የኤሜሪካ ኤምባሲ በምርጫ 2012 ዙሪያ የውይይት መድረክ አካሄደ

88183205 1571235663027776 5148564420850352128 n የኤሜሪካ ኤምባሲ በምርጫ 2012 ዙሪያ የውይይት መድረክ አካሄደበዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ የኤሜሪካ ኤምባሲ አገር አቀፍ ብዙሃን መገናኛዎችን ማጎልበት ለነፃ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በሚል ምርጫ 2012 ዓ.ም ላይ የውይይት መድረክ አካሄዷል፡፡

በመድረኩ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን እንዲሁም ከተለያዩ ብዙሃን መገናኛዎች የተውጣጡ ባለሞያዎች ተሳታፊ ሲሆኑ፤ ለውይይት በቀረቡ ሐሳቦች ላይ ጥያቄዎቻቸውንና አስተያየታቸውን አቅርበዋል፡፡

በደህንነት ምርምር ተቋም ከፍተኛ ተመራማሪ ዶክተር ሠሚር ዩሱፍ፤ ብዙሃን መገናኛዎች በአገሪቱ ሠላማዊ ዴሞክራሲያዊ ሽግግር ዕውን እንዲሆን ዓላማ አድርገው መሥራት እንደሚጠበቅባቸው በመድረኩ ተናግረዋል፡፡ ይህንን ለማድረግ ደግሞ የዴሞክራሲ ተቋማት እንዲጎለብቱ የተለያዩ ተግባራትን ማከናወን ይገባል፡፡

በዚህም ልዩነት ያላቸው ሐሳቦች ጨዋነት በተላበሱ መንገድ እንዲራመዱ፣ ከልሒቃን ተኮር ዘገባ ባሻገር ሠፊው ማሕበረሰብ ምን ያስባል? በሚል ማስተናገድ እንዲሁም አንዱን ማሕበረሰብ ከሌላው የሚያጋጩና ሁከት ቀስቃሽ ሁኔታዎችን በጥልቀት በማጤን ብዙሃን መገናኛዎቹ የተለያዩ አስተሳሰቦችን ሊያስተናገዱ ይገባል፡፡ ጋዜጠኞችም ሙያቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁና በሥነምግባር የታነፁ ሊሆኑ እንደሚገባ መዘንጋት የለበትምእንደሌለበት ጠቁመዋል፡፡

በአገሪቱ ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ብዙሃን መገናኛዎች በመንግሥትና በግል ቁጥጥር ሥር በመሆናቸው ራሳቸውን ችለው እንዳይቆሙ አድርጓቸዋል፡፡ ይህም የመንግሥት አስተሳሰብን እንዲሁም በግል የተቋቋሙትም ያቋቋሟቸውን የፖለቲካ ድርጅቶች ወግነው የተለያዩ የፖለቲካ አስተሳሰቦች ማራመጃ እንጂ ብዝሃነት የማይስተዋልባቸው በመሆናቸው ምን ዓይነት መፍትሔዎች ይሻሉ?፣ ግጭት ቀስቃሽ ዘገባዎችን ለሕብረተሰቡ ተደራሽ የሚያደርጉ ብዙሃን መገናኛዎች ላይ ምን እርምጃ ተወሰደ? ምን መሻሻሎችስ ተገኙ?፣ ሕብረተሰቡ በቅርብ የሚከታተላቸው የማሕበረሰብ አቀፍ ሬድዮዎችንስ ለምርጫ እንዴት መጠቀም ታስቧል የሚሉ ጥያቄዎች ከተሳታፊዎች ተነስተዋል፡፡

ዶክተር ሠሚር ከተሳታፊዎች ለተነሱ ሐሳበች በሰጡት ምላሽ፤ ምንም እንኳ ሁሉም ብዙሃን መገናኛዎች ሲቋቋሙ የበለጠ ማገልገል የሚሹት የሕብረተሰብ ክፍል ቢኖርም መሠረታዊ የጋዜጠኝነት መርሆዎችና ሥነምግባርን በማክበር ማጣጠን ግን እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡ ፖለቲካና ብዙሃን መገናኛ ተነጣጥለው የሚታዩ አለመሆናቸውን በመግለጽ፤ የፖለቲካው ጤንነት፣ ትኩሳት ብሎም ግብግብ ሚድያውን አውድማ ማድረጋቸው አይቀሬ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ መንግሥትም ሆነ ተፎካካሪ የፖለቲካ ተጠቃሚ የሚሆኑት ዴሞክራያዊ ሽግግር ሲኖር እንደሆነ ከግምት በማስገባት ሥራዎቻቸውን በዚህ መልኩ ሊቃኙ ይገባልም ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን አንዱዓለም፤ ባለሥልጣኑ ከዚህ ቀደም ከብዙሃን መገናኛዎቹ ጋር በአይጥና ድመት የሚመሰል ግንኙነት እንደነበረው አስታውሰዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ግንኙነቱን የተሻለ ለማድረግ የተሠራ ሥራ ቢኖርም ከሚደረገው ቁጥጥር በተጨማሪ የተለያዩ ጥቆማዎች ይደርሳሉ፡፡ ምንም እንኳ ባለሥልጣኑ በአዋጅ ሚድያዎቹን ክትትልና ቁጥጥር የማድረግ ሥልጣን ቢሠጠውም ይህንን የማያውቁ አካላት መኖራቸውም ተደርሶበታል፡፡ በመሆኑም ቅድሚያ አቅም ማጎልበት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራና ጎን ለጎን ደግሞ የሕግ ማዕቀፎቹንም ለማስከበር እየሠራ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሕዝብ ግንኑነት ኃላፊ ሶልያና ሽመልስ በበኩላቸው፤ መሀል ከተማ ውጪ በየክልሉ የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠናዎች እየተሠቱ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከሁለት ሣምንት በፊት በአገሪቱ የሚገኙ ሁሉም ማሕበረሰብ አቀፍ ሬድዮኖች ሥልጠና እንዲወስዱ የተደረገ ሲሆን፤ በቀጣይም ሕብረተሰቡ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃዎች እንዲደርሱት ይሠራል፡፡ በዚህም በተለያዩ ማሕበራዊ ሚድያዎች ተፅዕኖ ፈጣሪ ለሆኑ ግለሰቦችንም ያካተቱ መድረኮች እንደሚኖሩ አመላክተዋል፡፡

ፍዮሪ ተወልደ
ፎቶ ፀሐይ ንጉሤ

(ኢ.ፕ.ድ)

2 Comments

 1. Can someone please catch the diplomats that are illegally financial outflawing .
  You know Abiy is worried about his financial future and his children’s financial future President Sahleworq too.

  Addis Standard
  News: Illicit financial flows transferred across Africa amount to a staggering …

  http://addisstandard.com/news-illicit-financial-flows-transferred-across-africa-amount-to-a-staggering-loss-of-us100-billion-annually/

  Ato Bacha Gina is suspected of stealing too much money too quickly from the Commercial Bank of Ethiopia thus he made Commercial Bank of Ethiopia forced to ask emergency 50 billions loan from the National Bank of Ethiopia on top of the 100 billion birrs the Commercial Bank of Ethiopia borrowed from the National Bank of Ethiopia without returning it yet.

  Abit & Co. needs money to smuggle out of the country quick before the next “election” to have somewhere to run to depending on the outcome then who better to do the money smuggling than Bacha Gina , Berhanu Tsegaye and associates?

  Bacha Gina who robbed the Commercial Bank of Ethiopia making the Bank reach the verge of closing it’s doors , Berhanu Tsegaye who tortured and killed the whistleblowers. Now Abiy gave both Berhanu Tsegaye and Bacha Gina diplomatic immunity so they launder the money they stole using their newly gotten diplomatic immunity .

  https://www.ethiopianregistrar.com/amharic/?p=75549

  Ethsat.com › 2018/06 › loans-to-go…
  Web results
  Loans to govt projects by Commercial Bank of Ethiopia reaches 14.5B USD …

  Ethsat.com › 2018/12 › ethiopia-los…
  Ethiopia lost $36B in illicit financial flows – The Ethiopian Satellite Television and …

  http://addisstandard.com/news-illicit-financial-flows-transferred-across-africa-amount-to-a-staggering-loss-of-us100-billion-annually/

 2. Abay Tsehaye’s Ethiopian Bank files along with the sugar projects files, need to get audited extensively so Prosperity Party can win votes in Tigray region during the next election.

  CGTN › africa › Africa Live
  Web results
  UN seeks $1 billion for Ethiopia humanitarian response for 2020 …

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.