ኦፊኮ ዋጋው ስንት ይሆን? – ከታምራት ይገዙ 

ovalየዚህ ጹሁፍ አቀራረብ የፖለትካ አመለካከትን ለመተቸት አይደለም፡ አሊያም ቅድሚያ ሊሰጣቸው ከሚችሉ ከዋና ሀገራዊ እሳቤ ወረድ ያሉ የጉልበታምን የተፎካካሪ ድርጅት መሪዎችን ማብጠልጠልም ወይም የፈደራሊስቶች ነን ባዮቹን አላግባብ መፈራገጥንም ጥፋታቸውን ነቅሶ ለማውጣት አይደለም። አሊያም የኦፊኮ አባል መሆን ወደፊት ሰቆቃና መከራ መሆኑ መራራ ሐቅ እንደሚሆን ለመገመትም አይደለም።

ሰሞኑን በአንዳንድ የኦፊኮ አመራሮችና አባላቶች እየተነገሩ ያሉት መራራ አባባሎች በድርጅቱ መሪ በፕ/ር መረራ ሰም የሚጠሩ መራራ ውሸቶች ከመሆናቸው በላይ ድርጅቱን ኦፊኮንም ሆነ ኩሩውኑ የኦሮሞ ህዝብ በተለይ የኦፊኮን ደርጅት የመሰረቱት የሸዋን ኦሮሞዎችን የማይወክልና የሸዋን ኦሮሞን ስነ ልቦና ያላገናዘበ ነው ብል መሳሳት አይመስለኝም።

እንደሚታወቀው ኦፊኮ የሁለት የኦሮሞ ድርጅት ወህደት ሲሆን እነርሱም በነ አቶ ገብሩ ገብሩ ማርያም እና በፕ/ር መራራ የሚመራ የነበረው ኦሮሞ ብሄራዊ ኮንግረስ በመባል የሚታወቀው ድርጅት እና በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ይመራ የነበረው የኦሮሞ ፌደራሊስት ዴሞክራቲክ ንቅናቄ ድርጅት የፈጠረው ውህደት ነው። ኦፊኮ የነዚህ የሁለት ድርጅቶች ውህደት ሆኖ ሲዋሀድ በመሪዎቹ ሆነ በድርጅቱ አመራሮች በኩል የOLF አመለካከት የሉም አልነበሩም ብዪ አስ ባለው ምክንያቱም ኦፊኮን ከመሰረቱት አመራሮች ውስጥ እንደነ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ያሉ  የእድሜ ባለጸጉች ሆኑ አንደነ አቶ ገብሩ ገብረ ማርያም ያሉ ሰዎች ኦፊኮን በተለያዩ እርከኖች ላይ ሆነው መርተዋልና።

ሰሞኑን የኦፊኮ ዋና ሊቀመንበር ፕ/ር መረራ በተገኙበት የአደባባይ ሰብሰባ ላይ መራራ የሆነ እና ኦፊኮ ከተነሳበት፤ ከቆመለት ራይ የአፈነገጠና የኦነግ አጀንዳ ሲነገርበት ሲሰማ የሁሉንም የኦፊኮ አባላቶችን ማለት በሚቻል ደረጃ ልባቸውን በከባድ ሀዘን የሰበረ፤ በቁጭት ያንገበገበ አሳ ዛኝ የፖለቲካ ደራማ ነበር ቢባል ማጋነን አይሆንም።

ርግጥ ነው እንዲህ አይነቱ ከሞራል ውጪ የሆነ ነገር የኦሮሞን ህዝብ በሐይማኖቱና በዘሩ አማካኝቶ በውስጣቸው እልቂትና መከራ እንዲነግስ ነጋሪት ሲጎሰም ከጀመረ ዓመታት ነጉደዋል፤ ነገር ግን መነሻ ክፍለ ሀገሩ በሸዋ  ውስጥ አይደለም ብል መሳሳት አይሆንም።

ይህንን በኦፊኮ ስም በተጠራ የአደባብይ ንግግር ላይ የወቅቱ የኦፊኮ ሊቀመንበር ፕ/ር መረራ የተገኙ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የኦፊኮን መሪ ለመሆንና ኦፊኮን ጨብጦ ሊዘውር እየዳዳ ያለው ሰሞኑን ኦፊኮን ተቀላቅያለው ያለው አቶ ጀዎርም በሰብሰባው ላይ ተሰይሞል፤ ንግግሩንም ያደረገው አንድ የኦሮሞ ቤተ ክህነት መስራች ነኝ የሚሉ ሐሰተኛ ነብይ ሲሆኑ በንግግራቸው ወቅት የአቶ ጀዋርን አካላዊ እንቅስቃሴ ምን እንደሚመስል እና የሀሰተኛውንም ነብይ ንግግር ለማድ መጥ ይህንን ሊንክ ይጫኑት https://www.facebook.com/ZemedkunBekeleB/videos/ 496258974647858/

እኔ ልዩ ኦሮሞ ነኝ ግን ኦነግ ሆኜ አላውቅም የተከበሩ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ!! ይህ አባባል ለኦፊኮ አመራሮች ምን ማለት ይሆን? ይህ አባባል ለእኔ እንደገባኝ ከሆነ ኦፊኮ ኦነግ ሆኖ አያ ውቅም አየደለምም የኦፎኮ መስራቾችና የሸዋ ኦሮሞዋች ኩሩ ኢትዮጵያውያኖችና በኢትዮጵያ ሏአላዊነት የማይደራደሩ ልዩ ኦሮሞዎች ናቸው እኔም ከነሱ የተገኘው ኩሩ ኢትዮጵያዊ የኦሮሞ ተወላጅ ነኝ ማለታቸው ይመስለኛል።

እኔ በዚህ ሰዓት የኦፊኮ አመራሮ ከሆኑትና ከነበሩት ለምሳሌ ለነ አቶ ገብሩ ገብረ ማርያም ለነ አቶ ሙላቱ እንዲሁሁም ለመላው የኦፊኮ ድርጅት አባላቶችና ደጋፊዎች ያለኝ ጥያቄ በአሁኑ ሰዓት በኢት ዮጵያ ሉአላዊነት ላይ አቋማችሁ እንዴት ነው? ኦፊኮን ስትመሰርቱ እንደነበራችሁት ነው? ወይስ አቶ ጀዋር አገር ውስጥ ከገባና ድርጅታችሁን ከመቀላቀሉ በፊትም ሆን ከተቀላቀለ ቦሃላ የሱን ኦነጋዊ አመለካከት ተላበሳችሁት ትገኛላችሁ? እንደዚያ ከሆነ በአሁኑ ሰዓት ኦፊኮ ስንት ይሆን ዋጋው? ብዪ ለመጠየቅ እገደዳለው።

እናንት የኦፊኮ አመራሮች ሆይ በኢትዮጵያ ሉአላዊነት የሚያምኑት አባላቶችና ደጋፊዎቻችሁ “እናንት የበላችሁበትን ወጪት……..” ብለው ሳይነሱባችሁ በመሃላችሁ ሰርግረው የገቡትን እና ያልነበረባችውን የኦነግ አመለካከት የተጸናወታቸውን አመራሮቻችሁን ከመሃላችሁ ነቅሳችሁ ማውጫችው ሰዓቱ አሁን ነው እላለው። በሌላ በኩል ኦነጋዊ ሃይል ከውጪ በመግባት ሰብርብራችሁ ከማውጣቱ እና ከመክሰማችሁ በፊት እናንተ እንደ እንቁላሉ ከውስጥ ሰብራችሁ ወጥታችሁ ነፍስ ዘርታችሁ ድርጅታችሁን የምትታደጉበት ሰዓቱ አሁን ነው።

ያለዚያ ግን “ሰዶ ማሳደድ ካማረህ ዶሮህን በቆቅ ለውጥ” የሚለው የአባቶቻችን ብህላዊ አባባል በኦፊኮ ላይ መድረሱ አይቀሬ ነው። በተጨማሪ ባለፈው የአዲስ አበባን ዲሚግራፊ በመለወጥ ስም በሀረር ተወልደው ያደጉ የኦሮሞ ተወላጅ ወንድሞቻችን በጀዋር አጋፋሪነት በአቶ ለማ መገርሳ እሺ ባይነት  በሱሉልታ ሁለት ቦታዎች በሻሸመኔና ጥቁር ውሀ /አዋሳ መህል ፣ በለገጣፎ/ለገዳዲ ፣ ብቡራዩ አካባቢ ሰፍረው ይገኛሉ ካልተሳሳትኩ እነዚህ ቦታዎች ተደጋጋሚ ታይቶ የማይታወቅ ግጭት ተከስቶባቸዋ ብል ማጋነን አይሆንም። በነዚህ ከላይ በጠቀስኩባቸውም ሆነ በሌሎች የሸዋ ኦሮሞዎ አካባቢ ጭምር ሰፍረው የሚገኙት ኦሮሞ ወንድሞቻች እና እህቶቻችን በአቶ ጀዋር ተእዛዝ ኦፊኮን አፍረሰው ኦነግ የሚያደርጉት እነርሱ ናቸው የሚል እምነት አለኝ። ስለሆነም ኦፊኮዎች ውስጣችሁን መርመር ከውጪ በመጣ ሃይል ከመጨፍላቃችሁ በፊት እናንተ ከውስጥ ሰብራችሁ በመውጣት ኦፊኮን ታደጉት እያልኩ ለዛሬ ልሰናበት።

3 Comments

 1. Professor Merira Gudina of the Oromo Federalist Congress (OFECO) served his country as a Professor among so many other noble capacities for so many decades, he was finally given a token of appreciation by concerned good Samaritans, a residential house gift in a quiet part of the city where he can concentrate on his work to OFECO party and to his other work of intellectual cultivation.

  • Binijam Dogali

   Obeying elders command is a must whether the elder giving the order got a tiny mind or a big mind.

   ትናንሽና ትላልቅ ጭንቅላቶች!! – ፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር)

 2. What Tamirat Yigezu wrote is a political conspiracy to divide the Oromos into what he called ” Oromos of Shawa” and other Oromos. I think this reveals his stupidity for missing that Oromos are Oromoh from wherever geographical location they come. By the way, there is no such a naming as “Shaw Oromo’. All Oromos that live in what you call Shawa province, as named by Abyssinian rulers, consider themselves as belonging to the Tuulama Oromoo, an Oromo clan name. Shawa is the name used by Abyssinians.
  Tamirat used the name Shawa Oromo and wanted to differentiate from other Oromos as a means of dividing the one Oromo people. Tamirat with his devilish thinking and plan for dividing Oromos disguising under the context of advising OFCO to take care of political extremism, he was injecting poisonous massages. But his devilish plan will not succeed at this point in time when Oromos are more conscious than Tamirat about their rights to live as a first rank citizen in their own country. Religion and geographical location will not divide Oromo People. Irrespective of religion, geographical location, these days, Oromos have the same political motive and motto – self rule without any intervention in their internal affairs. The divide and rule tactic that Minilik used at the end of 19th century by arming Abbich Oromo to fight the Galan Oromo will not work today. Be from Abbichu or Gala, Arsi, Guji, Borana Ittu, Karrayyu, etc. all Oromos have the same objective – the right to self determination for self rule in Oromia and decide to live with other neighboring people peacefully without one supressing the other. Few Abyssinian political elites didn’t like this. One of these is Tamirat who posted such devilish idea to divide Oromo in what he called “Shawa Oromo” and non-Shawa Oromo. There is no such joke as your stipulated to divide Oromo People. Oromo is indivisible and stop your devilish plan to divide Oromos as it has been during Minilik.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.