ምክር ቤቱ የሚኒስትሮችን ሹመቶች አፀደቀ

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።

በመደበኛ ስብሰባውም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቀረበለትን የተለያዩ የሚኒስትሮች ሹመት ተቀብሎ አጽድቋል።

cabnet ethiopian Registrarበዚህ መሰረት፦

1 ወይዘሮ አዳነች አቤቤ – የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ

2 ዶክተር ሊያ ታደሰ – የጤና ሚኒስትር

3 አቶ ላቀ አያሌው – የገቢዎች ሚኒስትር

4 ወይዘሮ ፊልሰን አብዶላሂ – የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር

ምክር ቤቱም የቀረበለትን የሚኒስትሮች ሹመት በ21 ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።

በዛሬው እለት የተሾሙት ሚኒስትሮችም በምክር ቤቱ ቀርበው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የቀረበለትን የፌደራል
የሥነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሹመትም አጽድቋል።

በዚህ መሰረት፦

1 አቶ ፀጋ አራጌ – የፌደራል የሥነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን ተሾመዋል።

ምክር ቤቱ የፌደራል የሥነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሹመቱን በ11 ተቃውሞ፣ በ6 ድምጸ ተአቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።

እንዲሁም ምክር ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበለትን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አመራር አባላት ሹመትንም

አጽድቋል።

 የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባላት ሹመትን አጸደቀ

በዚህም መሰረት

1. አቶ አወሉ አብዲ የቦርድ ሰብሳቢ
2. ወ/ሮ አበበች ከታ አባል
3. ዶ/ር አጋረደች ጀማነህ አባል
4. አቶ ማንያዘዋል እንደሻው አባል
5. ዲ/ን ዳንኤል ክብረት አባል
6. አቶ ኦባንግ ሜቶ አባል
7. ዶ/ር ወዳጄነህ ማህረነ አባል
8. ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ አባል
9. አቶ ጌትነት ታደሰ የቦርዱ ጸሀፊ እና አባል

1 Comment

  1. ምን አደረገ አሁን እንደነ አህመዲን ጀበል እንደነ አቡበከር ሰዉ ግደሉ ብሎ ለተከታዮቹ ትእዛዝ አልሰጠ። ተቃዉሞዉ የበረታበት ምክንያቱ ግልጽ ነዉ ጥልቅ እዉቀት አለዉ፤ ለአንድነት የቆመ ነዉ፤ የማንኛዉምንም እምነት ሆነ ፖለቲካ ጽንፍ ባግባቡ ይመክታል።
    ሌሎች ዜጎች እንዲሳተፉበት የተሰጠዉን እድል ይህን ላገሩ የደከመን ሰዉ ማግለል አግባብ ስላልሆነ ለወደፊቱም እንደሱ አይነት አገራቸዉን የሚወዱ ዜጎችን ማጥቃት አግባብ ባለመሆኑ መታረም ይኖርበታል እላለሁ። እንዲህ ያለዉ አካሄድ ቀደም ባለዉ ጊዜ እነ ፕሮፌሰር አስራትን አሳጥቶናል አሁንም ይህ አካሄድ መታረም አለበት።
    አዎ ዲያቆን ዳንኤል በዛ ከተገኘ እንደልብ የጥላቻ ፖለቲካችንን የምናራማድበት መንገድ ይዘጋል ከሚል ከነአህመዲን ጀበልና ከነጁዋር ደጋፊዎች የሚመጣ ጸረ ኢትዮጵያ አስተሳሰብ ነዉ። የጊዜ ጉዳይ ነዉ እንጂ በትክክለኛዉ መንገድ እንድቴሄዱ ይደረጋል ሰዉ እያረዳችሁ እያሸማቀቃችሁ እድሜ ልክ የምትኖሩበት ስርአት ይኖራል ብላችሁ አታስቡ።
    ዲያቆን ዳንኤል ከመሰረተህ እንዳትናወጥ ይህ ጫጫታ ዜጋ ሲሰክን ወደፊት የሚያፍርበት ይሆናል አንተም የህዝብን ሙቀት እየለካህ ሳይሆን እዉነት እዉነትን አስተምር የሀይል ሚዛን እያየህ የደቦ ደጋፊና ተቃዋሚንም እያየህ ከሚዛንህ አትዉረድ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.