ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉና ትላልቅ ስብሰባዎች እንዳይካሄዱ ተወሰነ

banner 2በኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክንያት የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና ትላልቅ ስብሰባዎች ለሁለት ሳምንታት እንዲዘጉና እንዳይካሄዱ መወሰኑን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለጹ።

በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር አምስት መድረሱም ተነግሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ኮሮናን ለመከላከል ከተቋቋመው የሚኒስትሮች ኮሚቴ ጋር ባካሄዱት ውይይት ውሳኔው ተላልፏል።

በውሳኔውም ትላልቅ የመንግስትም ሆኑ የግል ስብሰባዎች፣ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ሳምንት እንዲዘጉ ተወስኗል።

ስፖርታዊ ክንውኖችና ሕዝባዊ ስብሰባዎችም ለቀጣዮቹ ሁለት ሳምንታት እንዳይካሄዱ ተከልክሏል።

አነስተኛና አስፈላጊ የሆኑ ስብሳበዎች በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ክትትል እንዲደረጉ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ባሉበት ሆነው በሽታውን እንዲከላከሉ ተብሏል።

የእምነት ተቋማት ቫይረሱ የከፋ ደረጃ ደርሶ ዜጎች ለጉዳት እንዳይጋለጡ ባይሰበሰቡ ይመረጣል ነው ያሉት።

ይህን ተከትሎ በተለያዩ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ህገ-ወጥ ነጋዴዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ መንግስት አስጠንቅቋል።

ምንጭ ኢዜአ
ፎቶ ዳኜ አበራ

ተጨማሪ ያንብቡ:  አቡነ መልኬጼዲቅ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ በኦርጋን መዘመር አለበት፤ ካህናቱም ኦርጋን መማር አለባቸው አሉ - ቪድዮ

1 Comment

  1. ጥሩ እርምጃ ነው። ሆኖም ት/ቤቶቹ ከመከፈታቸው በፊት በርካታ የዘመቻ ስራ ቢሰራ ጥሩ ነው። ልክ ድሮ እንደተደረገው ህዳር ሲታጠን በየመንደሩ የፅዳት ዘመቻ ቢደረግ። የመድሃኒትና ውሃ የመርጨት ስራ በሚኖሩ መኪኖች በሙሉ ት/ቤቶችና ዋና ዋና አካባቢ ቢደረግ የተሻለ ነው። ሁሉም መተባበር አለበት።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.