ግብፅ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያን በመቃወም ለዓረብ ሊግ ያቀረበችውን ሰነድ ሱዳን እንደማትቀበለው አስታወቀች

Areb unionግብፅ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያን በመቃወም ለዓረብ ሊግ ያቀረበችውን ሰነድ ሱዳን እንደማትቀበለው አስታውቃለች፡፡

በግብጽ ካይሮ በተካሔደው የዓረብ ሊግ 153ኛ የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ግብጽ በግድብ ዙሪያ የሊጉ አባል አገራት ከጎኗ እንዲቆሙ ያቀረበችውን ሰነድ ላይ ነው ሱዳን ያላትን ልዩነት የገለፀችው፡፡

በስብሰባው ላይ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሽኩሪ፣ የአረብ ሀገራት በግድቡ ዙሪያ ከግብጽ እና ሱዳን ጎን እንዲቆሙ ጥያቄ አቅርበው ነበር፡፡

ነገር ግን ሱዳን በህዳሴ ግድብ ላይ የዓረብ ሊግ ከግብፅ ጋር ለመቆም ያሳለፈውን የትብብር ውሳኔም እንደምትቃወም አስታውቃለች፡፡

በግብጽ የተዘጋጀውን ሰነድ እንደማትቀበል ያስታወቀችው ሱዳን ከሰነዱ ስሟ እንዲወጣም አድርጋለች፡፡

ግብጽ ኢትዮጵያን በመወንጀል ለሊጉ ያቀረበችው ረቂቅ የድጋፍ ሰነድ፣ የዓረብ ሀገራት ኢትዮጵያን በመቃወም ከግብጽና ሱዳን ጋር እንዲቆሙ የሚጠይቅ ነው፡፡

የዓረብ ሊግም ግብጽ በአባይ ዉሀ ላይ ያላትን ታሪካዊ መብት የሚደግፍ እና የኢትዮጵያን የተናጥል ውሳኔ የሚኮንን ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ይሁንና ሰነዱ አይመለከተኝም ያለችው ካርቱም ከህዳሴ ግድብ ጋር ተያይዞ ሊጉ ከግብፅ እና ሱዳን ጋር እንዲቆም የሚጠይቀውን ረቂቅ የድጋፍ ሰነድ ውድቅ አድርጋለች፡፡

በግብጽ የቀረበው ሰነድ፣ ኢትዮጵያን የሚያስቀይም ከመሆኑም ባለፈ የሀገሯን ብሔራዊ ጥቅም እንደሚጋፋም ነው ሱዳን በስብሰባው ላይ ያነሳችው፡፡

ሱዳን እንደዚህ ያሉ ሰነዶች እና መግለጫዎች በግድቡ ዙሪያ የሚደረጉ ድርድሮችን ሊያደናቅፉ እና የዓረብ እና የኢትዮጵያን ግንኙነት የበለጠ ሊያበላሹ እንደሚችሉ አንስታ መከራከሯ አግራሞት መጫሩም አህራም የተሰኘውን የግብፅ ሚድያ ጠቅሶ ኢቢሲ ዘግቧል።
(ኢ.ፕ.ድ)

1 Comment

  1. Baravo Sudan!! Your stand is a reminding of great historians and liberation front who have been struggle for independence and sovereignty. You are an icon on this century as others are clapping and vowing on support of immoral, unethical and unlawful actions.

    Truth never dies for ever but always flourish as you did. No way for imposition on this modern generation despite we are vulnerable to political unrest, poverty & drought. But we can unleash our resources and work to grow together for sake of our people. So you political leaders have free field to play the game and move your people one step forward. Don’t depend and agitate by mischief world politics.

    Great job by Sudan!!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.