሎጂ ፈጠራ በማበራከት ስለጣሩ ነው። በኢትዮጵያ ግን ሆዳም እና አጎብዳጅ ምሁር ነኝ ባይ ቢበራከት፣ ተጠያቂው የአቢይ አይነቶቹ ደናቁርት መሪዎች ናቸው! እነዚህ ከተራ ማህይም በተሻለ ደረጃ ማሰብ የማይችሉ፣ የሃገር ዕድገት እና የህዝቡ የኑሮ መሻሻል ሳይሆን የፖለቲካ ስልጣናቸውን ዘላለማዊ ለማድረግ፣ በአደንቁረህ አደህይተህ ግዛ በሚል የጥንት የሃበሻ ነገስታት ፈሊጥ በመከተል ምንም አይነት ሂስ የማይቀበሉ እኔ ብቻ አዋቂ ባይ የዕውቀት ጠላት አምባገነኖች፣ ምሁራንን በጠላትነት በመፈረጅ ሲጨፈጭፉ ሲያስሩ እና ሲያሳድዱ፣ በዬት ብሎ አዋቂ እና ዕውቀት ባገር ይኑር??

  በዚህ ንግግሩ አቢይ ራሱ ከዕውቀት ነጻ መሆኑን ብቻ ነው ያስመሰከረው! ዘራፊና ሌባ ሰብስቦ ስልጣኑን ከማደራጀት አልፎ፣ በዝርፍያና በሌብነት ቱጃር የሆኑትን በማመስገን ያን ጥቂት እውነተኛ ምሁራን ለማስመታት በአደባባይ ማወጅ ወዴት ልወስደን እንዳሰበ ግልጽ ነው። ይች ላትድን በጠና የታመመች ሃገር እንዲያበቃላት፣ ምድረ መሃይም ተያይዞ ገደል እንዲገባ እውነትም “ጠቅላይ ምኒስትሩ ደግ አደረጉ!”

 3. Fact 1. Intellectual or not intellectual we all need protein in our diets to use our knowledge . Neurotransmitters in the brain are made up of Amino acids , amino acids are gotten by eating meat poultry , that’s why the Ethiopian government needs to ban exporting meat poultry to outside Ethiopia mainly to Arabs oil countries , keep the meat locally available for Ethiopians.

  Fact 2. Whether a person is an intellectual or not, does not make a difference on how good or how bad he acts . His intentions counts on how he uses his skills not whether he is intellectual or not. Meles Zenawi used all his skills to attack Amara , now PM Abiy is using his skills to attack Amara too, no reform is done for Amara , only Tigre’s regime Amara attacker got replaced by Oromo’s regime Amara attacker.

  Fact 3. Amara is the backbone of the moral standard , that’s why EPRDF PP attack Amara , now Abiy is attacking intellectuals and praising Arab Oil money investors, well if that is the case give Amara the chance to live in peace so we can work and become investors , why only Arab investors china and their puppet crumb eaters banda’s use Ethiopians natural resources while other Ethiopians are hunted down in their own country for having good intentions and world reknown moral character standard they adhere to.

  For example
  -If Universities sell degrees to iletrate individuals it is illegal is wrong.

  -If an illetrate day laborer carries empty boxes back and forth pretending to be carrying products within the boxes then at the end of the day threatening violence if he doesn’t get paid $10 birrs per trip for each box it is illegal and it is wrong.

  -If a rebel fighter illetrate Prime Minister illegally holds the Arat Kilo then goes back and forth to cameras with empty promises for two whole years pretending to reform then at the end of the month collecting a salary as if he did bring a reform it is illegal and wrong.

  -If a policeman used his gun to shoot and kill innocent civilian the way he used his ammunition illegall is wrong.

  -If a butcher sells donkey meat as if it is a meat from a cow it is illegal is wrong.

  -If a farmer sells truck full of cow manure as if it is coffee crop it is illegal it is wrong.

  -If a University history Professor teaches in his classrooms how Sefari Menilik cut Oromo women breasts Anole ,it is illegal is wrong.

  -If a taxi driver backs his taxi into a stoped diaspora tourist vehicle then claim the diaspora rear ended him hitting his taxi from behind and demanding money for his damage and severe personal injuries it is illegal is wrong .

  -If judges set criminals free while punishing innocent people it is illegal is wrong.

  Conclusion : Until the ethnicity of an Ethiopian is nomore significant than his moral character ….. Ethiopians will not be able to use their knowledges.

 4. ፅሁፍሕ መልካም ነገር ቢኖረውም ብዙ ነገሩ ራስህን ነው የገለፅክበት ??? አንተም ያው ነህ

 5. ማንም ቢሆን የሚያጭደው የዘራውን ነው ። መንግሥትም ሆነ ምሁራን የሕዝባችን ነጸብራቅ ናቸው። ጭቆናን ፣ ብዝበዛን ፣ ሌብነትን ፣ ሙስናን ፣ ዋልጌነትና አጎብዳጅነትን መሸከም የማይችል ትከሻ ያለው ህብረተሰብ ጭነት እንደከበዳት አህያ ተሸክሞ አይንገዳገድም መጎዳቱን ቢያውቅም አብሮ ወድቆ ጭነቱን አራግፎ ይነሳል ። እኛ ግን 50 ኪሎ ድንጋይ ከብዶን 100 ኪሎ ጥጥ ስንጫን የቀለለ ይመስለናል ። እንዲህ አይነቱ ህብረተሰብ ውስጥ ያሉ በጣት የሚቆጠሩ እውቀታቸውን የዋጋ ተመን አውጥተው በሚያዋጣቸው ወይንም ትርፍና ኪሳራን አስልተው ሸጠው የማይኖሩ ምሁራንን የኃፍት ምንጩ ከማይታወቅ ተራ ነጋዴ ጋር ማነጻጸርና እንዲሁም አሳንሶ ማየትን እያውም ከአንድ መሪ የሚጠበቅ ተግባር አድርጎ ማየትና እንዲያውም አንሷል ብሎ ሞራል መስጠት የሚያሳፍር ተግባር ነው ። መንግሥት ምሁራን የኑሮ ደረጃቸው ከተራው ህዝብ ያልተሻለ ሆኖ መኪና መግዛት አለመቻላቸው ሊያሳስበው ሲገባ መኪና የላቸውም ወይንም መኪና መፈብረክ አልቻሉም ብሎ መቀለድ ያሳፍራል ። ለአዲሱ ትውልድስ የሚያስተላልፈው ምልእክት ምንድነው ? ተማሪ ሆነን በጣም ለፍተውና አጥንተው ለውጤት የሚበቁ ተማሪዎችን ሞራል ለመንካት ሰነፍና ኮርጀው ነጥብ የሚያመጡት ተማሪዎች “ከአመት ጥናት የአንድ ቀን የአይን ጥራት” ይሉ ነበር። እነሱ መኮርጃቸውን እንጂ አመት የለፋው ጎበዝ ከጎናቸው ባይኖር መስረቅ እንደማይችሉ አልተረዱም ። የጽሁፉ አቅራቢ ወንድሜ ፍርድህ አመክኒዮ አልባ ነው የሚል እምነት አለኝ።

 6. ስለ ምሁር ያለህ አስተሳሰብ ውስን ለመሆኑ በሚገባ አስመስክረሃል። የፓለቲካ ሳይንስ መማር በግድ ፓለቲከኛ እንደማያደርግ ሁሉ፣ ስለ ኤኮኖሚ የተማረ ሁሉ ነጋዴ እንደማይሆን ዓለምም ምስክር ነች።እኛም በኢትዮጵያችን ጠ/ሚራችንን ማየት ይበቃል። ባንተ አስተሳሰብ አገሪቷን ምሁራን ካበላሿት ፣ ምሁራን እንደሚሉት፣ አሣ መበላሸትና መግማት የሚጀምረው ከጭንቅላቱ(ከራሱ) ነው የሚሉትን በኢትዮጵያችን እየታየ ነው።
  እንግዲህ አያ ጅቦ ሳታመሃኝ ብላኝ እንዳለችው ፣ ጠ/ሚሩን ማወደስ ከፈለግህ ሳትዟዟር አቋምህን ግለፅ እንጂ በስንት መከራ የተማሩትን ያሉትን ምሁሮች አጠቃለህ እንደ ጠ/ሚርህ አትፈርጅ ። ተምሮ መሀይም መሆን ወ/ ካለመማር አንደኛውን አለመፈጠር ይሻላል ይላሉ የግእዝ ምሁራን ። ከገባህ።

 7. አት ዘላለም ጸጋዬ ጠ/ሚ አብይ አህመድ ጥፋታቸውን አምነው ይቅርታ ጠየቁ አሁንም ደግ አደረጉ ነው የሚሉት ወይንስ ተጸጽተው እርሶም ይቅርታ ይጠይቃሉ ? በጭፍን መደገፍ ወይንም መቃወም ሁኔታው ያልተጠበቅ ውጤት ሲያስከትል እንዲህ ማጠፊያው ያጥራል ። አሁን ነው የሞራል ልእልናዎ ፈተና ላይ የወደቀው እባኮ በነካ እጅዎ እንደ ጠ/ሚ አብይ ወይ ይቅርታዎን ካልሆነም በአቋሞ መጽናትዎን በዚሁ በዜሀበሻ ጀባ ይበሉን እንጠብቃለን ።

  • Zegeyedelu

   Please be specific why you think I should ask for forgiveness because I got no clue , if anything just so I don’t repeat the action I deserve to be told what is it I did which you expect me to apologize for, otherwise If I ask for forgiveness now without having any clue why I might repeat the actions after apologizing which defeats the whole purpose of the forgiveness process, as many in our society are doing since I was not made aware what specific thing or action I am apologizing for , as we see happening in our country since many apologizing without the specific action not discussed.

   Asking for forgiveness is being thrown around as a used old socks in every instance within the Ethiopian society currently , some ask for forgiveness with noone knowing why including themselves the ones asking forgiveness not knowing to what specific reason they are asking the forgiveness for.

   In our society many who knowingly commit crimes also plan before hand when and to whom they will ask forgiveness after they commit the crimes, as long as they donot get asked for restitution there are people ready to ask for forgiveness all-day everyday for the rest of their lives they plan to ask for forgiveness ahead of time before they commit their crimes nowadays , sadly forgiving is loosing it’s sincerity among the children who grew up looking at such examples .

   Bekentu simen atitra
   Donot call my name in vain

   Donot ask for forgiveness in vain

   Many in our society encourage asking for forgiveness by calling his name all-day everyday only to repeat the action they had been apologizing for every night .

 8. ጎበዝ ብርሀኑ ነጋ ነው ወንድሙ ያልከኝ ስምህን?
  አንተን መሰሎችህ አካኪ ዘራፍ አላችሁ እንጅ ግለሰቡ እኮ አልተሳሳተም እንደምንም ብላችሁ አቶ የሚሉውን መጠሪያ በገበሬው ታክስ ከለወጣችሁ በሁዋላ የላችሁም መገልገልን እንጅ ስታገለግሉ አናይም ውጭ ለመውጣት ከማንም በላይ እድሉ አላችሁ ኑሮ ስታመቼቹ እንጅ በሀገር ጉዳይ ከጥፋት በስተቀር የሰራችሁትን አላየንም። እንደው ምን ይሙት እናንተን ከግብጽ ምሁራን ከሻቢያ ምሁራን አንጻር ስናያችሁ በጣም እናፍርባችሁዋለን በእርግጥ የእውቀትና የእውነት ልክ የሆኑትን እነ ፕሮፌሰር ጌታቸው ሀይሌን ሀይሌ ላሬቦን ሻለቃ ዳዊትን ኢንጅነር ይልቃልንም ውለታቸውን በክፉ ቀን አንረሳውም። ተው አትነካኩን ሰላማዊ ሰልፍ ወጥቶ ግፈኞችን መቃወም ለተራው ዜጋ የተሰጠ ይመስል ሰልፍ ሲባል ድራሻችሁ የለም ወይም ሰብስብ ብላችሁ ለተመድ ወይም ላለው መንግስት የዜጎችን በደል ስታሰሙ እናይም እንደውም ከግፈኛው ደርግ ዘመን ጀምሮ እስከ ትግሬዎች መንግስት አሁን ደግሞ እስከ ቄሮ መንግስት ዋና መሪዎች ማን ሁናችሁ ነው አትንኩን የምትሉን። ሽመልስ ታውቁታላችሁ ልዩ መለያው ባንድራው የሆነውን እስክንድር ነጋ ሀብታሙ አያሌው አንዱአለም አራጌን የልጅነት ዘመናቸው በግፈኞች የተቀማውን ለነሱ ክብር አለን ኢትዮጵያ ወደ ቀድሞ ክብሯ ስትመለስ ሜዳልያቸውን እንሰጣለን።
  አይ ምሁራን ይልማ ዴሬሳ አዲስ አለማየሁ አክሊሉ ሀብተወልድ ከተማ ይፍሩ በተፈጠሩበት አገር በቴክስት ምሁር ነን ስትሉን አይመችም ለነገሩ ለነሱስ መወገድ ዋናው አርቴስቶቹ በረከት ሐስላሴና ፕሮፌሰር መስፍን አይደሉ? ሰውን ብዙ ጉድ አለን ወረቀት ተስጥቷችሗል እውነት ነው ምሁር ነን ግን አትበሉን።

 9. My grandfather in his shorts was at a boarding school in Addis Ababa when pegeaut 404 was the choice of transportation of Haile Selassie’s ministers. Him and his friends would go to SEYTAN BET to watch movies and get inspired to say all those uneducated ministers would leave their cars and their positions to them one day. They were still in high school mind you.

  I think very little has changed since. The students of the 1960s were sure they were the first educated class of Ethiopia.

  My generation didn’t feel entitled to anything. We were all about surviving and dodging the military service. We didn’t have any political leaders or even politics. Some of my generation went straight to college at home and most of us did go to college part time for years and quit and went back again eventually.

  At my last class in High School we were about 40, 22 girls and 18 boys. We are now in eight different countries. The top students chose science and engineering and two of them are physicians. For some reason none of us are in politics. Typical to our part of the city we came from diverse back ground. Only after we started to have children did religion become important.

  I think we are very much Ethiopians. Because some of us kept communicating for decades we are generally aware of each other’s whereabouts. Most of us left at early age. I look at 17 and 18 year old kids and wonder how a mother would let her child leave the nest into the wilderness; a father with the means to provide would rather gamble on his child’s life than see him dead in a useless war that was lost before it started.

  I didn’t graduate from the best school of Europe or America but some of the entitlement issues that hasn’t changed since my grand father’s high school days 70 years ago makes me wonder.

  I like my generation. The love was very strong. We really cared and helped each other leave the country. My generation dreamed of leaving the country since elementary school. I remember my third grade teacher beautiful Sophie getting sad when she found out going to America was the most popular thing her class wanted to be.

  And then two years ago everything changed. We started to think of going back home for good when our kids leave the nest. Is it selfish? Ethiopia never left our hearts. Some of us have been out of the country for twice as long as we lived in. We waived the flag and protested some times. We said ‘shame! shame! shame!’ in winter and summer at Ethiopian Embassies and ‘free Teddy Afro’, free Birtukan etc. etc. We gave money to causes we thought were worth fighting fore. We were there when Tamagn Beyene came to town and got inspired by his pure gold speeches of love of country and danced at Teddy Afro’s concerts.
  We didn’t really believe Berhanu, NeAmin and Ephrem will make it alive but we supported them even more after Andy got picked in Yemen because they were the real ones who were putting up a fight.
  Abiy Ahmed changed everything.

  My generation was not poisoned by ethnic politics. Genral Kasaye Chemeda or General Tesfaye Habte Mariam or the many Ethiopian war heroes that are alive today are just Ethiopians like their forefathers. They were good at their jobs and they left a legacy which will be remembered for generations to come.

  Abiy is younger than myself. I don’t think he is perfect and I don’t agree with everything he does but I’ve never read anywhere in Ethiopian history the leader bringing back Ethiopian prisoners back home in his plane. I don’t think Abiy’s Ethiopia is political for him, it is Ethiopia in a normal sense. And his young Govt is avoiding bloodshed the best it can. If it was Mengistu he would have bombed Mekele by June 2018 after the failed attempt on his life.

  There are things he can do right now and there are things he can not do to my understanding. There are some who are breaking the law and they know it and he knows it and the rest of us know it too. What would’ve happened if he purged those responsible for killing the Addis kids after he came to power?

  I think our culture of being happy with absolute dictator that has full control of the entire land no matter how cruel…MEYSAW KASSA in 21st century rather than the wise men of Shawa and Jimma proper that knew when to let go in 19th century and made a miracle….If Emperor H/Selassie didn’t rush in destroying the federation probably will cause a constitutional and only symbolic monarchy but there wouldn’t be any war. THAT UGLY SENSLESS WAR of 30 years. LEMMA BEGEBEYA was the Amharic text book which symbolized their struggle and they had no problem with living together, where were you for 50 years big brother?

  NO RUSH NO MORE.

  In 1961 some African countries didn’t have college educated natives to take over from colonialists. IDI AMIN was one of the only two African officers at the time of independence and he didn’t read or write in any language. In the same year Ethiopian university students were in thousands at home and abroad. Ethiopian army colonels were getting medals for what they did ten years earlier in the Korean war. Ethiopia was doing stuff internationally to be inspiration to the Ho CHI MINH and chairman Mao let alone Africans. And you thought the Rastafarians were crazy for thinking Haile Selassie was Jah.

  The British colonizers tried to tell the west Africans they were two generations ahead of their Eastern Africa colonies. But you didn’t need to be colonized to go to high school, Menelik had a school in Addis and had to fire the Coptic teachers because they were useless.

  The same people who told Africans that Ethiopians were not really ‘black’ told the Arabs that Ethiopian blacks were colonizing Arab Eritreans.

  My grandfather was sent to Europe for some education against his will. He was sent anyways kicking and screaming. He protested he doesn’t want to be catholic or protestant and that was why he didn’t want to go. His teachers were Canadian Jesuits from Montreal so if they didn’t make him catholic he would be fine he was told. He was homesick on his way to Europe and was in Ethiopian embassy 50 miles away from his graduation ceremony trying to get a plane ticket. And when I was a kid he used to boast about the blondes he dated in school. He talked about Europe for the rest of his life but never about the racism. Never. I miss him. He didn’t like alcohol or Khat and he didn’t come from rich family, his father was a common peasant. He only had one wife and only two kids, FETARI ALALEWM he said often, but he raised his nephews from childhood up.

 10. This maths didnt add up ur grandfather was in high school 70 years ago born ur dad lets say say ur dad is in his 40th I think you are unborn child communicating us in miracle. This is what they said semntgnawu shih.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.