መንግሥት የህዝብ አንድነት እንዲሸረሸር በሚያደርጉ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የመገናኛ ብዙሃን ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ

Tilahun መንግሥት የህዝብ አንድነት እንዲሸረሸር በሚያደርጉ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የመገናኛ ብዙሃን ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀመንግሥት የህዝብ አንድነትና አብሮነት እንዲሸረሸር በሚያደርጉ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የመገናኛ ብዙሃን ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ በህዝባዊ መድረኮችና መገናኛ ብዙሃን በኩል የሚተላለፉ የጥላቻ ንግግሮች በሃገር አንድነትና አብሮነት ላይ አደጋ ይደቅናሉ።

ከዚህ አንጻርም በመሰል ድርጊት በሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የመገናኛ ብዙሃን ላይ ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣንና ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር በመሆን ተገቢና ተመጣጣኝ ዕርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ አስታውቀዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም በትናንትናው ዕለት ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን በተመለከተ በአዲስ አበባ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ (ኦፌኮ) ባዘጋጀው መድረክ በ”ኦ ኤም ኤን” (OMN) አማካኝነት ህገ መንግስታዊ ድንጋጌን የጣሰና ኢትዮጵያዊ ዕውነታን ያላገናዘበ የጥላቻ ንግግር ለዘመናት በአብሮነት ወደኖሩ ህዝቦች መተላለፉን ተከትሎ ፓርቲውም ሆነ የመገናኛ ተቋሙ ተገቢውን ኃላፊነት መውሰድ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የተፈጠረው ነገር ስህተት ብቻ ሳይሆን ጥፋት መሆኑንም አቶ ንጉሱ ተናግረዋል።

አቶ ንጉሱ መንግሥት ለረጅም ጊዜ በመማማርና መመካከር ላይ የተመሰረተ እንቅስቃሴን አማራጭ አድርጎ በትዕግስት መቆየቱን አንስተዋል።

አሁን ግን በሃገሪቱ ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ተግባራት በግልፅ እየተበራከቱ በመምጣታቸው መንግስት እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምር ነው የገለፁት።

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣንና ብሄራዊ ምርጫ ቦርድም በዚህ ረገድ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በፍጥነት እንዲታረሙ የማድረግ ኃላፊነት እንዳለባቸውም አውስተዋል።

በሶዶ ለማ እና ትዕግስት ስለሺ /ኤፍ.ቢ.ሲ

1 Comment

  1. እርምጃ መወስድ ግድ ይላል፡፡ በአለም ላይ ለተሰሩ ከባድ ወንጀሎች፣ ህዝብ ከህዝብ ለሚያጣሉ ጥፋቶችና ብሎም አገራት መፈራረስ ሚዲያዎች ትልቁን ሚና ሲጫወቱ እንደነበረ መማር ያስፈልጋል፡፡ አንድ ሚዲያ ተቋም ከግለሰብ፣ ቤተሰብና ማህበረሰብ አይበልጥም እኮ፡፡ ስለዚህ አፈጣኝ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል፡፡ ሆን ተብሎ በተዘጋጀ ፕሮግራም ላይ ሳናውቅ ቀጥታ ስርጭት ስለሆነ ነው ማለት ማፈሪያ ነው፡፡ ከተናገሪያዋ ጀምሮ ሲስቁና ሲሳለቁ የነበሩ በሙሉ ማፈሪያ ናቸው፡፡

    እንደው በተከበረ የሴቶች ቀን ላይ ማፈሪያ የሆነች ሴት ተናጋሪ ይህንን ማቅረብ የሴቶችን የአለምና የአገር ለውጥ ጥረት በቆሻሻ መልክት መገለፁ ማፈሪያ ነው፡፡ በዚህ ትልቅ ፕሮግራም ላይ መቅረቡ ምን ያህል የወረደ አመለካከት እንዳለ ነው፡፡ ለሊት ለሊት አማራ ወይም ሌላ ብሔር የሆነች ሚስታቸውን እያቀፉ ሌላ የወረደ ነገር መናገር ሰዎች ምን ያህል የወረዱ እነደሆነ ነው፡፡ እነዚህ ለልጆቻቸው ምንድን ነው የሚያስተምሩት፡፡ ተናጋሪዋም ተጠያቂ መሆን አለባት፡፡ መዋደድና መፈቀርን ሰው ስለፈላገ እኮ አያለያየውም፡፡

    ፍቅርና መዋደድ ስለፈለጉት ብቻ የሚሆን አይደለም፡፡ በዓለም ላይ ባለ ግንኙነት አገር አቋርጦ ፈረንጅ ወይም የሌላ አገር ዜጋ በማግባት ምን ያህል ፍቅር እንደሚያሻንፍ ይታወቃል፡፡

    አረ በስንቱ ነው ማፈር!!!!!!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.