የአዲስ አበባ ምክር ቤት መግለጫ
ሰኔ 12፣ 2018 ዓ.ም
የኢትዮጰያ ሕዝብ እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በአገዛዙ እና ኦነግ/ሸኔ ጥምር ኃይል ጦርነት ከተከፈተበት የደራ አማራ ሕዝብ ጎን መቆም ይገባቸዋል!!!
ሰኔ 12፣ 2018 ዓ.ም
ቁጥር—12 /10/2018/ 012
በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መርሃቤቴ አውራጃ፣ ደራ ወረዳ ላይ እራሱን ኦነግ (OLA) እያለ የሚጠራው እና ከአገዛዙ ጋር እየተናበበም እየተቀናጀም የሚንቀሳቀሰው ኃይል በአማራ ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት መክፈቱን ለማወቅ ተችሏል።
ጥቃቱ ከሰኔ 9 ቀን 2018 ጀምሮ በውድቅት ሌሊት የተጀመረ ሲሆን፣ ላለፉት ሶስት ተከታታይ ቀናት በተካሄደ አረመኔያዊ ጥቃት በርካታ ንጹሀን አማሮች በማንነታቸው እየተለዩ ተገድለዋል፣ በርካቶች ቀላል እና ከባድ የመቁሰል አደጋ ገጥማቸዋል፣ በርካቶችም ታግተዋል፣ እንዲሁም ከፍተኛ የንብረት ዘረፋ እና ውድመት ተፈጽማል። በአማራ ሕዝብ ላይ የጭፍጨፍ ጥቃት የከፈተው የኦሮሞ ነጻ አውጪ ሰራዊት/ሸኔ (OLA) የሚባለው ታጣቂ ኃይል ሲሆን፣ በአገዛዙ የመከላከያ ሰራዊት እና የአካባቢው ባለስልጣናት ከፍተኛ እገዛና ሽፋን እንደተሰጠው ከስፍራው ያሰባሰብነው መረጃ ያመላክታል።
ታጣቂው ኃይል ሰኔ 9 ቀን 2018 በጉንዶ መስቀል ጥቃቱን በመጀመር፣ በመርሃቤቴ በኩል ወደ ደራ አቅጣጫ፣ በስላሌ በኩል ወደ ደራ አቅጣጫ እና በምእራብ ወሎ በኩል ወደ ደራ አቅጣጫ በሶስት ግንባር ጨፍጫፊ ኃይል አሰማርቶ መጠነ ሰፊ ጥቃት መክፈት ችላል።
የአከባቢው የአገዛዙ ባለስልጣናት፣ በስፍራው የነበረውን ሚሊሻን ከባዶ ከተማ በማስወጣት፣ ከተማዋን ክፍት በማድረግ እና ነዋሪውን ያለአንዳች ተከላካይ ኃይል በማስቀረት፣ የኦነግ/ሸኔ ኃይል ጥቃት እንዲፈፀም ሁኔታዎችን አመቻችተዋል።
የመርሃቤቴ አውራጃ አካል የሆነችው ደራ ወረዳ፣ በብአዴን አመራሮች አሳልፎ ሰጪነት ከአማራ ክልል ተነጥላ ለኦሮሚያ ክልል የተሰጠች ሲሆን፣ ነዋሪዎቿ በአብዛኛው አማሮች ናቸው። ወረዳዋን የወሰደው የኦሮሚያ ክልል፣ የህዝብ ስብጥሯን ለመቀየር ላለፉት 35 ዓመታት ተከታታይ ሙከራዎች ያደረገ ሲሆን፣ አማራን ከስፍራው ጨፍጭፎ የማጻዳት ዘመቻ በስፋት ሲፈጸምባት የቆየች የደም መሬት ናት።
የአዲስ አበባ ሚዲያ ምክር ቤት በአገዛዙ እና በኦነግ/ሸኔ በደራ ሕዝብ ላይ የተከፈተውን ጥቃት በእጅጉ ያወግዛል። መላው የኢትዮጵያ እና የአማራ ሕዝብ፣ እንዲሁም የአማራ ፋኖ ለተጠቃው ሕዝባችን በአፋጣኝ ትደርሱለት እና የጄኖሳይድ ኃይሎችን ከጎኑ ሆናችኹ ትመክቱ ዘንድ ጥሪ እናቀርባለን። ይህንን ፀረ አማራ ዘመቻን ለማክሸፍ የአማራ ፋኖ እያደረገ ያለውን ተጋድሎ ምክር ቤታችን በእጅጉ ያደንቃል።
ጦርነቱ በነገደ አማራ ሕዝብ ላይ ከተከፈተው የብልጽግናው አገዛዝ የዘር ማጥፋት ዘመቻ አንደኛው ገፅታው ሲሆን፣ በወለጋ፣ በአጣዬ፣ በአርሲ፣ በመተከል፣ በባሌ፣ በሀረርጌና መሰል የኢትዮጲያ ግዛቶች ውስጥ የተፈጸመ ሀገር አቀፍ ጭፍጨፋ አካል ነው። ጄኖሳይደሮቹ በተደጋጋሚ እንደሚዝቱትም፣ መቋጫው አዲስ አበባ ነው። ዓላማውም የኢትዮጰያ ህዝብ ደሙን አፍሶ፣ አጥንቱን ከስክሶ ምትክ የለሽ ብርቅዬ ህይወቱን ሰውዕቶ የገነባት እና ነጻነቷን ጠብቆ ለዛሬ ትውልድ ያስተላለፋትን ሀገረ ኢትዮጵያ ማፈራረስ ነው።
የአማራ ሕዝብ የተከፈተበትን ነገዳዊ ጥቃት መክቶ ለማክሸፍ መታገል ከጀመረ ሶስተኛ ዓመቱን በያዘበት በዚህ ወቅት፣ “የደራ አማራ ጥቃት ተከፈተበት” ብለን ከምናሰማው ጩህትም ሆነ ለቅሶ ባሻገር፣ ንፁሃንን በማንነታቸው በጅምላ እየገደለ፣ እያገተ እና ሀብት እና ንብረቱን እየዘረፈ ያለውን ይህንን የጄኖሳይድ ኃይል መላ ኢትዮጰያዊያን በሙሉ ኃይላችን ልንገጥመው እና ህልውናችንን ልንከላከል ይገባል። በዚህም ሂደት የዓለም ህዝብ ከመላው ኢትዮጰያ ህዝብ እና ቀጥተኛ የዘር ማጥፋት ጦርነት ከተከፈተበት የአማራ ህዝብ ጎን ሊቆም ይገባል።
ስንተባበር እንጠነክራለን፣ እናሸንፋለን!!
/
የአዲስ አበባ ሚዲያ ምክር ቤት፣
ሰኔ 12፣2018 ዓ.ም።