ተባንዳ ግድብ ስብከት ተጅቦች መንጋጋ የሚሰቃዩ ተማሪዎችን ጣር መስማት ይቅደም! – በላይነህ አባተ

በላይነህ አባተ ([email protected])

የኮሮና ቫይረሶች ክረምትን ጠብቀው የሰውን አፍንጫ እደሚወሩት ገለባ ምሁራንም የግድብ ወሬን ጠብቀው ድህረ ገጦችን ራዲዮኖችንና ተሌቪዥኖችን የሚያጥለቀልቁ ተውሳኮች ናቸው፡፡ የኮሮና ቫይረሶች በበጋ እንደሚያደፍጡት የኢትዮጵያ ገለባ ምሁራንም ወንበዴው የይህ አድግ መንግስት ሕዝብ እንደ ጫካ ሲጨፈጭፍ፣ ሲያቃጥል፣ ሲያመክንና በተጠለፉ ተማሪዎች ሲያፌዝ ጪጭ ብለው የግድብ ስብከት ሲነሳ እንደ ዝናብ አብራ ድህረ ገጡን የሚወሩ አንበጣዎች ናቸው፡፡

የምሁራን መንጋዎችና ገለባም ተመሳሳይ ናቸው፡፡ የገለባ ባህሪ ተምስራቅ የመጣ ነፋስ ሲገፋው እየተንሿሿ ወደ ምዕራብ መንጎድ ነው፡፡ ገለባ ተምዕራብ የመጣ ሽውታ ሲቀትለው ተመልሶ ወደ ምስራቅ የሚከንፍ ቀላል ገለፈት ነው፡፡ ገለባ ተደቡብ ነፋሱ ሲነዳውም ወደ ሰሜን፤ ተሰሜን መልሶ ሲቀትለውም ወደ ደቡብ የሚከንፍ ፍሬ አልባ ብናኝ ነው፡፡

Denbi Delo Students ethiopian registrar..ነፋስ ገለባን እንደሚነዳው የይህ አድግ ትንፋሽም የ”ምሁራን” መንጋዎችን ተገመድ እንደተንጠለጠለ ጡት ማያዣ ውዣውዤ እያጫወታቸው ነው፡፡ ይህ አድግ ልጆችን፣ ወጣቶችን፣ ጎልማሳዎችን፣ አባቶችን፣ እህቶችንና ወንድሞችን በመደዳ መግደሉ፣ መግረፉ፣ ማምከኑና አገር መሸጡ ዓለም ያወቀው ነው፡፡ ይኸንን ዓለም ያወቀውን ዘግናኝ ወንጀል ችላ ብለውና የወገናቸውን እርም እንደ ቋንጣ ቅርጥፍ አድርገው በልተው ገለባ ምሁራን ይህ አድግ ግድብ እያለ ሲያንቧርቅ በአውሎ ነፋስ ተጠርገው ወደ ቦንድ መድረክ መንጎዳቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ ይህ አድግ መተከል ድንጋይ መኮልኮል የጀመረው የፍልስጤም ደጋፊ እስልምና አክራሪዎችን ልክ ለማስገባት ታዝዞ መሆኑን ስተው በባንዳው ለገሰ ትንፋሽ መጠረጋቸው ታሪክ ሲያወሳው የሚኖር አሳፋሪ ታሪካቸው ነው፡፡

የበቀለበትን ዛፍ ክዶ በነፋስ የሚኮበልል የኮሸሽላ ቅጠልና ያስተማረ ወገኑን ክዶ በባንዳው ይህ አድግ  የሚነዳ ምሁር ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ይህም በመሆኑ እነሱ ሙሴ የሚሉት የለገሰ ጆሮ ጠቢ ትንፋሽ ምሁራንን እንደ ገብስ ገላባ እያበነናቸው ነው፡፡ ይህ ጆሮ ጠቢ አረቦችንና የ”ዓለም” ባንኮችን እንደ አሳዳጊ አባቱ  አኮፋዳ ይዞ እየለመነ በዓባይ ጉዳይ ሳያጎበድድ የሚቀር መስሏቸው ምሁራን አሁንም በፓስተራዊ ትንፋሹ እንደ ሰሃራ አቧራ እየተጠረጉ ነው፡፡ ገላባ ምሁራን ጭነነዋል የሚሉት ዲግሪም ሆነ የፕሮፌሰርነት ማእረግ በካድሬዎች ትንፋሽ እንደ ትቢያ ተመብነን  አላድናቸው እያለ ነው፡፡

ይህ አድግ ክብርና ማእረግን የማያውቅ በቅኝ ገዥዎች እርጥባን የሚንቀሳቀስ ዘራፊና ለማኝ ድርጅት መሆኑ ከሳላሳ ዓመታት በላይ የታየ ነው፡፡ እነዚህ ገላባ ምሁራንም ይኸንን የይህ አድግ የባንዳነት ባህሪ እንደ ስንክሳር በረዘመው ጠልሰማቸውና በቀላማጅ አንደበታቸው ሲነፉት እንደነበረ የታወቀ ነው፡፡ ዳሩ ግን በገለባ ምሁራን ዘንድ ተቃል መሰንበትና ተእውነት ጀርባ መቆየት የተሰሩበት ዝሃ የማይፈቅደው ባህሪ ነው፡፡ ይህ አድግን “አገር ሻጭና ነፍሰ ገዳይ!” እያሉ ሲያንባርቁ ኖረው ጆሮ ጠቢውን የይህ አድግ አንበል “ሙሴ መጣ!” እያሉ በየአዳራሹ እጃቸው የአላባ በርበሬ እስቲመስል እያጨበጨቡ ይህ አድግ በመላ አገሪቱ ለሰላሳ ዓመታት በፈጀው ሕዝብ መቃብር የደነሱ ህሊና ቢሶች ናቸው፡፡

እነዚህ ገለባ ምሁራን ዛሬም ይህ አድግ ሶስት ሚሊዮን ሕዝብ ተመንገድ ሲያሳድር ጪጭ ብለው ካድሬው ሙሴአቸው የግድብ እስተንፋስ ሲተነፍስ አውሎ ነፋስ እንዳነሳው የኮሸሽላ ቅጠል እየበነኑ ነው፡፡ ገለባ ምሁራን ተጅቦች መንጋጋ ተማሪዎች ሲገቡ ሰጥ ብለው ጀሮ ጠቢው ግድብ ሲሰብክ  “ምሁራዊ ትንታኔ” እንደ ገደል ማሚቶ ተቀብለው እያንባረቁ ነው፡፡ ለገለባ ምህራን ግድቡ ተጅብ መንጋጋ ተሚሰቃዩት ተማሪዎች ህይወት የሚቀድም አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡፡

ገለባ ምሁራን ተማሪዎችን ተአገር ጅቦች መንጋጋ የማያላቅቅ ባንዳ አገዛዝ ውኃ ተጠማው የውጪ ጅብ ተከላክሎ  ሁለተኛውን ወንዝ ያስከብራል ብለው የሚያምኑና በካድሬ እስተንፋስ እንደ ፊኛ ተዳመና ሥር የሚንሳፈፉ ቀላል ፍጡራን ናቸው፡፡ በእነዚህ ፊኛ ምሁራን እይታ የባንዳ ግድብ ስብከት ተጅብ መንጋጋ ተሚሰቃዩ ተማሪዎች ህይወት በላይ ነው፡፡ ተጅቦች መንጋጋ የሚሰቃዩትን ልጆቹን ጩኸት ችላ ብሎ ስለባንዳ ግድብ የሚሰብኩ ገለባ ምሁራንን የሚሰማ ማህበረሰብም ያልተባረክ ነው፡፡ የባንዳ ግድብን ስብከት ጆሮ ዳባ ብሎ ተጅቦች መንጋጋ የሚሰቃዩትን ተማሪዎችን ጣር መስማት በምድርና በሰማይ የሚያጸድቅ ነው፡፡

ህብረተሰብ ሆይ! ሴት ልጆችን ለጅብ አስረክቦ እንኳን የባንዳ ድስኩር መስማት በልቶና ጠጥቶ ማደርም ባህልህ አልነበረም፡፡ስለዚህ የባንዳን ግድብ ሰበካ ጀሮ ዳባ በልና ተጅብ መንጋጋ የጣር ጩኸት የሚያሰሙትን ልጆችህን አድምጥ፤ አድን! ገለባ ምሁርም ባባንዳ ካድሬ እስተንፋስ እየተነዳህ ያስተማረህን ህብረእሰብ እርም ለዘላለም መቆርጠምህን አቁም! አመሰግናለሁ፡፡

መጋቢት ሁለት ሺ አስራ ሁለት ዓ.ም.

 

2 Comments

  1. Let’s make the 100th day from when the students were abducted a date of action everywhere especially those of us residing near or in Washington DC area in USA should voice our concerns about the stability of Ethiopia including the marking of the 100th days days of the abducted students, by joining a protest rally organized by our Oromo brothers and Oromo sisters to shed light on the Prime Minister Abiy Ahmed government’s security apparatus’s human rights abuses , the rally is expected to be held on Friday the 13th of March 2020 starting from the Whitehouse by 9:30am in the morning heading towards the World Bank finally ending up at the State Department at11:30am.

  2. A Mother of two from Ethiopia got shot and killed in San Francisco California USA by two males this year in January 2020 , even though the killers admitted to the killing of the 32 years old mother of two from former state of Ethiopia Eritrea while Eritrea was under Ethiopia, no charges are filed against the killers by the USA government authorities . The international communities should know that denying Ethiopians water and their chance of being self reliant with food got so many unforseen negative consequences not only to Ethiopia but to the whole world since Children who grow up malnourished witnessing starvation related disasters got less stamina throughout their lifetime .

    A former Ethiopian famine victim as a little child who witnessed the death loosing of her parents to the Ethiopian famine starvation in the state of Eritrea who is now an independent country , who later got adopted and moved to USA later ended up having two children of her own got shot and killed by two male individuals a couple of months ago in San Francisco , California USA , ingniteing one of the most controversial legal conflicts since the killers are not charged with murder but charged the admitting killers with only gun charges since these Ethiopian lady was a former famine victim in the former Ethiopian State of Eritrea who terrorized the two males that were charged with only gun charges even if they admitted to killing the 32 years Ethiopian who was born from Eritrean family , the two men claimed they feared for their life before they shot and killed Emma Hunt so no murder charge is being filed for this 32 years old Ethiopian mother of two despite the Ethiopian Eritrean Community continuous outcry to charge the killers with murder the prosecutor is inclined to not charge them with murder saying she acted threatening towards the two male individuals exhibiting her African sides of when she grew up fending for herself and her younger sister homeless in Ethiopia after her parents died of starvation famine .

    ines-to-file-murder-14978176.php

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.