ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY
(ክፍል አንድ) ሚሊዮን ዘአማኑኤል (ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY)
‹‹መለስ ዜናዊ ኤርትራን አስገንጥሎ ገዛ፣ አብይ አህመድ ትግራይን አስገንጥሎ ይገዛል!!!›› ቃል ለምድር ለሰማይ!!!
የጫካ ኢኮኖሚ ምንም ይሁን ምን፣ አንበሣ በፍፁም ሳር አይበላም!!! (የአፍሪካውያን ምሳሌዊ አነጋገር)
ጦርነቱን ማስቆም ካልቻልን፣ ጦርነቱ ጨርሷን በራሱ ጊዜ ይቆማል!!!
ታላቁ ጦርነት ሃገሪቱን በሦስት የወታደር ዓይነቶች ይፈርጃቸዋል፤ አካልጉዳተኞ ወታደሮች፣ ለቀስተኛ ወታደሮችና፣ ሌባ ወታደሮች ናቸው፡፡ (የጀርመን ምሳሌዊ አነጋገር)
የብልፅግና ህወኃት የጦርነት ኢኮኖሚ!!! ይህ የኢኮኖሚ ትንተና በኢትዮጵያ የጦርነት ኢኮኖሚ በህብረተሰቡ ላይ የደረሱ ቀጥተኛና ቀጥተኛ ባልሆነ መንገዶች የደረሱ የስብዓዊና ቁሳዊ ኃብት ውድመት ወደር አይገኝለትም፡፡ በምድረ ኢትዮጵያ ጦርነት፣ ርሃብና ስደት የህዝባችን የዕለት ተዕለት ቀለባችን ሆኖል፡፡ እንደ ዓለም ባንክ መረጃ ዘገባ መሠረት በ2021 እኢአ የኢትዮጵያ የምጣኔ ኃብት እድገት ሁለት በመቶ እንደሚያቆለቁል ተተንብዬል፡፡ በኢትዮጵያ የፖለቲካና የደህንነት አለመረጋጋት ሁኔታ የተነሳ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ውድቀት በማስከተል የሃገር ውስጥና የባህር ማዶ ኢንቨስትመንት መንኳታኳትና የህዝቡም የኑሮ ደረጃ ማሽቆልቆል አስከትሎል፡፡ በኢትዮጵያና ህወሓት ጦርነት መረጃ እጦት የተነሳ ያስከተለውን ቀጥተኛ የምጣኔ ኃብት ውድመት በጥናት አካቶ መቃኘት አልተኛለም፡፡ ሆኖም ጦርነቱ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ያስከተለውን ጉዳትን እንቃኛለን፡፡ ‹‹This analysis seeks to focus on the economic cost of the ongoing civil war in Ethiopia and its direct and indirect impact on Ethiopia’s economy. estimates for Ethiopia’s economic growth to 2 per cent for 2021, from 6 per cent in the previous year, according to the World Bank. No doubt, the political and security developments in Ethiopia caused a fast-paced economic deterioration that not only slowed down the economic growth, but also were reflected in the domestic and foreign performance indices and led to a deterioration of the living standards of Ethiopians. Despite a lack of data on the direct economic cost of the ongoing war between the Ethiopian army and the TPLF, the implications of the conflict for Ethiopia’s economy can be laid out as follows: ›› ……….(1)
- የውጭ ዕዳ (Defaulting on Debts:)
የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስቴር የዕዳ መግለጫ ሰነድ መረጃ መሠረት፤ የአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ ውዝፍ ዕዳ ከጁን 30 ቀን 2021 እኤአ ድረስ 2.4 (ሁለት ነጥብ አራት) ትሪሊዮን ብር ሆኖ መመዝገቡን ይፋ አድርጎል፡፡ አጠቃላይ የአገሪቱ የዕዳ መጠን በውጭ ምንዛሪ ሲሰላ ደግሞ 55.6 (ሃምሳ አምስት ነጥብ ስድስት)ቢሊዮን ዶላር እንደደረሰ የዕዳ መግለጫ ሰነድ ያመለክታል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባለፈው አንድ አመት ባደረገው የብር ምንዛሪ ተመን ለውጥ ምክንያት የብር የመግዛት አቅም በከፍተኛ ደረጃ በመውረዱ ፤ በብር የምንዛሪ ተመን ማሽቆልቆል ሳቢያ አጠቃላይ የአገሪቱ ውዝፍ እዳ በ221.5 (ሁለት መቶ ሃያ አንድ ነጥብ አምስት) ቢሊዮን ብር እንዲያሻቅብ ምክንያት ሆኖል፡፡
- ከጁን 30 ቀን 2020 እኤአ ድረስ፣ የአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ ውዝፍ ዕዳ 1.929 (አንድ ነጥብ ዘጠኝ መቶ ሃያ ዘጠኝ) ትሪሊዮን ብር ሲሆን ከዚህ ውስጥ የአገር ውስጥ ውዝፍ ዕዳ መጠን 918.9 (ዘጠኝ መቶ አስራ ስምንት ነጥብ ዘጠኝ)ትሪሊዮን ብር እንዲሁም የውጭ አገር ውዝፍ ዕዳ መጠን 1.01 (አንድ ነጥብ ዜሮ አንድ )ትሪሊዮን ብር ነበር፡፡ መንግሥት 64.03 (ስልሳ አራት ነጥብ ዜሮ ሥስት) ቢሊዮን ብር ወይም ሁለት ቢሊዮን ዶላር ለውጭ አበዳሪዎች ከፍሎ ነበር፡፡
- ከጁን 30 ቀን 2021 እኤአ ድረስ፣ የአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ ውዝፍ ዕዳ 2.4 (ሁለት ነጥብ አራት) ትሪሊዮን ብር ሲሆን ከዚህ ውስጥ የአገር ውስጥ ውዝፍ ዕዳ መጠን 1.14 (አንድ ነጥብ አስራ አራት)ትሪሊዮን ብር እንዲሁም የውጭ አገር ውዝፍ ዕዳ መጠን 1.29 (አንድ ነጥብ ሃያ ዘጠኝ)ትሪሊዮን ብር ሆኖል፡፡መንግሥት በዘንድሮው በጀት አመት 73.1 (ስባ ሦስት ነጥብ አንድ) ቢሊዮን ብር ወይም 1.8 (አንድ ነጥብ ስምንት) ቢሊዮን ዶላር ለውጭ አበዳሪዎቹ ከፍሎል፡፡…………..(2)
- There are indications that if the war continues, Ethiopia will fail to pay off due its foreign loans, especially as the government increased borrowing in recent years to finance infrastructure projects. In October, Moody’s Investors Service lowered Ethiopia’s sovereign credit rating, a sign of the country’s deteriorating economy and growing concerns over the country’s ability to pay off debts. Back in February, the Ethiopian government sought help from the International Monetary Fund to benefit from debt relief under the G20 “Common Framework” aimed at helping the country to alleviate the damage caused by the Covid-19 pandemic.
2. የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ክምችት መመናመን(Ethiopia: Foreign exchange reserves)
በ2020 እኤአ በዓለም 148 አገራቶች አማካይ የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ክምችት 102.95 (መቶ ሁለት) ቢሊዮን ዩኤስ ዶላር ነው፡፡ በ2020 እኤአ የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ክምችት 3.05 ቢሊዮን ዩኤስ ዶላር ነበር፡፡ የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ክምችት ምንጩ ከውጪ ንግድ ገቢና (export products) ከውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት የሚገኝ ነው፡፡ በዚህ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ሃገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ታገኛለች፡፡ በተገኘው የውጭ ምንዛሪም ከባህር ማዶ አገራት እቃዎች በማስገባት በገቢ ንግድ ወጪ (imports) በማድረግ ያገለግላል፡፡በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቀሪው የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ክምችት ሆኖ ይቀመጣል እንዲሁም ከፊሉ ክምችት በወርቅ ተቀይሮ መጠባበቂያ ክምችት ይሆናል፡፡
“ For that indicator, we provide data for Ethiopia from 1960 to 2020. The average value for Ethiopia during that period was 0.88 billion U.S. dollars with a minimum of 0.06 billion U.S. dollars in 1960 and a maximum of 3.99 billion U.S. dollars in 2018. The latest value from 2020 is 3.05 billion U.S. dollars. For comparison, the world average in 2020 based on 148 countries is 102.95 billion U.S. dollars. See the global rankings for that indicator or use the country comparator to compare trends over time.”……………….(3)
የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ መጠባበቂያ ክምችት የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ መጠባበቂያ ክምችት የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ መጠባበቂያ ክምችት Top of Form
Bottom of Form
“The reserves of Ethiopia and other countries include their holdings of foreign currencies and gold. These are the reserves of the central bank and the treasury of the country, not the private sector. When countries export products or attract investment from other countries, they receive foreign currencies. They use some of these currencies to buy imports and to invest in other countries. The rest is held in reserves and some of the reserves may be converted to gold.
Definition: Total reserves comprise holdings of monetary gold, special drawing rights, reserves of IMF members held by the IMF, and holdings of foreign exchange under the control of monetary authorities. The gold component of these reserves is valued at year-end (December 31) London prices. Data are in current U.S. dollars.”
የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ መጠባበቂያ ክምችት/ Ethiopia foreign reserves በ2013 (2.36) ቢሊዮን ዶላር፣ በ2014 (3.53 ቢሊዮን ዶላር)፣ በ2015 (3.84 ቢሊዮን ዶላር)፣ በ2016 (3.03ቢሊዮን ዶላር)፣ በ2017 (3.05 ቢሊዮን ዶላር)፣ በ2018 (3.99 ቢሊዮን ዶላር)፣ በ2019 (2.99 ቢሊዮን ዶላር)፣ በ2020 (3.05ቢሊዮን ዶላር)፣ መጠባበቂያ የውጭ ምንዛሪ ክምችት የባር ግራፉ መረጃን ከላይ ይመልከቱ፡፡ በአሁኑ የጦርነት ኢኮኖሚ ጊዜ የሃገሪቱ የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ክምችት በመሟጠጡ ከውጭ እቃዎች ለመግዛት ለአንድ ወር ከአስራምስት ቀን ብቻ የሚበቃ ገንዘብ እንደቀረ መረጃው ያሳያል፡፡
“Ethiopia is also heavily dependent on the planned – now uncertain – restructuring of its debt by the International Monetary Fund, without which it will be in default on the external debt it has accumulated over the years due to the persistent deficits in its balance of payment. Currently, the country’s international reserve can finance imports only for the next month and half. For all intents and purposes, therefore, Ethiopia is looking at the abyss in terms of economic activities, without the promised debt restructuring by the IMF……….(4)
- የውጭ ኢንቨስትመንት መዳከም ( Fleeing foreign investments)
የአፍሪካ ሃገራት ናይጀሪያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት 6.6 ቢሊዮን ዶላር በመሳብ አንደኛ ስትሆን፣ በሁለተኛነት ደቡብ አፍሪካ 3.8 ቢሊዮን ዶላር፣ በሦስተኛነት አንጎላ 3.1 ቢሊዮን ዶላር፣ በአራተኛነት ሞሮኮ 2.4 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ከውጭ በመሳብ ይከታተላሉ፡፡ ……………………..(5)
የኢትዮጵያ ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት ከ2017 ወደ 2018እኢአ በ707 ሚሊዮን ዶላር ቀነሰ፣ ከ2018እኢአ ወደ 2019እኤአ በ794 ሚሊዮን ዶላር ቀነሰ፣ ከ2019 እስከ 2020እኤአ በ1.384 ቢሊዮን ዶላር እድገት አሳየ፣ ከ2020 እሰከ 2021 እኤአ በ2.56 ቢሊዮን ዶላር አሽቌልቁሎል፡፡ ዶክተር አብይ አህመድ ይህን የኢትዮጵያ ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት ሁኔታ በግልፅ ለፓርላማው አላስረዱም፡፡ በኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ ዘመን ኢትዮጵያ ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት ከ3.9 (ከሦስት ነጥብ ዘጠኝ) ቢሊዮን ዶላር 1.34 (አንድ ነጥብ ሠላሳ አራት) ቢሊዮን ዶላር በመውረድ የ2.56 (የሁለት ነጥብ ሳምሳ ስድስት) ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ማሽቌልቁሉን ታውቆል፡፡ የኢትዮጵያ ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት ዳግም ለማንሰራራትም የብዙ አመታት ጥረት ይጠይቃል፡፡ የውጭ ኢንቨስተሮች በሃገሪቱ በተከሰተ ጦርነት የደህንነትና የፀጥታ ሁኔታ የውጭ ኢንቨስተሮችን ያለው የጦርነት ሁኔታ ሊስባቸው አይችልም፡፡ በትግራይ ፣ በአማራና አፋር ክልሎች የተቀጣተለ የጦርነት እሳት ብዙ የሰውና የቁስ ውድመትን አስከትሎል፡፡ የመሠረተ ልማቶች ወድመዋል፣ የጤናና የትምህርት ተቆማት ወድመዋል፣ የቴሌ፣ የመብራት እንዲሁም የውኃ ተቆማት ወድመዋል፡፡
Many factories and mines were shut down across the region, but the economic impact of the war spilled over into other regions in recent months. Global companies closed their operations in Ethiopia. Global fashion giant PVH Corp. has closed its manufacturing facility, the largest factory in Ethiopia’s model industrial park in the city of Hawassa.
ምንጭ
(1) Future Center – How the war in Tigray is impacting Ethiopia’s economy? (futureuae.com)/ Dr.. Samar Bagouri/ Monday، December 13، 2021
(2) መንግሥት ከአገር ውስጥና ከውጭ የተበደረው ውዝፍ የዕዳ መጠን 2.4 ትሪሊዮን ብር ደረሰ/ ሪፖርተር ጋዜጣ / 1 ሴፕቴምበር 2021
(3) Ethiopia: Foreign exchange reserves including gold, billion USD, 1960 – 2020:
(4) (US Sanctions on Ethiopia: Good Policy or Violation of Ethiopia’s Sovereignty?/By Teferi Mergo – 21 June 2021)
(5) የኢትዮጵያ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ቢቀንስም የኢኮኖሚው ዕድገት አዎንታዊ መሆኑ ተነገረ/ሪፖርተር ጋዜጣ 15 ዲሴንበር 2021