ምርጫ ቦርድ ነጥብ ጥሏል፡ በጃዋር ጉዳይ እጁን ተጠመዘዘ ይሆን? – ልጅ ተክሌ ቶሮንቶ

ክፍል አንድ፡

እንደመግቢያ፤

 • jawarይህንን ጽሁፍ ከመቋጨቴ በፊት፤ ምርጫ ቦርድ ከጃዋር መሀመድ ጋር በተያያዘ የሰጠው ብይን እንዳለ ፈለግኩ፤ ምንም አላገኘሁም፡፡ ምርጫ ቦርድ በመረራ ጉዲና ለሚመራው ኦፌኮ፤ የጃዋርን ኢትዮጵያዊ ዜግነት ማረጋገጫ ወረቀት እንዲያቀርብ የሰጠው የ10 ቀን ገደብ ቢያልፍም፤ ቦርዱ በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን ምንም ይፋዊ ብያኔ አልሰጠም፡፡ ቦርዱ፤ ምን ሊል እንደሚችልም እንጃ፡፡ ምናልባት ‹‹‹የጃዋርን የኦፌኮ አባልነት አንቀበልም፤ በዚህም መሰረት ለቀጣይ ምርጫዎች በእጩነት ሊቀርብ አይችልም››› ይል እንደሆን እንጂ፤ መቼም በዚህ የተነሳ የኦፌኮን ፈቃድ ሊሰርዝ አይሞክርም፡፡ ጃዋር ደግሞ፤ ምርጫ ቦርድ ተቀበለው አልተቀበለው፤ የፖለቲካ ተሳትፎውን አይገታውም፡፡ ቀድሞውንም ነገር ምርጫ ቦርድ ከጃዋር ጋር በተያያዘ የመጣበት መንግድ ስህተት ነው፡፡

 

 • ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ፤ ከጃዋር ዜግነትና ኦፌኮ አባልነት ጋር በተያያዘ፤ ቦርዱና ድርጅቱ ኦፌኮ፤ ወይም ጃዋር የገቡትን እሰጥ አገባ በተመለከተ ስትጠየቅ የምትሰጠው መልስ፤ የገባችበትን አስቸጋሪ የፖለቲካ ቅርቃር እንዳልተረዳችና የያዘችው ሀላፊነት፤ ብልጠት፤ ብልሀት፤ ትእግስት፤ አርቆ አሳቢነት፤ የኢትዮጵያንም የተወሳሰቡ ፖለቲካዊና ታሪካዊ እውነታዎች መረዳት፤ በግል የማይመቹንንም አመለካከቶች ማቀፍ እንደሚያስፈልገው በቅጡ እንዳልተረዳች ያሳብቃል፡፡ ልምድና እድሜ፡፡

 

 • ወ/ት ብርቱካን የፖለቲካ ፓርቲዎችን አባል ማንነት፤ ምንነት፤ ጾታ፤ እድሜ፤ ዜግነትም መከታተል፤ ፓርቲዎቹን መቆጣጠር፤ በማቋቋሚያ አዋጁና በፖለቲካ ፓርቲዎችና ምርጫ አዋጅ የተዘረዘረ፤ የምርጫ ቦርድ ተቋም ሀላፊነትና ስልጣን እንደሆነ ተናግራለች፡፡ ነገር ግን፤ ይሄንን የጃዋርን ዜግነት በተመለከት እንድትከታተሉና እንድታፋጥጡት መነሻችሁ ምንድነው ስትባል፤ ድርጅቱ ኦፌኮ በመገናኛ ብዙሀን በይፋ አባልነቱን ስላወጀ፤ ያንን መነሻ አድርገን ነው ስትል መልሳለች፡፡ ብዙ ፈተና ለሚጠብቀው፤ ገለልተኛነቱ ጥያቄ ውስጥ ላለ፤ በክር ላይ ለሚራመድ ተቋም፤ ይሄ መጥፎ መነሻ ነው፡፡ ምክንያም አዋጁ እንዲህ አይነት ሁኔታ ሲከሰት ምርጫ ቦርድ እንዲህ አይነቱን የማፋጠጥ ሂደት እንዲጀምር እንደሚያዝ ወይም እንደሚያስገደድ አይገልጽም፡፡

 

 • ምርጫ ቦርድን የሚያህል የአንድን አገር ምርጫ የሚዳኝና የሚያስፈጽም ድርጅት፤ ዜና እየለቃቀመ ምርመራና ክትትል የሚጀምር ከሆነ፤ ስራው ከባድ ይሆናል፡፡ ይሄንን; መገናኛ ብዙሀን የሚዘግቡትን ዜና ተከታትለን የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎችን የሚመለከቱትን አዋጅ/ጆችን እናስፈጽም የሚል መንገድ ከጀመረው፤ ስራውን መጀመር ያለበት፤ ራሱን ገዢውን ፓርቲ በመመርመርና በመገሰጽ ነው፡፡ ገዢው ፓርቲ፤ መገናኛ ብዙሀንን ያላግባብ ይጠቀማል፤ በመንግስት ገንዘብ ወይንም የገንዘብ ምንጩ ግልጽ ባልሆነበት ሁኔታ ስብሰባዎችንና ስልጠናዎችን ያካሂዳል፡፡ የመንግስት ድርጅቶችን ለስብሰባና ለስልጠና ይጠቀማል፡፡ በቅርቡ፤ መንግስት; ከሌሎች ፓርቲዎች፤ የንግዱን ማህበረሰብ እያስገደደና እያስፈራራ ገንዘብ ይሰበስባል የሚል ክስ ቀርቦበታል፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ስብሰባዎች ያደናቅፋል፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ፊርማዎችና ሰነዶች ይዘርፋል፤ ያስዘርፋል፡፡ ስብሰባዎችናና ሰልፎችን ይከለክላል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የሚመለከተው አዋጅ ደህንነቶች የፓርቲ አባል እንዳይሆኑ ቢከለክልም፤ እስካሁን ድረስ፤ ከፓርቲው አባልነት መልቃቀቸው የማይታወቅ የኦህዴድና የብአዴን አባላት (የብልጽግና) የደህንነቱን መስሪያ ቤት ይመሩታል፡፡ ይሄም ብቻ አይደለም፡፡ ለምሳሌ፤ የፓስፖርት ምርመራ ከተጀመረ፤ ጃዋር ስለብርሀኑ ነጋ ፓስፖረት የጠቀሰው የኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ዘገባ አለ፡፡ ነገሩ፤ የት ጋር እንደሚቆም እንጃ፡፡

የብርቱካን ምሳሌዎችና ሌሎች ነጥቦች ስለምርጫ ቦርድ፤

 • ምርጫ ቦርድ በዚህ ከጃዋርና ኦፌኮ ጋር በገጠመው እሰጥ አገባ ጉዳይ ላይ ስትጠየቅ፤ ብርቱካን፤ ጃዋርን ብቻ ነጥለው እንዳልጠየቁ፤ ስለሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችም የሰጠችው ምሳሌ አያስኬድም፡፡ የከማል ገልቹና የኦነግ ድርቶች የላኳቸው የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው ተወካዮች እንዲለወጡና ምርጫ ቦርድ እነዚህ ፓርቲዎች የላኳቸውን ሰዎች እንደማይቀበል የተናገረው፤ ሰዎቹ ወደምርጫ ቦድ ቢሮ ሲመጡ ወይም ከምርጫ ቦርድ ጋር በሚያገናኛቸው ስራ ላይ ሲሰማሩ ነው፡፡ የምርጫ ቦርድ ሰዎች፤ የጃዋር መዝገብ ይፋ በሆነ መልኩ እነሱ ቢሮ እስኪመጣ፤ ወይንም ከሳሽ እስኪነሳ መጠበቅ ነበረባቸው፡፡ ኦፌኮ ጃዋርን ይዞ ደጇ ካልረገጠ በስተቀር፤ ወይንም፤ ቅሬታና ክስ ከግለሰቦች ወይንም ከመንግስት አካላት ካልመጣ በስተቀር፤ ወሬ ከመገናኛ ብዙሀን ለቃቅሞ፤ ኦፌኮን ሚናህን ለይ ብሎ ማስጨነቅ የምርጫ ቦርድን ተአማኒነት ጥያቄ ውስጥ ይከታል፡፡ በስማበለው፤ ጃዋር ላይ እርምጃ መጀመራቸው፤ ጉዳዩ ህግና ስርአት የማስፈጸም ብቻ ሳይሆን፤ የፖለቲካ አጀንዳ የማስፈጸምም ያስመስልባቸዋል፡፡

 

 • ምርጫ ቦርድ እያስፈጸመ ያለው፤ መንግስት ማስፈጸም ያቃተውን ወይም የፈራውን፤ ጃዋርን ከፖለቲካ ውጪ የማድረግ ሴራ ይመስላል፡፡ መንግስት ጃዋርን ፈርቶታል፡፡ መንግስት፤ ጃዋርን ፊት ለፊት ሊገጥመው አይፈልግም፡፡ መንግስትና ጃዋር ፊት ለፊት ሊጋጠሙ የሚችሉባቸው ብዙ አጋጣሚዎች ነበሩ፡፡ ነግር ግን፤ መንግስት ያንን አላደረገም፡፡ ይልቅስ፤ የምርጫ ቦርድ በዚህ በጃዋር-ኦፌኮ ውዝግብ ውስጥ መዘፈቅ፤ መንግስት እርምጃው ቅቡልነት ያለው እንዲመስል፤ መንግስት ምርጫ ቦርድን እንደሽፋን ተጠቅሞ፤ ጃዋርን ከፖለቲካ ለማግለል ጥሩና ሕጋዊ መስሎ በታየው ሴራ መሳተፍ ይመስላል፡፡ ብርቱካን፤ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ፤ በዚህ ሴራ ውስጥ ዋና ተዋናይ ሆና መገኘቷ ባይገርመኝም፤ በዚህ ፍጥነትና በዚህ መልክ፤ በዚህ የዋህነት ይከሰታል ብዬ አልጠበቅኩም፡፡ ከዚህ የተሸለ ሴራ መፍጠር ይቻል ነበር፡፡ ጃዋርን በዚህ መልኩ ማሸነፍ ይቻላል፡፡ ግን ከባድ ነው፡፡ ዋጋም ያሥከፍላል፡፡ ጃዋር ያሁኑን ቦታውን በትግሉ ነው ያገኘው፡፡

 

 • ምርጫ ቦርድ እንደጠበቀው፤ ጃዋር የዜግነት ማረጋገጫውን ባያቀርብ እንኳን፤ ጃዋርን በእጩነትና በመራጭነት እንዳይሳተፍ ይገድበው ይሆናል እንጂ፤ ከፖለቲካ ተሳትፎ አያቆመውም፡፡ ወትሮም ቢሆን፤ ጃዋር ፖለቲካ ውስጥ ሲሳተፍና ተጽእኖ ፈጣሪ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ፓስፖርትና በኢትዮጵያ መንግስት መልካም ፈቃድ አይደለም፡፡ በትግሉ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከገባ በኋላም ባሉት ወራት፤ ጊዜያት፤ ጃዋር፤ ፖለቲካ ውስጥ ሲሳተፍ፤ በምርጫ ቦርድ ቡራኬ አይደለም፡፡ በራሱ ድፍረትና በህዝብ ድጋፍ እንጂ፡፡

የብርቱካንና የመንግስት ሴራ፤ የምርጫና ፖለቲካ ፓርቲዎች ሕግ

 • ጃዋርን ከፖለቲካም ከአገርም ለማስወጣት; በምርጫ ቦርድ በኩል ዞሮ መምጣት፤ ይሄንን ያህል ጊዜ መውሰድም አያስፈልግም ነበር፡፡ ጃዋር ቢወደውም ባይወደውም፤ ቢጫንበትም ባይቀበለውም፤ በትውልድ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ በምርጫና በእምነት፤ በትውልድም ኦሮሞ ነው፡፡ በምርጫና በፓስፖርት አሜሪካዊ ነው፡፡ የአገሮች ሁሉ አንዱ የእለት ተእለት የሉአላዊነት መገለጫ ወደአገራቸው የሚገባውን ሰው መምረጥ መቻላቸው ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት፤ ጃዋርን ከኢትዮጵያ ለማስወጣት፤ ምክንያት ሁሉ አያስፈልገውም፡፡ ሟቹ መለስ ዜናዊ እንዳሉት፤ የውጭ ዜጎችን ያይናችኁ ቀለም አላማረንም ብለን ማባረር እንችላለን፡፡ መንግስት ልብ ካለው፤ ያንን በራሱ ማድረግ ይችል ነበር፡፡ ምርጫ ቦርድን እዚህ ውዝግብ ውስጥ መክተት፤ ምርጫ ቦርድም፤ ዜና ሰምቶ፤ አገኘሁት ብሎ፤ ቸኩሎ እዚህ ውስጥ መሰንቀሩ፤ ስህተት ነው፡፡

 

 • የፖለቲካ ፓርቲ አባልነት ለኢትዮጵያዊያነ ብቻ የተገደበ እንደሆነ የኢትዮጵያ ህግ ይደነግጋል፡፡ ከዚያ ውጪ አዋጆቹ፤ ምርጫ ቦርድ፤ በራሱ አነሳሽነት የውጭ ዜጎች የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ መሳተፋቸውን ሲሰማ፤ ለይቶ ምርመራ ያደርጋል አይልም፡፡ አዋጆቹን ተመልክቼ ወደዚህ ወደምርጫ ቦርድ ሰሞንኛ ድርጊት ሊጠጋጋ የሚችል ያገኘሁት አንቀጽ፤ በፓርቲ ምዝገባ ፊርማ ማሰባሰብ ሂደት ውስጥ ያልተመዘገበን ወይም የሌለን ሰው እንደተመዘገበ አድርጎ መጓዝ በጠቋሚዎች መነሻነት ወይም በራሱ በምርጫ ቦርድ መነሻነት ምርጫ ቦርድ ሊያጣራና እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል የተደነገገው ነው፡፡ ኦፌኮ የቆየ ፓርቲ ከመሆኑም አንጻር፤ ሁለተኛም፤ ኦፌኮ ምናልባትም ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ጃዋርን ማርከናል ይበል እንጂ፤ የጃዋርን አባልነት በተመለከት ለምርጫ ቦርድ ያቀረበው ሰነድ ስለሌላ፤ እንዲሁም ምርጫ ቦርድ ሌላ ጥቆማ ደረሰኝ ስላላለም፤ የጃዋርን ጉዳይ ለመመርመር የተነሳበት አመክንዮ ህጋዊ ጉልበት ያንሰዋል፡፡ ምናልባት ስልጣኑ አለን ካሉም እንኳን፤ ምርጫ ቦርድ ወደመገናኛ ብዙሀን ሳይሄድ ስራውን መስራትም ይችል ነበር፡፡ በተረፈ፤ የጃዋርን ጉዳይ የኦፌኮን መግለጫ ወይም ፕሮፓጋንዳ በመገናኛ ብዙሀን ሰምተን ነው መመርመር የጀመርነው የሚለው ንግግር፤ በዚህ መልክ እርምጃ የጀመሩበት ሌላ ሰው እንዳለ አይገልጽም፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ሕግ የማስፈጸም ወይም ስርአት የማሲያዝ ብቻ አይመስልም፡፡

 

 • ነገሩ እንዲህ ነው፤ ብርቱካንና ምርጫ ቦርድ የጃዋርና ኦፌኮን የእጮኝነት ዜና ሰሙ፡፡ ምናልባትም ከመንግስት ባለስልጣናት በኩል ቀጥተኛ፤ ወይም ዘዋዋሪ፤ ጥቆማ ወይም ቅሬታ፤ ቀረበላቸው:: እርምጃ መውሰድ ጀመሩ፡፡ ብርቱካን ከጀርባ የሚገፋት ሀይል ከሌለ በቀር፤ ጃዋር ከኦፌኮ ጋር የፖለቲካ ዘመቻ ሲጀምር፤ የህዝቡን ድጋፍ ተመልክቶ፤ ኦፌኮንም ይሁን ጃዋርን መከታተልና እንዲህ ያለውን ማረጋገጫ አምጡ ማለት፤ ጃዋርን ለይቶ ከማሳደድ አይለይም፡፡ ምርጫ ቦርድ ይሄንን እንደጥሩ መነሻ መስዶ ውጭ ዜጎችን የፖለቲካ ተሳትፎ በተመለከተ ማብራሪያ ወይም ማሳሰቢያ ማውጣት ሲችል፤ ጃዋርን ብቻ ነጥሎ መከታተሉ አግባብነት የለውም፡፡ የተአማኒነት ግንባታ ሂደቱን ያሰናክለዋል፡፡ ለይሉኝታ ሲል እንኳን፤ ከአንድነት ሀይሉ ሌላም ሰው ደብለቅ ቢያደርግና ቢመረምር፤ እንዴት ያለ ብልጠት ነበር፡፡

ጉዳዩ ጥንቃቄ ይሻል፤

 • ምርጫ ቦርድ አለማዳላት ብቻ ሳይሆን፤ የሚያዳላ መምሰልም የለበትም፡፡ ገለልተኛ መሆን ብቻ ሳይሆን፤ ገለልተኛ አይደለም ወይም አይመስልም የሚያሰኝ ሂደት ውስጥ መሳተፍም የለበትም፡፡ በዚህ በጃዋር ጉዳይ ምርጫ ቦርድ የተዘፈቀበት ነገር፤ እነዚህን መርሆች የሚጥስ ነው፡፡ ምርጫ ቦርድ እጁን ተጠምዝዞ ካልሆነ በስተቀር፤ ወይንም ስለጃዋር የሚጋራው የቆየ የፖለቲካ አስተሳሰብ ወይም አተያይ ከሌላ በስተቀር፤ የጃዋርን የዜግነት ጉዳይ የሚያሳድድበት የሕግና ስረ-ነገር ጠባብ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች፤ ጉዳዩን የሕግ ብቻ አድርገው ይመለከታሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ፤ ምርጫ ቦርድ አስቀድሞ ይሄንን ማድረጉ፤ በኋላ በመጨረሻው ሰዓት ላይ ጃዋርን ከእጩነት ከልክሎ ከሚመጣው ተቃውሞ ያድነዋል የሚል ክርክር ያሰማሉ፡፡ ምርጫ ቦርድ ሁለቱንም ጉዳዮች ጃዋርን ሳይነጥል፤ ለሁሉም የውጭ ዜግነት ላላቸው ኢትዮጵያዊያን በሚሰራ መልኩ ማበጀት ይችል ነበር፡፡

 

 • ጃዋርን በዜግነቱ ምክንያት ከአገርም ይሁን ከፖለቲካ ማስወጣት ካስፈለገ፤ ያንን ሊያደርግ የሚችለውም የሚገባውም ስራ አስፈፃሚው የመንግስት አካል ነው፡፡ እንጂ፤ ምርጫ ቦርድ አይደለም፡፡ ጃዋር፤ በዜግነቱ ምክንያት፤ በኢትዮጵያ ውስጥ፤ ምርጫ እንዳይወዳደር፤ በይፋ ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ መሪ ወይም አባል እንዳይሆን የሚያግደው ሕግ አለ፡፡ ጃዋር በመገናኛ ብዙሀን የኦፌኮ አባል ሆኛለሁ ስላላና ኦፌኮም አባላችን ነው ስላለ ብቻ፤ ያ በርግጥም ሕጋዊ የኦፌኮ አባል አያደርገመው፡፡ ያ የኦፌኮና የጃዋር መግለጫ፤ ፖለቲካዊ እንጂ ሕጋዊ ፋይዳ የለውም፡፡ የውጭ ፓስፖርት ይዘው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የሚፈተፍተው ጃዋር ብቻ አይመስለኝም፡፡ ምርጫ ቦርድ ይሄንን የጃዋርን የኦፌኮ ፓርቲ አባልነት ዜና እንደሰማ ማድረግ የነበረበት፤ ሁሉንም መሰል ሰዎች የሚመለከት መግlጫ፤ ወይም ትእዛዝ፤ ወይንም መመሪያ ማውጣት ነበር፡፡ ጃዋርን ነጥሎ በማጥቃቱ፤ ምርጫ ቦርድ ክፉኛ ተሸውዷል፡፡ ወይንም የምርጫ ቦርድ አካሄድ በከረመና እነጃዋር በሚታገሉት የቆየ፤ ለአንድ ቡድን ባለ ድብቅ ጥላቻ፤ ወይንም ለአንድ አስተሳሰብ ወይም ርእዮተአገር ባለ ጥልቅ ፍቅር የተቃኘ ወይም የተቀፈደደ አካሄድ ነው፡፡

 

 • ምርጫ ቦርድ ሕጋዊ ፋይዳ ያላቸው ጉዳዮች ላይ እንጂ፤ ፖለቲካዊ አንድምታ ያላቸውን ጉዳዮች እየለቃቀመ መጠመድ የለበትም፡፡ ምርጫ ቦርድ ከሕግ-ነክ ጉዳዮች ወጥቶ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ውስጥ ከተዘፈቀ፤ ወይንም በሕግ ሽፋን፤ ፖለቲካዊ አንድምታ ያላቸውን ብያኔዎችን መስጠት ከጀመረ፤ ያ የተቋሙን ተአማኒነትና ቅቡልነት ጥያቄ ውስጥ ይከተዋል፡፡ በጃዋር ጉዳይ የሆነው ያ ነው፡፡

 

 • ምርጫ ቦርድ ከዚሀ አጣብቂኝ ለመውጣት ምን ማድረግ አለበት? ጉዳዩን፤ ከጃዋር ጉዳይነት አውጥቶ፤ ሁሉንም የውጭ ዜግነት የያዙ ፖለቲካኞች የሚመለከት እንደሆነ በማሳሰብ፤ ከግለሰባዊ ጉዳይ ወደአገራዊ ጉዳይ እና ተግዳሮት በመለወጥ፤ ከዚህ አጣብቂኝ ማምለጥ ይችላል፡፡ ምርጫ ቦርድ፤ በአዋጁ በተሰጠው ስልጣንና ሀላፊነት መሰረት፤ ሁሉም ፓርቲዎች የአባላትን ዝርዝር እንዲያቀርቡ ያወጣውን መመሪያ አጠናክሮ በመቀጠል፤ ጃዋርን በተናጠል ማጥቃቱን መተው አለበት፡፡ የጀመረው፤ ጃዋርን ብቻ ነጥሎ ማጥቃት አካሄድ ምርጫ ቦርድንም አገሪቱንም አላስፈላጊ ፈተና ውስጥ ይከታል፡፡ በተረፈ፤ በዚህ ሰዓት፤ ጃዋርን መግፋት አያዋጣም፡፡ ማቀፍ እንጂ፤ Engage him !! ወይም ዜግነቱ ይሰጠውና/ይመለስለትና፤ እሱ አልፍ አልፎ እንደሚያደርገው፤ በርግጫ ሳይሆን፤ በምርጫ ይዋጣልን፡፡ ብርሀኑ ነጋ የኤርትራን ፓስፖርት የተጠቀመው ለትግሉ ከሆነ፤[1] የጃዋር የአሜሪካ ፓስፖርትም ለትግል የተወሰደ የማይሆንበት ምክንያት አይታየኝም፡፡

 

ተክሌ፤ ቶሮንቶ፤ ካናዳ፤ የካቲት፤ 2012፤ ይቀጥላል …

ክፍል ሁለት ሲቀጥል …. የጃዋር ፖለቲካ በከፊል አይመቸኝም፤ ግን የኢትዮጵያም አንዱ ገጽ ነው; …… የፓስፖርት ጉዳይ፤ የዜግነት ጉዳይ;

[1] https://www.nytimes.com/2016/09/04/magazine/once-a-bucknell-professor-now-the-commander-of-an-ethiopian-rebel-army.html?auth=login-email&login=email

9 Comments

 1. This write up is a good example of ad hominem attack on Bertukan M.

  Tekle – the writer of the write up published above is focused on Bertukan’s experience and age (ልምድና እድሜ), question her character and motivations rather than her position on the issue. I hate ad hominem attack because it appeals to emotions rather than to logic and reason and that’s what I see here. I hope Tekle will think hard and long before he sends any other write up.

  In every country including where the Tekel lives, foreign nationals are legally barred from joining political parties and run for office. Why is this done? Because national interests need tobe protected. Who enforces the protection? An organ designated by law to register parties and organize elections.

  Given this international practice, why is Tekle attacking the electoral organ and Birtukan – the officer who heads it? Jawar is a clever political activist who mixes rhetoric, persuasion and violence to advance his goals. Now he has achieved a celebrity status to whom many want to associate with and identify. Tekle appears starstruck.

  Jawar is a U.S. national and Birtukan (by virtue of the law vested on her) can ban Meerreera’s ONC and because it has a foreigner as a member. It does not matter how the issue was brought to her attention – once she knows, she has to act which she did. I say, “Bravo” to her. What remains is to make her decision public which is a little bit overdue.

  I agree that enabling Jawar to leave the dark world of activism and join mainstream politics is better but not by breaking the law of the country and intimidating officers.

  Finally, please refrain from ad hominem attack.

 2. ልጅ ተክሌ ቶሮነቶ
  መጠፉንስ የመሰለዎትን ይጠፉ፤ እሺ ይህን እንደጥጌ ራዳ አበባ የደመቀውን ሰው ፊት ለምድነው ያጠቆሩት? እኮ ለምን?

 3. “ብርሀኑ ነጋ የኤርትራን ፓስፖርት የተጠቀመው ለትግሉ ከሆነ፤[1]
  የጃዋር የአሜሪካ ፓስፖርትም ለትግል የተወሰደ የማይሆንበት ምክንያት አይታየኝም፡፡“ …

  ሁለት ሊገናኙ የማይችሉ ደካማ ንፅፅሮች ናቸው:: የአሜሪካ ፓስፖርት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት እንዳሻው ለሚፈልገው የሚያድለው ደብተር አይደለም:: በአፍሪካ ግን አንድ መሪ ዜጋ ላልሆነው የውጪ ሰው ሊሰጥበት የሚችልበት ብዙ አጋጣሚዎች አሉ:: ቀዳማዊ ሀይለስላሴ ለኔልሰን ማንዴላ እንግሊዝ ሀገር እንዲገባ ሰጥተዋል:: መለስ ዜናዊም በሶማሌ ፓስፖርት ይጠቀም እንደነበር ይታወቃል:: ብርሀኑ ነጋ ከኤርትራ ፓስፖርት ማግኘቱ የዜግነት ጉዳይ ሳይሆን አንድ የአፍሪካ መሪ ለሌላ ፖለቲካ ታጋይ የሚያደርገው ችሮታ ነው::
  ይህንን ደካማ ሎጂክ አንድ የአሜሪካ ዜጋ ከሆነው ጃዋር መሀመድ ጋር አምጥተህ መደንቆርህ ትርጉም አልባ ነው::ጥያቄው መሆን ያለበት ጃዋር ዛሬ ህጋዊ የኢትዮጵያ ዜግነት አለው?

 4. ጅብ የማያቁት ሀገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ አለ አሉ… ለመሆኑ ልጅ ተክሌ የካናዳ ሕግ ከኢትዮጵያ ሕግ በልጦ ሊፈላሰፍ ነው? የካናዳ የስደተኛ ሕግ ዕውቀት የምርጫንም የፖለቲካውንም የቤተሰብ የእንስሣ ሕግ አብሮ መቀወጥ ካናዳ የተለመደ ነው? ለነገሩ ካናዳ ጠበቃ ለመሆን ካለው ደንቆሮ ስደተኛ ትንሽ በለጥ ብሎ ከተገኘ ድሮ ኢትዮጵያ ውስጥ የሳይንስ አስተማሪው፡ የኅብረተሰብ አስተማሪ ሲቀር እንደሚተካው፡ የሙዚቃ አስተማሪው የሰዕል አስተማሪን ተከቶ እንደሚሰራው ካናዳም እንዲሁ መበጥረቅ ይቻላል። ወረቀቱ ታትሞ ኮምፒተሩ ወስጥ አለ። ተሳሳትኩ?
  ካናዳ በአንድ ገፅ የክስ ማመልከቻ ወረቀት ሥም፡ አድራሻ፡ ፆታ፡ ቀን ቀይረህ አንድሺህ ባለጉዳይ ማስተናገድ ይቻላል። ምክንያቱም በዲሞክራሲ ፍርድ ለሁሉም አንድ ይሁን ስለሚባል ዳኛው ሳይጨነቅ ጠባቃው ሳይሟገት በስልክ ፍርድ የሚሰጥበት የከብት ሀገር ነው። ከከፍተኛው ፍርድ ቤት በስተቀር (እዚያ ደሞ ሽንጥህን ገትረህ ከተናገርክ ቃልህን አባዝተው በክብር ከየት እንደመጣህ፡ እንዴት ይህንን መሞገት እንደቻልክ ተጠንቶ በፍርድ ቤቱ ለሌላ ግዜ ለልምድ ተሞክሮ ይወሰዳል)ሌላውን ተወው ኢትዮጵያ ውስጥ በድሮ ፲፭ ሳንቲም፡ ወረቀትና ክላሰር ከአንተ፡ ጉልበታቸው ላይ በቁራጭ ካርቶን አስደግፈው በእየ ፍርድ ቤቱ አጥር ሥር የሚፅፉ ራፖር ጸሐፊያን ድንቅ የቃላት አሰካክና አገላልፅ፡ እነተክሌ በሰዓት ሁለት መቶ ዶላር ለሚነጩት ድሃ ስደተኛ የበለጠ እንደሆነ እንመሠክራለን! ካናዳውያንም ያውቃሉ!!
  ኢትዮጵያዊ ሆነህ ኢትዮጵያ ትንሽ የሕግ ዕውቀት ካለህ የካናዳ ፍርድ ቤት ከገባህ አዳምጠህ ስትወጣ እራስህን ታጠፋለህ!! ወይንም እዚያው ከጠበቃህ አንንገት ለአንገት ተያይዘህ ሌላ ወንጀል ውስጥ ትገባለህ።
  ለነገሩ ጠበቃህ ፍርድ ቤት ይዞህ ገብቶ አስፈርዶብህ በጓዳ በር ይጠፋል። አንተ ፍርድ ቤት ሳትገባ ሁለቱም ጠበቆች ሳይደክሙ በስልክ ድርድር ብለው እየተቀባበሉ ገንዝብህን ስትጨርስ ፪፻ ጠይቀህ ፯፭ ማግኘትህን እንደትልቅ ስኬት ደወለው ያበስሩሃል። አንተ አንጀትህ ያራል እነሱ ጉዳዩን ፍርድ ቤት ባለመወሰዳቸው ድንቅ ጠበቆች ይባላሉ።
  ወዳጄ ሁሉን ቢያወሩት ሆድ ባዶ ይቀራል…የባሰ አለ ሀገርህን አትልቀቅ አለ የሀገሬ ሰው..

  ይህ ሰዬ እዚህ የዘበዘበው በአማርኛ የገባው ይጻፍልኝ…”ብርቱካን የሰው ጥቆማ ቢደርሳት የጀዋርን ዜግነት ማረጋገጧ ትክክል ነበርች፡ ዜናውን ከሚዲያ በመስማት ዜግነት ማረጋገጫ መጠየቋ ትክክል አደለም!? (ካናዳ ማለት ይህ ነው)ስምህ ማነው? እና ስሙ ማን እንደሆነ ጠይቁት፧ ስሙ ማነው? ማለት የተለያዩ ናቸውን? ድንቄም የካናዳ አቮካ ፡ አቮካዶ በለው!

 5. በለው !

  ምነው በለው ስላሉህ ዝም ብላህ አንደመጣልህ ታወርደዋልህ። በተክሌ መናደድ አንድ ነገር ነው። ንዴትን ለማስተንፈስ ሲባል ብቻ ያልሆነ ያልሆነ ነገር መጻፍ መረጃ የሌለውን አንባቢ ያሳስታል። ስለካናዳ የህግ ስርዓት የጻፍከው በአብዛኛው ውቨት ነው። አንዳንድ እውነት የሚመስሉ ነገሮች ቢኖሩበትም እነሱም ተውገርግረና ተክሌን ለማናደድ ስትል ያልቅጥ ያጋነንካቸው ናቸው። ካናዳ የዲሞክራሲና የህግ ሃገር ነው። በዚህም ልናከብራቸውና ከነሱም ልንማር ይገባል። የማታውቀውን ስለዘባረቅህ የምትለውጠው ነገር የለም።

  ከላይ እንዳየሁት አንድ ወንድማችን የተክሌን የብርቱካን ተከለ ሰውነት ላይ ያተኮረ የማጣጣል ጽሁፍ በሚገባ ተቃውሟል። እሷ የምትመራው ተቋምና ቦርዱ ላይ መጻፍ ነበረበት ባይ ይመስለኛል። አሁን አንተ ደግሞ ተደገምክበት፤ያሳዝናል። ብታርመው ደህና መሰለኝ። ማረሙ የተቫለና ጠቃሚ ነገር ለማሰብና ለመጻፍ ይረዳሃል። ተክሌ በምንም ዓይነት ህግ ይስራ ምርጫውና ሙያው ሊከበርለት ይገባል። ዝም ብሎ ስው መዘርጠጥ ሕግ መጣስም ይሆናል። በዚህ (IT) ዘመን ደግሞ ሥም አጥፍቶ ከክስ ማምለጥ ቀላል አይደለም። በተለይም ከካናዳ ክስ።

  አይ በለው ! ስምን መልዓክ ያወጣዋል ይበሉ። እስቲ ተክሌ ስለጻፈው የምትለው ነገር ካለህ አካፍለን። አለበለዚያ “አህያውን ፈርቶ ዳውላውን” እንልሃለን። ከአጻጻፍህ የህግ “ሃ ሁ” የቆጠርክ ትመስላለህ።

  • ወንድም(የ)በላይነሽ ታዬ (AAU)
   ስለካናዳ የህግ ስርዓት የጻፍከው በአብዛኛው ውቨት(ውሸት) ነው። ካናዳ የዲሞክራሲና የህግ ሃገር ነው። በዚህም ልናከብራቸውና ከነሱም ልንማር ይገባል። የማታውቀውን ስለዘባረቅህ የምትለውጠው ነገር የለም።””የፈረደበት “ዲሞክራሲ የሕግ የበላይነት” በጡጦ ነው የተሰጣችሁ ወይስ እትብታችሁ ሲቆረጥ በምትኩ ተነቅሳችሁታል?”ሁላችሁ በቀቀን ሆናችኋል?
   ***ይህንን ካነበብኩ በኋላ ልስቅ ፈለኩና” ማልቀስም ከጀለኝ “ጅል አይሙት እንዲያጫውት የሚሉት ያዘኝ…”ይህ እኔ ምን አገባኝ የምትሉት ነገር አረዳት ሀገሬን እንደበግ እኔም ምን አገባኝ የሚል ግጥም መጻፍ ፈለኩና ምንአገባኝ ብዬ ተውኩት እንደገና ያለ የፒያሳ ልጅ ግጥም መጣብኝ…ይችን ግጥም ከአነበብኩ በኋላ ምንገባኝ ያልኩትን እንዴት ተደርጎ! ብዬ ተናግሬ ሀገሬን ማስከበሬን ሳውቀው ሁልግዜ አደንቀዋለሁ።
   **ተክሌ”ብርቱካን የምትመራው ተቋምና ቦርዱ ላይ መጻፍ ነበረበት ባይ ይመስለኛል። አሁን አንተ ደግሞ ተደገምክበት፤ያሳዝናል። ብታርመው ደህና መሰለኝ።”
   መጀመሪያ ለማረም የታራሚው ፍቃደኝነት ይጠይቃል፡ ድሮ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሊ/መ ነኝ ብሎ አንገቱ ላይ ሻርብ ይጠመጥም ነበር መሰለኝ እንግዲህ አንቺም መሪያችን ተነካ ብለሽ ዘራፍ ማለትሽ መሰለኝ…ያ ካናዳ ሲነሳ ተክሌና ኢትዮጵያ ፈርስት ቢኒያም ከበደ ድቅን ይሉብኛል…የት ሄደ? ደሀና ነው? ሰላም በይልኝ!።
   ….ዝም ብሎ ስው መዘርጠጥ ሕግ መጣስም ይሆናል። በዚህ (IT) ዘመን ደግሞ ሥም አጥፍቶ ከክስ ማምለጥ ቀላል አይደለም። በተለይም ከካናዳ ክስ።” “አታስቢ አታስቢ” ቢሏት የመገዘዝ ዓይጥ ምን ትበላ ይሆን ብላ አሰበች ይሉሻል ይህ ነው። ይህንን ካናዳውያኑ ቢሰሙ (ሀ) በላይነሽ ታዬ እንዴት ለካናዳ ፎንቃ ያዛት? (ለ)ከዚህ በፊት ገብታ የጠፋች ትሆን እንዴ እንዴት ከእኛ በላይ አወቀችን ብለው ይስቃሉ?(ሐ)ካናዳ መሔድ ፈለጋ ነው ቢባል ” እኛ መስፈርታችን ምን ታውቂያለሽ እንጂ ማን ታውቂያለሽ አደለም ቢሉስ?
   *** መሆን ያለበት ይህ እጁን እግር አድርጎ ግብር እየከፈለ የሚያኖርሽን ገበሬ አድንቂ!!ውለታ ከፋይ ያድርግሽ፡ በግልሽ ከፍለሽም ብትንማሪ እንኳ ሆድሽን የሚሞላው የሀገሬ የዋህና ደሃ ገበሬ እንጂ ካናዳዊው የተክሌ አበበ ወሬ አደለም።
   ካናዳ ከጥቂት ምሁራን በቀር የሚያወቅሽ በስንዴ ለማኝነት ነው የሰው የስንዴ ዘር ባለቤትነታችን ተረስቷል። ነጭ አምላኪዎችም እንዲህ እንደአንቺው የማያቁትን ይዘረጥጣሉ”
   ** ዩኒቨርሲቲ ስላለሽ THE LAW OF PHYSICAL PERSON (1-393) by JACQUES VANDERLINDEN የእኛን የኢትዮጵያን የቤተሰብ ሕግ ተችቶ ከአውሮፓውያን ጋር እንዴት መመሳሰል እንዳለበት ሲውተረተር ቆይቶ እንዲህ ይላል። “ሁሉን ተችተን ከእኛ(ፈረንሳይ)(አውሮፓውያን)ሕግና ሕዝብ ጋር እንዴት ቢመሳሰል ይሻላል ብለን ጥረት አደረግን እንጂ ሙሉ በሙሉ አልነቀፍንም!። ይልቁንም የኢትዮጵያ አንዳንድ የሕግ አንቀፆች በሚያስገርም ሁኔታ ላልተማረ(ፊደል) ላልቆጠረ ሕዝባቸው ያለ ጠበቃ እንዲቆሙ የሚያደርግ የሚከላከልላቸው ስለሆኑ፡ ኢትዮጵያውያን ፍርድ ቤት ለመሔድ ለጠበቃም አይጭነቁም እነሱም ፍርድ ቤት ሲሟገቱ ሕግን አይፈሩም” ይላቸዋል። ተግባባን ?! ይቺ ናት የኔ ሀገር በለው!

 6. አቶ ተክሌ ካሁን በፊትም የሚጽፋቸውን መጣጥፎች የማንበብና ቀለመጠይቆችን የመስማት አጋጣሚዎች ነበሩ እንደታዘብኩት በጣም controversial (አወዛጋቢ) ከእውነታና ከብዙኃኑ አመለካከት ያፈነገጠ ፤ የሚያቀርባቸው መረጃዎችም ሆኑ logic (አመክንዮ) አሳማኝ አይደለም ። አቶ ተክሌ እንደ አንድ የህግ ባለሞያ ወይዘሪት ብርቱካንን የሚተቸው ህግ ተላልፋለች ብሎና ጀዋርም የአሜሪካንን ዜጊነት ይዞ መምረጥና መመረጥ ይችላል ብሎ አይደለም እያለ ያለው አቶ ጃዋር ያለውን ይዞ ሌሎችም የባእድ ዜጋ ሆነው አልተጠየቁም ነው ለዚህ ደግሞ ወይዘሪት ብርቱካን በአሜሪካ ሬዲዮ ተጠይቀው ከጀነራል ካማል ገልቹ ፓርቲ አንድ ግለሰብ የእንግሊዝ ዜግነት ያለው ኃላፊነቱን እንዲለቀ ማስደረጋቸውን ገልጻለች ሌላው ደግሞ በአባላት ምዝገባ የአቶ ትግሥቱ አወሉ አንድነት ፓርቲ የሌሉ ሰዎች ስም ዝርዝር ስጥተው ምርጫ ቦርድ ጉዳዩን ለፖሊስ ሰጥተው ምርመራ እየተካሄደ ነው ። ታዲያ ጃዋር ከህግ በላይ ሆኖ ንጹኃን ዜጎቻችን ለእልቂት መዳረጉን እያወቀ አቶ ተክሌ መንግሥት ፈርቶ ይሁን በሌላ ምክንያት የተወውን ጃዋር የምርጫ ቦርድ በድፍረት ህግ ተላልፈሀል አልጣስኩም ካልክ መረጃ አቅርብ ማለቱ በምን መስፈርት ሴራ ሊሆን ይችላል ? ሌላው የምርጫ ቦርድ በህግ የተሰጠውን ኃላፊነት ለመወጣት ግለሰቦችም ሆኑ ድርጅቶች ህግ መተላለፋቸውን ቢያውቅም ሌላ ሰው ክስ እስከሚያቀርብ መጠበቅ ነበረበት የሚለው የአቶ ተክሌ አባባል ምንም እንኳን የህግ ባለሙያ ባልሆንም ህጋዊ መሰረት ያለውና ቦርዱን ከመንግሥት ጋር መመሳጠሩን አያሳይም። አቶ ተክሌ ጃዋርን በተመለከተ ያላቸው አመለካከት መብታቸው በመሆኑ የምለው አይኖረኝም ።

 7. ይሄን ሰዉዬ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ አየዋለሁ አንድ ዉል ያለዉ ነገር ሲናገር አልሰማዉም በዚህ ላይ በጣም እይታን የሚፈልግና አስተሳሰቡ ያልተቀረጸ ነገርን ከራሱ ግንዛቤ ብቻ የሚመለከት ሰዉ ነዉ። አንድ ሰሞን ከወያኔ በላይ ወያኔም ሁኖ ነበር የሚያሳዝነዉ በቅርቡ ኢትዮ 360 ብዙ የምንማርበትን የአየር ሰአት ለእሱ አዉሎ ግለሰቡ እራሱን ሲያስተዋዉቅበት ዉሎ ተቋጨ።
  አቶ ተክላይ ኢትዮጵያ የምሁር ደሀ አይደለችም አቅሙ ካለህ እንደነ አቻምየለህ በሰነድ አስደግፈህ ተቃዋሚህን በክንድ ጠምዝዝ ክርክር ሳይሆን ሎጂክን ተከተለህ ታሪክ አጣቅሰህ አስተምረን አለበለዚያ እይታ ፍለጋን እያነፈነፈክ መከራችንን አታብዛዉ የአባይ ጉዳይ ቀስፎ ይዞናል ወያኔ እንዳያስቡ ያደረጋቸዉ ዜጎች በነጁዋር የዉሎ አበል አገርን መከራ ያበላሉ እነ በቀለ ገርባ መራራ ጉዲና አቅጣጫ ማሳያቸዉ ተበላሺቶ ተከታዮቻቸዉን ይመርዛሉ በዚህ ላይ አንተ ተጨምረህ አንችለዉም።
  ጁዋር መሀመድ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም ብሎ በአለም ሚዲያ የነገረን ሲሆን የአሜሪካ ዜግነትነቴን አልመልስም የክፉ ጊዜ መጠለያዬ ነች ብሎ ነግሮናል። አንተ ቡርኪና ፋሶ ሂደህ አገር አታምስም፤ ምረጡኝም አትልም፤ ባስተሳስብ የተጎዱ ህጻናትን ጉርሻ እየሰጠህ ሰዉ ግደሉ አትልም እባክህ ትኩሳታችንን አትጨምረዉ በዚህ ላይ ጠበቃ ነኝ ስትል የሰማሁ መሰለኝ።
  ወይ ነጻ አስተሳስብ ያለዉ ብለዉ እንዲያጨብጭቡልህ አቶ ሕዝቅኤል ጋቢሳ ተስፋዬ ገ/አብ እና የቀድሞ ወዳጆችህ ጋር አንድ ድርጅት ነገር ፍጠር በዚህ ጉዳይ ትግሬዎችም ሳይረዱህ አይቀሩም። አንተም ትግሬ ከሆንክ ጥንቃቄ እንድናደርግ ንገረን።
  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

 8. Prosperity Party is a fairy tale which is created illegally by bribing the electoral board .
  The electrical board is illegitimate since it recognized Prosperity Party illegally, as Prosperity Party is illegitimate also.
  Prosperity Party got no legal right to govern the country , Prosperity Party is not fit to govern even one Qebele since it doesn’t legally exist .

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.