አይ ባሕር ኃይላችን !!! –  በኮማንደር አሰፋ ሰይፉ

ባሕር ኃይል ሊቋቋም ነው!! ሲባል ያልተደሰተ ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለኝም፡፡ ከተደሰቱት ወገኖቼ ጋር እኔም ስቆጠር የእኔ ደስታ ለየት ያለጥቅምንም የያዘ ነበር፤፡ ይፈቀድልኝና ላብራራው፡፡

አኹን ግን ሃዘኑ ይክበደኝ ብስጭቱ አላውቅም !!!

ethiopian navyበቀደምት ግን፦ ራሴን ላስተዋውቅ፦ ይኸውም ኢትዮጵያችን በን። ነገሥቷና መንግሥታቸው ጥረት የባሕር በሯን ስታገኝና የባሕር ጠረፏን የመጠበቅ ግዴታዋን የመጠበቅ ግዴታዋን ለመወጣት የባሕር ኃይል ስታቋቋም የጀመሪያችው የባሕር ኃይል ኮሌጅ ( አካዳሚ) ስትከፍት በእጩ መኮንነት ከገቡት ውስጥና  የጦርነት ግዳጃቸውን ሲወጡ ካለፉትና ጌታ ከጠራቸው ከቀሩት ከመጀመሪያዎቹ አንዱ ነኝ፡፡

ለመኮንንነትና ለባለ_ማረገኞች እንዲሁም ለተለያዩ ሞያዎች ለውጪ አገር አሠልጣኞች እምዬ ያወጣችው፦ ያውም ሳይኖራት ፦ አንገት ያስደፋል፡፡ ይኽን አልፋ በአጠቃላይ ግዳጇን በገዛ ልጆችዋ ልትወጠው በደረሰችብት ጊዜ፦ የግልበጣና የጦርነቱ ጊዜ ተፋፋመ፡፡ ስንቱ አገራችን በየትምሕርቱና ሞያ ያስተማረችውንና ያሠለጠነችውን አፈር በላው፡፡ ያደለው (ሕይወቱን ለማቆየት) ለስደት ተዳረገ፡፡ ይህ  ለባሕር ኃይሉ ብቻ ሳይኾን ለኹሉም የተረፈ ዕጣ ፈንታ ነበር/ነውም፡፡

Ethiopia US Navy officersበርዕሱ ላይ ለማተኮር፦ ያስደሰተኝ ኤትዮጵያችን ባሕር ኃይሏን በራሷ ልጆች ታቋቁማለች ብዬ ነበር፡፡

እዚህ ላይ አንድ ታሪክ እጠቅስ ዘንድ ፍቀዱልኝ፡፡ ሃተታዬን ያሳጥርልኝ፦ ያብራራልኝምና!

ያገሩን ስም  ልዝለለውና፦ አንድ የምዕራብ አፍሪካ አገር ነጻነቷን እንዳገኘች መሪዋ ለእንግሊዝ የባሕር ኃይል፡

“አንድ የቺፍ ልጅ ልልክ ነውና የአድሚራል ኮርስ እባካችሁ አዘጋጁልኝ!” የሚል ነበር፡፡ ያነዬ ዐቢይ የለ አርአያ የሚኾናቸው፡፡

ዐቢይማ በቀኃሥ ዘመን የሠለጠኑ በወታደራዊው መንግሥት ጊዜ በሚያኮራ ባለሞያነት የጦር ግዳጃቸውን የተወጡ የባሕር ኃይል መኮንኖች እያሉት የመርከቢቱን ፊትና ኋላ የማያውቀውን  አድሚራል አድርጎ ሾመ;፡፡

እኔ ደግሞ በደስታ ተውጬ ያሉትን መኮንኖች በመሰብሰብ አዛዥ እነርሱ ከመኽከላቸ ው መርጠው እንዲሰጡት ቢያደርግ ይጠቅማል የሚል ዓይነት ምክር በኤምባሲ በኩል ልኬ ነበር፤፡ እነርሱም የምሥረታውን ጉዳይ እንዲያዘጋጁ፡፡

በእሳት አደጋ መከላከያ በኩልም ባሕር ኃይል ያሠለጠናቸው አይጠፉምና ይህን “ ኢንደስትሪአል ፓርክ!” እያሉ በየቦታው ያቋቋሟቸው፦ ለጠላት ምቹ በመኾናቸው እነርሱንም በመደብደብ የምጣኔ ሃብት ጉዳት ( በዕዳ ላይ) ስለሚያስከትል ከሌሎች አሳቦች ጋር ልኬለት ነበር፡፡ ( የቀድሞ ወታደሮችን በመጨመር)

ዋናው ጉዳይ ላይ በማተኮር፦ ክ.ጠ.ሚ። አፈርኩብህ!!

 

እምዬ የሚያስብልሽን ያምጣልሽ!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.